TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ

መደበኛ ባልሆነ ማቆያ ቦታ፣ ያሉበት ሳይገለጽ እንዲቆዩ የተደረጉ እና አስገድዶ መሰወር ሁኔታን ሊያቋቁም በሚችል ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ተጎጂዎች እና የተጎጂዎች ቤተሰቦችን በተመለከተ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ እና ፍትሕ ሊሰጣቸው  እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሳስቧል።

ኮሚሽኑ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ሪፖርት ልኮልናል።

ከሪፖርቱ ውስጥ የተገኘ ማሳያ ፦

(የአስገድዶ መሰወር ሁኔታን ሊያቋቁም በሚችል ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ተጎጂዎች)

🔴 አቶ መንበረ ቸኮል ምስጋናው፣ የግንባታ ባለሙያ፣ የ7 እና የ4 ዓመት ዕድሜ ያላቸው 2 ሕፃናት ልጆች አባት ሲሆኑ፣ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ “ሰፈራ” ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በጸጥታ አካላት ሰሌዳ በሌለው ተሽከርካሪ የተወሰዱ ሲሆን፣ ያሉበት ቦታ እና ሁኔታ የማይታወቅ በመሆኑ ቤተሰቦቻቸው ለከፍተኛ ጭንቀትና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ተጋልጠው ይገኛሉ።

🔴 አቶ ዘላለም ግሩም ፍላቴ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባልና አሽከርካሪ ሲሆኑ፣ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ ልዩ ስሙ “ዲቦራ ትምህርት ቤት” ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በጸጥታ አካላት ሰሌዳ ቁጥሩ ባልታወቀ ተሽከርካሪ ከተወሰዱ ጀምሮ፣ ያሉበት ቦታ እና ሁኔታ የማይታወቅ በመሆኑ ቤተሰቦቻቸው በከፍተኛ ጭንቀትና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ውስጥ ይገኛሉ።


(በተለያየ መደበኛ ባልሆኑ ቦታዎች ወይም ያሉበት ሳይታወቅ በተራዘመ እስር ሁኔታ ቆይተው የተለቀቁ)

አቶ አማረ ግዳፍ፣ ባለ3 እግር ተሽከርካሪ በተለምዶ “ባጃጅ” በማሽከርከር ሥራ ላይ የተሰማሩ ሲሆኑ መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ በአዲስ አበባ ከተማ፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ በተለምዶ “ወሰን መስቀለኛ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 6 የሲቪል ልብስ እና 1 የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ በለበሱ ሰዎች እና ሰሌዳ በሌለው ተሽከርካሪ ተወስደው፣ ላለፉት 6 ወራት ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ ቆይተው በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም. ተለቀዋል።

አቶ ዓለማየሁ ከፈለ ተሰማ የተባሉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ነሐሴ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 1 በተለምዶ “ፍላሚንጎ” በሚባለው አካባቢ ሲቪል ልብስ ለብሰው መታወቂያ በያዙ 6 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተወስደው፣ በሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም. ተለቀዋል።

አቶ መቼምጌታ አንዱዓለም፣ ባለትዳርና የ2 ሕፃናት ልጆች አባት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት አካባቢ “ብስራተ ገብርኤል” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የታክሲ አገልግሎት ከሚሰጡበት አካባቢ ከነተሽከርካሪያቸው የሲቪል ልብስ በለበሱ የጸጥታ አካላት ተወስደው፣ በተለምዶ “ራሺያ ካምፕ” ተብሎ በሚጠራው የመከላከያ ሰራዊት አባላት መኖሪያ ለ7 ወራት ከቆዩ በኋላ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ተለቀዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የቤተሰብ አስተዳዳሪ እና የልጆች አባት የሆኑ ተጎጂ፣ ነሐሴ 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ገደማ ከግል የሥራ ቦታቸው ሲቪል እና የደንብ ልብስ ለብሰው ቀይ ቦኔት ባደረጉ የጸጥታ አባላት ተይዘው፣ ሰሌዳ በሌለው ተሽከርካሪ ጦር ኃይሎች አካባቢ በተለምዶ “ራሺያ ካምፕ” ተብሎ በሚጠራው የመከላከያ ሰራዊት አባላት መኖሪያ እንደቆዩ አስረድተዋል። ከዚያ ቀን ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ እና የፌዴራል ፖሊስ ጣቢያዎች ቢያፈላልጓቸውም በምን ምክንያት እንደተያዙ ለማወቅ ሳይቻል፣ ለ2 ወራት ከቆዩ በኋላ ጥቅምት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ተለቀዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሌላው ተጎጂ ነሐሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሚሠሩበት አካባቢ ሲቪል እና የደንብ ልብስ ለብሰው ቀይ ቦኔት ባደረጉ የጸጥታ አካላት በተለምዶ “ፓትሮል” በሚባል ተሽከርካሪ በግዳጅ ተወስደው ባልታወቀ ቦታ ከቆዩ በኋላ፣ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ተለቀዋል።

ሌላ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ተጎጂ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ እና ባለትዳር ሲሆኑ፣ ታኅሣሥ 24 ቀን 2016 ዓ.ም.  እኩለ ቀን ላይ በተለምዶ “ስታዲየም” በሚባለው አካባቢ ከሚሠሩበት ቦታ ሲቪል በለበሱና ሽጉጥ በታጠቁ፣ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ በለበሱና ቀይ ቦኔት ባደረጉ የጸጥታ አካላት ሰሌዳ ቁጥር በሌላቸው ዳለቻ ቀለም እንደሆኑ በተገለጸና በተለምዶ “ሎንግቤዝ” እና “ፓትሮል” ተብለው በሚጠሩ መኪናዎች ተጭነው ተወስደው፣ ከ6 ወራት እስር በኋላ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ተለቀዋል።  

በተመሳሳይ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ተጎጂ ከግል የሥራ ቦታቸው የተወሰኑት ሲቪል እና ሌሎች የደንብ ልብስ በለበሱና በታጠቁ የጸጥታ አካላት መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተያዙ በኋላ፣ ዐይናቸውን በጨርቅ ተሸፍነው ተወስደው ያሉበት ሳይታወቅ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቆዩ በኋላ፣ በድጋሚ ዐይናቸውን በጨርቅ ተሸፍነው አዲስ አበባ ከተማ፣ “ኃይሌ ጋርመንት” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንዲወርዱ መደረጋቸውን አስረድተዋል።


(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

🌍በሳፋሪኮም ሮሚንግ ጥቅሎች የውጭ ሃገር ቆይታችንን ያለስጋት እናሳልፍ! በአፍሪካ ፣ በአውሮፓ ፣ በእስያ እና በሰሜን አሜሪካ ወዳሉ የተመረጡ ሃገራት ስንጓዝ ሳፋሪኮም አብሮን ነው! ከዳር እስከ ዳር አለምን ከአስተማማኙ ኔትወርክ ጋር እንቃኝ!

የቴሌግራም ቦታችንን https://t.iss.one/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#1Wedefit #Furtheraheadtogether
“ ጡረታ፣ ህክምና ይከበርልን። እኛ ወድቀናል፤ ከስረናል፤ ከሽፈናል። ቢያንስ እንደ ዜጋ እንታከም ” - የሶማሌ ክልል ቀድሞ ሰራዊት አባላት

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶማሌ ክልል ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር የአጀንዳ ማሰባሰብ የውይይት መድረክ አድርጎ ነበር።

በዚህ መድረክ ከተሳተፉት ባለድርሻ አካላት መካከል አንዱ የሶማሌ ክልል የቀድሞ ሰራዊት አባላት ነው።

ኮሚሽኑ ስለቀድሞ ሰራዊት ጉዳይ ምን ማተኮር እንዳለበት፣ ስለታጠቁ ኃይሎችና የመንግስት አካሄድ የተመለከቱ ጥያቄዎች ያቀረብንላቸው የክልሉ የቀድሞ ሰራዊት አባላት ሊቀመንበር ሻለቃ ሴባ ቶንጃ ምላሽ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

ሥርዓት ሲወድቅ የሚወድቅ ሥርዓት ሲነሳ የሚነሳ ሰራዊት ካለ ሀገርና ሕዝብ ዋስትና የለውም። ማንም እንደገባ ከዚያም ከዚህም ያዋክበዋል፤ ህዝብ ጉዳት ያደርስበታል።

ቀጣዩ ትውልድ እንዴት ይኑር? ለምን በባንዲራ እንጨቃጨቃለን? ከጥንት ጀምሮ ቅድመ አያቶቻችን ያወረሱን ነው እዚህ ላይ ያለው ስህተት ምንድን ነው? ለምን በአድዋ ድል እንጨቃጨለን? ስህተት ካለ ተመካክረን እናስተካክል እንጂ ለምን እንጋደላለን ?... በሚል ለሀገር የሚጠቅም አጀንዳ እየቀረጽን ነው።

ጡረታ ያልተከበረልን ነን፤ ጡረታ ይከበርልን፤ እንደዜጋ ለሀገር አገልግለናል፤ ሜዳ ላይ መውደቅ የለብንም። አሁንም እየተጠራን እየተሳተፍን ነው።

እኛ ለሀገር አሁንም ዝግጁ ነን፤ አላኮረፍንም፡፡ ሁሉም በእኩልነት ይታይ፡፡ የተወሰኑትን ብቻ መዞ ይዞ የተወሰነው ጭራሽ እስከነመፈጠሩም ይረሳል፡፡

ጡረታ ይከበርልን፤ ህክምና ይከበርልን፤ እኛ ሁሉን ትተን ለሀገር ብለን ስለንዘምት የነበረ ተማሪ አሁን ዶክተር ፕሮፌሰር ነው። እኛ ወድቀናል፤ ከስረናል፤ ከሽፈናል። ቢያንስ እንደ ዜጋ እንታከም። እኛ ስንዋጋ ተምረው ዶክተር የሆኑ ያክሙን።

መንግስት የሕክምና፣ የጡረታ ዋስትና ይስጠን። ከራሳችን ገንዘብ ተቆርጦ ገቢ ሲሆን የነበረውን ተከልክለናል። ይህ ይስተካከል።

እንደዜጋ በክብር እንኑር። በመስሪያ ቤቶች ተቀጥረን ጥበቃ ለመስራት እንኳ የታገደበት ሁኔታ ነበር፤ ‘እንዳይቀጠሩ’ የሚል። ዜጋ ነን፣ ይሄ ያሳምጻል ነገር ግን አላመጽም በሀገራችን አናምጽም፤ ህዝብ ይበጠበጣል ብለን።

ችግራችንን አምቀን ይዘን አሁንም ለህዝባችን ደኀንነት እየታገልን ነው።

ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ግጭቶች በአያያዝ ስህተት የተፈጠሩ እንደሆኑ እናምናለን። በአጠቃላይ የእርስ በእርስ ግጭት የወንድማማቾች እልቂት አንደግፍም። 

እገሌ እገሌ የሚል ስያሜ መንግስት ይስጠው እኛ የወንደማማቾች ግጭት አንደግፍም፡፡ ግን መጥተው ህዝቡን እንዲጨፈጭፉና ተቋም እንዲያወድሙም አንፈልግም፡፡ 

ይልቁንም ወደ መድረክ እንዲመጡ እንፈልጋለን፡፡ ለዚያ ደግሞ መንግስት በሆደ ሰፊነት ቀረብ ብሎ መሳብ ያስፈልጋል። ግጭት እስከወዲያኛው ይቁም።

አሁን የተፈጠረው ግጭት በአያያዝ ስህተትነው የተፈጠረው አይፈጠርም ነበር፡፡ ለምሳሌ ጊዜውን መጠበቅ ሲገባ ያልበሰለ አጀንዳ ወደ ህዝብ ይለቀቃል፡፡ 

በሚስጥር ተይዞ ቆይቶ በኋላ ሁኔታው ሲፈቅድ መልቀቅ ነው እንጂ ጊዜውን ያልጠበቀ አጀንዳ ከለተለቀቀ ግጭት ይፈጥራል፡፡ ጊዜውን ያልጠበቀ አጀንዳ መዓት ነገር ነው፡፡ 

ለምሳሌ ፦ ለመጥቀስ የፋኖም ራሱ ጊዜውን ያልጠበቀ አጀንዳ ሆኖ በግድ ስለተኬደበት እንጂ አይዋጉም ነበር፡፡ ትላንትና ራቁቱን የተባረረውን መካላከያ ሰራዊትን ያዳኑ እነርሱ አይደሉምን ?

አሁን የተፈጠረውን ብቻ ኮንነን መንግስት ይውደደን ብዬ አልናገርም፡፡ ሚዛናዊ ህሊና አለኝ፡፡ አሁን የሚሰሩት ሥራ ጥሩ ነው እያልኩ ሳይሆን ወደ መጥፎ ተገፋፍተው በእልህ የተገፉት ነገር ጥሩ ስላልሆነ ነው፡፡ 

በእርግጥ አሁን መንግስት ጥረት እያደረገ ነው በዚሁ ይቀጥል፡፡ ወደ ሰላም ቢያመጣቸው ጥሩ ነው፡፡ 

መጪው ትውልድ በሰላም እንዲኖር ከእንግዲህ በአገራችን የወንድማማቾች ጦርነት እንድናይ፣ እኛ ያየነው ችግር በእነርሱ ላይ እንዲደርስ አንፈልግም፡፡

ሁሉም የበኩል ድርሻ ተቀብሎ መንግስትም ያለውን ስህተት አርሞ ብለድርሻ አካላት በሙሉ ለሰላም አስተቃጽኦ አድርገው ከተንቀሳቀሱ ሰላም ይመጣል፡፡ ይህ ካልሆነ ከዚህ በባሰ እንጠፋፋለን፡፡ አሁን በዚህ ውይይት መፈታት አለበት ከዚህ ካለፈ አካሄዱ አያምርም፡፡

ከተሞክሯችን ተነስተን ነው መልዕከት የምናስተላልፈው፡፡ እሳት የጎረሰ መሳሪያ ይዘን ውሃ ጠምቶን ለምነን እየጠጣን ነበር፡፡

ከደረሰብን ጉዳት አንጸር እኛ ለመሸፈት ነበርን ቅርብ፡፡ አሁንም ቢሆን አኩርፈን ለመሄድ እኛ ነን ቅርብ፡፡ ጸጉራችንን ተላጭተን እድሜያችንን የጨረስነው በርሃ ውስጥ ነው፡፡

በውጊያ አውድ ያሉ አካላት እርግጥ ምክንያት ኖሯቸው ትግል ቢጀምሩም የትኛውም ግጭት ሂዶ ሂዶ በስምምነት መጠቃለሉ አይቀርም፡፡ ዞሮ ዞሮ ሰላም ይመጣል፤ በእድሜያችን እያየን ያለነው ይሄው ስለሆነ፡፡ ከብዙ መተላለቅ ይልቅ ለስምምነቱ፣ ለእርቁ፣ ለውይይቱ እድል ቢሰጡ ጥሩ ነው"
ብለዋል።

ምን ያክል ቀድሞ ሰራዊት አባላት አሉ ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ በምላሻቸው “ ባለንበት አካባቢ በርካታ የቀድሞ ሰራዊት አባላት አሉ፡፡ ወደ 5 ሺሕ የሚሆኑ አሉ ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ንፁኃንን ያለ አበሳቸው የማይገባቸውን ሰቆቃና ፍዳ እየከፈሉ ነው ! "

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ምን ጠየቀ ?

ከተጀመረ ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረውና በአማራ ክልል በሁለት ተፋላሚ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት እየደረሰ ያለውን የከፋ የመብት ጥሰት፣ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ምርመራ እንዲያደርጉበት በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ጠይቋል።

ከሰሞኑን ፎረሙ በጦርነት እየታመሰ ባለው የአማራ ክልል የጤና ተቋማትና አገልግሎት ላይ እየደረሰ ነው ላለው ቀውስ ምላሽ መስጫ ስትራቴጂ ይፋ አድርጓል፡፡

ይፋ በተደረገው ባለ 45 ገጽ ስትራቴጂ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ዩኒሴፍ፣ የአለም ጤና ድርጅት፣ የተመድ የሥነ ሕዝብ ድርጅት፣ የአማራ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተሳትፈውበታል፡፡

ፎረሙ በስትራቴጂክ ሰነዱ ምን አለ ?

➡️ የጤናው ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ተደቅኖበታል።

➡️ በጦርነት ምክንያት በርካታ የጤና ተቋማት ሥራ አቁመዋል።

➡️ ከ1,100 በላይ ሠራተኞች ተፈናቅለዋል ፤ ተገድለዋል።

➡️ ከ5,000 በላይ ሰዎች ለፆታዊ ጥቃት ተጋልጠዋል። ይህ ቁጥር የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት ውስጥ ወደ ጤና ተቋም የመጡትና የተመዘገቡትን ብቻ የሚይዝ ነው።

➡️ በቀጠለው የደኅንነትና የፀጥታ ሥጋት የተነሳ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትና የልማት አጋሮች በክልሉ የሚያደርጉት እንቅስቃሴና ድጋፍ በጊዜያዊነት ለማቆም እየተገደዱ ነው።

➡️ በጦርነቱ በመንገድ መዘጋት ምክንያት ወደ ክልሉ የሚላኩ መድኃኒቶችና የሕክምና መሣሪያዎች እንዳይገቡ ከመገደቡ ባሻገር፣ ከክልሉ ዋና ከተማ ባህር ዳር ወደ ዞንና ወረዳዎች ለመላክ አስቸጋሪ ሆኗል።

➡️ በርካታ የጤና ተቋማት በክልሉ ዝቅተኛውን የጤና አገልግሎት እንኳ ለህዝቡ ማቅረብ ተስኗቸዋል።

➡️ በሱዳን የሚካሄደውን ጦርነት ፈርተው ወደ አማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር መተማ የገቡ ሱዳናውያን ቁጥር ከ140 ሺሕ በላይ ደርሷል። የስደተኞች ቁጥር የጤና አገልግሎት ችግሩን አባብሶታል።

➡️ የኮሌራ በሽታ በክልሉ በ12 ዞኖችና በአራት የከተማ አስተዳደሮች ተከስቷል። የኮሌራን በሽታ ለመቆጣጠር አልተቻለም።

➡️ የአማራ ክልል ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦርነት ውድመት ካለማገገሙ ባሻገር የሱዳን ጦርነት አማራ ክልል የቀጠለው ጦርነት፣ ድርቅ፣ ወባና ኩፍኝ ክልሉን አደጋ ውስጥ ጥለውታል።

➡️ መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ጨምሮ ሁሉም የሰብዓዊ ድጋፎች ያለምንም መስተጓጎልና ክልከላ ለሕዝቡ ተደራሽ እንዲሆን በጦርነት ውስጥ ያሉ ሁሉ ወገኖች ተባባሪ ሊሆኑ ይገባል።

የፎረሙ ዋና ጸሀፊ ታፈረ መላኩ (ዶ/ር) ለሪፖርተር በሰጡት ቃል ፥ " ንፁኃንን ያለ አበሳቸው የማይገባቸውን ሰቆቃና ፍዳ እየከፈሉ በመሆኑ፣ ሁለቱም ውጊያ ላይ ያሉ ወገኖች ያለምንም መስተጓጎል የጤና እና ሌሎች የሰብዓዊ አገልግሎትና አቅርቦቶችን ለሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እንዲደርሱ መፍቀድ አለባቸው " ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ፤ ሰነዱ በውጊያ ላይ ያሉ ሃይሎች ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ሕጎችን እያከበሩ ባለመሆኑ ይህን እንዲያከብሩ የሚጠይቅ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡

አክለውም " የሴቶች መደፈር ትልቅ የሆነ ልብ የሚሰብር የመብት ጥሰት በመሆኑ ይህን ጉዳይ የመብት ተቆርቋሪዎች ሊመረምሩት ይገባል " ብለዋል፡፡

" የጤና ባለሙያዎች ደኅንነታቸው ሊከበር ይገባል ፤ የጤና ተቋማት በጦርነቱ ምክንያት በገጠማቸው የግብዓት አቅርቦት የደኅንነት ችግር የትራንስፖርት ችግርና የሰው ኃይል ችግር የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዳይሰጡ አድርጓቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" የጤና ተቋማት አምቡላንስ በጣም በሚያሳዝን መንገድ ከተፈለገው ዓላማ ውጭ እየዋለ በመሆኑ ይህ ሊታረም ይገባል " ብለዋል፡፡

" በሰነዱ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ተብሎ የቀረበው ሰነድ በጤና ተቋማት የመጣውን ብቻ የያዘ ስለመሆኑ የሚገልጽ ነው። የሰብዓዊ ቀውሱን ሙሉ መረጃ የማያሳይ ቁንጽል መረጃ በመሆኑ የሰብዓዊ ተሟጋች ድርጅቶች  የመብት ጥሰቱን እንዲመረምሩ ጥሪ እናቀርባለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ስትራቴጂክ ሰነዱ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ችግሩን ተረድቶ ጫና እንዲያደርግና ሕጎች እንዲከበሩ በሚል ታስቦ የተዘጋጀ ነው። #ሪፖርተር

@tikvahethiopia
" አደጋው በሸገር የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ነው የደረሰው ፤ እስካሁን የአንድ ሰው ህይወት አልፏል " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ' አዲሱ ገበያ ' አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

አደጋው በሸገር የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ መድረሱን ፖሊስ ጠቁሟል።

በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ገልጿል።

" እስካሁን በአደጋው የ1 ሰው ህይወት አልፏል " ያለው ፖሊስ " የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ነው " ብሏል።

ፖሊስ ከአደጋው ጋር የተያያዙ ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ ለህዝብ እንደሚገልጽም ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጠው ቃል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አደጋው በሸገር የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ነው የደረሰው ፤ እስካሁን የአንድ ሰው ህይወት አልፏል " - ፖሊስ በአዲስ አበባ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ' አዲሱ ገበያ ' አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል። አደጋው በሸገር የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ መድረሱን ፖሊስ ጠቁሟል። በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ…
የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኤ ኤም ኤን በሰጡት ቃል ፥ ከሰሜን ሆቴል ወደ አዲሱ ገበያ ይሄድ የነበረ ኮድ 3 43994 ሸገር ባስ ላይ ነው አደጋው የደረሰው።

እስካሁን የ1 ሰው ህይወት አልፏል። እድሜው ከ36 እስከ 40 የሚገመት ነው።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ህክምና ተቋም ተልከዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BRICS+ 16ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በሩሲያ ይጀመራል። የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ለመሳተፍ ካዛን ከተማ ገብተዋል። ከኢትዮጵያ መሪ በተጨማሪ ፥ - የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን - የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬድራ ሞዲ - የደቡብ አፍሪካው ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ ሩስያ፣ ካዛን ገብተዋል። የቻይናው…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ካዛን ፦ ከ16ኛው የ #BRICS+ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሀገራት መሪዎች የተናጠል ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በተጨማሪም ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፦
° ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ፕሬዜዳንት  ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን ፣
° ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ
° ከኢራን ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዥሺካን ... ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

ቪድዮ ፦ አርቲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray🚨 በሓውዜን ወረዳ በተጣለ ተተኳሽ #የ4_ሰዎች ህይወት ጠፋ።   በትግራዩ ጦርነት ምክንያት በየቦታው የተቀበሩ እና የተጣሉ ተተኳሾች ፣ ፈንጂዎች አሁንም በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረሳቸው ቀጥሏል። ሰኔ 1/2016 ዓ.ም በትግራይ ክልል በምሰራቃዊ ዞን ፤ ሓውዜን ወረዳ ማይጎቦ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በፈነዳ ተተኳሽ የ4 ወገኖች ህይወት #ተቀጥፏል። ከአራቱ የአደጋው ሰለባዎች ሶስቱ የአንድ…
#ትግራይ

" ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ ብቻ ባልመከኑ ተተኳሾች ከ51 በላይ ወገኖች ሲቀጠፉ ፤ ከ286 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት ሰለባ ሆኗል " - በትግራይ ማእከላይ ዞን የየጭላ አበርገለ ወረዳ የፀጥታ ፅ/ቤት

በትግራይ በነበረው አውዳሚ እና አሰቃቂ ጦርነት ወቅት ተቀብረው እና ተጥለው ያልመከኑ ተተኳሾች የንፁሃን ዜጎችን ህይወት መቅጠፍና አካል ማጉደል ቀጥለዋል።

በየጭላ አሸርገለ ወረዳ የእምባ ሩፋኤል ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ አርሶ አደር ባልመከነ ተተኳሽ 2 ልጆቻቸው ሲያጡ አንዱ ቆስሎ ተርፎላቸዋል።

ሌላዋ እናት ቁርስ አብልተው ለእንጨት ለቀማ የላኩዋቸው ልጆቻቸው አንዱ በተጣለ ተተኳሽ ሲሞት ሌላኛው የአካል ጉዳተኛ ሆኗል።

በጦርነቱ ወቅት በአከባቢው በነበረው የጦር መሳሪያ ዲፓ የቀሩ የተጣሉና የተቀበሩ በርካታ ያልመከኑ ተተካሾች መኖራቸው የጦቆሙት የጥቃቱ ሰለባዎች ፤ በሰው እና በእንስሳ ከፍተኛ አደጋ በማድረስ የሚገኘው ተተኳሽ እንዲወገድላቸው ጠይቀዋል።

የክልሉ እንዲሁም የፌደራሉ መንግስት የአደጋው አስከፊነት በመረዳት አከባቢያቸው ከተተካሾች እንዲታደጉላቸውም ተማፅነዋል።

የወረዳው የፀጥታ ፅ/ቤት የአርሶ አደሮቹ አስተያየት በመጋራት ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ ከ51 በላይ ወገኖች ባልመከኑ ተተኳሾች ህይወታቸው ሲቀጠፍ ፤ ከ286 በላይ ደግሞ ለአካል ጉዳት እንደተጋለጡ ገልጸዋል።

" ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ ነው " ያለው ፅ/ቤቱ ህዝቡ ከስጋት ድኖ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ መንግስትና ለጋሽ ደርጅቶች አከባቢውን ከተተኳሾች ለማፅዳት የበኩላቸው እንዲተባበሩ ጠይቋል።

" ዘላቂው መፍትሄ በአከባቢው ላይ ያለውን ተተኳሽ ማፅዳት ነው ፤ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት የወዳደቁና የተቀበሩ ተተኳሾችን በማስወገዱ በኩል አከባቢያችን ትኩረት ያሻዋል " ሲል ፅ/ቤቱ አስገንዝቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከድምፂ ወያነ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዶላር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዶላር ዋጋ አሽቆለቆለ። ባለፉት በርካታ ቀናት በንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ112 ብር ከ3957 ሳንቲም እየተገዛ በ123 ብር ከ6353 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር። ዛሬ ባንኩ ይፋ ባደረገው የዕለታዊ የምንዛሬ ተመን አንዱን የአሜሪካ ዶላር የሚገዛበትን ዋጋ ወደ 113 ብር ከ1308 ሳንቲም አሳድጎ መሸጫውን ወደ 115 ብር ከ3934 ሳንቲም አውርዶታል። እንደ ዛሬው…
#ExchangeRate

የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ጭማሪ አሳየ።

ባለፉት ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ113 ብር ከ1308 ሳንቲም እየተገዛ በ115 ብር 3934 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር።

ዛሬ ይፋ በተደረገው የምንዛሬ ዋጋ ተመን አንድ ዶላር መግዣው ከ3 ብር በላይ ጨምሮ  116 ብር ከ6699 ሳንቲም የገባ ሲሆን መሸጫው ከ3 ብር በላይ ጨምሮ 119 ብር ከ0033 ሳንቲም ገብቷል።

በተመሳሳይ በሌሎችም የውጭ ሀገር የገንዘብ ምዛሬ ላይ ጭማሪ ታይቷል።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ ፦ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የነዳጅ ማደያዎች እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠንን ከትላንት ጀምሮ ይፋ ማድረግ ጀምሯል።

አሁን ላይ በከተማዋ 123 ማደያዎች ግልጋሎት እየሰጡ ነው ተብሏል።

ቢሮው ፤ " በየዕለቱ የነዋጅ ማደያዎችን እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠን ይፋ ማድረግ የተጀመረው በአገልግሎቱ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም የተገልጋች እንግልት ለመቀነስ ነው " ብሏል።

ነዳጅ ማደያዎች የት ቦታ እንደሚገኙ እና በእለቱ የተራገፈው ነዳጅ መጠን እንዲሁም የጥቆማ ስርዓቱ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ እንደሚገለጽ አሳውቋል። ሚኒስቴሩ ፤ " በ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ይገለጸል " ብሏል። ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል። @tikvahethiopia
#MoE

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.iss.one/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity