TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar በአፋር ክልል ዱለሳ ወረዳ በተከሰተ " የመሬት መንቀጥቀጥ " ምክንያት ከተፈጠረ የመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውሃ መፍለቅ መጀመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የወረዳው አስተዳደር ተናግረዋል። ከትናንት ሌሊት ጀምሮ መፍለቅ የጀመረው ፍል ውሃ መጠኑ እየጨመረ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። አፋር ክልል ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እያስተናገደ ነው። በክልሉ…
#Afar

በአፋር ክልል ፣ ዱለቻ ወረዳ ሳጋንቶ ቀበሌ በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የፈለቀውን ፍል ውኃ ጥናት ሳይደረግበት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ ተላለፈ።

ማሳሰቢያውን ያስተላለፈው የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ነው።

ዩኒቨርሲቲው " በክልሉ በቅርቡ በተከሰተው እና ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ከተማ ድረስ በተሰማው ርዕደ መሬት ሳቢያ በአካባቢው ከተፈጠረ የመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውኃ መፍለቅ ጀምሯል " ሲል ገልጿል።

ይህንን ፍል ውኃ ጥናት ሳይደረግበት ሰዎችም ሆኑ እንስሳት እንዳይጠቀሙት ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

በሬክተር ስኬል 4.9 በተመዘገበው ርዕደ መሬት የተሰነጠቀው መሬት 1.5 ሜትር ስፋት ያለው ስለመሆኑ አመልክቷል።

ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ በአፋር ክልል የተከሰተው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ በአንዳንድ አካባቢዎች የመሬት መሰጠንቅ፣ መኖሪያ ቤቶች ላይ መፍረስና መሰንጠቅ እንዲሁም እስሳት ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ እና መጠነኛ ጉዳት ስለማስከተሉ ዩኒቨርሲቲው አስረድቷል።

ህብተረተሰቡ በተፈጥሮ አደጋው ከተሰነጠቁ አካባቢዎች፣ ድልድዮች እና ተራራዎች እንዲርቅ ጥሪ ቀርቧል። #ኢቢሲ

@tikvahethiopia
" አደጋው እጅግ አሰቃቂ ነበር " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ ዛሬ ረፋድ 4 :00 ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ከጎሮ ወደ ኮዬ እየተጓዘ የነበረ ኮድ 3-69867 ቱርቦ የሆነ የጭነት ተሽከርካሪ  ከከተማ አውቶቢስ ጋር ተጋጭቶ ነው አደጋ የደረሰው።

በዚህም የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 7 ሰዎች ላይ ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሷል።

በአደጋው የሞቱት ሁሉም ሴቶች ናቸው። ዕድሜያቸውም ከ20 እስከ 52 የሚገመቱ ናቸው።

3ቱ ሴቶች የአውቶቢስ ትኬት በመቁረጥ ላይ እያሉ ነው አደጋው የደረሰባቸው።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በቤጂንግ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ " አደጋው እጅግ አሰቃቂ ነበር " ብለዋል።

የአደጋው ምክንያት እየተጣራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" ከአዲስ መንጃ ፈቃድ ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ በየአራት ዓመቱ ይታደሳሉ " - የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን

ከአዲስ መንጃ ፈቃድና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ በየአራት ዓመቱ እንደሚታደሱ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

ባለሥልጣን መ/ቤቱ ፤ " ባለፉት 6 ዓመታት የመልካም አስተዳደር እና የፍትኃዊነት ጥያቄን ሲያስነሳ የነበረው የሁለት ዓመት እና የአራት ዓመት የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል " ብሏል።

በዚህም ከአዲስ መንጃ ፈቃድ እና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአራት ዓመት እንደሚታደሱ አስታውቋል፡፡

አዲስ መንጃ ፈቃድም ከሁለት ዓመት የሙከራ በኋላ፣ ባለው አሰራር መሠረት በየአራት ዓመቱ እንደሚታደስ ተመላክቷል።

ነገር ግን ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ ግለሰቦች በየሁለት ዓመት የሚታደስ ሆኖ ክፍያው የአራት ዓመቱ ክፍያ ግማሽ (50%) እንደሚሆን ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በህዝቡ ውስጥ የመረበሽ ስሜት ተፈጥሯል ፤ ... ችግር ሲፈጠር ዝም ብለን አንመለከትም " - የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች በተፃራሪ መግለጫዎች ምክንያት በትግራይ ውስጥ ማንኛውም የፀጥታ ችግር እና ስርዓት አልበኝነት እንዲፈጠር እንደማይፈቅድ የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች አስታውቋል። የፀጥታ ሃይሎች ባወጡት አጭር የፅሁፍ መግለጫ ፥ " መስከረም 27 ጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚመለከቱ ሁለት ተፃራሪ መግለጫዎች መውጣታቸው…
መቐለ ?

የመቐለ ከተማ ም/ቤት ዛሬ አካሂዶታል በተባለ ሰብሰባ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው ህወሓት ውስጥ የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው የተመረጡትን ዶ/ር ረዳኢ በርሀ የከተማዋ ከንቲባ ሆኖው እንዲያገለግሉ በ1 የተቃውሞ በ5 ድምፀ ተአቅቦ እንደመረጣቸው ተሰምቷል።

የከተማዋ ም/ቤት ከተማዋ በከንቲባነት ሲመሩ የቆዩት በዶ/ር ደብረፅዮን በሚመራው ህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑትን አቶ ይትባረክ ኣምሃ በክብር እንዳሰናበተ ተነግሯል።

አዲሱ ' የመቐለ ከንቲባ ሆነው ተመርጠዋል ' የተባሉት ዶ/ር ረዳኢ በርሀ በድርጅቱ የቁጥጥር ኮሚሽና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና በተነፈገው 14ኛ የህወሓት ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ  አባላት ዝርዝር ስማቸው እንደሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አረጋግጧል።

በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት  ቡድን ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 13  የቢሮ ፣ የኮሚሽን ፣ የኤጀንሲ እንዲሁም የዞን አመራሮችና አስተዳዳሪዎች ከሃላፊነት በማንሳት ባካሄደው ጉባኤ በተሳተፉ 14 አመራሮች " ለመተካት ወሰኛለሁ " ማለቱ ይታወሳል።

የፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አመራር ደግሞ እንቅስቃሴው የመንግስት ግልበጣ ነው ብሎ መግለጫውን በማውገዝ መግለጫውን ባወጡ የህወሓት ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ላይ " ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ " ማለቱ ይታወሳል። 

በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ስለ አዲሱ የመቐለ ከተማ ተሿሚ እስካሁን ያለው ነገር የለም። 

ይህን መረጃ እስከተዘጋጀበት ቀን እና ሰዓት ድረስ ምዕራባዊ ዞን ጨምሮ 6 የትግራይ ዞኖች በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በተሾሙ አመራሮች የሚመሩ ሲሆን መቐለ ከተማ ዛሬ በዶ/ር ደብረፅዮን በሚመራው ህወሓት የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑ አዲስ ከንቲባ ተሹሞላታል ተብሏል።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia
#Amhara

" በአማራ ክልል ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎችን ቅበላ አራዝመዋል። ትምህርት ከፓለቲካ ነጻ መሆን አለበት " - የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት

በአማራ ክልል በ " ፋኖ " ታጣቂዎችና በመንግስት መካከል ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረው የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ ጊዜ ማራዘማቸው ይህም ደግሞ በተማሪዎች ላይ ጭንቀት መደቀኑ ተሰምቷል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የተማሪዎቻቸውን የቅበላ ጊዜ ማራዘማቸውን እንደተረዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጸው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት ነው።

የህብረቱ ፕሬዚዳንት ሓየሎም ስዩም፣ " አራት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎችን ቅበላ አራዝመዋል " ብሎ ተማሪዎች በጭንቀት ውስጥ በመሆናቸው ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ ትከረት እንዲሰጡ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

በጸጥታው ችግር የተማሪዎቻቸውን የቅበላ ጊዜ ያራዘሙት፣ " ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ ፣ ደብረ ታቦር እና ኢንጅባራ ዩኒቨርሲቲዎች " መሆናቸውንም  ተናግሯል።

" ወሎና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች አሁን መንገድ ስለተከፈተ ይቀበላሉ " ያለው የህብረቱ ፕሬዚዳንት ደባርቅ ዩኒቨርቲንም ቅበላውን ሳያራዝም እንዳልቀረ፣ " ሀፋ፣ ሀፋ " የሆነ ሀሳብ ላይ እንደሆነ አስረድቷ።

ህብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ " ትምህርት ከፓለቲካ ነጻ መሆን አለበት " ሲል አሳስቧል።

በአንጻሩ ወልዲያ እና ወሎ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ተቀብለው እያስተማሩ መሆኑ ሲነገር ተስተውሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የተማሪዎቹን ቅበላ አራዝሟል ወይስ አላራዘመም ? ተማሪዎቹን ተቀብሎ እያስተማረ ነው ወይስ አልተጀመረም ? ሲል ወልዲያ ዩኒቨርሲቲን ጠይቋል።

ዩኒቨርሲቲው በምላሹ፣ " አላራዘመም። ተማሪዎቹ እስኪገቡ ድረስ እንጠብቃለን። የመንገድ መዘጋጋቱ ስለሚታወቅ እንደ ሀገር በይፋ ባናራዝምም የቻሉ እየገቡ ነው ያልቻሉ ይገባሉ በፈለጉት ሰዓት " ብሏል።

" በውስጥ ኮሚዩኒኬት ስላደረግን ከተማሪው ከተለያዩ ቅርብ ቦታ (ለምሳሌ ደሴ) እየመጡ  ስላሉ አላራዘምንም " ሲልም አክሏል።

ትምህርት ተጀምሯል ? ስንል ላቀረበነው ጥያቄ " ትምህርት አልተጀመረም " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንለት ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ፣ " ተማሪዎችን ተቀብለን እያስተማርን ነው። የኛ ተማሪዎች ገብተዋል። ሲኔር ተማሪዎች በሙሉ ግቢ ነው ያሉት " ብሏል።

" የአዲስ ገቢዎችን በተመለከተ ግን ትምህርት ሚኒስቴር አልመደበም ገና። እንደመደበ እንጠራለን። እኛ ምንም የምናራዝምበት ምክንያት የለም " ነው ያለው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የተማሪዎቹን ቅበላ ያራዘሙ ዩኒቨርሲቲዎችን በተመለከተ ምን እየተሰራ እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።

ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉት ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር)፣ ' ዩኒቨርሲቲዎቹ የራሳቸው ስኬጁል አለ። እኛም የሰጠነው ስኬጁል አለ። ዩኒቨርሲቲዎቹ ይጠየቁ " ከማለት ውጪ ማብራሪያ ለመስጠት ተቆጥቧል።

#TikvahEthioiaFamilyAA

@tikvahethiopia
በመሬት ናዳ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጉባ ቆርቻ እና ሻናን ዱንጎ ወረዳዎች ትላንት ማክሰኞ በጣለው ከባድ ዝናብ የተነሣ በተከሠተው የመሬት መናድ፣ 10 ሰዎች መሞታቸውን ወረዳዎቹ አሳውቀዋል።

የጉባ ቆርቻ ወረዳ አስተዳዳር ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ/ም በጃርጃታ ቀበሌ ውስጥ በተከሰተው የመሬት መናድ ምክንያት 4 ሰዎች ሲሞቱ በሌላ ቀበሌ በደረሰው አደጋ ደግሞ አንድ ሰው ሞቷል።

በሻናን ዱንጎ ወረዳ በሌሊስቱ ቀበሌ በዚሁ ቀን በተከሰተው ሌላ የመሬት መናድ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው አስተዳዳር ለሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።

ነፍስ ይማር !

@tikvahethiopia
ስቴም ፖወር !

ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣት ሴቶች ለ3ተኛ ዙር የቀረበ ጥሪ !

ስቴም ፖወር (STEMpower) ከፊንላንድ ኤምባሲ (Embassy of Finland Ethiopia) እና ከአይቢኤም (IBM) ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ከ1,000 በላይ ሥራ አጥ ወጣት ሴቶችን ተግባራዊ የሥራ ክህሎት ለመስጠት ያለመ " ትጋት " የተሰኘ ፕሮግራም አስተዋውቀዋል።

ባለፉት 2 ዙሮች 1700 በላይ ለሚሆኑ ሴቶች በ Project Management, Web Development , Cyber Security, Digital Marketing , Data Analytics , Information Technology , Job Readiness , Work Readiness ስልጠና የሰጠ ከመሆኑ በተጨማሪ የስራ እድል በመፈጠር ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድል አመቻችቷል፡፡

#ነጻ በሚሰጠውና ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርተፊኬት በሚያስገኘው በዚህ ስልጠና እነዚህን ኮርሶች ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ ሴቶች ምዝገባ የጀመርን መሆኑን እያሳወቅን ምዝገባው የሚቆየው ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 10 , 2017 ዓ/ም ሲሆን ቀድማችሁ በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እንጋብዛለን፡፡

እነዚህን ኮርሶች ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ ከስር ባለውን ሊንክ ይመዝገቡ
👉Link: https://forms.office.com/r/bJedLrdqmd
ቴክኖ !

የፊልም አድናቂ ከሆኑ ቴክኖ እና አዲሱ የሆሊውድ ፊልም ትራንስፎርመርስ ዋን በጋራ ስለተጣመሩበት ስፓርክ 30 ስልክ ሰምተዋል?

ካልሰሙ አዲሱን ስፓርክ 30 ስልክ በቅርበት እንዲሁም በቅርብ የተለቀቀውን ትራንስፎርመርስ ፊልም ከልጆት እና ቤተሰቦት ጋር እንዲኮመኩሙ ከ 7 ሰዓት ጀምሮ እሁድ ጥቅምት 3 በሴንቸሪ ሲኒማ በነፃ ጋብዘኖታል፡፡ ይሙጡ በስጦታ እየተንበሸበሹ እሁዶን ፈታ ይበሉ!

@tecno_et @tecno_et
እሁድ ጥቅምት 3 ከሰዓት 9፡15 ብርቅዬ አትሌቶቻችንን በችካጎ ማራቶን ይሳተፋሉ!

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን! 💚💛❤️

ይህንን ደማቅ ሩጫ በቀጥታ በSS Africa ቻናል 227 በቤተሰብ ፓኬጅ ይከታተሉ! ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/dg1

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
መቐለ ? የመቐለ ከተማ ም/ቤት ዛሬ አካሂዶታል በተባለ ሰብሰባ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው ህወሓት ውስጥ የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው የተመረጡትን ዶ/ር ረዳኢ በርሀ የከተማዋ ከንቲባ ሆኖው እንዲያገለግሉ በ1 የተቃውሞ በ5 ድምፀ ተአቅቦ እንደመረጣቸው ተሰምቷል። የከተማዋ ም/ቤት ከተማዋ በከንቲባነት ሲመሩ የቆዩት በዶ/ር ደብረፅዮን በሚመራው ህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑትን አቶ…
" መንግስትን በሃይል ለመፈንቀል የሚደረግ ሙከራ የሚወገዝና ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን ይፋ አደርገናል " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ መስከረም 29/2017 ዓ.ም ከቢቢሲ FOCUS ON AFRICA ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት በውይይት የሚፈታበት መንገድ ዝግ እንዳልሆነ አመላክተዋል።

" ሆኖም በጊዚያዊ አስተዳደሩ ላይ እየተደረጉ ያሉ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት / መንግስትን በኃል ለመፈቀል የሚደረግ ሙኩራ  የሚወገዙና ተጠያቂነት የሚስከትሉ መሆናቸው ህዝብ እንዲያውቃቸው ማድረጋችን ልክ ነው " ብለዋል።

" ሂደቱን ተከትሎ የተጠያቂነት አስራር ተግባራዊ እንደሚሆን ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ ጉዳይ ነው " ሲሉ አክለዋል።

የትግራይ ህዝብ ችግሮች በተባባሱበት ወቅት ለምን አንድነታችሁ መጠበቅ አቃታችሁ ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ጌታቸው " ይህ ትልቅ ወድቀት ነው ፤ እንደ ድርጅት እና ስራ አስፈፃሚ አባል የሆንኩበት ህወሓት ወድቀዋል ፤ ቢሆንም ጥቂት አመራሮች መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ እውነት በመረዳት ለመፍታት ስንሞክር ቀላል የማይባል ፈተና እና እንቅፋት እየገጠመን ይገኛል " ብለዋል።

ከዚህ በመመለስ ግን ፈተናውን ለማለፍ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል። 

@tikvahethiopia