TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ጉዳይ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከደቂቃዎች በፊት ማብራሪያ ሰጥቷል።

ቢሮው እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከአውድ ውጪ በተተረጎመ መንገድ እንደሆነ ጠቁሟል።

" የ1997 የጋራ መኖርያ ቤት ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ሰሞኑን በተለያዩ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው የተሳሳተ መረጃ ትክክል ባልሆነ መልኩ  ከአውድ ውጪ ተተርጉሞ የቀረበ ነው " ብሏል።

ቢሮው በሰጠው ማብራሪያ ምን አለ ?

" ከተማ አስተዳደሩ የጋራ መኖሪያ እና ንግድ ቤቶች ለማስተላለፍ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 3/2011 መሰረት ክፍል 3 አንቀፅ 13 ንኡስ አንቀፅ 1 እና 2 መሰረት ብቁ እና ንቁ ማለትም ' የቤት ፈላጊዎች በገቡት ግዴታ መሰረት የቁጠባ መጠን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትክክል ተቀማጭ ማድረጋቸውን ከእጣ በፊት ያረጋግጣል ' ይላል።

ስለሆነም የ1997 ተመዝጋቢዎች በወቅቱ በመረጃ ቋት ውስጥ ንቁ እና ብቁ  የነበሩ ተመዝጋቢዎችን ከተማ አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉ አስተናግዶ ያጠናቀቀ ሲሆን ነገር ግን በወቅቱ ብቁ ያልነበሩትን የ1997 ተመዝጋቢዎች እና ሌሎች የ2005 እጣ ያልደረሳቸው የቤት ፈላጊዎች እየተተገበሩ ባሉ የተለያዩ የቤት ልማት አማራጮች እያስተናገደ ይገኛል፡፡

ስለሆነም በወቅቱ ብቁ እና ንቁ  ያልነበሩ የ1997 ተመዝጋቢዎች ከየትኛውም የቤት ልማት መርሃ ግብር ውጪ እንደተደረጉ ተደርጎ የተሰራጨው የሀሰት መረጃ ተገቢ እንዳልሆነ ህብረተሰቡ እንዲገነዘብ እና ይህንን ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩትን ከተማ አስተዳደሩ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል።

ከተማ አስተዳደሩ ተመዝግበው የሚጠባበቁትን ሆነ ሌሎች የከተማችዋን የቤት ፈላጊዎች ቤት ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ አዳዲስ የቤት ልማት አማራጮችን በመቀየስ እየተገበረ ይገኛል " ብሏል።


NB. ቢሮው ስለ 1997 ተመዝጋቢዎች የትኛው ሚዲያ ከአውድ ውጭ የተተረጎመ ሀሰተኛ መረጃ እንዳሰራጨ በግልጽ ያለው ነገር የለም ነገር ግን መረጃውን የሚያሰራጩትን በህግ እጠይቃለሁ የሚል ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል።

#AddisAbabaHousingDevelopmentandAdministrationBureau

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EthiopianInstitutionoftheOmbudsman

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ስለ 1997 ተመዝጋቢዎች ምን አለ ?

" ለ20 ዓመታት ያህል ' ቤት ይደርሰናል ' ብለው እየጠበቁ ቢሆንም መንግሥት ምላሽ አልሰጠንም ያሉ ቢያንስ 67 ሰዎችን አቤቱታ ተቀለን እየመረመርን ነው።

' በ1997 ተመዝግበን ቤት ሳይደርሰን ለሌሎች ተሰጥቷል ' ፤ በሚል ተደራጅተው ጠይቀዋል፣ እኛም ጥያቄ አቅርበናል፡፡ ነገር ግን የከተማ አስተዳደሩ እስካሁን መልስ አልሰጠንም።

መልስ የማይሰጠን ከሆነ ለረዥም ጊዜ ጠብቀው ምላሽ ያልተሰጣቸውን ሰዎች አቤቱታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ የመጨረሻ ዕልባት እንዲያገኝ እናደርጋለን። "

ይህ ቃል ከሪፖርተር ጋዜጣ የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopia
#ዶክተርነቢያትተስፋዬ 👏 #ኢትዮጵያ

ከስፓይና ቢፊዳ የጤና እከል ጋር የተወለዱት ግለሰብ በማሌንዢያ የስፓይና ቢፊዳ ዓለም አቀፍ ኮንግረንስ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ሆኑ።

ከ30 ዓመታት በፊት ከህመሙ ጋር የተወለዱት ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬ ፣ በማሊዥያ የስፓይና ቢፊዳ ዓለም አቀፍ ኮንግረስ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የሕይወት ዘመን ተሸላሚ የሆኑት፣ ያሳለፉትን የሕይወት ውጣ ውረድ ሌሎች ልጆች እንዳያልፉ በሕይወት ልምዳቸውና በሙያቸው ኢትዮጵያውያንን ለማገልገል በሚያደርጉት ጥረት ነው።

ለኢትዮጵያውያን የሚሰጡትን አግልግሎት አድማስ ለማስፋት “ አለያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት ” የተሰኘ በስማቸው ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት በመመስረት አገልግሎት መስጠት እንደጀመሩም ተናግረዋል።

ድርጅታቸው ከሀገር ውስጥና ውጭ ካሉ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በስፓይና ቢፊዳ እና ተያያዥ የጤና ችግር ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሟላ ድጋፍ ለማድረግ ሽልማታቸውን ከተቀበሉ በኋላ ቃል ገብተዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናት በዓመት ከስፓይና ቢፊዳና ተያያዥ የጤና እክሎች ጋር አብረው የሚወለዱ ሲሆን፣ በኢትዮጵያም በርካታ ሕፃናት ከዚህ ችግር ጋር አብረው ከሚወለድባቸው ሀገሮች ግንባር ቀደም መሆኗን አስረድተዋል።

በመሆኑም ከጤና ሚንስቴር ፣ ከሆስፒታሎችና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር በዚህ ችግር የተጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎች የክትትልና የማገገም አገልግሎት እንዲያገኙ በትጋት እየሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።

የተሸላሚው የሕይወት ጉዞ ምን ይመስላል ?

ከ30 ዓመታት በፊት ከዚህ የጤና ችግር ጋር ተወልደዋል። ከዚህ ችግር ጋር አብረው በመወለዳቸው በሕይወታቸው ውስጥ ብዙ ውጣውረዶች አሳልፈዋል።

የተለያዩ ቀዶ ጥገና ሕክምናዎችንም አድርገዋል።

በልጅነት ጊዜያቸው በዚሁ በሽታ ሳቢያ ትምህርታቸውን ቤት ተቀምጠው እስከመከታተል ተገደዋል። በተለያዩ የጤና ችግሮች ውስጥም አልፈዋል።

እነዚህን ሁሉ ችግሮች በትጋትና በጥንካሬ ከቤተሰቦቼ ጋር በመሆን አልፈው የህክምና ትምህርት መማር ችለዋል።

ለአምስት አመታት የህክምና ትምህርታቸውን ተከታትለው ከጨረኩበት ማግስት ጀምረው እንደሳቸው ሁሉ ከዚህ የጤና ችግር ጋር ለሚወለዱ ሕፃናት የተለያዩ ድጋፎችና የህክምና አገልግሎቶች እንዲያገኙ በማድረግ በሺዎች ለሚቆጠሩ ቤተሰቦች ተስፋ ለመሆን በቅተዋል።

ልጆች ከዚህ ከባድ የጤና ችግር ጋር አብረው እንዳይወለዱና መከላከል እንዲቻል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ፎሊክ አሲድ በምግብ እንዲበለፅግ የማስተማርና የማስተዋውቅ ሥራ እየሰሩ ይገኛሉ።

ለሁለት አመታት Reachanother foundation በሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ውስጥ የአገልግሎት ዳይሬክተር በመሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ 8 ሆስፒታሎች ሕፃናት ጥራት ያለው የቀዶ ሕክምና አገልግሎት  እንዲያገኙ ባለሙያዎች ማስልጠን እና ግብቶችን የሟሟላት ሥራ በመስራት ላይም ይገኛሉ።

ስለ ስፓይና ቢፊዳ ይወቁ ፦
https://t.iss.one/tikvahethiopia/74429?single

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ረቂቅአዋጅ

የከተማ መሬትን በድርድር በሊዝ ማስተላለፍ የሚፈቅድ የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ሊቀርብ ነው።

የከተማ መሬትን ከጨረታ እና ከምደባ በተጨማሪ #በድርድር በሊዝ ማስተላለፍ የሚፈቅድ የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ሊቀርብ መሆኑን ' ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ' አስነብቧል።

አዲሱ የአዋጅ ረቂቅ፤ ከተሞች በምደባ ለማቅረብ ካዘጋጁት መሬት መጠን ውስጥ፤ ቢያንስ 20 በመቶውን ለቤት ግንባታ አገልግሎት መዋል እንዳለባቸው ግዴታ ይጥላል። 

" የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ " እንደወጣ የተገለጸው ይህ አዋጅ፤ ነገ በሚካሄድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ እንዲቀርብ አጀንዳ ተይዞለታል።

ረቂቅ አዋጁ " መሬትን በድርድር በሊዝ ለማስተላለፍ " ምን ይላል ?

➡️ ረቂቅ አዋጁ መሬትን በድርድር በሊዝ ለማስተላለፍ የሚፈቅደው ድንጋጌ ይገኝበታል።

➡️ 13 ዓመት ያስቆጠረው ነባሩ አዋጁ፤ የከተማ ቦታ በሊዝ እንዲያዝ የሚፈቀደው በጨረታ ወይም በምደባ ስልት ብቻ ነበር።

➡️ በአዲሱ አዋጅ የተካተተው ' የድርድር ' ስልት፤ በጨረታ እና በምደባ አግባብ ለተጠቃሚ ሊተላለፉ በማይችሉ የከተማ መሬቶች ላይ፤ አንድ አልሚ " ለተለዩ ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው አገልግሎቶች " መሬት በሊዝ ይዞ ማልማት የሚፈቀድበት ነው። 

➡️ ይህ ተግባራዊ የሚደረገው " አግባብ ያለው አካል " ከአልሚዎች ጋር በሚያስቀምጠው " የልማት እቅድ መሰረት " እና " ከአልሚው ጋር በመደራደር " ነው።

➡️ የከተማ መሬት በድርድር ሊተላለፍ የሚችለው " ሀገራዊ እና ክልላዊ የከተማ ልማት ስፓሻል ፕላንን " መሰረት በማድረግ ነው ይላል ረቂቅ አዋጁ።

➡️ በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ ለሚቀርቡ የልማት ጥያቄዎች፤ መሬት በድርድር አግባብ ሊተላለፍ እንደሚችል በአዲሱ አዋጅ ተደንጓል።

➡️ በፌደራል መንግስት ለሚተዳደሩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለከፍተኛ የትምህርት እና የጤና ተቋማት እንዲሁም ለምርምር ዘርፍ ፕሮጀክቶች የከተማ መሬት በድርድር ሊተላለፍ እንደሚችል ተዘርዝሯል።

➡️ የአገልግሎት ዘርፉን የሚደግፉ ባለኮከብ ሆቴሎች እና ለቱሪስት ልማት ለሚውሉ ሪዞርቶችም የሚቀርቡ የመሬት ጥያቄዎች በድርድር አሰራር ሊስተናገዱ ይችላሉ።

➡️ በግሉ ዘርፍ አሊያም በመንግስትና በግሉ ዘርፍ በሽርክና ሊለሙ የሚችሉ የከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክቶችም፤ በዚሁ የመሬት አሰጣጥ አግባብ እንደሚስተናገዱ በአዋጁ ላይ ሰፍሯል።

➡️ ለሪል ስቴት ወይም ለቤት ልማት የሚቀርቡ የመሬት ጥያቄዎች፣ የግዙፍ የገበያ ማዕከላት (ሞል) ፕሮጀክቶች፣ ትላልቅ የነዳጅ ማጠራቀሚያዎች እና ማከፈፋያዎች፣ ለዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ህንጻ ግንባታዎች የሚውሉ ቦታዎች፤ በተመሳሳይ መልኩ በድርድር ማግኘት እንደሚቻልም ተመላክቷል።

➡️ በድርድር አግባብ የሚስተናገዱ ፕሮጀክቶች " የሚመጣዉ ልማት ይዘት፣ ስፋትና ጥልቀት፤ ለልማት በተመረጠው ቦታ ነባር ተጠቃሚ የሆኑ ባለይዞታዎች መስተንግዶና ተጠቃሚነት፣ በዙሪያ ባሉ ማህበረሰቦች ተጠቃሚነትና ጉዳት ቅነሳ እንዲሁም የመሰረተ ልማት አቅርቦት ድርሻ " ከግምት ውስጥ እንደሚገባ የአዋጅ ረቂቁ አትቷል።

➡️ የከተማ ቦታ በድርድር አግባብ እንዲተላለፍ የሚደረገው፤ በክልሎች፣ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ አስተዳደሮች " ካቢኔ ሲወሰን ብቻ " ነው።

➡️ መሬት በድርድር የማስተላለፊያ ዋጋ፤ ከአካባቢው አማካይ የሊዝ ጨረታ ዋጋ በታች መሆን እንደሌለበትም በአዲሱ አዋጅ ተደንግጓል። 

በምደባ ስለሚሰጥ የከተማ መሬትስ ምን ይላል ?

🔴 አዲሱ ድንጋጌ ' ከተሞች በምደባ ለማቅረብ ካዘጋጁት የመሬት መጠን " ውስጥ " ቢያንስ 20 በመቶ የሚሆነውን " ለቤት ግንባታ አገልግሎት መዋል እንዳለባቸው ግዴታ ይጥላል።

🔴 በአንድ ከተማ በመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር፣ በጋራ መኖሪያ ቤት ልማት ፕሮግራም ወይም በተናጠል የከተማ መሬትን በምደባ ተጠቃሚ የሆነ ግለሰብ፤ በዚያው ከተማ " ለሁለተኛ ጊዜ በምደባ ተጠቃሚ እንዳይሆን " የሚያግድ አዲስ ድንጋጌም ተካቷል።

🔴 በአዲሱ አዋጅ፤ መሬት በጨረታ የሚያሸነፉ ግለሰቦች ለሚያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶች ላይ ማሻሻያ ተደርጎበታል። እስካሁን በስራ ላይ ባለው የሊዝ አዋጅ፤ አንድ ተጫራች የመሬት ጨረታ አሸናፊ የሚሆነው፤ ባቀረበው የጨረታ ዋጋ እና የቅድመ ክፍያ መጠን ላይ ተመስርቶ በሚደረግ ስሌት ከፍተኛውን ነጥብ ሲያገኝ ነው። በአዋጅ ረቂቁ ላይ ይህ ተቀይሮ የሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች የሚለዩት፤ ከጨረታ ዋጋ እና የቅድሚያ ክፍያ በተጨማሪ የሊዝ ክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜ ተሰልቶ በሚገኘው የድምር ውጤት ነው። የጨረታ ዋጋ 65 በመቶ፣ የቅድሚያ ክፍያ 20 በመቶ እና የሊዝ ክፍያ ማጠናቀቂያ 15 በመቶ ነጥብ ይኖራቸዋል።

ተጨማሪ መረጃ ፦

🔵 አዲሱ አዋጅ የሊዝ መነሻ ዋጋ የሚከለስበትን ጊዜ ከ2 ዓመት ወደ 3 ዓመት ከፍ አድርጎታል።

NB. " የሊዝ መነሻ ዋጋ " ማለት ዋና ዋና የመሰረተ-ልማት አውታሮች የመዘርጊያ ወጪን፣ ነባር ግንባታዎችና ንብረቶችን ለማንሳት የሚያስፈልገውን ወጪና ለልማት ተነሺዎች የሚከፈል ካሳአን እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን መስፈርቶች ታሳቢ ያደረገ የመሬት ዝቅተኛ ዋጋ ነው።

🔵 ረቂቁ የመሸጋገሪያ ድንጋጌም ያያዘ ሲሆን አዋጁ ከመውጣቱ በፊት አግባብ ላለው አካል ለቀረቡ የከተማ መሬት ጥያቄዎች የሚሆን አንቀጽ አስቀምጧል። እነዚህ ጥያቄዎች አዋጁ ከጸናበት ቀን ጀምሮ እስከ 6 ወራት ድረስ፤ በነባሩ አዋጅ እና አዋጁን መሰረት አድርገው በወጡ ደንብ እና መመሪያዎች ውሳኔ የሚያገኙ እንደሚሆን ገልጿል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የ ' ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ' ድረገጽ ነው።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአቢሲንያ የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎች የATM ካርድ በቆማችሁበት በሰከንዶች ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ።

የአቢሲንያ ባንክ ፌስቡክ ፔጅን ሊንኩን በመጠቀም ይቀላቀሉ፡ https://www.facebook.com/BoAeth

#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ረቂቅአዋጅ

የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 ለማሻሻል የወጣው ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል።

የተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል ? ምን ዋና ዋና ማሻሻያ ተደርጓል ?

🔵 ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን የስራ አመራር ቦርድ አሰያየም እና አወቃቀር ጋር በተያያዘ ማሻሻያዎች ተደርገዋል።

በአዋጁ የተዘረጋው የቦርድ አሰያየምና አወቃቀር የተንዛዛ እና ረጅም ሂደትን የሚከተል መሆኑ ከዘርፉ ተለዋዋጭ ሁኔታ አንጻር አብሮ የማይሄድ መሆኑ፣ ይህም ባለሥልጣኑ መደበኛ ተልእኮዎችንና አስቸኳይ ውሳኔዎችን ከመስጠት አንጻር የመፈጸም አቅሙን የሚያስተጓጉል መሆኑ፣ እንዲሁም በነባሩ አዋጅ የተካተተው የቦርድ አባላት ስብጥር ከባለሥልጣኑ ሬጉላቶሪ ሚና ጋር በተያያዘ የጥቅም ግጭትን የሚፈጥር ሆኖ መገኘቱ እንደክፍተት ተገልጿል።

የተደረጉ ማሻሻያዎች ፦

" አንቀፅ 9/5/ሀ/ የቦርዱ አባላት ለመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ቅርበትና አግባብነት ካላቸው የተለያዩ አካላት እና የሕብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ይሆናሉ " በሚል በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ የተደረገበት ሲሆን የቦርድ አወቃቀር ላይ አስቻይ ያልሆኑ ገደቦች እንዲሻሻሉ ተደርጓል፡፡

🔵 የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን የስራ አመራር ቦርድ በወሳኝ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩር ለማድረግ የሚያስችሉ ማሻሻያዎች ተደርገዋል።

በረቂቁ ማብራሪያ ላይ ፥ " በመርህ ደረጃ የባለሥልጣኑ ስራ አመራር ቦርድ ባለሥልጣኑን በፖሊሲ የሚመራ አካል ቢሆንም፣ በአዋጁ አንቀፅ 13(2) መሰረት በዕለት ተዕለት የሚከወኑ የሬጉላቶሪ ሥራዎች በቦርድ እንዲከናወኑ ተደርጓል " ይላል።

" በተጨማሪም የሀገርን ደህንነት ወይም የሕዝብን ሰላምና ፀጥታ የሚያደፈርስ ዘገባ በማናቸውም መገናኛ ብዙሃንና በማናቸውም ጊዜ ቢሰራጭ በአንቀፅ 81 መሰረት ፈቃድ የማገድ፣ የመሰረዝና አለማደስን የተመለከተ አስተዳደራዊ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን ለቦርድ ተሰጥቷል " ሲል ያብራራል።

" ስለሆነም አዋጁ ቦርዱ ከሚጠበቅበት የፖሊሲ አቅጣጫ ሰጪነት ሚና ውጭ በዕለት ተዕለት የሬጉላቶሪ ተግባርና ሃላፊነት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡  ይህም ባለሥልጣኑ በህግ የተሰጠውን ተልእኮ ለመፈጸም ወቅቱን የጠበቀ ውሳኔ መስጠት እንዳይችል ገድቦታል " ይላል።

" በተመሳሳይ የሚዲያውን አውድ ታሳቢ ያላደረገ የውሳኔዎች መዘግየት በዴሞክራሲ ግንባታም ሆነ በሀገር ደህንነት ላይ አሉታዊ ጎኑ አመዝኖ ይታያል " ሲክ አክሏል።

የተደረጉ ማሻሻያዎች ፡-

" የፈቃድ አለማደስ፣ የፈቃድ ማገድ፣ ወይም የፈቃድ መሠረዝ የሚያስከትሉ ውሳኔዎችን የመወሰን ሥልጣን የባለሥልጣኑ ቦርድ ይሆናል" የሚለው ድንጋጌ ተሻሽሏል።

የፈቃድ ወይም የምዝገባ ምስክር ወረቀት አለማደስ፣ ማገድ፣ መሰረዝ፣ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ከባድ የገንዘብ ቅጣት ወይም አንድ ፕሮግራም ማገድ ወይም መሰረዝ የሚያስከትሉ ውሳኔዎችን የመወሰን ሥልጣን
#የባለሥልጣኑ_ይሆናል፡፡

ረቂቁ " ባለሥልጣኑ የፈቃድ ወይም የምዝገባ ምስክር ወረቀት አለማደስ፣ መሰረዝ፣ ከባድ የገንዘብ ቅጣት ወይም አንድ ፕሮግራም መሰረዝ የሚያስከትል ቅጣት የሚዳርግ ክስ ሲቀርብለት ባለፈቃዱ ወይም የምዝገባ የምስክር ወረቀት የተሰጠው መገናኛ ብዙሃን በጉዳዩ ላይ ያለውን ምላሽ በፅሁፍ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ለባለሥልጣኑ እንዲያቀርብ እድል ሊሰጠው ይገባል "  ይላል።

" በተወሰኑት ውሳኔዎች ቅር የተሰኘ ባለፈቃድ ወይም የምዝገባ ምስክር ወረቀት የተሰጠው የመገናኛ ብዙሃን ውሳኔው በደረሰው በ14 የሥራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለቦርዱ ሊያቀርብ ይችላል፤ ቦርዱ አቤቱታው በደረሰው በ30 የሥራ ቀናት ውስጥ ውሳኔ መስጠት አለበት " በሚል በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡

🔵 የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አሿሿምን በተመለከተ ማሻሻያ ተደርጓል።

" የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በቦርዱ ተመልምሎ በመንግስት አቅራቢነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሰየማል " የሚለው ድንጋጌ እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡

የተደረገው ማሻሻያ፡-

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማል፡፡

🔵 ከብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃድ ግዴታዎች ጋር በተያያዘም ማሻሻያ ተደርጓል።

የረቂቁ ማብራሪያ ላይ " በመገናኛ ብዙሃን አዋጁ ከቀጥታ ሥርጭት ውጭ የማናቸውም ፕሮግራም ይዘት በጣቢያው ከመሠራጨቱ በፊት ሕግን የሚያከብር መሆኑን የማረጋገጥ፤ ግዴታ እንዳለበት ይደነግጋል፡፡

ይህ ድንጋጌ በቀጥታ ስርጭት ወቅት ህገወጥ ይዘቶች ከተሰራጩ የብሮድካስት አገልግሎት ሰጪዎችን ተጠያቂ የማያደርግ በመሆኑ፣ አስፈላጊውን ኤዲቶሪያል ጥንቃቄ እንዳያደርጉ ያደርጋል፡፡

በመሆኑም የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በሚፃረር እና በሀገር ሉአላዊነት ላይ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ እንደ ጦርነት ጥሪ እና የጥላቻ ንግግር የመሳሰሉ ይዘቶች እንዲሰራጩ መንገድ ይከፍታል፡፡

በመሆኑም ይህን ለመከላከል የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በመውሰድ ማሻሻል አስፈልጓል " ብሏል።

የተደረገው ማሻሻያ፡-

የማናቸውም ፕሮግራም ይዘት በብሮድካስት አገልግሎት ጣቢያው ከመሠራጨቱ በፊት ሕግን የሚያከብር መሆኑን የማረጋገጥ፤ በሚል በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሹመት ሰጥተዋል። በቅርቡ ፕሬዜዳንት ሆነው በተሰየሙት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ምትክ የፍትሕ ሚኒስትሩን ጌዴዮን ጢሞቲዮስን (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል። የኢትያጵ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩትን ሃና አርዓያስላሴን ደግሞ የፍትህ ሚኒስትር አድርገው ሹመዋል። በተጨማሪም ፥ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ…
#HoPR

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ እያካሄደው በሚገኘው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ የ5 ሚኒስትሮችን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጸድቋል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመት እንፀድቅላቸው በደብዳቤ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነው ሹመቱ በምክር ቤቱ እንዲጸድቅ የተደረገው።

ሹመታቸው የፀደቀው ፦

- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዎስ(ዶ/ር)፣
- የፍትሕ ሚኒስትር ሃና አርዓያ ሥላሴ፣
- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣
-  የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ
- የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ናቸው፡፡

ምክር ቤቱ ሹመቱን በአንድ ተቃውሞ፣ በሁለት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አጽድቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ እያካሄደው በሚገኘው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ የ5 ሚኒስትሮችን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጸድቋል። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመት እንፀድቅላቸው በደብዳቤ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነው ሹመቱ በምክር ቤቱ እንዲጸድቅ የተደረገው። ሹመታቸው የፀደቀው ፦ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዎስ(ዶ/ር)፣…
#HoP

" የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታችን (immunity) ሳይነሳ እንደ ሽፍታ ተጎትተን ስንታሰርና ለወራት ስንቀመጥ ምን ሰሩ ? " - ደሰለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በቀድሞ የፍትህ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዬስ (ዶ/ር) ላይ ከፍተኛ ወቀሳ ሰነዘሩ።

የቀድሞው የፍትህ ሚኒስትር አሁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ላይ ጥያቄ አንስተዋል።

" የፍትህ ዘርፉን ከፍተኛ ችግር ውስጥ የከተቱ ስለሆኑ ትራክሪከርዳቸው የውጭ ጉዳይን ለመምራት ብቁ ሊያደርጋቸው አይገባም " ብለዋል።

ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ፥ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ዶ/ር ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ሲመጡ ከፍተኛ ተስፋ አድርገው እንደነበር ጠቁመዋል።

ነገር ግን ከሳቸው በፊት ከነበሩት ሚኒስትሮች ምን የተለየ ነገር አሳኩ ? ሲሉ ጠይቀዋል።

በህግ ከውጭ ዩኒቨርሲቲ ፒኤችዲ ይዘው መምጣታቸውና እዚህም ትልቁ የሀገራችን ተቋም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማስተማራቸው ላይ ምን ለውጥ አመጡ የሚለው አልተገመገመም ብለዋል።

በፍትህ ሚኒስትርነት ያላቸው ትራክሪከርድ / የሰሯቸው ስራዎች ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ብቁ ያደርጋቸዋል የሚለውም አልተገመገመም ሲሉ ተናግረዋል።

" እኔ በግሌ ቅሬታ አለኝ " ያሉት ደሳለኝ (ዶ/ር) " በፍትህ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን የእውቀት ችግር አለባቸው ብዬ አይደለም ፤ በተለያዩ መድረኮች አይቻቸዋለሁ ሞያቸውን በጣም ጠንቅቀው ያውቃሉ ፤ ነገር ግን አፈጻጸማቸውን ካየነው የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት ሲጠይቅ የነበረውን የፍትህ ጥማት ከማስታገስና ያን ከማርካት ይልቅ አሁንም የፍትህ ስርዓቱ የፖለቲካ መሳሪያ እንዲሆን አድርገዋል " የሚል ወቀሳ አቅርበዋል።

" በሀገራችን በተለይ በኢህአዴግ ዘመን የፍትህ ስርዓቱ ተቃዋሚዎችን ማጥቂያ፣ የፖለቲካ መሳሪያ፣ የገዢው ፓርቲ አንድ አርም ተደርጎ ሲሰራ ነበር አሁንም ያ ተቀይሯል ብዬ አላስብም " ብለዋል።

" የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታችን (immunity) ሳይነሳ እንደ ሽፍታ ተጎትተን ስንታሰርና ለወራት ስንቀመጥ ሌሎች የምክር ቤት አባላት የፌዴሬሽን ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተገቢ ፍትህ ሳያገኙ ለአመታት ሲንገላቱ የፍትህ ሚኒስትር ምንም የሰራው ነገር የለም። ከሳሹ እራሱ የፍትህ ሚኒስትር ነው። " ሲሉ ተናግረዋል።

ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) " እንደኔ እንደኔ ዶክተር ጌዲዮን የእውቀት ችግር የለባቸው ግን የፍትህ ሚኒስትር ላይ ያላቸው ትራክሪከርድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሀገሪቱን ለመምራት የሚያስችላቸው አይደለም። የፍትህ ዘርፉን ከፍተኛ ችግር ውስጥ የከተቱ ስለሆነ ለዛ ቦታ ሊቀርቡ አይገባቸውም " ብለዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoP " የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታችን (immunity) ሳይነሳ እንደ ሽፍታ ተጎትተን ስንታሰርና ለወራት ስንቀመጥ ምን ሰሩ ? " - ደሰለኝ ጫኔ (ዶ/ር) የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በቀድሞ የፍትህ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዬስ (ዶ/ር) ላይ ከፍተኛ ወቀሳ ሰነዘሩ። የቀድሞው የፍትህ ሚኒስትር አሁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር…
" ሲሾሙ ' ወጣት ፣ በትምህርት ዝግጅታቸው ጥሩ '  ተብሎ ይሾማል ሲወርዱ ግን በምን ፐርፎርም እንዳደረጉና እንዳላደረጉ አይነገረንም " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉ እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጩ ደሳለም ጫኔ (ዶ/ር) ከሚሰጡ ሹመቶች ጋር በተያያዘ ያላቸውን ጥያቄ በምክር ቤት አንስተዋል።

ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ፥ " የሚነሱ ሚኒስትሮች ከሾናቸው በኃላ ምን አጉለው እንደተነሱ ፤ ምን ድክመት እንዳሳዩ ፤ ወይ ምን የስነምግባር ጥሰት እንዳሳዩ አይቀርብም ፤ በተጨማሪም እነሱን የሚታኳቸው ሚኒስትሮች ከነሱ በምን እንደሚሻሉ አይነገረም " ብለዋል።

" እርግጥ ሲሾሙ ' ወጣት ፣ በትምህርት ዝግጅታቸው ጥሩ ' ምናም ተብሎ ይሾማል ሲወርዱ ግን በምን ፐርፎርም እንዳደረጉ በምን ፐርፎርም እንዳላደረጉ አነገረንም። " ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ ከግልጽነት እና ከተጠያቂነት መርህ አንጻር ጥያቄ እየሚያስነሳ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ሚኒስትሮች ከቦታቸው ሲወርዱ ለምን በምን ምክንያት እንደወረዱ ፤ በምትካቸው የሚመጡትም ከነሱ በምን እንደሚሻሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ፤ ምክር ቤቱም ማወቅ የለበትም ? ሲሉ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ጠይቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ExchangeRate የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ጭማሪ አሳየ። ባለፉት ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ113 ብር ከ1308 ሳንቲም እየተገዛ በ115 ብር 3934 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር። ዛሬ ይፋ በተደረገው የምንዛሬ ዋጋ ተመን አንድ ዶላር መግዣው ከ3 ብር በላይ ጨምሮ  116 ብር ከ6699 ሳንቲም የገባ ሲሆን መሸጫው ከ3 ብር በላይ ጨምሮ 119 ብር ከ0033 ሳንቲም ገብቷል። በተመሳሳይ…
#ExchangeRate

የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ጭማሪ አሳየ።

ባለፉት ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር መግዣው 116 ብር ከ6699 ሳንቲም  ፤ መሸጫው ደግሞ 119 ብር ከ0033 ሳንቲም ነበር።

ዛሬ ይፋ በሆነው ምንዛሬ ዋጋው ጨምሯል።

ባንኩ በመግዣ ዋጋው ላይ ከ2 ብር በላይ ጭማሪ በማድረግ 119 ብር ከ2044 ሳንቲም አስገብቶታል።

መሸጫውም በተመሳሳይ ከ2 ብር በላይ ጨምሮ 121 ብር ከ5885 ሳንቲም ገብቷል።

በግል ባንኮችም ዶላር ከ119 ብር - 120 ብር ባለው እየተገዛ ፤ እስከ 123 ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል።

(በግል ባንኮች ያለውን የዶላር የምንዛሬ ተመንን እንዲሁም የሌሎች ሀገራት ገንዘብ ምንዛሬ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia