TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DStvEthiopia

ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓም በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት አዳራሽ ( ወመዘክር ) በተከናወነው “የአቦል አዳዲስ ይዘቶች ማስተዋወቂያና የአፋፍ ቴሌኖቬላ ማጠናቀቂያ” የአቦል አዳዲስ ተከታታይ ድራማዎች አዘጋጆች በመድረኩ ልምዳቸውንና የአቦልን አስተዋፅኦ ያጋሩ ሲሆን ይዘቶቻቸውንም አስተዋውቀዋል።

አንተህ ኃይሌ ስለ “የእሳት እራት” ቴሌኖቬላ፣ ኑር አክመል ስለ “አሻራ” ቴሌኖቬላ፣ ፌቨን ከተማ ስለ “የልቤ” ድራማ እንዲሁም ኡስማን አወል ስለ ማዲ አቦል ይዘቶች ገለፃ አድርገዋል።

የአቦል አዳዲስ ተከታታይ ድራማዎች አዘጋጆች በመድረኩ ልምዳቸውንና የአቦልን አስተዋፅኦ ያጋሩ ሲሆን ይዘቶቻቸውንም አስተዋውቀዋል።

አንተህ ኃይሌ ስለ “የእሳት እራት” ቴሌኖቬላ፣ ኑር አክመል ስለ “አሻራ” ቴሌኖቬላ፣ ፌቨን ከተማ ስለ “የልቤ” ድራማ እንዲሁም ኡስማን አወል ስለ ማዲ አቦል ይዘቶች ገለፃ አድርገዋል።

መርሃግብሩ አስተዋፅኦ ላደረጉና በአፋፍ የዝግጅት ሂደት ለተሳተፉ ባለሙያዎች የዕውቅና የምስክር ወረቀት በመስጠት ተጠናቋል።

#ሁሉምያለውእኛጋርነው
TIKVAH-ETHIOPIA
" በአስቸኳይ ተማሪዎቹ መብታቸው ተጠብቆ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ያመለጣቸው ትምህርት ይካካስ " - ከፍተኛ ምክር ቤቱ ካለፋት 2 ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ በአለባበሳቸው ምክንያትና በእምነታቸው ላይ ያነጣጠረ ከእለት ወደ እለት እየሰፋ ያለ ጫናና እንግልት እየተከሰተ መሆኑን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር…
ዛሬም ድረስ አንዳንድ ተቋማት ኢ-ህገመንግስታዊ የሆኑ የአለባበስ (ድሬሲንግ) ኮዶችን በመጥቀስ ብዙ ሙስሊሞችን በትምህርት፣ በስራ ገበታ ላይ አስተዋፅኦ እንዳያደረጉ እንቅፋት እየሆኑ እንዳሉ የፓርላማ አባሉ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ተናግረዋል።

ይህንን ያሉት ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ነው።

ዛሬ እንኳን አሉ ኡስታዝ " ዛሬ እንኳን እኛ እዚህ ቁጭ ብለን ተማሪዎች በኒቃባቸው በሂጃባቸው ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ተገለው አንዳንድ አካባቢዎች እስከ ሁለት ዓመት ድረስ የሄዱ በሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች አሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ አይነት ድርጊት እጅግ ጎጂ መሆኑን በማንሳት መንግሥት መሰል ድርጊቶች እንዲታረሙ እንዲያደርግ የሚያስገነዝብ ሃሳብና ጥያቄ በይፋ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ ቤት ሰሞኑን በከተማው በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በመዋቅሮቹ አማካኝነት በየደረጃው ተከታታይ ውይይቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

ትላንትና የከፍተኛ ምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ስራ አስፈፃሚዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት  በጉዳዩ ላይ ውይይት መደረጉን ተገልጿል።

በዚሁም መሰረት ችግሩ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለና ዘላቂ መፍትሔ የሚያሻው ከመሆኑ አንጻር ከፍተኛ ም/ቤቱ ከፌደራል መጅሊስ እንዲሁም ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ ዘላቂ እልባት የሚያመጣ የመፍትሔ ሀሳብ እንዲያቀርብ ከስምምነት መደረሱ ተነግሯል።

ከወሩ መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ ከትምህርት ገበታ የተገለሉ ተማሪዎችን በተመለከተ ግን በጊዜያዊነት ከመገለላቸው በፊት ይስተናገዱ በነበረበት ሁኔታ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ  ከስምምነት መደረሱን ምክር ቤቱ ይፋ አድርጓል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሌሊት 10 ሰዓት ነው በትዳር አጋሯ የተገደለችው ፤ አንቆ ነው የገደላት " - የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ በትግራይ፣ በውቕሮ ከተማ ድል ባለ ሰርግ ከተሞሸረች በኃላ በአራተኛው ቀን በትዳር አጋሯ ታንቃ ስለተገደለችው ሊዲያ ዓለም ጉዳይ የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ አስተያየቱን ሰጥቷል። ለቢቢሲ አማርኛው ቃላቸውን የሰጡት የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ ኮማንደር ሙሉ ብርሃን ካህሳይ ፥ " ሊዲያ ረቡዕ፣ጥቅምት…
#መቐለ

መቐለ ከተማ ውስጥ በጭካኔ የተገደለች እንስት አስከሬንዋ ከ2 ቀን በኋላ መገኘቱን ፓሊስ አስታውቋል።

የጭካኔ ተግባሩ የት ፣ መቼ ፣ እንዴት ተፈፀመ ?

የጭካኔ ተግባሩ በትግራይ ፣ መቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ተብሎ በሚጠራው ልዩ ሰፈር በሚገኝ የአንድ ሆቴል ክፍል ነው የተፈፀመው።

ሓበን የማነ የ19 ዓመት ወጣት ስትሆን በሆቴል ክፍል #በቢላዋ ተገድላ መገኘትዋና ጥቅምት 20 /2017 ዓ.ም ከሰአት በኋላ የቀብርዋ ስነ-ሰርዓት መከናወኑ ተሰምቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል የጭካኔ ተግባሩ የሚመለከት ተጨባጭ መረጃ ለማግኘት ወደ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፓሊስ ፅህፈት ተጉዟል።

ፓሊስ የጭካኔ ተግባሩ የሚመለከት ዝርዝር መረጃ በማሰብባሰብ ላይ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የጭካኔ ግድያ ተግባሩ በፍቅኛሞች መካከል መፈፀሙን እና በግድያ ወንጀል የተጠረጠረ ዳዊት ዘርኡ የተባለ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ህዝቡ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጠይቋል። 

በተያያዘ በያዝነው ወር የመጀመሪያ ሳምንት ውቕሮ ከተማ ላይ እሁድ ጥቅምት 5 ተድራ ሓሙስ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም በባሏ በጭካኔ የተገደለችው ሙሽሪት ሊድያ ጉዳይ ተጣርቶ ወደ አቃቤ ህግ መተላለፉን የወቕሮ ከተማ ፓሊስ አሳውቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#NBE : ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፤ ባንኮች እርስ በርሳቸው የሚበዳደሩበት የገንዘብ ግብይት ይፋ አድርጓል።

ንግድ ባንኮች የአጭር ጊዜ ማለትም ለአንድ ቀን ወይም ለሰባት ቀናት መቆየት የሚችል ገንዘብ መበደርና ማበደር የሚችሉ መሆናቸውንም አብስሯል።

በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት መጀመሩ ፦

➡️ ባንኮች የአጭር ጊዜ የገንዘብ ጉድለትን በመሸፈን ወይም ትርፍ ገንዘብን ለሌሎች ባንኮች በማበደር የገንዘብ ፍሰትን በብቃት እንዲያስተዳደሩ ያስችላቸዋል።

➡️ የገንዘብ ግብይቱ የአጭር ጊዜ ማለትም የአንድ ቀን ወይንም የሰባት ቀናት የመክፈያ ጊዜ ያላቸው ብድሮችን ያካትታል ፤ ይህ ባንኮች የአጭር ጊዜ የገንዘብ ጉድለትን በመሸፈን ወይም ትርፍ ገንዘብን ለሌሎች ባንኮች በማበደር የገንዘብ ፍሰትን በብቃት እንዲያስተዳደሩ ያስችላቸዋል።

➡️ የገንዘብ እጥረት ስጋትን በመቀነስና በተረጋጋ የወለድ ተመን ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ሲል ብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።


በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ የግብይት መድረክ ላይ ብቻ እንዲሆ ብሔራዊ ባንክ ፈቅዷል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#NBE

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኦርቶዶክስተዋሕዶ " ...አለመግባባት በዝቷል፤ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቷል ፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቷል " - ቅዱስነታቸው የጥቅምት 2017 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጀመረ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የስራ…
#ቅዱስሲኖዶስ

" በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለም !! ... ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን የሰላም ጥሪ እናቀርባለን " - ቅዱስ ሲኖዶስ

የጥቅምት 2017 ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ተጠናቋል።

ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲካሄድ ሰንብቷል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈሳዊ፣ በማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል።

የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ተሰጥቷል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ 

ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡ "


(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት)

/ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል /

@tikvahethiopia