TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
"ገንዘቡ ስላልሞላልኝ ልጄ በህመም እየተሰቃዬ ይገኛል " - ልጃቸው በጠና የታመመባቸው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሁለት ዓመት ልጃቸው በሁለት የልብ ክፍትት ህመም በጠና የታመመባቸው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህር ገ/መድህን መብርሃቱ ለህክምና 665 ሺህ ብር ተጠይቀው ከዚህ ቀደም እናንተኑ እርዳታ ጠይቀው ነበር። ላደረጋችሁላቸው እርዳታም በቅድሚያ ልባዊ ምስጋና አቅርበውላችኋል። ሆኖም ልጃቸው በቶሎ መታከም…
#ተመስግናችኋል🙏

" የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍና ጸሎት ልጄን ከአስከፊው የልብ ህመም ታድጎልኛል " - የመቐለ የኒቨርሲቲ መምህር

የሁለት ዓመት ከ5 ወር ልጃቸው ታሞባቸው የነበሩ የመቐለ ዩኒቨርሲቲው መምህር አቶ ገ/መድህን መብርሃቱ ለህክምና የተጠየቁት ገንዘብ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ድጋፍ እንድታደርጉላቸው እናንተኑ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ተማጽነው ነበር።

" የልጅነት ልጄን አድኑልኝ። ሁለት የልብ ክፍተት ህመም አለበት፤ ለህክምና 665 ሺህ ብር ተጠይቄአለሁ " ነበር ያሉት።

የህፃኑ አባት ዛሬስ ምን አሉ ?

ልጃቸው ህክምናውን ማጠናቀቁን ገልጸው ልባዊ ምስጋና አቅርበውላችኋል።

" የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍና ጸሎት ልጄን ከአስከፊው የልብ ህመም ታድጎልኛል። አመሰግናለሁ " ነው ያሉት።

" ለሁሉም በዚህ የእርዳታ ጥሪ የተሳተፋቹ ወገኖቼ በሙሉ ከመሬት እጅጉን ከፍ ከሰማይ ደግሞ ዝቅ ያለው ምስጋናዬ ይድረሳቹ ፈጣሪ ጤናችሁን፣ ፀጋችሁን አብዝቶ ይባርክ " ሲሉ መርቀዋል።

ልጃቸው ህፃን ኢዮብ ገ/መድህን በሁለት የልብ ክፍተት (VSD+PDA) ሲሰቃይ ነበር።

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

ስለ ብርሃን ስኩልፔይ (school pay) በጥቂቱ፤
#ለወላጆች ወይም #ለተማሪዎች የትኛውም ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ የትምህርት ቤቱን መለያ ኮድ በመጠቀም የትምህርት ክፍያዎችን መክፈል፤ የክፍያ ማረጋገጫዎችን፤ የክፍያ ሪፖርቶችን እና ተያያዥ መረጃዎችን በእጅዎ ባለው ስልክዎ በቀላሉ ማግኘት ያስችልዎታል፡፡

#ለትምህርት_ቤቶች ደግሞ ክፍያ ሲፈጸም ደረሰኝ ይዞ መሄድ ሳያስፈልግ ት/ቤቱ ሁሉንም ክፍያዎች በስኩልፔይ ሲስተም ማየት እና በቀላሉ መቆጣጠር ከማስቻሉም በላይ ሙሉ የሆነ የተማሪዎችን መረጃ በመያዝ ምቹ አሰራርን ይፈጥራል፡፡

ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube
መንግስት አልፈጽምም ቢል ለኢትዮጵያ ህዝብ የማሳወቅ ኃላፊነት ተሰጥቶታል” - ኮሚሽኑ

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ አጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር መድረክ ምዕራፍ ዛሬ በይፋ መጀመሩን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም አብስረዋል።

እስከ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ/ም ባሉት ቀናትም ከክልሉ 10 የማህበረሰብ መሰረቶችን የወከሉ ከ2,000 በላይ ተሳታፊዎች በጅግጅጋ፣ በጎዴ እና ዶሎ አዶ ማዕከላት ተከፋፍለው ከወከሉት ማህበረሰብ ባመጧቸው አጀንዳዎች ይመካከራሉ።

በአጠቃላይ የምክክሩን የመጨረሻ ውጤት መንግስት አልቀበልም ቢል የምክክሩ ውጤት ተፈጻሚነት የማግኘት እድል አይኖረመውም የሚሉ ስጋቶች ሲሰነዘሩ ይስተዋላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ኮሚሽኑ አስገዳጅ አንቀጽ አለው ወይ ? ሲል ለኮሚሽነር መላኩ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን እሳቸውም ምላሽ ሰጥተዋል።

“ አስገዳጅ አንቀጽ አለው። ቢቲውን ዘላይንስ ማንበብ አለብን። እንደገና ደግሞ ሕግን ስንተረጉም ብሮዴሊ ነው መተርጎም ያለብን። ለኮሚሽኑ የተሰጠው ስልጣን ሪሊይ ከፍተኛ ነው። 

ምክንያቱም በሀገራዊ ምክክር ጉባዔው የተካሄዱ ምክክሮችና አውት ካሞች በስርዓት ተሰንደው፣ ከዚያ በኋላ  የማፈጸሙበት የአተገባበር እቅዱ ወጥቷላቸው መሬት ላይ እስከሚወርዱ ድረስ የመከታተል ኃላፊነት የኮሚሽኑ ነው ይላል።

ዝም ብሎ የሀገራዊ ምክክር ጉባዔው በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል ብሎ አሳውቆ የሚገባ ብቻ ኮሚሽን አይደለም። 

ውጤቶቹ መፈጸማቸውን እስከሚረጋገጥ ድረስ የሚሄድ ኮሚሽን ነው። መንግስት አልፈጽምም ቢል ለኢትዮጵያ ህዝብ የማሳወቅ ኃላፊነት ተሰጥቶታል። 

የተመካከርክበት ጉዳይ ይሄ ነው፤ የወሰንከው ጉዳይ ይሄ ነው፣ ውሳኔህን አስተላልፈናል፤ ውሳኔህን ተፈጻሚ ለማድረግ ያልፈለገ ወገን አለ፤ ይሄ ወገን ደግሞ ይሄ ነው፤ ብለን ማሳወቅ ነው።

ለዚህም ነው ይሄ ምክክር የኢትዮጵያ ህዝብ መብቱን የሚያረጋግጥበት ሂደት፣ ባለቤትነቱን የሚያረጋግጥበት ሂደት መሆን ያለበት።


የተወሰኑ ሰዎች የሚወስኑበት አግባብ ከዚህ በኋላ ማቆም አለበት። መጨረሻም የጉዳዩ ባለቤት ወደሆነው ወደ ህዝብ ነው የምናመጣው። ህዝቡ ግፊት እንዲያደርግ፣ እንዲፈጸም እንዲጠይቅ ማለት ነው ” ብለዋል።

የታጠቁ ኃይሎች በምክክሩ እንዲሳተፉ ጥሪ ከተደረገላቸው ኮሚሽኑ ጋር ለመመካከር ፈቃደኞች ናቸው ? ሲል ቲክቫህ ላቀረበው ጥያቄ የኮሚሽነሩ በምላሻው፣ “ ጥረት እየተደረገ ነው ” ብለው ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ጦርነቱ፣ ግጭቱ፣ ግድያው፣ እገታው፣ መፈናቀሉ እንደቀጠለ ከመሆኑ አንጻር የኮሚሽኑ የምክክር ውሰኔ ውጤት ዘገዬ የሚል አስተያዬት ሲዘነዘር ይስተዋላልና ኮሚሽኑ ምላሹ ምንድን ነው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።

በዚህም፣ “ አልዘገዬም። ምክንያቱም ሀገር ነው የምንመሰክረው ” ነው ያሉት።

“ ኢትዮጵያ ትልቅ ናት የህዝብ ቁጥር ብዙ ነው። ሁሉም መሳተፍ አለበት እያልን ነው። እስከዛሬ ድረስ እንኳ ከ180 ሺሕ በላይ በቀጥታ ያገኘናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ። ይሄ ትልቅ ቁጥር ነው ” ሲሉም አክለዋል።

የ3 ሺሕ ዘመናት ችግር በ3 ዓመታት ለመፍታት አሁን ዘገዬ መባል እንደሌሉበት አስረድተው፣ “ ችግሩ መፈታት አለበት በእርግጥም። እኛ ከተመደበልን ከተርማችን ማለው አንፈልግም። በዚያ ጊዜ ውስጥ አንድ ነገር ለመስራት አስበናል ” ነው ያሉት።

ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል እያደረገው ስላለው አጀንዳ የማሰባሰብ የምከክር መድረክ መረጃ የምናቀብላችሁ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ " በቀን ከ500 እስከ 600 ህሙማን ይስተናገዳሉ " - አማኑኤል ሆስፒታል በየዓመቱ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 10 የሚከበረው " የዓለም የአዕምሮ ጤና ቀን " ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ " በሁሉም የሥራ ቦታ ቅድሚያ ለአዕምሮ ጤና ጊዜው አሁን ነው " በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል።  በኢትዮጵያ ጫፍ እስከ ጫፍ ያሉ የአዕምሮ ህሙማን ወገኖችን በማከም የሚታወቀው አማኑኤል ስፔላይዝድ የአዕምሮ ህሙማን…
#አማኑኤልየአዕምሮስፔሻላይዝድሆስፒታል

" በአብዛኛው ዋርድ ያሉት ህሙማን ወንዶች ናቸው። በሦስቱ ዋርዶች ሴቶች፣ በአስሩ ዋርድ ደግሞ ወንዶች የአዕምሮ ህሙማን ናቸው ያሉት " - ሆስፒታሉ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሆስፒታሉን የውስጥ ግንባታዎች እያከናወነ መሆኑ ከዚህ ቀደም መነገሩ ይታወሳል።

በዚህም ታካሚዎች የውስጥ ግንባታ መጠናቀቁና አለመጠናቀቁን ሲጠይቁ የተስተዋሉ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም እድሳቱ ከምን ደረሰ ተጠናቀቀ ወይስ ገና ነው? ሲል ለሆስፒታሉ ጥያቄ አቅርቧል።

ሆስፒታሉ በሰጠን ቃል፣ " ውስጥ ላይ ያለ የተወሰነ የማስፋፊያ ግንባታ አለ። አሁን በቅርቡ ተመርቆ ወደ ሥራ ይገባል " ብሏል።

" ጥቅምት መጀመሪያ አካባቢ ይጠናቀቃል " ሲል አክሏል።

ህክምና የሚሰጠው ጠባብ በሆነ ቦታ መሆኑ በእጅጉ ፈታኝ እንደሆነበት አስረድቶ፣ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠውም አሳስቧል።

" እንደ ስትራቴጂ በእርግጥ ጤና ሚኒስቴር የያዘው ጉዳይ አለ። ሁሉም የጤና ተቋማት ባሉበት ቦታ የአዕምሮ ህክምና ልክ እንደ ማንኛውም ህመም መሰጠት አለበት የሚል አቅጣጫ ተይዟል " ሲልም ገልጿል።

" ይህ ጥሩ ነገር ነው። ምክንያቱም በሆስፒታሉ ያለውን ጫና ስለሚቀንስ " ብሎ፣ ' ሁሉም የሚሰጡ ከሆነ ከጫናው ባለፈም ማንኛውም ሰው ለትራንስፖርት ወጪ ሳይዳረግ፣ ጉልበቱ ሳይበዘበዝ፣ ማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ክስረት ሳይደርስበት በአካባቢው የሚታከምበት ሁኔታ እንዲፈጠር ይረዳል " ነው ያለው።

" ግን አሁን ያም ቢሆን በአጥጋቢ ሁኔታ እየተሰራ ነው ብሎ መውሰድ አይቻልም፣ ተጠናክሮ ሊሄድ ይገባዋል የሚል መልዕክት አለኝ " ሲል አሳስቧል።

በሆስፒታሉ የሚገኙት የአዕምሮ ህሙማን በብዛት ሴቶች ናቸው ወይስ ወንዶች ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ሆስፒታሉ ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል።

" እንደኛ ሆስፒታል በአብዛኛው ዋርድ ያሉት ህሙማን ወንዶች ናቸው። ወደ 13 ዋርዶች አሉን።

ከእነዚህ ውስጥ በሦስቱ ዋርዶች ሴቶች፣ በአስሩ ዋርዶች ደግሞ ወንዶች የአዕምሮ ህሙማን ናቸው ያሉት።

ከአስሩ ዋርድ አንዱ የሱስ ታካሚዎች ያሉበት
ነው። "

በሆስፒታሉ እንደ አጠቃላይ ምን ያክል በአስተኝቶ ታካሚዎች አሉ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ " በአንድ ዋርድ ላይ 25 ታካሚዎች ናቸው የሚኖሩት። ስለዚህ 13 በ25 ሲባዛ 325 ይሆናሉ " ነው ያለው።

ከዚህ ቀደም ሆስፒታሉ የአዕምሮ ህሙማን ቁጥር እንደጨመረ ህሙማኑ በአብዛኛው የአፍላ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ መሆናቸው መገለጹ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia #1Wedefit

🥇የሳፋሪኮም #1ወደፊት ዲጂታል ሙዚቃ ውድድር ምርጥ አስሮቹ ታውቀዋል!
የ#1Wedefit ዲጂታል የሙዚቃ ውድድራችን ምርጥ 10  አሸናፊዎች እነዚህ ናቸው! እስቲ 💫 ክዋክብቶቻችንን አብረታቱልን! አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፐርፐዝብላክ ° " ሥራ ላይ የነበሩ ሱቆችም የቤት ኪራይ መክፈል ስላልተቻለ ሊዘጉ ነው " - የፐርፐዝ ብላክ ባለአክሲዮኖች ° " በፍርድ ቤት የተያዘ ጉዳይ ስላለ ምንም  አይነት መግለጫ አንሰጥም " - ድርጅቱ የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ባለአክሲዮኖች፣ የድርጅቱ አካላት መታሰራቸውን ተከትሎ ድርጅቱ ላይ ባላቸው ሼር ላይ ሥጋትና ቅሬታ እንዳደረባቸው፣ ለቅሬታቸው አፋጣኝ ምላሽ  እንዲሰጣቸው በቲክቫህ…
በእነ ፍስሐ እሸቱ (ዶ/ር) ላይ የተመሰረተው ተደራራቢ ክስ ምንድነው ?

የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ የፐርTዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱን (ዶ/ር) ጨምሮ በ10 ግለሰቦች እና ሁለት ድርጅቶች ላይ ክስ መስርቷል።

ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾቹ ፦
1ኛ የፐርTዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱ (ዶ/ር)፣
2ኛ የተቋሙ ም/ስራ አስፈጻሚ ኤርሚያስ ብርሃኑ (ዶ/ር)፣
3ኛ የተቋሙ ቺፍ  ኦፕሬሽን ኦፊሰር እና የቦርድ አባል ወ/ሮ ኤፍራታን ነጋሽን ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ግለሰቦች እንዲሁም ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ እና ኖትር ዲዛይን ሃ/የተ/የግ/ማህበር ናቸው፡፡

ተከሳሾቹ ፦

➡️ በአዲስ አበባ ከተማ መሃል ሜክሲኮ ላይ በ100 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ  ባለ 3 መኝታ ቤት መኖሪያ ቤት በ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚሸጥ መሆኑን በሚዲያ በማስተዋወቅ ሰዎች ቤት ለመግዛት ሲሄዱ "መጀመሪያ ገንዘቡን አስገቡና ውሉን ትመለከታላችሁ " በማለት ከሌሎች ግብረዓበሮቻቸው ጋር በመሆን አሳሳች ቃላቶችን በመጠቀም፣

➡️ ሰዎች ገንዘቡን ካስገቡ በኋላ ደግሞ የአክሲዮን ግዢ ውል እንዲፈርሙ በማድረግ ምንም አይነት የግንባታ ቦታ ባልተረከቡበት ሁኔታ 2 ቢሊየን 234 ሚሊየን 200 ሺህ ብር በመሰብሰብ፣

➡️ ቤቱን ሰርተው ሳያስረክቡ በመቅረት

➡️ ግማሹን ገንዘብ ወደ ውጭ እንዲሸሽ በማድረግ፣

➡️ ኮሚሽን በመቀበልና በማታለል  ወንጀል ተጠርጥረው በአዲስ አበባ ፖሊስ በኩል በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ሲከናወን ነበር።

በዚህ መልኩ ፖሊስ ሲያከናውነው የቆየው የምርመራ ማጣሪያ ሥራ መጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ዐቃቤ ሕግ ተደራራቢ ዝርዝር ክሶችን በየደረጃቸው  አቅርቦባቸዋል።

ከቀረቡ ክሶች መካከል በአንደኛው ክስ ላይ ከ1ኛ - 9ኛ ባሉ ተከሳሾች ላይ እንደተመላከተው በኢፌዲሪ የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ) እና (ለ) እንዲሁም  የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 32 (2) ላይ የተመላከተውን ድንጋጌ መተላለፍ የሚል ክስ ይገኝበታል።

እንደ አጠቃላይ በቀረበው ተደራራቢ ክስ ዝርዝር ችሎት ለቀረቡ 4 ተከሳሾች ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን የተከሳሾቹ ጠበቆች በደንበኞቻቸው ላይ የቀረበውን ክስ ዝርዝር ተመልክተው ዋስትና ላይ ክርክር ለማድረግ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም ዋስትና ላይ የሚደረገውን የግራ ቀኝ ክርክር ለመከታተል ለፊታችን ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ተዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ችሎት ያልቀረቡ ተከሳሾችን ፖሊስ በአድራሻቸው አፈላልጎ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ መስጠቱን #ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ፍስሕ እሸቱ (ዶ/ር) ሀገር ጥለው አሜሪካ ሀገር መግባታቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
" አሻራ የሚቀመጠው ታሪክን በመደምሰስና በሕዝብ ሰቆቃ ላይ አይደለም ! " - አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች

አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ልከዋል።

ፓርቲዎቹ ፦

➡️ እናት
➡️ መኢአድ፣
➡️ ኢሕአፓ፣
➡️ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ ናቸው።

ፓርቲዎቹ ምን አሉ ?

" ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ በመጀመሪያ የወንዝ ዳር ልማትና የጫካ ፕሮጀክት በሚል ተጀምሮ አኹን ላይ የኮሪደር ልማት በሚል መጠኑንና አድማሱን አስፍቶ ሙሉ ከተማ ወደማፍረስ የተሸጋገረው ሥራ አሻራ በማሳረፍ ሰበብ የመቶ ሺህዎችን ሕይወት እያመሰቃቀለ እንደሚገኝ ባደረግነው ዳሰሳ ተረድተናል " ብለዋል።

" በድንገት ቤታቸው የፈረሰባቸውና የይፈርሳል መርዶው ሲነገር ለጠና ሕመም የተዳረጉ፣ ከለመዱት ማኅበራዊ መሠረት የተናጠቡ፣ ሥራቸው ሙሉ ለሙሉ የተቋረጠና ለከፋ ችግር የተዳረጉ፣ ቍጥሩ በውል ያልታወቀ በድንጋጤም የሞቱ እንዳሉ ለመረዳት ችለናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከዋና ባለቤቶች/ባልይዞታዎች ባልትናነሰ ተከራዮች ከፍ ላለ ስቃይ እንደተዳረጉ፣ አካል ጉዳተኞችና አቅመ ደካሞች የከፋ ችግር ላይ መውደቃቸውን ታዝበናል " ሲሉም ጠቁመዋል።

ፓርቲዎቹ " ይዋል ይደር እንጂ ይህ የሕይወት መመሰቃቀል የማይነካው የከተማዋ ነዋሪ እንደማይኖር ለመገመት ነቢይ መሆን አይጠይቅም " ብለዋል።

" አዲስ አበባ በዓለም ሦስተኛዋ ድፕሎማቲክ ከተማ በመኾኗ ንፁሕ መሆን፣ የበለጠ ማማርና መዘመን እንዳለባት ኹሉም የሚቀበለው ሀቅ ነው " ያሉት ፓርቲዎቹ  " ይህ ማለት ግን ከተማው ' ያረጀ ነው፤ የቤቶቹ ግድግዳ ጭቃና እንጨት ነው፤ ሸራ ነው፤ አብዛኛው የመንግሥት ቤቶች ናቸው፤ ...' በሚል ሰበብ በአንድ በኩል አዛኝ በመምሰል በግልባጩ ግን ከተማው ' የእኛ ' አሻራ የለበትም በሚል ከስሁት ትርክት በተወለደ ጥላቻ የማፍረሻ ምክንያት እየፈለጉ የከተማዋን ነዋሪ በማፈናቀልና በአንድ ጀምበር ኑሮውን ወደ ሲዖልነት መለወጥ ፍጹም ተቀባይነት የሌለውም " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈው " ሀገር የምትተዳደርበትን ሕገ መንግሥት (አንቀጽ 40፣ 41፣ 89፣ 90፣ 91፣ 92) እና አዋጅ ቍ. 1161/2011 ዓ.ም በመሠረታዊነት የጣሰና ይጠብቀው ዘንድ ሓላፊነቱን በተቀበለ መንግሥት እየተፈጸመ የሚገኝ ከፍተኛ ወንጀል ነው ብለን እናምናለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቤት ንብረታቸው በአንድ ጀምበር እንዲፈርስ የሚደረጉ ዜጎች በአብዛኛው ካሳም ሆነ ምትክ ቦታ እንዲሁም በቂ የመዘጋጃ ጊዜ ሳይሰጣቸው በማኅበረሰብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ጭምር ለመኖር እየተገደዱና ሌሎች ደግሞ ጊዜያዊ መጠለያ በቆርቆሮ ሠርተው እንዲገቡ መመሪያ የተሰጣቸው መሆኑን ከተረኛ የጉዳቱ ሰለባዎች ለመረዳት ችለናል " ብለዋል።

" ከእነዚህ ዜጎች ‘እድለኛ’ የሆኑ ጥቂቶቹ በማካካሻ መልክ የሚሰጣቸው ኮንዶሚኒዬም ቤት ብዙ 100 ሺዎች ለአሥርት ዓመታት ቆጥበው የተሠራና እጣው ባለመውጣቱ እንጂ ባለቤት ያለው ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።

አራቱ ፓርቲዎች ፥ 

° " በአያገባህም " ስሜት የከተማ ልማት መሪ እቅድ ወደ ጎን ተወርውሮ በጥናትና ስሌት ሳይሆን በስሜት ብቻ ከላይ ወደታች በሚወርድ ውሳኔ፣

° ጥቅምና ጉዳታቸው በዘርፉ ባለሙያዎች ያልተመዘነ፣

° በፕሮግራም/strategy/ ያልተያዙና የአጭር ጊዜ ትርፍ ብቻ ያላቸው (project based) አካሄድ እንዲህ የኑሮ ውድነት፣ የቤት/የቦታ እጥረትና ዋጋ መናር፣ የመጓጓዣ፣ የውሐና መሰል መሠረተ ልማት ችግር ጠፍሮ ለያዛቸው ከተሞች የእግረኛ መንገድ፣ የሕንጻ ላይ መብራትና ቀለም፣ ሣርና ዘንባባ ተከላ እና መሰል የተብለጨለጩ ማሸብረቂያዎች የወረት ያህል ለጊዜው ከላይ ሲታይ ያማረ ቢመስልም የከተማውን ነዋሪ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ችግር ቢያወሳስበው እንጂ እሴት ጨምሮ ችግራቸውን አይፈታውም፤ የሥርዓቱንም ስም አይገነባም ብለዋል።

" ከተማን የማሳመርና ማዘመን ሀሳብ ከየትኛውም ወገን ሊነሳ ቢችልም ከመሪዎች ፍላጎት /inspiration/ በላይ በዘርፉ ልምድና እውቀት ጠገብ በሆኑ ባለሙያዎች ኹለንተናዊ ምልከታና ሙግት ተደርጎበት ትርፍና ኪሳራው ተሰልቶ ሊሆን እንደሚገባ በጽኑ እናምናለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" አሻራ ማኖር በራሱ የሚጠላ ባይሆንም ፖለቲካዊ ፍላጎት የተጫነው፣ ሕዝብን ያገለለ፣ ታሪክን የሚያፈርስ፣ የማኅበረሰብን በዘመናት የተገነባ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የሚያናጋ፣ ነዋሪዎችን በአንድ ጀምበር ጥሪት አልባ የሚያደርግ፣ ብዙ መቶ ሺዎች የሚተዳደሩበትን የንግድ ሥራ ሙሉ በሙሉ የሚገድል፣ ግብታዊና ነዋሪው ‘በአብሬ አድጋለሁ’ ተስፋ ሳይሆን ‘በያፈናቅሉኛል’ ሥጋትና ኹል ጊዜ መጻተኛ ስሜት እንዲሰማው የሚያደርግ መሆን እንደሌለበት የሚታመን ቢሆንም በአዲስ አበባ ከተማ እየተተገበረ ያለው ይህ መራራ እውነት ነው " ብለዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ " አኹን ላይ በአዲስ አበባ በ4ኪሎ፣ 5ኪሎ፣ ፒያሳ፣ ቤላ፣ አምባሳደር፣ ፈረንሳይ፣ ቦሌ፣ ካዛንችስ፣ ገርጂ እና በኹሉም ወንዝ አለባቸው በሚባሉ የከተማዋ አካባቢዎችና በሌሎችም አካባቢዎች በዋና ዋና መንገዶች ዳርቻ  ከፍተኛ ፈረሳዎች እየተካሄዱ/እንደሚካሄዱ በይፋም ይፋዊ ባልሆነ መንገድም እያየንና እየሰማን ነው " ሲሉ ጠቁመዋል።

" በኑሮ ውድነትና ሰላም እጦት ወገቡ የጎበጠን ማኅበረሰብ አለፍ ሲልም ገሃድ የወጣ የከተማ ውስጥ ረሃብ ባለበት በተጣደፈ አኳኋን ዜጎችን ከድጡ ወደ ማጡ መውሰድ ለምን እንደተፈለገ አፍራሾቹ ብቻ የሚገባቸው እውነት ኾኖ ዋናው ግን ልማት ሳይሆን ፦
• ነባሩን ማኅበረሰብ ከማኅበራዊ መሠረቱ መነጠልና ማሳሳት፣
• የእምነት ቦታዎችን ያለሰው ማስቀረት፣
• ሰውን ከመሐል መግፋት ከዳር ማስጨነቅ፣
• መንግሥት የገጠመውን በጀት እጥረት ከሊዝ ሽያጭ መሰብሰብ፣
• ሥርዓቱን ተጠግተው ፍርፋሪ ለሚጠብቁ " የአየር ባየር ባለሀብቶች " ማበልጸጊያ እንደሆነ እሙን ነው " ብለዋል።

" በሌላ በኩል እንደሥርዓት በሀገር ደረጃ ያጣውን ቅቡልነትና ቁጥጥር በማዕከል አለሁ ለማለትና አዲስ የከተማ ትርክት/narration/ ከመፍጠር የመነጨ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቢያንስ ቢያንስ ተነሽዎችን ከአልሚዎቹ/ባለሀብቶች ጋር በመስማማት ከሚሠራው ሕንፃ አንደአቅማቸው የድርሻቸውን አግኝተው እንዲኖሩ ማድረግ በተገባ ነበር " ያሉት ፓርቲዎቹ " እየተፈጸመ ያለው ነገር ኢ ሕገ መንግሥታዊ፣ አግላይ፣ የበላይና የበታች አካሄድ በመሆኑ በጽኑ እናወግዛለን " ብለዋል።

አራቱ ፓርቲዎች ፦

1ኛ. " መንግሥት በሕገ መንግሥቱ የተደነገገውን የዜጎች መብት እንዲያከብርና ማኅበረሰቡን መሠረታዊ በሆነ መልኩ ከሚያናጋ በልማት ሽፋን የሚተገበር ደባ እንዲያቆም " ብለዋል።

2ኛ. " የፈረሳው ሰለባ የሆነው የአዲስ አበባ ነዋሪ ባገኘው አጋጣሚ ኹሉ ድርጊቱን በሰላማዊ መንገድ በመቃወም ሕገ መንግሥታዊ መብቱን እንዲያስከብር " የሚል ጥሪ አቅርበዋል።

3ኛ. " ከቦታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የነበሩበትን ቦታ ካርታና መሰል የነዋሪነት/ባለ ይዞታነት/ ማስረጃዎች በጥንቃቄ እንዲያስቀምጡ " አስገንዝበዋል።

4ኛ. " አዲስ በፈረሱ አካባቢዎች ላይ እየገነችሁ ያላችሁ ባለሀብቶች የተፈናቀለ ወገናችሁ አንድ ቀን ተመልሶ እንደሚመጣ አድርጋችሁ ማሰብም መሥራትም አለባችሁ " ሲሉ አሳስበዋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኮሬ “ ባለፉት ዓመታት ከ300 በላይ ንጹሐን በታጣቂዎች ተገድለዋል ” - ኮሬ ዞን ኮሚዩኒኬሽን  “መንግስት ቸልተኛ ሆኗል የሚል ግምገማ አለን። ዛሬ ጠዋትም ሰው ተገድሏል” - የክልሉ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ  ንጹሐን ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች፣ ዞኑና የክልሉ ተወካዮች ምክር ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በዞኑ ጎርካ ወረዳ ዳኖና ኬረዳ…
#ኮሬ

🛑 “ አሁንም ግድያው እንደቀጠለ ነው። ዛሬም 3 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል” - ኮሬ ዞን

🔵 “ ምንም መፍትሄ የሌለው ጉዳይ ነው የሆነው። ግድያና መፈናቀሉ ቀጥሏል” - በፌደራል ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኮሬ ህዝብ ተወካይ

ዛሬ (ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም) ሦስት ንጹሐን ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ከምዕራብ ጉጂ በተነሱ ታጣቂዎች መገዳላቸውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮሬ ዞን አስተዳደር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል።

“ ችግሩን ማስቆም የሚችል መንግሥት አካል አልተገኘም ” ያሉት አንድ ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ በዞኑ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ አካል፣ በሁለተኛው ዙር የመኸር ወቅት ብቻ 11 ሰዎች ሲገደሉ አራት ደግሞ መቁሰላቸውን ገልጸዋል።

“ ጉዳቱ የደረሰባቸው ቀበሌዎች ዳኖ፣ ጎልቤ፣ ጋሙሌ፣ ኬረዳ፣ ሻሮ ናቸው። በአጠቃላይ ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት በታጣቂዎች ተዘርፏል ” ነው ያሉት።

በአካባቢው ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ የሚፈጸመው ግድያ ለምን ይሆን መቋጫ ያጣው ? ምን እየተሰራ ነው ? የሚል ጥያቄ ያቀረብንላቸው በፌደራል ተወካዮች ምክር ቤት የኮሬ የህዝብ ተወካይ አምዛዬ አወቀ (ዶ/ር) ምላሽ ተሰጥተዋል።
 
“ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ምንም መቋጫ አላገኘም። እኛም በተደጋጋሚ ለመንግስት አመልክተናል። ግን ምንም መፍትሄ የለም። በየቀኑ ግድያ እንሰማለን ” ብለዋል።

“ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እኛም ሁሉም በዬቦታው እየጮኸ ነው ግን መፍትሄ የለም። ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ነው ” ሲሉም አክለዋል።

የኮሬን ህዝብ የወከሉት በፌደራል ደረጃ እንደመሆንዎ ለመንግስት ቅርብ ነዎትና ጉዳዩን በግልጽ ለመንግስት አንስታችሁ ነበር? ከሆነስ የመንግስት ምላሽ ምንድን ነው? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄም ፦

“ በየጊዜው ነው የሚነሳው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርላማ በተገኙበት ጊዜ ኦፊሻሊ ጥያቄ ሁሉ አንስቼ ነበር በ2016 ዓ/ም። ‘ሁኔታውን ለማርገብ የተወሰነ የመከላከያ ኃይል ይላካልና ሁኔታው ይረጋጋል’ ብለው ነበር።

ከዚያ በኋላ የተወሰነ ኃይል ሂዶ ነበር። እሱም አሁን በአገሪቱ ባለው ሁኔታ ይመስለኛል ተቀነሰ። ከዚያ በኋላ ግን ሁኔታው እየተባባሰ ነው የሄደው።

ወር በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ 10 ሰዎች ተገድለዋል። ህዝቡ በዬቀኑ ይዘረፋል። መንገድም የለም። የዲላ ህዝብ ጋር ነው የኮሬ ዞን የሚገናኘው ይሄ መንገድም ከተዘጋ ዘጠኝ ዓመት ሆኖታል።

ይሄን ሁሉ በማመልከታቸም አመልክተናል። ሽማግሌዎች ወጥተው ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት፣ ለሰላም ሚኒስቴር አመልክተዋል፤ ለክልሉ መንግስት በዬጊዜው የሚቀርብ ጉዳይ ነው። 

ነገር ግን ምንም መፍትሄ የሌለው ጉዳይ ነው የሆነው። ግድያና መፈናቀሉ ቀጥሏል ”
ሲሉ መልሰዋል።

ስለዚህ የመፍትሄው ጉዳይ ምንም እየተሰራበት አይደለም ማለት ነው ? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ ምላሻቸው፣ “ ምንም መፍትሄ የለም ” የሚል ነው።

“ አንዳንድ ጊዜ ‘እርቅ ተደርጓል’ ይባላል፤  አምና እርቅም ለማድረግ ተሰብስበው የነበሩት የብልጽና ፓርቲ ኃላፊም ጭምር የተገደሉበት ሁኔታ አለ። መንግስት የራሱ ፓርቲ አባል ሲገደል እንኳ ገዳዮች እነማን ናቸው ብሎ ተከታትሎ ሊያቀርብ አልቻለም ” ሲሉም ተናግረዋል።

በመሆኑም መንግስት፣ ሚዲያዎችም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ህዝቡን እንዲታደጉ በህዝቡ ስም ጥሪ አስተላልፈዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ዛሬና ነገ በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም በአፍሪካ እጅግ ትልቁ የቴክኖሎጂ ውድድር ”A2SV - AI for Impact Hackathon Expo” ይከናወናል! ለሁለተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ የሚካሄደው ይህ ውድድር የአፍሪካ ድንቅ ባለ ተሰጥኦ ወጣቶች አርተፊሻል አስተውሎትን በመጠቀም ችግር ፈቺ የሆኑ ፈጠራዎች የሚያሳዩበት ነው።

ሁላችሁም ይሄንን የቴክኖሎጂ ኤክስፓ መታችሁ እንድትጎበኙ እንጋብዛለን ። እንዲሁም ረቡዕ ጥቅምት 6 የሚካሄደውን ከ 7 የአፍሪካ ሀገራት የመጡትን ተወዳደሪዎች የመጨረሻ ለ 30,000 ዶላር ሽልማት የሚያደርጉትን ፍልምያ እንድትታደሙ ጋብዘኖታል ። በእለቱም የአዲስ ኣበባ ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ የመክፈቻ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ።

የፕሮግራሙ መርሀግብር
- ኤክስፖ: ጥቅምት 5 - 6 2017 ከጠዋቱ 3 ሰአት እስከ ምሽት 12 ሰዓት
- መዝጊያ ፕሮግራም: ጥቅምት 6 2017 ከምሽት 12 ሰአት እስከ ምሽት 1 ሰዓት
- ቦታው: የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚያም

መግቢያ በነፃ !

(አዘጋጆቹ)