TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia #USA

አሜሪካ በአማራ ክልል እየተባባሰ የሄደው ግጭት እንዳሳሰባት ገለጸች።

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ብሊንከን " የርስ በርስ ግጭቶች እልባት ያገኙ ዘንድ የፖለቲካ ውይይቶች መደረግ አለባቸው " ብለዋል።

አንቶኒ ብሊንከን ይህንን ያሉት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት እንደሆነ ተነግሯል።

ብሊንከን "በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ያሳስበኛል" ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ሌሎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶችን ጨምሮ የውስጥ ግጭቶችን ለመፍታት የፖለቲካ ውይይት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ከጠቅላይ ሚንስትር አቢይ ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ " በፕሪቶሪያው ስምምነት እና አፈጻጸሙ ዙሪያ " መነጋገራቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት የሀገራቸው እገዛ እንደማይለያት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ብሊነክን በአፍሪቃ ቀንድ ቀጣና እየተባባሰ ነው ያሉት ውጥረት እንዲረግብም በዚሁ ጊዜ መጠየቃቸውን ተዘግቧል።

#AFP #DW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው በአፍሪካ የመጀመሪያው ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን ዛሬ ኢትዮጵያ ገብቷል።

#EthiopianAirlines🇪🇹

@tikvahethioia
#አቢሲንያ_ባንክ

ቀጣይ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር ቅዳሜ ጥቅምት 30 ከረፋዱ 4:30 በፌስቡክ ፔጃችን ላይ ይደረጋል፡፡ በየሳምንቱ አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ!
ዛሬውኑ የፌስቡክ ፔጃችን በመቀላቀል እና ቀላል ጥያቄዎችን በመመለስ ይሸለሙ!

የፌስቡክ ሊንክ፡ https://www.facebook.com/BoAeth

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#Facebook #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
#ረቂቅአዋጅ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅን ለማሻሻል ያለመ ረቂቅ አዋጅ ትላንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። ረቂቁ ምን ይዟል ? 🔵 የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንደ ትምህርት አይነትነት እና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የሚሰጥ ሆኖ እንደ ትምህርት አይነትነትና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት መሰጠቱ የሚያበቃበትን የክፍል ደረጃ ክልሎች ይወስናሉ። 🔵 የእንግሊዘኛ ቋንቋን በማስተማሪያነት…
#አጠቃላይየትምህርትረቂቅአዋጅ

በአገር አቀፍ፣ በክልል ወይም በአካባቢ ደረጃ ያለው የትምህርት ደረጃና ጥራት ከተጠበቀው በታች መወረዱ ሲረጋገጥ የሚመለከታቸው ፦
➡️ የፌደራል፣
➡️ የክልል
➡️ የአካባቢ የትምህርት አስተዳደር ኃላፊዎችን ተጠያቂ የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ለፓርላማ ቀርቧል።

የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ ባለፈው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት ለሰው ሀብት ልማት የሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ በአብላጫ ድምፅ ተመርቷል፡፡

ረቂቁ ምን ይዟል ?

🟢 የትምህርት ደረጃና ጥራት ከሚጠበቀው በታች የወረደ መሆኑ ሲረጋገጥ የትምህርት ተቋሙ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን፣ ሌሎች ለችግሩ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትና ግለሰቦች ተጠያቂዎች እንደሚሆኑ ተደንግጓል፡፡

🟢 በሒደቱ የትምህርት ደረጃና ጥራት መርማሪዎችን ሥራ ለማሰናከል የሚደረጉ ተግባራት የተከለከሉ መሆናቸው ተደንግጓል።

🟢 የአጠቃላይ የትምህርት ደረጃ ጥራትን በባለቤትነት የሚያስጠብቅ የትምህርት ቁጥጥርና ክትትል አገልግሎት የሚሰጥ መንግሥታዊ ተቋም በትምህርት ሚኒስቴር ሥር እንደሚቋቋም ተካቶበታል፡፡

🟢 የመንግሥት ዋነኛ ተግባር ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ማንኛውም ሕፃን ለአጠቃላይ ትምህርት ያለውን መብት ተግባራዊ ማድረግ፣ ተማሪውም የአንደኛና መለስተኛ ትምህርቱን ለመከታተል ያለበትን ግዴታ መወጣቱን ማረጋገጥ ያስችላል።

🟢 በትምህርት ዘርፍ ለሚሳተፉ ባለሀብቶችና ሌሎች መንግሥታዊ ላልሆኑ አካላት፣ በአገሪቱ የኢንቨስትመንት ሕግና አግባብ ባላቸው ሕጎች መሠረት ማበረታቻ ይሰጣል።

🟢 ስለትምህርት ክፍያ አለመኖር በሚያብራራው አንቀጽ በማንኛውም የመንግሥት አጠቃላይ የትምህርት ተቋም ውስጥ በመደበኛው የትምህርት መርሐ ግብር ከሚማር ተማሪ ከወላጆች ወይም ከአሳዳሪዎች የትምህርት ክፍያ፣ የመማርያ መጻሕፍት ዋጋ ወይም የመመዝገቢያ ክፍያ መቀበል ክልክል ስለመሆኑ ተደንግጓል፡፡

🟢 ክልሎች በሚያወጠት ሕግ መሠረት ለሌሎች የትምህርት መሣሪያዎች የሚውል መጠነኛ ክፍያ ከተማሪ ወላጆች የመክፈል አቅም ጋር በተጣጣመ መንገድ ሊያስከፍሉ እንደሚችሉ ተደንግጓል። ድንጋጌው ቢኖርም ይህንን አላሟላህም ተብሎ ተማሪው ከትምህርት ገበታው እንዲለይ ማድረግ አይቻልም።

🟢 የቅድመ አንደኛ ደረጃ መግቢያ ከአራት ዓመት እስከ ስድስት ዓመት ሲሆን፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕድሜ ደግሞ ሰባት ዓመት ተደርጓል፡፡

🟢 ተማሪዎች ቢያንስ ሦስት ቋንቋዎችን እንዲማሩ እንደሚደረግ ተደንግጓል። እንግሊዝኛ ቋንቋ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ይሰጣል። እንዲሁም አንድ ተጨማሪ የውጭ ቋንቋ ክልሉ በሚመርጠው መሠረት ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ በአማራጭነት እንዲሰጥ ይደረጋል።

🟢 ማንኛውም ሰው ተገቢው የማስተማር ሥራ ፈቃድ ሳይኖርው በአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በመምህርነት ሊሠራ እንደማይችል የተደነገገ ሲሆን፣ ለዚህ የሚረዳና የሥራ ፈቃድ አሰጣጥን የተመለከተ ስታንዳርድ መመርያ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ይወጣል።

🟢 ከቅድመ ሥራ ሥልጠና በኋላ በመምህርነት የሚመደብ ሰው በቅድሚያ የሁለት ዓመት የትውውቅ ሥልጠና የመከታተልና ለዚህም የሚሰጠውን መመዘኛ ፈተና የማለፍ ግዴታ አለበት። ይህን ግዴታ ከተወጣ በኋላ በዚህ አንቀጽ የሥራ ፈቃድ እንደሚሰጠው ተደንግጓል፡፡

🟢 የመምህራን የሙያ ፈቃዱ በየሁለት ዓመቱ መታደስ ያለበት ሲሆን፣ ዕድሳቱ ከማንኛውም የፈቃድ ክፍያ ነፃ ተደርጓል፡፡ ይህ ዕድሳት ለመምህራን ደረጃ ዕድገት እንደሚረዳ ተቀምጧል፡፡

🟢 በውጭ አገር ማኅበረሰቦች የሚቋቋሙ ትምህርት ቤቶች ከሚያስፈልጋቸው በጀት በአገራቸው መንግሥት 30 በመቶ የሚደገፉ እንደሆኑ፣ ቀሪውን 70 በመቶ ራሳቸው መሸፈን የሚችሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ማረጋገጫ ማምጣት አለባቸው።

🟢 ኢትዮጵያ ውስጥ በሚቋቋሙ የውጭ አገር ማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶችና ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ከሚመለከተው አገር የሥራ ፈቃድ ማምጣት እንደሚገባቸው ተደንግጓል፡፡ (ሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia
#MesiratEthiopia

ኢትዮጵያ ውስጥ የጊግ ኢኮኖሚን ጥቅም ማወቅ ይፈልጋሉ?

በቢዝነስ፣ በህግ እና በፋይናንስ ዙርያ የሚሰጠውን የጊግ ኢኮኖሚ ስልጠና በቴሌግራም ቦት በኩል ይውሰዱ!

https://t.iss.one/mesirat_academy_bot?start=Mesirat_Socials ተመዝግበው ስልጠናውን ይጀምሩ!

ስልጠናውን ሲጨርሱ ሰርተፍኬቶን እንዳይረሱ!

#Entrepreneurship #BusinessGrowth #GigEconomy #Workshops #Mesirat
TIKVAH-ETHIOPIA
#US ነገ በአሜሪካ ከሚደረገው ኦፊሴላዊ የድምፅ መስጫ በፊት ባሉት ጥቂት ቀናት ብቻ ከ78 ሚሊዮን በላይ ሰዎች " ለሀገራችን ይሆናታል ፣ ይበጃታል " ያሉትን መርጠዋል። አሜሪካ እና ዜጎቿ በዓለም ከሚታወቁባቸው ጉዳዮች አንዱ የምርጫ ስርዓታቸው ነው። የሀገሪቱ ዜጎች በምርጫ ጉዳይ ቀልድና ፌዝ አያውቁም ምክንያቱም የነገ ዕጣፋንታቸው የሚወስነበት ስለሆነ። ለዚህ ነው በነቂስ እየተሳተፉ " ይሆነናል…
#USElection

አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ይገኛል።

ዶናልድ ትራምፕም በበርካታ ግዛቶች ድል ቀንቷቸው ምርጫውን እየመሩ ይገኛሉ።

የአሜሪካ ምርጫ ውጤት የሚታወቀው መቼ ነው ?

የምርጫ አሸናፊ በድምፅ መስጫው ምሽት ፣ አሊያም በነጋታው ካልሆነ ደግሞ ከቀናት ወይም ከሳምንታት በኋላ ሊታወጅ ይችላል።

ያለፈው ምርጫ በአውሮፓውያኑ 2020 ማክሰኞ ኅዳር 3 ነው የተደረገው። ነገር ግን ጆ ባይደን አሸናፊ መሆናቸው የተሰማው ቅዳሜ ኅዳር 7 ቀን ነበር።

በወቅቱ አብዛኞቹ ግዛቶች ድምፅ በተሰጠ በ24 ሰዓታት ውስጥ ውጤት ቢያሳውቁም በአንዳንድ ግዛቶች ላይ ቆጠራው ቀናትን ወስዷል።

በ2016 ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ሲመረጡ ውጤት የታወቀው ከድምፅ መስጫው ቀጥሎ ባለው ቀን ነበር።

በ2012 ደግሞ ባራክ ኦባማ ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዝደንት ሆነው ሲመረጡ ውጤቱ ይፋ የተደረገው በድምፅ መስጫው ቀን እኩል ለሊት ገደማ ነው።

ነገር ግን በ2000 በጆርጅ ደብሊው ቡሽ እና አል ጎር መካከል የተደረገው ምርጫ ከሌሎቹ ለየት ይል ነበር።

ዕጩዎቹ የነበራቸውን ጠባብ ውጤት ተከትሎ ድምፅ ድጋሚ እንዲቆጠር ቢታዘዝም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጣልቃ በመግባት በግዛቲቱ በውጤት እየመሩ የነበሩት ቡሽ አሸናፊ እንዲሆኑ ወስኗል።

ቁልፍ ግዛቶች የትኞቹ ናቸው ?

የአሜሪካ ምርጫ ውጤት የሚወሰነው በጥቂት ግዛቶች በሚገኝ ድምፅ ነው።

ለዚህ ምክንያቱ ኢሌክቶራል ኮሌጅ የተባለው ሥርዓት ነው። ይህ ማለት አሜሪካ ፕሬዝደንቷን የምትመርጠው ዕጩዎች በሚያሸንፉት ግዛት መሠረት ነው። አብዛኛዎቹ ግዛቶች ዲሞክራት አሊያም ሪፐብሊካን ናቸው።

ዘንድሮ በጣም ወሳኝ የሚባሉት ግዛቶች ሰባት ናቸው። እነሱም ፦
° አሪዞና፣
° ጆርጂያ፣
° ኔቫዳ፣
° ኖርዝ ካሮላይና፣
° ዊስኮንሲን፣
° ፔንስሊቪኒያ እና ሚሸጋን ናቸው።

ድምፅ የሚቆጠረው እንዴት ነው ?

ብዙውን ጊዜ ቅድሚያ የሚሰጠው በምርጫው ቀን ለሚሰጡ ድምፆች ነው። ቀጥሎ ከድምፅ መስጫው ቀን በፊት የመረጡ እና በፖስት ድምፃቸውን ያስገቡ ሰዎች ቆጠራ ይካሄዳል።

ከውጭ ሀገራትና ከወታደራዎ ካምፖች የሚላኩ እንዲሁም ድጋሚ እንዲቆጠሩ የተደረጉ ድምፆች ይከተላሉ።

የአካባቢ የምርጫ ባለሥልጣናት አንዳንዶቹ የተሾሙ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ተመርጠው የመጡ ናቸው። እነዚህ የምርጫ አስተባባሪዎች ናቸው።

አስተባባሪዎች የተሰጠውን ድምፅና የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ያመዛዝናሉ፤ መረጃዎችን ያጣራሉ፤ ጉዳት የደረሰባቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን ይፈትሻሉ፤ አለመመሳሰል ካለበት ደግሞ ምርመራ ያደርጋሉ።

ወረቀቶቹ ወደ ኤሌክትሮኒክ ሥርዓት ገብተው ውጤታቸው እንዲቆጠር ይደረጋል።

አንዳንዶቹ ድምፆች በእጅ ሊቆጠሩ ይችላሉ።

ድምፁ ትክክለኛ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ መጀመሪያ በክፍለ-ግዛት ቀጥሎ ወደ ግዛት ይሸጋገራል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USElection አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ይገኛል። ዶናልድ ትራምፕም በበርካታ ግዛቶች ድል ቀንቷቸው ምርጫውን እየመሩ ይገኛሉ። የአሜሪካ ምርጫ ውጤት የሚታወቀው መቼ ነው ? የምርጫ አሸናፊ በድምፅ መስጫው ምሽት ፣ አሊያም በነጋታው ካልሆነ ደግሞ ከቀናት ወይም ከሳምንታት በኋላ ሊታወጅ ይችላል። ያለፈው ምርጫ በአውሮፓውያኑ 2020 ማክሰኞ ኅዳር 3 ነው የተደረገው። ነገር ግን ጆ ባይደን…
#USElection2024

የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ገና ቢሆንም እስካሁን ባሉ ቆጠራዎች ድሉ ወደ ሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕ ያጋደለ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

ትራምፕ በሀገሪቱ ወሳኝ ናቸው ከሚባሉ ግዛቶች መካከል የሰሜን ካሮላይና ግዛትን ያሸነፉ ሲሆን ሌላኛዋን ወሳኟን ጆርጂያ ግዛትንም ማሸነፍ ችለዋል።

የኢሌክቶራል ውጤትን የሚያሳየው ካርታ ትራምፕ ከ4 ዓመት በፊት ከነበረው በተለየ በአውሮፓውያኑ 2016 ያሸነፉበትን መስሏል።

በመላው አሜሪካ ውጤታቸውን ይፋ ባደረጉት ግዛቶች የቀድሞው ፕሬዚዳንት በሚታይ ልዩነት እየመሩ እንደሆነ አሳይቷል።

ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ በከተሞች እና በከፊል ከተሞች መካከል ያገኙት ድምጽ ከዚህ ቀደም ጆ ባይደን ካገኙት ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም ከትራምፕ ጋር ያላቸውን ልዩነት ማጥበብ አልቻሉም ሲል በዘገባው አስፍሯል።

በሌላ በኩል ፤ ኒውዮርክ ታይምስ ዶናልድ ትራምፕ በፕሬዜዳንትነት ለመመረጥ ከ95 በመቶ በላይ እድል አላቸው ብሏል።

በበርካታ ግዛቶችም እንዳሸነፉ አክሏል።

ሌሎች መገናኛ ብዙሃንም ከወዲሁ ዶናልድ ትራምፕ ፤ ሃሪስን በዝረራ አሸንፈው 47ኛው የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት መሆናቸው አይቀርም ሲሉ ዘግበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USElection2024 #Result ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደሚሆኑ ' ፎክስ ኒውስ ' ጠቁሟል። ትራምፕ፣ ካማላን ሃሪስን በማሸነፍ ቀጣዩ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ይሆናሉ ሲል አሳውቋል። አሁን ባለው ውጤት የቀድሞ ፕሬዜዳንት ትራምፕ ዳግም ሀገሪቱን የመምራት እድል ይሰጣቸዋል። @tikvahethiopia
#USElection2024

የኤልሳልቫዶር ፕሬዜዳንት ማንም ሳይቀድማቸው ከወዲሁ ለዶናልድ ትራምፕ የ ' እንኳን ደስ አልዎት ! ' የደስታ መልዕክት መልዕክት ያስተላለፉ የመጀመሪያው የሀገር መሪ ሆነዋል።

ፕሬዝዳንት ናይብ ቡክሌ ፤ ትራምፕን ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሲሉ ጠርተዋቸው " እንኳን ደስ አለህ ! አምላክ ይባርክህ ፤ ይምራህ  " ብለዋቸዋል።

ምንም እንኳን የ2024 የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ውጤት ይፋ ባይሆንም አሁን ላይ ባለው የውጤት የበላይነት ዶናልንድ ትራምፕ ፤ ካማላ ሃሪስን በማሸነፍ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት የመሆናቸው ነገር እርግጥ እየሆነ መምጣቱ ተዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USElection2024 የኤልሳልቫዶር ፕሬዜዳንት ማንም ሳይቀድማቸው ከወዲሁ ለዶናልድ ትራምፕ የ ' እንኳን ደስ አልዎት ! ' የደስታ መልዕክት መልዕክት ያስተላለፉ የመጀመሪያው የሀገር መሪ ሆነዋል። ፕሬዝዳንት ናይብ ቡክሌ ፤ ትራምፕን ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሲሉ ጠርተዋቸው " እንኳን ደስ አለህ ! አምላክ ይባርክህ ፤ ይምራህ  " ብለዋቸዋል። ምንም እንኳን የ2024 የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ…
ከወዲሁ ለትራምፕ የደስት መልዕክት ከላኩት ውስጥ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ አንዱ ሆነዋል።

ኔታንያሁ ትራምፕ ምርጫውን እንዳሸነፉ ባመላከቱበት የደስታ መልዕክት " ይህ ትልቅ ድል ነው " ብለውታል።

የትራምፕን ወደ ዋይትሃውስ መመለስን " ታራካዊ " ሲሉ ገልጸውታል።

" ለአሜሪካ አዲስ ጅምርና በእስራኤል እና በአሜሪካ መካከል ላለው ታላቅ ህብረት ዳግም ጠንካራ የሆነ ቁርጠኝነትን የሚያመጣ ነው " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከወዲሁ ለትራምፕ የደስት መልዕክት ከላኩት ውስጥ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ አንዱ ሆነዋል። ኔታንያሁ ትራምፕ ምርጫውን እንዳሸነፉ ባመላከቱበት የደስታ መልዕክት " ይህ ትልቅ ድል ነው " ብለውታል። የትራምፕን ወደ ዋይትሃውስ መመለስን " ታራካዊ " ሲሉ ገልጸውታል። " ለአሜሪካ አዲስ ጅምርና በእስራኤል እና በአሜሪካ መካከል ላለው ታላቅ ህብረት ዳግም ጠንካራ የሆነ ቁርጠኝነትን…
" አስደናቂ ድል ተቀዳጅቻለሁ " - ትራምፕ

ዶናልድ ትራምፕ " አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ " አሉ።

የሪፐብሊካኑ ዕጩ ትራምፕ ድላቸውን ለደጋፊዎቻቸው የተናገሩት በፍሎሪዳ በተካሄደ መድረክ ነው።

ትራምፕ ይህ የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን እንደሚሆን ተናግረዋል።

" ይህ ለአሜሪካ ህዝብ ታላቅ ድል ነው፤ አሜሪካን እንደገና ታላቅ ለማድረግ ያስችለናል " ብለዋል።

በድንበሮች ያሉ ጉዳዮችን እልባት እንደሚሰጡ ቃል ገብተው ፓርቲያቸው እና እሳቸው ታሪክ የሰሩት በምክንያት እነደሆነ ተናግረዋል።

ትራምፕ ፥ " አሜሪካ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ ስልጣን ሰጥታናለች " በማለት ፓርቲያቸው የህግ መወሰኛ ምክር ቤቱን የበላይነት ከዲሞክራቶች በመውሰድ መቆጣጠራቸውን እንዳሳወቁ ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከወዲሁ ለትራምፕ የደስት መልዕክት ከላኩት ውስጥ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ አንዱ ሆነዋል። ኔታንያሁ ትራምፕ ምርጫውን እንዳሸነፉ ባመላከቱበት የደስታ መልዕክት " ይህ ትልቅ ድል ነው " ብለውታል። የትራምፕን ወደ ዋይትሃውስ መመለስን " ታራካዊ " ሲሉ ገልጸውታል። " ለአሜሪካ አዲስ ጅምርና በእስራኤል እና በአሜሪካ መካከል ላለው ታላቅ ህብረት ዳግም ጠንካራ የሆነ ቁርጠኝነትን…
#ETHIOPIA #USA

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ለዶናልድ ትራምፕ " የእንኳን ደስ አለዎት " መልዕክት አስተላለፉ።

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፤ ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን እና ዳግም ወደ ፕሬዜዳንት ስልጣን መመለሳቸውን ባለመላከተው የደስታ መልዕክታቸው " የእንኳን ደስ አለዎት !! " ብለዋል።

በስልጣን ዘመናቸእ የኢትዮጵያን እና የአሜሪካን ግንኙነት ለማጠናከር በትብብር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

@tikvahethiopia