" በዩኒቨርሲቲው አመራር ለደህንነታችን ስጋት ወደ ሆነ አካባቢ ትሄዳላችሁ ተብለናል "- ተማሪዎች
በቁጥር 1,300 አካባቢ ይሆናሉ የተባሉ የደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ከዋናው ግቢ 5 ኪ/ሜ ያህል ርቆ ወደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ትዘዋወራላችሁ መባላቸው ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ የሚዘዋወሩበት ግቢ " በመንግስት እና በታጣቂዎች መካከል አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ የሚደረግበት አካባቢ ነው " ያሉ ሲሆን " በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች እየለቀቁ ባለበት ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው ለደህንነታችን ስጋት ወደ ሆነ አካባቢ ትሄዳላችሁ ብሎናል " ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ ከደብረማርቆስ ከተማ በ5 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በ2015 ዓ/ም ህዳር ወር ጀምሮ ለ7ወር አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ በክልሉ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ከየካቲት 7/2016 ዓም ጀምሮ ተማሪዎቹን ወደ ዋናው ግቢ በማዘዋወር ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አደርጎ ነበር።
እስከ አሁን በዋናው ግቢ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት የጤና ተማሪዎች " ከሚመጣው ቅዳሜ 10/05/17 ዓም ጀምሮ ወደ ቀድሞ ግቢ እንደምንዘዋወር ተነግሮናል " ብለዋል።
ተማሪዎቹ ትዘዋወራላቹ የሚል ውሳኔ ከሰሙበት ቀን ጀምሮ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር በተደጋጋሚ ሲጠይቁ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል።
በ 02/05/2017 ዓም የጤና ኮሌጅ ዲን አና ሌሎች የጤና ትምህርት ክፍል ተጠሪዎች በተገኙበት ባደረጉት ስብሰባም " ለሚደርስባቹ የህይወት አደጋ ዩኒቨርሲቲው ምንም አይነት ኃላፊነት አይወስድም እርስ በእርሳቹ ተጠባበቁ አናንተ ስትሄዱ የቦታዉ ሰላም ይረጋገጣል " መባላቸውን ተናግረዋል።
በትላንትናው ዕለት የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት ጨምሮ የሚመለከታቸው የክፍል ተጠሪዎች በተገኙበት በድጋሚ ባደረጉት ስብሰባ ተማሪዎች ውሳኔያቸውን እስከ አርብ እንዲያሳውቁ እና ከቅዳሜ ጀምሮ እንደሚዘዋወሩ እንደተነገራቸው ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲው ምን ምላሽ ሰጠ ?
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ስሜ አይጠቀስ ያሉ የዩኒቨርሲቲው አመራር ዝርዝር ማብራሪያ ጠጥተዋል።
ምን አሉ ?
" እንዲሄዱ የሚደረግው የቦታ ጥበት በመኖሩ ነው ተማሪዎቹ መጀመሪያ ግቢያቸው ይህ አልነበረም ተደርበው ነው ያሉት።
የትምህርት ማቴሪያሎቻቸው በሙሉ እዛ ነው የሚገኙት ዩኒቨርሲቲውም የሚቀበላቸው አዳዲስ ተማሪዎች አሉ ይሄ ሁሉ ተጨማምሮ የመማሪያ ክፍል እጥረት ስላለ እና ጸጥታውም በአንጻራዊነት መሻሻል ስለሚያሳይ ነው እንዲሄዱ የተወሰነው።
ተማሪዎቹ ' እንሂድ ' ብለው ሰኔ ወር ላይ ጠይቀው ነበር እንዲዘገዩ ያደረግነው እኛ ነን በወቅቱ ጸጥታው ይህንን ለማድረግ የማያስችል በመሆኑ አሁን እንሂድ ስንል ነው ቅሬታ የተፈጠረው " ብለዋል።
በአካባቢው በሚታየው የጸጥታ ችግር አካባቢያቸውን የሚለቁ ሰዎች እንዳሉ ተሰምቷል ምን አስተማማኝ የጸጥታ ሁኔታዎች ኖረው ነው ተማሪዎቹ የሚዘዋወሩት ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ አመራሩን ጠይቋል።
እሳቸውም ፦
" አካባቢውን እየለቀቀ ያለ ሰው አለ የሚለው ውሸት ነው የሚለቅ ሰው ሊኖር ይችላል ክረምት እና ከክረምት በፊት በፍርሃት የሚወጡ ነዋሪዎች ነበሩ አሁን ግን ነዋሪውን በአካል አወያይተናል ነዋሪውም መምጣታቸውን ይፈልጋል።
ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ ነው ልል አልችልም ካለው ተለዋዋጭ ሁኔታ አንፃር አሁን ያለንበትም ተቋም ቤቱም ሆነ ከተማው ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም ግን የተለየ ስጋት የለም የሚል ድምዳሜ ነው ያለው " ብለዋል።
በዋናው ግቢ ቆይተው ቢማሩ ለደህንነታቸው የበለጠ አስተማማኝ አይሆንም ወይ ? ስንል ጥያቄ አንሰተናል።
" እዚህም ቢሆኑ እዛም ቢሄዱ ችግር የሚመጣ ከሆነ ሊደርስባቸው ይችላል ' ያኛው ግቢ የበለጠ ለአደጋ ተጋላጭ ያደርገናል ' ብለው ቢያስቡ እንኳ በአሁኑ ሰዓት በዋናው ግቢ ትምህርቱን ለማስቀጠል የማያስችሉ ሁኔታዎች አሉ ትምህርቱ እየተጎዳ ስለሆነ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔴 " እስከሚከፈለን ድረስ ወደ ሥራ ላለመመለስ ተስማምተናል ለሁሉም ባለሞያ እስከሚከፈል ድረስ አንሰራም " - የጤና ባለሞያዎች
🔵 " ዝም ያለ አካል የለም ዘግቶ መሄዳቸው ትክክል አይደለም " - የጤና ቢሮ ሃላፊ
በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ በዘጠኝ ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች የትርፍ ሰዓት ስራ(ዲዩቲ) ክፍያ ስላልተከፈላቸው 05/05/17 ዓ/ም ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የጤና ባለሞያዎች ተናግረዋል።
ባለሞያዎቹ ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከአሁን ድረስ በተለያዩ ጊዜያት ያልተከፈላቸው የ1 አመት ከ 5 ወር በላይ የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ መኖሩን ተናግረዋል።
እስከ ክልሉ የበላይ አካላት ድረስ ሄደን ጠይቀናል በተደጋጋሚ የሚሰጠን ምላሽ ግን " ታገሱ " የሚል ነው በዚህ ምክንያት ተነጋግረን ስራ ለማቆም ተገደናል ነው ያሉት።
" አብዛኛው ባለሞያ ከወረዳው ሸሽቶ ወደተለያዩ አካባቢዎች በመሄድ ተደብቆ ነው ያለው አመራሮችም በአንቡላንስ ቤት ለቤት በመሄድ የህክምና ባለሞያዎችን እያፈለጉ እያስፈራሩ ነው " ብለዋል።
ባለሞያዎቹ " በተለያዩ ጊዜያት ከወረዳ እና ከዞን አመራሮች ጋር በርካታ ውይይቶችን አድርገናል ነገር ግን ' ግብር እስከሚሰበሰብ ጠብቁ፣ ገንዘብ የለም ታገሱ ' ከማለት የዘለለ እስካሁን ምንም ምልሻ ባለመግኘታችን እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ተገደናል ነው " ያሉት።
" እስከሚከፈል ድረስ ወደ ሥራ ላለመመለስ ተስማምተናል ለሁሉም ባለሞያ እስከሚከፈል ድረስ አንሰራም የተጠራቀመ ክፍያው እስከ 100 ሺ የደረሰለት ባለሞያም አለ " ብለዋል።
" በዚህ ደመወዝ ፣በዚህ ኑሮ ውድነት መኖር አልቻልንም የመጨረሻ ደረጃ ላይ ነው የደረስነው ልጆች ያላቸው ልጆቻቸውን ማሳደግ አልቻሉም መስራትም መኖርም አልቻልንም ይሄንን እርምጃ ስንወስድም ወደ ፖለቲካ ተቀይሮ ' ትታሰራላቹ ' ወደ ሚል ማስፈራሪያ ተሸጋግረዋል " ሲሉ አክለዋል።
ባለሞያዎቹ በወረዳው በሚገኙ ሁሉም ጤና ጣቢያዎች አድማው ቢቀጥልም ለወሊድ ለሚመጡ እናቶች ብቻ አንዳንድ ጤና ጣቢያዎች ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ነገር ግን በሁሉም ጤና ጣቢያዎች መደበኛ ስራዎች ማቆማቸውን ተናግረዋል።
የአዳባ ወረዳ የጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሽመልስ ፈይሳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል የባለሞያዎቹ የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ አለመከፈሉን አረጋግጠዋል።
ሃላፊው በዝርዝር ምን አሉ ?
" በየደረጃ ያሉ ቢሮዎችን እየጠየቁ መምጣት ይችሉ ነበር እኔ የቢሮ ሃላፊ ነኝ ወደ እኔ የመጣ የለም ስራቸውን ነው ዝም ብለው ያቆሙት።
የኑሮ ውድነት በሃገሪቱ እና በአለም ያለ ሁኔታ ነው የትርፍ ሰዓት ስራ ባይሰሩም በመደበኛ ስራቸው መገኘት ነበረባቸው የሙያ ስነምግባሩ ይህንን አይፈቅድም።
የገቢ ማነስ ይኖራል፣ የጸጥታ ችግርም ሊኖር ይችላል በእነዚህ ምክንያቶች ነው እንጂ ዝም ያለ አካል የለም ዘግቶ መሄዳቸው ትክክል አይደለም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለሞያዎቹ የጠየቁት ከአመት በላይ ሳይከፈላቸው ስለቀረ ክፍያ ነው ችግሩ በምን ያህል ጊዜ ይፈታል ብለን እንጠብቅ ሲል ጠይቀናቸዋል ? በምላሻቸው ፦
" ከእዚህ በፊት ጥያቄውን ለበላይ አካል አቅርበው ጉዳዩ ወደ ወረዳ እንዲመለስ ተደርጎ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፈታል ተብሎ ነበር ለዚህ እንቅስቃሴ እያደረግን ባለበት ሰዓት ነው ይሄ የተፈጠረው ገቢ ላይ የተመሰረት አከፋፈል ነው የሚኖረው ከስር ከስር እየተከፈለ በጊዜ ሂደት ችግራቸው ይፈታል " ብለዋል።
የቦርድ አባላት በየጤና ጣቢያው በመሄድ ሰራተኛው መጥቶ የራሱን ቅሬታ እንዲያቀርብ ጠይቀው እስካሁን መጥቶ ያቀረበ አካል የለም እኛም መፍትሄ ለመስጠት ተቸግረናል ብለዋል።
ሃላፊው ባለው ሰራተኛ ስራው እንዲቀጥል ለማድረግ እየጣርን ነው ያሉ ሲሆን " የሰራተኛው ችግር ምን እንደሆነ በቢሮ ደረጃ አናውቅም መጥቶ ያቀረበልን አካልም የለም " ነው ያሉት።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወረዳው የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ከክፍያ ጋር ተያይዞ የሚያነሱትን ጥያቄ ለመቅረፍ ወረዳው ምን ያህል ብር ይፈልጋል ሲል ጠይቋል።
ሃላፊው " የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን በየጊዜው ስለሚጨምር ይሄን ያህል ነው ማለት ያስቸግራል ነገር ግን በ 2016 ዓም ብቻ ያልተከፈላቸውን ክፍያ ለመፈጸም እስከ 5 ሚሊየን ብር ያስፈልጋል " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake : ዛሬ ሰኞ ምሽት 5:24 ሲል በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 17 ኪ/ሜ ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አሳውቋል። የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባና ሌሎችም ከተሞች ተሰምቷል። " አሁን ላይ ቀንሷል ቆሟል ፣ ከአሁን በኃላ ምንም ነገር አይፈጠርም " በሚል መዘናጋት ጥንቃቄ እና ትኩረት ማጣት እንዳይመጣ መጠንቀቅ ይገባል። የመሬት…
“ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ነው እየመነጨ ያለው። ደብረ ብርሃን የተሰማ ነገር የለም” - አታላይ አየለ (ፕ/ር)
ትላንት ከሌሊቱ 10፡46 በደብረ ብርሃን አካባቢ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የጀርመን የጂኦ ሳይንስ ጥናትና ምርምር ማዕከል ድረጽ መረጃ አውጥቷል ፤ ይኸው መረጃም ሲዘገብ ተስተውለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵዮጵያ በበኩሉ፣ በጉዳዩ ዙሪያ ከዘርፉ ተመራማሪ ማብራሪያ ጠይቋል።
ደብረ ብርሃን አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል መባሉን እውነት ነው ? ብለን የጠየቅናቸው በአዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ሮ)፣ " ኧረ ውሸት ነው " ሲሉ መልሰዋል።
" ደብረ ብርሃን አካባቢ የለም። እዛው አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ነው እየመነጨ ያለው። ደብረ ብርሃን የተሰማ ነገር የለም " ነው ያሉት።
" የዘርፉ ተቋማት በሚያወጡት መረጃ፣ ' ከደብረ ብርሃን ይህን ያህል ኪሎ ሜትር፣ ወይ ከመተሃራ ይህንን ያህል ኪሎ ሜትር ' ይላሉ ስም እየጠሩ። ከዛ በመለስ ግን እንደዚህ የሚባል ነገር የለም። ደብረ ብርሃን አሁን ከየት የመጣ መንቀጥቀጥ ነው? " ሲሉ ነው ምላሽ የሰጡት።
ከዚህ ቀደም ከደብረ ሲና በ52 ኪሎ ሜትር ተከሰተ ለተባ የመሬት መንቀጥቀጥ በተለመለተ፣ ከሚከሰትበት የአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የቦታ ለውጥ አደረገ ማለት እንዳልሆነ ተመራማሪው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።
" በአንዳንድ አካባቢ ተደጋግሞ እየተከሰተ ነው ያለው እንጂ የቀረበ ነገር የለም " ነበር ያሉት።
አዋሽ ፈንታሌ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ንዝረቱ እየተሰማ እንደሆነ ይታወቃል።
ሌላው በተያያዘ፣ የአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንስ በምን ደረጃ ላይ ነው ያለው ? በሚል ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ለቀረበላቸው ተጨማሪ ምላሽ ሰጥተዋል።
አታላይ አየለ (ፕ/ር) ምን ምላሽ ሰጡ ?
" ምንም የተለዬ ነገር የለም እንደቀጠለ ነው። ከቀን ቀን ትንሽ ለውጥ ያለው ይመስላል። ግን ነገ ይቆማል የሚባል ነገር አይደለም።
ስቲል ይታያል እንቅስቃሴ። የሚረግብ አይመስልም በአጭሩ።
ዌብ ሳይት ተለጠፈ የሚለው ሳይሆን ለሊት 10 ገደማ ተፈጠረ የተባለው አካባቢ አንድ ነው ሪፓርት የተደረገው ግን ከእኩለ ለሊት ጀምሮ እስካሁን ስንት ተፈጠረ ብትለኝ ከ100ዎች በላይ ሊሆኑ ይችላሉ።
ያ ማለት የሚረግብ አይነት አይደለም " ብለዋል።

" ...ሙሉ ተሳፋሪውን ነው የወሰዷቸው። መጀመሪያ የተመታው ግን አንድ ሹፌር ነው - " ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር
አዋሽ ፓርክ አካባቢ ሰሞኑን አንድ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ሙሉ ተሳፋሪዎች ከነአሽከርካሪው መታገታቸውን ጣና የከባድ ተሽከርከሪ አሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ማኀበሩ በሰጠን ቃል " አዋሽ አካባቢ ፓርክ አለ። እዚያ አካባቢ ታጣቂዎች ተሽከርካሪውን በጥይት መትተውት ሰው ቆስሏል " ብሏል።
" ተሽከርካሪው ተቃጥሏል። ኤክስፓርት ይሁን ሌላ የጫነ ተሽከርካሪ አልታወቀም። ተሳፋሪ ሰዎችንም ይዞ ነበር " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።
ተሳፋሪዎቹና ሹፌሩ ከምን ደረሱ ? ለሚለው ጥያቄ ማኀበሩ በምላሹ፣ " ሹፌሩም ታግቷል። ተሳፋሪውንም እንደዚሁ ሙሉ ተሳፋሪ ወስደዋል " ነው ያለው።
ተሳፋሪ ከያዘ ተሽከርካሪው የህዝብ ማመላለሻ ነበር እንዴ ? ስንል ላቀረብንለት ጥያቄ ማኀበሩ፣ " በተለምዶ ' አባዱላ ' የሚባለድ ሚኒባስ ነው፣ አዎ የሕዝብ ተሽከርካሪ ነበር " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
ምን ያክል ሰዎች እንደታገቱ ሲጠየቅም፣ " ቁጥሩ አልታወቀም። ሙሉ ተሳፋሪውን ነው የወሰዷቸው። መጀመሪያ የተመታው ግን አንድ ሹፌር ነው " ሲል መልሷል።
ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት እንነማን እንደሆነ ሲያስረዳ፣ በዛ አካባቢ ላይ ከሸኔ ታጣቂዎች ውጪ ከማኀበረሱ የወጣ እንዲህ አይነት ድርጊት ከዚህ ቀደም አጋጥሞ እንደማያውቅ ነው የገለጸው።
ለአመታት ይኸው የሚባል ዘላቂ መፍትሄ ያልተገኘለት የታጠቁ አካላት ሹፌሮች ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት ልጅን ያለ አባት፣ ወላጅን ያለ ልጅ እያስቀረ በመቀጠሉ የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ አሁንም ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ ተጠይቋል።
ደረሰ ለተባለው ጥቃትና እገታ የባለስልጣናትን ምላሽ ለማካተት የተደረገው ሙከራ ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ለጊዜው አልተሳካም።

" ጉዳዩ ዓለም አቀፍ የወንጀል ገጽታ ያለው ነው " - የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር የታገቱት ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ከምን ደረሰ ? የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ፦ " በህገወጥ ዓለምአቀፍ ደላሎች ተታለው ወደ ማይናማር ፣ ታይላንድ፣ ቻይና ድንበር አዋሳኝ አካባቢዎች ወደሚገኙ ህገወጥ ካምፓች ተወስደው የሚገኙ ዜጎችን ለማስመለስ በመንግስት የተጀመሩ ጥረቶች ቀጥለዋል። ጉዳዩ…
#Update
🚨“ በጣም ብዙ ችግር ነው እየደረሰባቸው ያለው። ጣታቸው የተቆረጠ አሉ ” - የወላጆች ኮሚቴ
ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰጠው መግለጫ በመነሳት፣ “ አንዳንድ ሚዲያዎች መንግስት በማይናማር የታገቱ ዜጎችን አስለቀቀ ” በማለት መዘገባቸው ስህተት መሆኑን ጉዳዩን የሚከታተሉ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የታጋቾቹ ቤተሰቦች በዝርዝር ምን አሉ ?
“ አጋቾች ያገቷቸውን ልጆቻችንን ‘መንግስት አስለቀቀ’ መባሉ ትክክል አይደለም።
አጋቾቹ ሲቀጧቸው የተጎዱ፣ በህመም ሳቢያ መስራት የማይችሉ ልጆችን ከካምፕ አውጥተው ታይላንድ ድንበር ሲጥሏቸው ሰብአዊ መብት ላይ የሚሰሩ ኤን.ጂ.ኦ አንስተው ታይላንድ በመውሰድ አሳክመው ህንድ ካለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመሆን ነው ኢትዮጵያ እንዲገቡ ያደረጓቸው።
አንዳንድ ሚዲያዎች የዘገቡትና መንግስትም ድፍን ባለ መልኩ የሰጠውን መግለጫ መነሻ በማድረግ ማይናማር ያሉ ልጆች የተለቀቁ የመሰላቸው አድማጮች ‘ እንኳን ደስ አላችሁ ’ የሚለን በዝቷል። እውነታው ይሄ አይደለም።
ይህን ጉዳይ ህዝብ ይረዳው። ማይናማር ከታገቱት ልጆች መካከል እንዲለቀቁ በተደረገ ጥረት ማንም አልተለቀቀም።
ታይላንድ ያሉት ናቸው እንጂ ማይናማር ያሉት አይደሉም የወጡት። ዋሽተው ነው። ዜናውን አካብደውታል። እኛን ምንም ተስፋ አልሰጡንም። ‘አትምጡ’ ነው ያሉን ” ሲሉ አስረድተዋል።
የወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ምን አለ ?
“በዚህ መልኩ (ታጋቾች ተለቀዋል በሚል) የዘገቡት ሚዲያዎች ሁለት፣ ሦስት ጊዜ ድምፅ እንዲሆኑን ጠይቀናቸው ሳለ ‘ እንከሰሳለን ’ ብለው ነው የፈሩት። አሁን ግን ያልተወራውን ማስተላለፍ ከኢቲክስ ውጪ ነው። በጣም ቅር ብሎናል። እውነታውን አሳውቁልን።
በታይላንድና በማይናማር ድንበር ያሉት ልጆች እንጂ ወጡ የተባሉት ከማይናማር ግዛት ካሉት ጋር እንደማይገናኝ በህንድ የሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ነግሮናል።
የኤምባሲው ሰዎች ‘እኛ የሚመለከተን ታይላንድ አካባቢ ያለውን ብቻ እንጂ የማይናማሩ የሚመለከተው ቶኪዮ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነውና ማይናማር ያሉትን አንድም ነገር አልሰራንም’ ብለው ቃል በቃል ነው የነገሩን።
ከኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በመግቢያ ንግግራቸው ያስተላለፉት ትክክለኛውን ‘ታይላንድ አካባቢ ያሉትን’ ብለው ነው።
ነገር ግን አንዳንድ ሚዲያዎች በስቃይ ላይ ያሉ ልጆችን መንግስት እያስወጣ እንዳለ አድርገው ነው መግለጫውን የዘገቡት። ይህ ቅር አሰኝቶናል።
ሌሎች አገራት እኮ ዜጎቻቸውን ያስወጡት ከትራደሽናል ሊደሮች፣ ከኤምባሲዎች ጋር ሆነው በመስራት ነው። የኛዎቹ ግን ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ አይደሉም።
አንዱን ኢትዮጵያዊ የመራቢያ አካሉን የዘር ፍሬ ነቅለውታል። በጣም ብዙ ችግር ነው እየደረሰባቸው ያለው። ጣታቸው የተቆረጠ አሉ።
አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግሮ በችግር ላይ ያሉ ልጆችንን ካሉበት ስቃይ እንዲታደጋቸው በአጽንኦት እንጠይቃለን ” ብሏል።

“ የትራንስፓርትም ዋጋ ጨምሮባቸዋል። መድኃኒትም ከውጭ ነው የሚመጣውና በሁሉም ዋጋ ጨምሮባቸው በጣም በከፍተኛ ሲቃይ ናቸው ህሙማኑ ” - ማህበሩ
“ 400 ሺሕ ሰዎች ዲያሌሲስ ያስፈልጋቸዋል። አብዛኛዎቹ ዲያሊስ ማድረግ ስለማይችሉ ትተው ነው ያሉት ” በማለት የኩላሊት ህክምና እጥበት በጎ አድራጎት ማኅበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
የማኀበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰለሞን አሰፋ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ?
“ ብዙ ወጣቶች ናቸው ዲያሌሲስ እያደረጉ ያሉት። ኩላሊት ደግሞ ከዘመድ ካልሆነ ከእኛ ሀገር ከሌላ ቦታ ማገኘት አይቻልም።
ትልቁ ችግር የኩላሊት ማግኘት ነው። ህሙማኑ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ፍላጎት ቢኖራቸውም የሚሰጣቸው ሰው የለም። ቢኖርም እንኳ ቢኖር አንዳንዱ ማች አያደርግም።
አብዛኞቹ ዲያሌሲስ ማድረግ ላይ ነው ትኩረታቸውን የሚያደርጉት ንቅለ ተከላውን እስከሚያደርጉ ድረስ።
የትራንስፓርትም ዋጋ ጨምሮባቸዋል። መድኃኒትም ከውጭ ነው የሚመጣው በሁሉም ዋጋ ጨምሮባቸው በጣም ከፍተኛ ሲቃይ ላይ ናቸው ህሙማኑ።
ድጋፍ የሚያደርገው ሰውም በጣም እየቀነሰ ስለመጣ ህሙማኑ በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ነው። ዲያሌሲስ ሁለት ጊዜ፣ አንዴ የሚያደርጉ አሉ። አንዳንዶች የሚበሉትን፣ የሚጠጡትን እየቀነሱ ይገኛሉ” ብለዋል።
በኢትዮጵያ ስንት የኩላሊት ህሙማን አሉ ? ከእነዚህ መካከል ስንቶቹ ህክምና የመከታተል እድል አግኝተዋል ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።
ዋና ሥራ አስኪያጁ ፦
“ 400 ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች ዲያሌሲስ ያስፈልጋቸዋል። አብዛኛዎቹ ዲያሌሲስ ማድረግ ስለማይችሉ ትተው ነው።
ግማሹ ጸበል ይሄዳል። ስለማንሰማ እንጂ ህይወታቸው የሚያልፈው ይበዛሉ። ዲያሌሲስ በማድረግ የሚታገለውን ነው የምናውቀው። ያም ቢሆን ሲቸግረው አንድም ሁለትም ጊዜ ዲያሌሲስ የሚያደርግ አለ በወር ውስጥ።
ይተዛዘናሉ። ሦስት ጊዜ ዲያሌሲስ የሚያደርገው ሰውዬ ‘ሁለት ይበቃኛል’ ብሎ አንዱን ለሌላ ይሰጣል። በእንደዚህ እየታገሉ ነው ያሉት።
የምንችለውን እያደረግን ለተወሰኑ ሰዎች ነው ለመድረስ የቻልነው ለብዙ ሰዎች መድረስ አልቻልንም። ምንክንያቱም ድጋፉ በደንብ ተጠናክሮ እየቀጠለ አይደለም።
ህብረተሰቡም ደግሞ ስለ ጉዳዩ ያገባኛል ብሎ ትኩረት ሰጥቶ ሲረዳ አንመለከትም። የሚያጭበረብረው ሰውም በዝቷል ” ሲሉ አስረድተዋል።
ማህበሩ ፤ “ ሰው ለመርዳት ችግር የለበትም ይረዳል። ትልቁ ችግር ማስታወስ ላይ ነው ያለው። እናንተም ለህብረተሰቡ በማስታወስ እርዱን ” ሲል አሳስቧል።
“ ትልቅ መፍትሄ ይሆናል ብለን የምናስበው ከሞተ ሰው ኩላሊት እንዲወሰድ የህግ ማዕቀፍ ሲወጣ ነው ” ያለው ማኀበሩ፣ “ ሲጸድቅ ሰዎች ሰላም ያገኛሉ። እስከዚያ ድረስ ዲያሌሲስ እያደረጉ መቆየት ግድ ይላቸዋል ” ብሏል።

መታወቂያ መስጠት መቼ ይጀመራል ? " አሁን ማጣራት ጀምረናል የገቡትን መረጃዎች፣ አሰራሮችና ማኑዋሎች ጭምር ተዘጋጅቷል " - CRRSA የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከክልል ከተሞች መሸኛ ለሚያመጡ ዜጎች የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ መስጠት መቼ እንደሚጀምር ጠይቀነው የሰጠንን ምላሽ በተደጋጋሚ አድርሰናችሁ ነበር። ኤጀንሲውን ከዚህ ቀደም…
#አዲስአበባ #መታወቂያ
“ ወደ 33 ሺሕ የሚሆን መረጃ ለሰላምና ጸጥታ ልከናል በየክልሉ ተጠርቶ እንዲመጣ በአንድ ወር ውስጥ ” - CRSSA
ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው ለሚመጡ ተቋርጦ የቆየው የአዲስ አበባ መታወቂያ የመስጠት አገልግሎት መቼ እንደሚጀመር ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲን በተደጋጋሚ መጠየቁ ይታወሳል።
ከዚህ ቀደም አገልግሎቱ መቼ ይጀመራል? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቀው ኤጀንሲው፣ “ በጣም ባጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን ” የሚል መስጠቱ አይዘነጋም።
አገልግሎቱ ባለመጀመሩ በድጋሚ መቼ እንደሚጀመር ስንጠይቀውም፣ “ ነሐሴ አጋማሽ 2016 ዓ/ም የትምህርት ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኃላ እንሰጣለን ” ነበር ያለው።
ይሁን እንጂ ከዚያ በኋላም አገልግሎቱን የመስጠት ተግባሩ ሲጓተት ቆይቷል።
አሁንስ አገልግሎቱ ተጀመረ ?
አሁንስ ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው ለሚመጡ ተገልጋዮች የመታወቂያ አገልግሎት የመስጠት ስራው ተጀመረ ? ተብሎ የተጠየቀው ኤጀንሲው አገልግሎቱ እንደተጀመረ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የኤጀንሲው ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዮናስ አለማየሁ ምን አሉ ?
“ አገልግሎቱ ከተጀመረ ወር ሆኖታል። በሁለት መልኩ ነው ሥራውን እየሰራን ያለነው።
አንደኛው ቀርበው ሪፓርት እንዲያደርጉ፣ የፋይዳ ቅድመ ሁኔታ አደረግን። ከተጠሩት ውስጥ ቀድመው ሪፓርት ያደረጉት በጣም ጥቂት ናቸው።
ከዚያ ባሻገር ደግሞ ለሚዲያ በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ክልል የመጡ መሸኛዎችን መልሰን ለክልል እንልካለን ማንነታቸውን ለማረጋገጥ ብለን ነበር።
በዚህም በዛም መልኩ እንግዲህ እኛ ጋ ሪፓርት ያደረጉ ሰዎች ቁጥር ካመለከቱት ቁጥር ጋር ሲያያዝ በጣም አንሷል መጥተው ሪፓርት ያደረጉ ማለት ነው።
እናጣራለን ስንልም ሀሰተኛ ሰነድ ላይ ያለው ሁኔታ ትንሽ ፍርሃት ፈጥሯል መሰለኝ። ወደ 33 ሺሕ የሚሆን መረጃ ለሰላምና ጸጥታ ልከናል በየክልሉ ተጠርቶ እንዲመጣ በአንድ ወር ውስጥ።
ያ ማለት ሀሰተኛ መሸኛ ይዞ መጥቶ እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ያደረገውን፣ ሀሰተኛ መሸኛ ያስገባውንም ሰው ወደ ወንጀል ተጠያቂነት እናመጣለን የማይቀር ነው።
ዞሮ ዞሮ አገልግሎቱ ክፍት ነው ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ኤጀንሲው ከ42 ሺሕ በላይ ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው ወረፋ እየጠበቁ ያሉ አገልግሎት ፈላጊዎችን መረጃ አጣርቶ አገልግሎት እንደሚሰጥ ከዚህ ቀደም አስታውቆ ነበር።
(በቀጣይ ተጨማሪ መረጃ እናቀርባለን)

" ዌብሳይቱ ላይ የሚያሳየን ንግድ ፈቃዱ እንደታደሰ ነው ግን ፕሪንት አያደርግም። ... ክፍያውንም እንደ ከፈልን ያሳያል ግን ክፍያ አልከፍልንም ፤ ይሄ ደግሞ የሲስተም ችግር ነው " - ቅሬታ አቅራቢ
የንግድ ፈቃድ ያለ ቅጣት ማደሻ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ/ም ይጠናቀቃል።
የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ከሃምሌ 1 ቀን 2016 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ያለ ቅጣት እንዲካሄድ ፕሮግራም ወጥቶ ሲካሄድ ነበር።
በኃላም ተጨማሪ ቀን ተጨምሮ እስከ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ተራዝሟል።
ይህ የተጨመረው ቀን ማለትም ያለ ቅጣት ማደሻ ሊጠናቀቅ 3 ቀን ብቻ ቀርቶታል።
ተገልጋዮች በኦንላይን ፈቃድ ለማሳደስ በስራ ቀናት እስከ ምሽቱ 2:30 ድረስ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
የንግድ ፈቃድ በኦንላይን የሚታደሰው በ www.etrade.gov.et ላይ ሲሆን የአገልግሎት ክፍያ ፈጽመው ምስክር ወረቀት በመጠባበቅ ላይ ያሉ ' የምስክር ወረቀት ያትሙ ' (Print Certificate) የሚለውን ቁልፍ በመጫን የምስክር ወረቀታቸውን ማግኘት ይችላሉ።
ከዚሁ ከንግድ ፈቃድ እድሳት ጋር በተያያዘ ግን አንዳንድ ተገልጋዮች እክል ገጠመን ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክት ልከዋል።
ከነዚህ ቅሬታ አቅራቢዎች አንደኛው ፦
" ክሊራንስ በታህሳስ 30 ላይ ነበር የጨረስኩት ፤ ከጨረስኩበት ሰዓት ጀምሮ ንግድ ፈቃዱን ለማደስ ክፍያ በምከፍልበት ሰዓት አንደኛ ክፍያው እንደ ተከፈለ ነው የሚያሳየኝ ፤ ሁለተኛ የመክፈያ ቁጥር ተብሎ የተሰጠኝ ቁጥርን ቴሌብር ላይ ስሞክረ ' ይሄ ክፍያ ተከፍላል ' ነው የሚለው።
በሲስተሙ ምክንያት ምንም ነገር መስራት እና ፈቃዱን ማደስ አልቻልኩም። ዌብሳይቱ ላይ የሚያሳየን ንግድ ፈቃዱን ፕሪንት አያደርግም ግን እንደ ታደሰ ያሳያል። ክፍያውንም እንደ ከፈልን ነው የሚያሳየው። ግን ክፍያ አልከፍልንም ይሄ ደግሞ የሲስተም ችግር ስለሆነ ነገ ከነገ ወዲያ ያስጠይቀናል።
ሲስተም እስከሆነ ድረስ ቅጣቱን እና ወለዱን ይዞ ነው። አሁን ባለው እንኳን ቅጣት 2,500 ነው ከዛ የጊዜ ገደብ ተሰጥቶ ካለፈ ወደ 10 ሺህ ከፍ ይላል።
እኛ ባላጠፋነው ፤ በጊዜው ክሊራንስ ጨርሰን ብንገኝም በሲስተም ምክንያት ማደስ አልቻልንም። ለዚህ መፍትሄ እንፈልጋለን " ብለዋል።
በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?
" ኦንላይን ባሉበት ማራዘም ይችላሉ የሲስተም ችግርም የለም እስከ አሁን ያላደሱ ነጋዴዎች ቅጣት ውስጥ መግባት ይገባቸው ነበር ነገር ግን እስከ ጥር 15 ያለቅጣት እንዲያራዝሙ ተፈቅዶላቸዋል።
ችግርም ካለ የተጠቃሚዎች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ነው የሚሆነው አሁንም ሲስተሙ እየሰራ ነው ከሦስት ቀን በኃላ ግን ሊያበቃ ይችላል።
አዋጁ የሚለውን ትተን ለንግዱ ማኅበረሰብ በማሰብ ያለቅጣት ከታህሳስ 30 በኋላ ለ15 ቀን እንዲያድሱ ፈቅደናል ሲስተሙ 24 ሰዓት ይሰራል ኤረር (Error) የሚላቸው የአጠቃቀም ችግር ነው በጣም የለማ ሲስተም ነው ያለን።
ለውጤታማነቱም በዚህ አመት በ6 ወር ውስጥ ሁለት ሚሊየን ሃምሳ ሺህ (2,050,000) ሰዎች ንግድ ፈቃድ የማውጣት እና የማደስ አገልግሎት አግኝተዋል።
የሚቀር ነገር አይጠፋም አልፎ አልፎ የሲስተም መቆራረጥ ሊኖር ይችላል ነገር ግን በአብዛኛው አፈጻጸማችን ውጤታማ ነው።
ይህ ሁሉ ሰው ካሳደሰ የሚቀረው ጥቂት ነው በርካታ ሰው ተገልግሏል በነጋዴዎች ችግር ካልሆነ በቀር ከሃምሌ ጀምሮ ማሳደስ ይችሉ ነበር ለምን እስካሁን አረፈዱ በመጨረሻ ሰዓት እንደዚህ አይነት ቅሬታ ማቅረብ ምክንያታዊ ሊሆን አይችልም " ብለዋል።

🔴 “ እዛው አካባቢ በዘመናዊ መኖሪያ ቤት የማስፈር ሀሳብ ታጥፎብናል ” - ቅሬታ አቅራቢ ነዋሪዎች
🔵 “ በመመሪያው መሠረት እንደማንኛውም የቀበሌ ተነሽ እንዲስተናገዱ ነው አቅጣጫ የተሰጠው ” - የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቀድሞ መሬት ልማት አስተዳደር አካል
ከዓመታት በፊት ኤግል ሔልስ የተሰኘው ድርጅት ለገሀር አካባቢ በያዘው የግንባታ ፕሮጀክት ላይ የቦታው ነዋሪዎች መንግስት የገባላቸው ቃል ታጥፎ ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄዱ መገደዳቸው እጅጉን ቅር እንዳሰኛቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ስሞታቸውን ልከዋል።
“ ከስድስት ዓመታት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቃል የተገባውን እዛው አካባቢ በዘመናዊ ቤት የማስፈር ሀሳብ በማጠፍ ቦሌ አራብሳ በቆርቆሮ በተሰሩ ቤቶች ” እንዲሄዱ መገደዳቸውን ገልጸዋል።
ቅር ያሰኛቸውን ቆርቆሮ ቤት የሚያሳይ ቪዲዮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት ነዋሪዎቹ፣ ለጉዳዩ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደርን፣ የወረዳ 10 መሬት ልማት ጽሕፈት ቤትን ተጠያቂ አድርገዋል።
ለቅሬታው ማብራሪያ የጠየቅናቸው አዲሱ የክፍለ ከተማው መሬት አስተዳደርና ወረዳ 10 መሬት ልማት አስተዳደር አካላት የቅሬታውን ዝርዝር በጽሞና ከሰሙ በኋላ ለጊዜው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተጨማሪ ከ15 ቀናት በፊት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር የነበሩትን (አሁን ከስፍራ የለቀቁ) አካል ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቋል።
በቦታው ቤት ‘ይሰራላችኋል’ ተብለው የነበረ ቢሆንም ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄዱ ስለመገደዳቸው ነዋሪዎቹ ያቀረቡትን ቅሬታ የገለጽንላቸው እኚሁ አካል በሰጡት ምላሽ፣ “ 27 ናቸው እዛ አካባቢ ያሉት ነዋሪዎቹ። የዛኔ ተብሎ ነበር። አሁን ደግሞ ሰዎቹ እንዲነሱ ሆኗል ” ብለዋል።
“ ሙሉ ለሙሉ ይዞታቸውን ‘አስረክቡን’ እያሉ ነው። ስለዚህ መንግስት ምን አደረገ፦ ቤቶቹን ድሮ በምድር ባቡር ነበር ያከራየው ለሰዎቹ፣ ወደ መንግስትም አልተመለሰም ዝም ብሎ ለነዋሪዎቹ በምድር ባቡር ሰጣቸው ” ነው ያሉት።
“ ምድር ባቡር አሁን ጥሎ ሲወጣ መንግስት ወደ መንግስት አዞረና በመመሪያው መሠረት እንደማንኛውም የቀበሌ ተነሽ እንዲስተናገዱ ነው አቅጣጫ የተሰጠው ” ሲሉ አክለዋል።
በመርሀ ግብር ማስጀመሪያው ወቅት ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጭምር ነዋሪዎቹ ሳይፈናቀሉ በአካባቢው መኖሪያ ቤት እንደሚገነባ ገልጸው ነበር፤ አሁን ያ ቃል ታጥፎ ነው ? ስንል ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበናል።
የቀድሞው የክፍለ ከተማው መሬት አስተዳደር ለጥያቄው በሰጡት ምላሽ፣ “ 27 ብቻ አይደለም የነበሩት የዛኔ። እነዚህ 27ቱ የቀሩበት ምክንያት የምድር ባቡር ቤቶች ስለነበሩ ነው ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
“ ሌሎቹ የቀበሌ ቤቶችኮ ሙሉ ለሙሉ ተነሱ” ያሉት እኚህ አካል “ ይሄንን መንግስት ያደረገው እነዚህ ሰዎች ነዋሪ ናቸው። ነዋሪ መበተን የለበትም ቀበሌ ቤትም ባይሆን የመንግስት ቤት ስለሆነ በመንግስት ቤት መመሪያ መሠረት አገልግሎት ይሰጣቸው ነው ” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ወቅት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ምን ብለው ነበር ?
" የኛ ፍልስፍና ሀብታሞች ገንዘብና እውቀት ይዘው መጥተው እነርሱም ሞር ሀብታም የሚሆኑበት፣ በአካባቢው ያለውን ነዋሪ ሞር ስደተኛና ድሃ የሚደረግበት ሁኔታ መቆም አለበት የሚል ጽኑ አቋም አለን።
በዚሁ ምክንያት እዚህ አካባቢ ላይ የሚኖሩ ከ1,600 የሚበልጡ ቤተሰቦች፣ አባወራዎች አንደኛ ለዘመናት የኖሩበት፣ ከአዲስ አበባ ምናልባት ከአካባቢ አገራትም ከተማ በእነርሱ ይገነባል።
ሁለተኛ ለእነርሱ የመኖሪያ ቤት መስሪያ 1.8 ቢሊዮን ብር ኤግል ሔልስ ለመንግስት ስለሰጠ እዚሁ ቦታ ላይ ቤት ይገነባላቸውና አሁን ካላቸው የኑሮ ደረጃ የተሻለ የቤት ባለቤት ያደርጋቸዋል።
ሰፈሩ እዛም ውስጥ ያሉ እስከዛሬ ሲገፉ የነበሩ ሰዎችን ስናስታውስ ያንን ችግር የሚቀርፍ ይሆናል። ይህንን የመንግስት የተጀመረ አሰራር ወደ ፊት ወደ አርሶ አደሮች፣ ወደ ግለሰቦች ለማስፋፋት እንፈልጋለን።
አንድ ሰው ቦታ ኖሮት ሌላ ሰው በዚያ ቦታ ማልማት ሲፈልግ ሰውየውን ሳያፈናቅል፣ ከአጠቃላይ ፖሮጀክቱ 5ም፣ 10ም ፐርሰንት ሰጥቶ ሰውየውም አድጎ አዲስ የመጣውም ባለሃብት አብሮ የሚያድግበት ነገር ስለሚፈጥር እዚህ ቦታ ላይ ለኤግል ሔልስ አልሰጠንም።
ቦታውን መንግስት 27 ፐርሰንት ሼር ውስዷል። ይሄ የሆነበት ምክንያት ጆይንት ቤንቸር ለመፍጠር ነው።
የነበረውን እያጠፋን፣ በአካባቢው ያለውን ሰው እየገፋን ሳይሆን ሰው ባለበት፣ ታሪካችንም ባለበት ግን የተሻለና ያማረ ነገር መፍጠር በውስጡ የያዘ በመሆኑ ይህንን ለሚያደርገው ኩባንያውንም፣ ቸር ማኑንም በሙሉ ልብ ስለማምን ዝርዝር ዲዛይን ዝርዝር ውይይት አድርገናል።
ካሁን በኋላ ከዚህ ያነሰ፣ ሰው የሚያፈናቅል፣ ለአካባቢው ሰው ቤት የማይሰራ ባለሃበት ከሆነ ሂዳችሁ ከኤግል ልምድ ውሰዱ ይባላል ” ብለው ነበር።
ይሁን እንጂ ይህ ቃል ታጥፎ ነዋሪዎቹ ወደ ቦሌ አራብሳ እንዲሄዱ መገደዳቸውን ገልጸዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#iSonXperiences ከትላንት ጀምሮ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል ሰራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ የደረሰው መልዕክት ያሳያል። ሰራተኞቹ የሥራ አድማውን ያደረጉት መስሪያ ቤታችን ቅሬታችንን ሊመልስልን አልቻለም በሚል መሆኑን ገልጸዋል። ሰራተኞቹ ካቀረቡት ጥያቄዎች ዋነኛው " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል ሰራተኞቹን በራሱ ሥር ያካተን ፤ በኤጀንት…
የስራ ማቆም አድማ የመቱት ሰራተኞች ምን አሉ ?
🚨“ በቂ ደመወዝ አይደለም የምናገኘው። ከማክሮ ኢኮሮሚው ጋርም የሚመጣጠን ስላልሆነ ተመግበን ማደር አልቻልንም” - የሥራ ማቆም አድማ የመቱ ከ350 በላይ ሠራተኞች
➡️ “ በዚሁ ዙሪያ ስብሰባ ላይ ነኝ ” - ድርጅቱ
በአይሰን ኤክስፕሪያንስ መሠረታዊ የሰራተኞች ማኀበር ሥር እንደሚተዳደሩ የገለጹ የሳፋሪኮም ኮልሴንተርና የሲምካርድ አፕሩቫል ከ350 በላይ ሠራተኞች ዘርፈ ብዙ ቅሬታዎች ስላልተፈቱላቸው ከትላንት ከሰኞ ጅምሮ ሥራ ማቆም አድማ ለመምታት መገደዳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የሚከፈላቸው ደመወዝ በቂ እንዳልሆነ፣ ድርጅቱ 80 ሰራተኞችን ያለ አግባብ እንዳሰናበተ፣ የትራንስፓርት አገልግሎት ባለመኖሩ በድርጅቱ ለማደር የሚገደዱ ሰራተኞች እንዳሉ አስረድተዋል።
ሰራተኞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በዝርዝር ምን አሉ?
“ አይሰን ኤክስፕሪያንስ የሚባለው ድርጅት የሳፋሪኮምን የኮል ሴንተሩንና የሲምካርድ አፕሩቫሉን ፕሮሰስ ወስዶ የሚሰራ ድርጅት ነው።
በዚህ ድርጅት ላይ ያለን ቅሬታ፣ በቂ ደመወዝ አይደለም የምናገኘው። ከማክሮ ኢኮሮሚው ጋርም የሚመጣጠን ስላልሆነ ተመግበን ማደር አልቻልንም።
ማታ አራት ሰዓት ከሥራ ለሚወጡ ሰዎች ትራንስፓርት የለም። ግማሽ መንገድ ወስዶ ከዚያ ‘በራሳችሁ ሂዱ’ ነው የሚለው። ይህ አደጋ ላይ የሚጥል ነው። ጭራሽም ትራንስፓርት የሌላቸው ሠራተኞች ከመስሪያ ቤቱ አድረው የሚወጡ አሉ።
አመታዊ እረፍት ሠራተኞች በፈለጉት ጊዜ አይሰጣቸውም። ከሁለት ዓመት በላይ የተጠራቀመ የአመት እረፍት ያላቸው ልጆች አሉ። ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ ሠራተኞች ቅነሳ አለ። በርካታ ችግሮች ናቸው ያሉት።
በእነዚህ ጉዳዮች የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በተገኙበት ስብብሰባ አድርገን ነበር። የመጣው ለውጥ ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም።
የመጨረሻውን ስብሰባ ያደረግነው ያለፈው አርብ ነበር። እንደማንስማማና ኃላፊነታችንን እንዳነሳን ተናግረናል። ከሰኞ ጀምሮም ሠራተኛው መብቴን በሕግ አስከብራለሁ ብሎ የሥራ ማቆም አድማ እያደረገ ይገኛል።
አሁን የሰፋሪኮም የጥሪ ማዕከል አይሰራም። ሲም ሽያጭ ላይ አፕሩቭ ከሚሰሩ ልጆችም ጭምር ነው አድማ ያደረግነው ስለዚህ ሁለቱም ሰርቪሶች አይሰሩም።
ይህን ከማድረጋችን በፊት ከሁለት ዓመታት በፊትም ተወያይተን ስላልተስማማን አድማ አድርገን ነበር፡፡ አሁንም በ10 ቀናት ጥያቄያችንን መልሱልን ብለን ከወር በፊት ደንዳቤ አስገብተን ነበር፡፡ ምላሽ አልተሰጠንም፡፡
ደብዳቤውን ካስገባን በኋላ አንድ ወር በፈጀ መደራደር በአራት ጊዜ ቀጠሮ ለመደራደር ሞክረን ነበር፡፡
ኢሰማኮ፣ የሰራተኛ አሰሪዎች ፌደሬሽንና ሌሎች ተቋማት በመካከል ገብተው ለማደራደር ሞክረው ካቅም በላይ ስለሆነ ሥራ የማቆም አድማ ለማድረግ ተገደናል፡፡ ዛሬ ሦስተኛ ቀናችን ነው፡፡
አይሰን ኤክስፕሪያንስን ስንጠይቅ አሁን 'ግቡልንና እናስተካክላለን' የሚል ሀሳብ እያመጡ ነው። ግን የሚጨምሩት ደመወዝም የሚያስማማን አይደለም፡፡ እስከ 15 ፐርሰንት እንጨምራለን' ነው እያሉ ያሉት፡፡
ሥራ ለማቆም የተገደደው መሰረታዊ ፍላጎታችን ማሟላት ስላልቻለ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ በየጊዜው እየጨመረ ነው ያለውና ድርጅቱ መፍትሄ ይስጠን፡፡
የምንሰራበት ሰዓት ከቀኑ 2 እስከ 11 ሰዓት ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ሽፍት ሌሊትም ሥራ እንገባለን፡፡ በሌሊት ሽፍት የትራንስፖርት አገልግሎት አናገኝም። ህይወታችንን ለአደጋ የሚጥል ሥራ ነው እየሰራን ያለነው ” ብለዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ የሚመለከታቸው አካላትና ድርጅቱ ለቅሬታው የተሻለ ምላሽ ቢሰጡ ወደ ሥራ እንደሚመለሱ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገረ ሲሆን፣ ጉዳዩ በቀጥታ አይሰን ኤክስፕሪያንስን እንጂ እሱን እንደማይመለከት ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተጨማሪም፣ ለቀረበበት ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጥ ከአይሰን ኤክስፕሪያንስ አቶ በፍቃዱ አበራን ጠይቋል።
አቶ በፍቃዱ፣ በጉዳቹ ዙሪያ ስብሰባ ላይ እንደሆኑ የገለጹ ሲሆን፣ ተጠይቀው በሰጡት ቀጠሮ ወቅት ሲደወልም ስልክ ለማንሳት ለጊዜው ፍቃደኛ አልሆኑም።
በተጨማሪም ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለጉዳዩ አስተያዬት እንዲሰጡ ለኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኀበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዚደንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ለጊዜው የማይመች ሁኔታ ላይ እንዳሉ ገልጸው ቀጠሮ ሰጥተዋል።
የሚመለከታቸው አካላት በቅሬታው ላይ አሁንም አጥጋቢ ምላሽ ከሰጡ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል። (የቅሬታ አቅራቢዎቹ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)