ዋሪት !
የቤትም ሆነ የቢሮ እቃዎች መግዛት ሲፈልጉ ትክክለኛ ምርጫዎ ወደሆነው ዋሪት ብቅ ይበሉ። ወደየትኛውም ቅርንጫፋችን ጎራ ሲሉ የዓይን አዋጅ የሚሆኑብዎትን ምርቶቻችንን ከሙሉ ግርማ ሞገስ እና ውበት ጋር ያገኛሉ። ስለ ጥራታቸውም ሆነ ውበታቸው ሃሳብ እንዳይገባዎ።
ዋሪት ፈርኒቸር
ትክክለኛ ምርጫ!!
* 22- ዋሪት ህንፃ
* ጉርድ ሾላ- ሴንቸሪ ሞል
* ለቡ- ቫርኔሮ ፊት ለፊት
* ፒያሳ- ፍርዱ ኮሜርሻል
* ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት
* አዳማ- ሶረቲ ሞል
* ወሎ ሰፈር- ጋራድ ህንፃ
📞0911210706 | 0911210707
www.warytze.com
ፌስቡክ፡ www.fb.com/WARYTZE
ቴሌግራም፡ https://t.iss.one/warytfurniture
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/warytfurniture/
ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/@warytzefurniture

#ኮሬ
“ ባለፉት ዓመታት ከ300 በላይ ንጹሐን በታጣቂዎች ተገድለዋል ” - ኮሬ ዞን ኮሚዩኒኬሽን
“መንግስት ቸልተኛ ሆኗል የሚል ግምገማ አለን። ዛሬ ጠዋትም ሰው ተገድሏል” - የክልሉ ተወካዮች ምክር ቤት
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ንጹሐን ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች፣ ዞኑና የክልሉ ተወካዮች ምክር ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በዞኑ ጎርካ ወረዳ ዳኖና ኬረዳ ቀበሌዎች የምዕራብ ጉጂ ታጣቂዎች መስከረም 27 እና 25 ቀን 2017 ዓ/ም በዳኖና ኬረዳ ቀበሌዎች ታጣቂዎቹ በፈጸሙት ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ሁለት ቆስለዋል ብለው፣ አሁንም ከፍተኛ ስጋት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ስለጉዳዩ ማረጋጠጫ የጠየቅናቸው የኮሬ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ተወካይ አቶ አማረ አክሊሉ በበኩላቸው ፣ “ከምዕራብ ጉጂ ዞን ጋላና ወረዳ የሚመጡ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት በኬረዳ ቀበሌ አንድ አርሶ አደር ወዲያው ሲሞት፣ አንዱ ክፉኛ ቆስሏል” ብለዋል።
“በዳኖ ቀበሌ ደግሞ ማሳ ላይ በነበሩ አርሶ አደሮች ላይ ከፍተኛ የተኩስ ሩምታ ከፍተው አንድ አርሶ አደር ወዲያው ሲሞት፣ አንዱ ደግሞ ቆስሏል” ሲሉም አክለዋል።
“መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ/ም የ 'ሸኔ’ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አራት አርሶ አደሮች ሲገደሉ፣ አንድ አርሶ አደር ነበር የቆሰለው። የአሁኑን ጥቃት ያደረሰው ግን በምዕራብ ጉጂ ዞን ጋላና ወረዳ የተሰማራ ሌላ ታጣቂ ኃይል ነው” ብለዋል።
“በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ባለፉት ዓመታት ከ300 በላይ ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል” ነው ያሉት።
ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ የጠቅናቸው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የኮሬ ህዝብ የቀድሞው አማሮ ምርጫ ክልል ተወካይ አቶ ዘናነህ አዱላ ምላሽ ሰጥተዋል።
“አካባቢው ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ በጸጥታ ችግር የወደቀ አካባቢ ነው። በአካባቢው ከመንግስትን ተቃርኖ የሚንቀሳቀሰው የ‘ሸኔ’ ታጣቂ መኖሩ ሁኔታውን አባብሶታል።
ህዝቡ በጸጥታ ችግር ላይ ነው ያለው። ቀዳሚው ትኩረትም ሊሆን የሚገባው ሰላም ነው። በምዕራብ ጉጂ በኩል የመንግስት ክንፉ ሙሉ ለሙሉ የሚተገበርበት ነው ብዬ አላምንም። ምክንያቱም በሌሎች ታጣቂዎች እጅ የወደቀ ስለሆነ።
አሁንም ህዝቡ ቅሬታው 'ችግር ፈጣሪው ተለይቶ መንግስት ሙሉ ለሙሉ እርምጃ አልወሰደም' የሚል ነው። ህዝቡ መንግስት ላይ ቅሬታ አለው። የቀጠለ ችግር አለ እውነት ነው ህዝቡ የሚያነሳው” ነው ያሉት።
የአካባቢው ህዝብ ተወካይ እንደመሆናችሁ መጠን ችግሩ እንዲቀረፍ ወደ መንግስት ምን ግፊት አድርጋችኋል? ለሚለው ጥያቄ ምላሻቸው “በዚህ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ከመንግስት ጋር እያወራን ነው። አሁንም ህዝቡን ድምጽ እያሰማን ነው” የሚል ነው።
“መንግስት ሰፊ የኦፕሬሽን ሥራዎችን የሰራበት ሁኔታ አለ። ግን በመሀል አርሶ አደርን በማፈናቀል፤ የኮሬንና ጉጂን ህዝብ በማጋጨት የፓለቲካ ትርፍና ሀብት ለማግኘት የሚፈልግ ክንፍ ነው አስቸጋሪ የሆነው” ብለዋል።
ችግሩ የቆዬ ነውና መፍትሄው ለምን ዘገዬ? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ፣ “በዚህ ጉዳይ እኛም መንግስት ቸልተኛ ሆኗል የሚል ግምገማ አለን። ዛሬ ጠዋትም ሰው ተገድሏል። ስለዚህ መንግስት የህዝብን ችግር ይቅረፍ” ሲሉ አስተያየት ተሰጥተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray
" ለሚፈጠረው ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ብቸኛ ተጠያቂ ቡድኑና አመራሩ መሆናቸውን ለህዝባችን መግለፅ እንወዳለን " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ስርዓት አልበኝነት ለመቆጣጠር " የጥፋት ሃይል " ሲል በስም ባልገለፀው አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታወቀ።
" ህግና ስርዓት ለማስክበር የተጀመሩ ጥረቶች በማጠናክር የህዝቡ ስጋት ከግምት ያስገባ እንቅስቃሴ አደርጋለሁ " ብሏል ጊዚያዊ አስተዳደሩ።
በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት መስከረም 27/2017 ዓ.ም ያወጣውን የመንግስታዊ ስልጣን ሹም ሽር የነቀፈው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፤ " ቡድኑ ወደ ስርዓት አልበኝነት ለመሸጋገር የሚያስችለው ግልፅ መንግስታዊ ግልበጣ ማካሄዱን አውጇል " ሲል ከሰዋል።
" ቡድኑ የመንግስት ስልጣን እንዴትና በምን ሁኔታ እንደሚያዝ ተደብቆት ሳይሆን ከዛሬ መስከረም 27/2017 ዓ.ም ጀምሮ ስርዓት አልበኝነት ለማስፈን ያለው ከፍተኛ ፍላጎት ለማሳካት ሆን ብሎ ያደረገው ነው " ብሏል የጊዚያዊ አስተዳደሩ።
" ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህንን ስርዓት አልበኝነት በትእግስት አያልፈውም " ብሎ " የጥፋት ሃይል " ሲል በገለፀው አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ይጀምራል ብሏል።
" በሂደቱ ለሚፈጠር ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ብቸኛ ተጠያቂ ቡድኑና አመራሩ መሆናቸውን ለህዝባችን መግለፅ እንወዳለን " ሲል አስጠንቅቋል።
በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራ ህወሓት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው በጉባኤ ያልተሳተፉ 13 የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች በጉባኤ በተሳተፉ 14 አመራሮች ለመተካት " ወሰኛለሁ " የሚል መግለጫ ዛሬ መስከረም 27/2917 ዓ.ም ማውጣቱን መዘገባችን ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

#Tigray " ለሚፈጠረው ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ብቸኛ ተጠያቂ ቡድኑና አመራሩ መሆናቸውን ለህዝባችን መግለፅ እንወዳለን " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ስርዓት አልበኝነት ለመቆጣጠር " የጥፋት ሃይል " ሲል በስም ባልገለፀው አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታወቀ። " ህግና ስርዓት ለማስክበር የተጀመሩ ጥረቶች በማጠናክር የህዝቡ ስጋት ከግምት ያስገባ…
" በህዝቡ ውስጥ የመረበሽ ስሜት ተፈጥሯል ፤ ... ችግር ሲፈጠር ዝም ብለን አንመለከትም " - የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች
በተፃራሪ መግለጫዎች ምክንያት በትግራይ ውስጥ ማንኛውም የፀጥታ ችግር እና ስርዓት አልበኝነት እንዲፈጠር እንደማይፈቅድ የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች አስታውቋል።
የፀጥታ ሃይሎች ባወጡት አጭር የፅሁፍ መግለጫ ፥ " መስከረም 27 ጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚመለከቱ ሁለት ተፃራሪ መግለጫዎች መውጣታቸው ተከትሎ በህዝቡ ውስጥ የመረበሽ ስሜት ተፈጥሯል " ብለዋል።
" የትግራይን ሰላም እና ደህንነት እናረጋግጣለን " ያሉት የፀጥታ ኃይሎቹ " በተፃራሪ መግለጫዎች ምክንያት ስርአት አልበኝነት እንዲፈጠር አንፈቅድም ፤ ችግር ሲፈጠርም በዝምታ አንመለከትም " ሲሉ አሳውቀዋል።
በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 13 የጊዚያዊ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች በማንሳት በሌሎች 14 የድርጅቱ አባላት እንዲተኩ መወሰኑን ከገለፀ በኋላ ጊዚያዊ አስተዳደሩ " የመንግስት ግልበጣ ነው " ያለው ተግባር የሚያርም " ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ " ሲል ገልጿል።
#TikvahEthiopiaMekelleFamily

#Ethiotelecom
✨ አሁንም ቴሌብር ሱፐርአፕን መጋበዝ እስከ 10,000 ብር ያሸልማል!
ቴሌብር ሱፐርአፕ ላይ “ይጋብዙ ይሸለሙ” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም
💬 በአጭር መልእክት ወይም
🌐 በማኅበራዊ ሚዲያ
መተግበሪያውን ያጋሩ፤ ወዳጆችዎ ግብይት ሲጀምሩ እርስዎ የ30 ብር ስጦታ ያገኛሉ፡፡
💁♂️ በተጨማሪም ታብሌቶችና ስማርት ስልኮች እንዲሁም ሌሎች ሽልማቶችን ባካተተው ለዕድል ጨዋታ ብቁ ይሆናሉ!
🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ይጫኑ!
✅ ለዕድል ጨዋታው ብቁ የሚሆኑት 20 አዲስ ደንበኞችን ሲያገኙ ነው!
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia

#Update
በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ ለ4ኛ ጊዜ ቀጠሮ መሰጠቱ ተሰማ።
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ በተሰሙ የምስክሮችን ቃል መርምሮ ብይን ለመስጠት ለ4ኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ በተከሳሾች ፦
- ቄስ በላይ መኮንን፣
- በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ እንዳለ ወ/መስቀል፣
- በኮሚሽን ስራ ላይ በተሰማራው በረከት ሙላቱ ጃፋር
- አለምገና ሳሙኤል ዲንሳ
- የኒሞና ንግድ ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አበራ መርጋ ተስፋዬ በተባሉት ላይ ከባድ ማታለል ሙስና ወንጀል ክስ መመስረቱ ይታወሳል።
በዚህም ተከሳሾቹ ከአፍሪካ ህብረት ምንም አይነት የክፍያ ትእዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ ላይ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተራ ቁጥር ለተከሰሱ ተከሳሾች በተለያዩ የዶላር መጠን ክፍያ ይፈጸምላቸው የሚል አጠቃላይ የ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሀሰተኛ የክፍያ ሰነድ በአንደኛ ተከሳሽ መቅረቡ ተጠቅሶ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ከባድ ማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቷል።
በዚህ መልኩ የቀረበውን ክስ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ብቻ ችሎት የቀረቡና የክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በአድራሻቸው ባለመገኘታቸውና በተደጋጋሚ ቀጠሮ ባለመቅረባቸው ለጊዜው ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል።
ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ክሱ እንዲሻሻልላቸው ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ነጥቦችን ፍርድ ቤቱ መርምሮ ወደፊት በማስረጃ እንደሚጣራ ገልጾ መቃወሚያቸውን አልተቀበለውም።
ከዚህም በኋላ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው ተከሳሾቹ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ህግ የአፍሪካ ህብረት ቅርጫፍ የባንክ ባለሙያዎችን አጠቃላይ ሶስት ምስክሮችን አቅርቦ ምስክርነታቸውን አሰምቶ ነበር፡፡
በዚህም ዐቃቤ ህግ ቀረበ ስለተባለው ሀሰተኛ የክፍያ ሰነድና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የምስክር ጭብጥ በማስመዝገብ በዋና ጥያቄ ምስክሮቹን ቃል ያሰማ ሲሆን በዕለቱ የተከሳሽ ጠበቆች ለምስክሮች በመስቀለኛ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን በፍርድ ቤቱ የማጣሪያ ጥያቄ ተነስቶ ከምስክሮች መልስ ተሰጥቶበት እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ህግ ምስክር ቃል መርምሮ ብይን ለመስጠት ከሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሶስት ጊዜ ቀጥሮ ነበር፤ ይሁንና ዛሬም በነበረ ቀጠሮ በተለያዩ ስራዎችና ምክንያት መዝገቡ ተመርምሮ ተሰርቶ አለመጠናቀቁ መዝገቡን በሚመለከቱት ዳኛ በኩል ተገልጾ በድጋሚ ለ4ኛ ጊዜ ለጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ተቀጥሯል።
የመረጃው ምንጭ ኤፍ ቢ ሲ ነው።

#ኢትዮጵያ
በተቋማት እና ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል ተባለ።
የጥቅምት ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሳይበር ደህንነት ወር በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚሀም ወር በርካታ ሃገራት የዜጎቻቸውንና የተቋማቶቻቸውን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ሀሊናን ለመገንባት የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናሉ።
በኢትዮጵያም 5ኛ ጊዜ "የቁልፍ መሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 1-30/2017 ዓ/ም በኢንፎርሜሽን መረብ ደሀንነት አስተዳደር አዘጋጅነት የሳይበር ደህንነት ወር ይከበራል፡፡
በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የሳይበር ደህንነት ወር አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በተቋማት እና ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል ብለዋል።
ጥቃት የሚደርስባቸው እና ተጋላጭ ከሆኑ ተቋማት መካከል የፋይናንስ፣ የትራንስፖርት እና የኢነርጂ ተቋማት ይጠቀሳሉ።
በመሆኑም የሳይበር ደህንነት ወር የተቋማትን እና የኅብረተሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ሀሊና በማጎልበት ለሳይበር ደህንነት ተገቢ ትኩረት እንዲሰጡና ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል እንዲችሉ የሚያግዙ የተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚቀርቡበት ነው ብለዋል።
5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የመከፈቻ ፕሮግራም ጥቅምት 1/2017 ዓ/ም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም የሚከፈት ይሆናል፡፡

“ በሆስፒታሉ 600 አልጋዎች አሉ። ግን ተኝቶ መታከም የሚገባቸው 800 ሺህ ህሙማን ውስጥ ከአንድ አስሩ እንኳ ቢሆን ወደ 80 ሺህ ያስፈልጋል” - ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል
ወደ ሆስፒታሉ ከሚሄዱ በርካታ ህሙማን ጋር በተያያዘ የአልጋና የበጀት እጥረት እንደሚፈትነው ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
መንግስት በተወሰነ መልኩ ትኩረት ቢሰጥም ሆስፒታሉ ካለበት ችግር አንጻር ሲታይ ይመጥናል ተብሎ እንደማይታሰብ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኢክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አንዱዓለም ደነቀ (ፕ/ር) ተናግረዋል።
በሆስፒታሉ ትኩረት ስለሚሻው አንገብጋቢ ጉዳይ ዙሪያ በሰጡት ቃል፣ “ከፔሸንት ሎድ አንጻር ችግሮች ይከሰታሉ። የሚከተሰቱት ችግርች የእጥረት ችግሮች ናቸው። እጥረቱ የአልጋ፣ የበጀት ነው” ብለዋል።
“ከ50 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ፣ ለብዙ ዓመታት ጥገና ያልነበረው ሆስፒታል እንደመሆኑ መጠን ብዙ ተግዳሮቶች አሉ። እኛ ሆስፒታል ብቻ አይደለንም የመማሪያ ተቋምም ነን። በዚህ የተነሳ ጥቅምም ተግዳሮትም ይኖረዋል” ነው ያሉት።
የአልጋው እጥረት በምን ደረጃ ነው? አሁን ምን ያህል አለ? ከህሙማን ብዛት አንጻርስ ምን ያክል አልጋ መኖር ነበረበት? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።
“ ከድንገተኛ ክፍል ልጀምር። ያለን የድንገተኛ ክፍል በጣም ትንሽ መሆኑ ብቻ አይደለም ለማደራጀትም አስቸጋሪ የሆነ ከባድ ተግዳሮት ያለበት ክፍል ነው።
ስለዚህ አልጋው አይበቃንም። አልጋው ብቻ ሳይሆን ቦታውም አይበቃንም። አልጋውን እንሞላና ህሙማንን እንደገና ወንበር ላይ እናስቀምጣለን።
ታካሚን ወንበር ላይ አስቀምጦ ማከም ከባድ ዲስኮንፈርት አለው። ለታካሚ ብቻ ሳይሆን ለሀኪምም ጭምር። ግን ምንም አገልግሎት ካለማግኘት ትንሽ ማግኘት ስለሚሻል ያለውን ፋሲሊቲ በመጠቀም እናገለግላለን።
የችግሩ መኖር ህሙማን እርካታ ላይ ከፍተኛ ጫና ያመጣል። በዛ ላይ የቁሳቁስ እጥረት ሲኖር ‘ግዙ’ ሊባሉ ይችላሉ። የሚገዛው ቁስ ደግሞ የሚገኘው ውጪ ሊሆን ይችላል። ብቻ ብዙ የተያያዙ ችግሮች አሉ።
በሆስፒታሉ 600 አልጋዎች አሉ። አጣበንም ቢሆን ትንሽ እንጨምርበታለን። በዓመት ውስጥ እስከ 21 ሺህ ሰዎች አስተኝተን እናክማለን።
ይህ ሲሰላ ኦልሞስት አልጋው ሁል ጊዜ እንደተያዘ ነው ማለት ነው። ሆስፒታሉ ውስጥ ከ800 ሺህ ህሙማን በላይ ነው በዓመት የሚመጡት። ከእነዛ ውስጥ ነው 21 ሺውን ነው አስተኝተን የምናክመው።
ነገር ግን ተኝቶ መታከም የሚገባቸው ከ800 ሺህ ህሙማን ውስጥ ከአንድ አስሩ እንኳ ቢሆን ወደ 80 ሺህ ያስፈልጋል ማለት ነው። ይሄ ያለንን ችግር ያሳያል። ስለዚህ ቀጠሮ እንሰጣለን ማለት ነው።
ሌላው በቁሳቁስ እጥረት ምክንያት የማንሰራቸው፣ ቀጠሮ የምንሰጣቸው ተመልሶ ሲገኝ ደግሞ የምንሰራቸው አሉ። ይሄ ሁሉ ቻሌንጅ ቢኖርም ተስፋ ባለመቁረጥ የተቻለንን እያደረግን ነው ” ብለዋል።

#AddisAbaba
" የቀበሌና የፌደራል ቤቶች ውስጥ ለነበሩ 4,000 መኖሪያ ቤቶች ተዘጋጅተዋል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በአዲስ አበባ ይካሄዳል በተባለው 2ኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ለሚነሱ የግል ባይዞታዎች 5 ቢሊዮን ብር ካሳ እና 100 ሄክታር ምትክ መሬት መዘጋጀቱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል።
በሁለተኛው ምዕራፍ ከሚነሱት ውስጥ ፦
➡️ 80 በመቶው የቀበሌ ቤት፣
➡️10 በመቶው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቤቶች ነዋሪዎች
➡️ 10 በመቶው የግል ባለይዞታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የቀበሌ እና የፌደራል ቤቶች ውስጥ ለነበሩ 4,000 መኖሪያ ቤቶች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።
ለስራ እድል ፈጠራ በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ አካላት የማምረቻ፣ መሸጫ እና ምርት መያዣ ሼዶች በቀበሌ እና በንግድ በቤቶች ኮርፖሬሽን ሲሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች ተደራጅተው የንግድ ቦታ እንዲገነቡ እንዲሁም በአነስተኛ ሱቆች ሲሰሩ ለነበሩ 500 የሱቅ ኮንቴነሮች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።
በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እና መልሶ ማልማት በ8 ኮሪደሮች 132 ኪሎሜትር ርዝመት እና ከ 2,817 ሄክታር ቦታ ለማልማት ተቅዷል ብለዋል።
የሁለተኛው ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት መስመሮች የትኞቹ ናቸው ?
1. ካዛንቺስ፣ መስቀል አደባባይ፣ ሜክሲኮ፣ ቸርችል፣ አራት ኪሎ፣ እስጢፋኖስ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት 1000 ሄክታር ቦታ ስፋት እና 40.4 ኪሎሜትር ርዝመት ፤
2. ሳውዝጌት፣ መገናኛ ፣ ሃያሁለት፣ መስቀል አደባባይ የኮሪደር ልማት 128.7 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 7.1 ኪሎሜትር ርዝመት፤
3. ሲኤምሲ፣ ሰሚት ጎሮ፣ ቦሌ አየር ማረፊያ ቪአይፒ ተርሚናል፣ አዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚብሽን ማዕከል የኮሪደር ልማት 146 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 10.8 ኪሎሜትር ርዝመት፤
4. ሳር ቤት፣ ካርል አደባባይ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ አቦ ማዞሪያ፣ ላፍቶ አደባባይ፣ ፉሪ አደባባይ ኮሪደር ልማት 565 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 15.9 ኪሎሜትር ርዝመት፤
5. አንበሳ ጋራዥ፣ ጃክሮስ ጎሮ ኮሪደር ልማት 16.58 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 3.1 ኪሎሜትር ርዝመት
6. አራት ኪሎ፣ ሽሮ ሜዳ እንጦጦ ማርያም፣ ጉለሌ እጸዋት ማዕከል የኮሪደር ልማት 314 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 13.19 ኪሎሜትር ርዝመት
7. የቀበና ወንዝ ዳርቻ ኮሪደር ልማት 372.5 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 20 ኪሎሜትር ርዝመት፤
8. እንጦጦ፣ ፒኮክ ፓርክ የወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደር ልማት 274 ሄክታር የቦታ ስፋት እና 21.5 ኪሎሜትር ርዝመት፤
በአጠቃላይ በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት 2817 ሄክታር የቦታ ስፋት ሲኖረው 132 ኪሎሜትር ርዝመት ይሸፍናል።
#AddisAbaba #ShegerFM

#Attention🚨 በአዋሽ ፣ መተሀራ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አሳውቋል። " በሬክተር ስኬል 4.9 ነው። 150 ኪሎሜትር አካባቢ ርቀት ላይ የተፈፀመ ነው። ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል " ብሏል። " በስምጥ ሸለቆች ውስጥ ንዝራቱ ከማሰማት በሻገር የመሬት መንቀጥቀጥ ከፈንታሌ ተራሮች ውጭ የደረሰ ስለመኖሩ አልተረጋገጠም " ሲል አክሏል። " በደሴ…
#Afar
በአፋር ክልል ዱለሳ ወረዳ በተከሰተ " የመሬት መንቀጥቀጥ " ምክንያት ከተፈጠረ የመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውሃ መፍለቅ መጀመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የወረዳው አስተዳደር ተናግረዋል።
ከትናንት ሌሊት ጀምሮ መፍለቅ የጀመረው ፍል ውሃ መጠኑ እየጨመረ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
አፋር ክልል ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እያስተናገደ ነው።
በክልሉ ጋቢ ራሱ ዞን በሚገኘው ዱለሳ ወረዳ ሳንጋቶ ቀበሌ ፍል ውሃ መፍለቅ የጀመረው ትናንት ሰኞ መስከረም 27/2016 ዓ.ም. ምሽት " የመሬት መንቀጥቀጥ " ከተከሰተ በኋላ እንደሆነ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ደስታ እና ሁለት የቀበሌው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ነዋሪዎች ምን አሉ ?
- ትናንት ምሽት ሦስት ሰዓት ገደማ መከሰት የጀመረው የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ ሶስት ጊዜ ያህል ተደጋግሟል።
- የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የሚናገሩት ካቆመ በኋላ ሌሊት 10 ሰዓት ገደማ ላይ ድምፅ ሰማን። ጠዋት ላይ ድምፅ ወደተሰማበት ቦታ ስናመራ ከመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውሃ እየፈለቀ ተመልክተናል።
- ውሃው የወጣው የአካባቢው ማህበረሰብ በሚኖርበት ሰፈር ውስጥ ነው። ድምፅ ነበረው። ማታ ፈርተን ነው ያደርነው። በጠዋት ሄደን ሁሉንም ነገር ለማየት ችለናል።
- ውሃው በሚወጣበት የመሬት ስንጥቅ ስር ድምፅ ይሰማል። ወደላይ የሚፈናጠረው ፍል ውሃ መጠን እና የሚፈልቅበት ስንጥቅ መጠን እየጨመረ ነው።
ፍል ውሃው በወጣበት ሳንጋቶ ቀበሌ ውስጥ ፍል ውሃ ባለመኖሩ አዲሱ ክስተት ነዋሪዎች ድንጋጤ እና ስጋት ላይ ጥሏል።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አሊ ደስታ ምን አሉ ?
° ከትናንት በስቲያ ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አንጻር የትናንቱ ትንሽ ያነሰ ነው።
° ከዚህ በኃላ ነው ፍል ውሃ መፍለቅ የጀመረው።
° ሰዎች በቅርበት እዚያ አካባቢ ይኖራሉ። የእኛ አካባቢ ማህበረሰብ አርብቶ አደር ከመሆኑ አኳያ ከብቶቻቸውን ፍየሎቻቸውን የሚጠብቁበት ቦታ ነው።
° የወረዳው አስተዳደር ክስተቱን ለማጣራት ባለሙያዎችን ወደ ቀበሌው ልኳል።
° የሚፈጠረው ነገር ስለማይታወቅ ነዋሪዎች’ ከዚያ አካባቢ ለቅቀው ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄዱ የማድረግ ስራ እየሰራን ነው። እንደዚህ አይነት ነገር ታይቶም ስለማይታወቅ ከፍተኛ ስጋት ነው ያለው።
የአፋር ክልል ጋቢ ራሱ ዞን በተደጋጋሚ እያጋጠመ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ነዋሪዎች ከሰፈሩበት አካባቢ እንዲነሱ እየተደረገ ነው።
አንዱ አካባቢው ይኸው የዱለሳ ወረዳ ነው።
አጎራባቹ አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ከሁለት ሳምንት በፊት በአካባቢው በሚገኘው ከሰም ግድብ እና ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የሚኖሩ ከ700 በላይ ሰዎችን ገላጣ ሜዳ ወደሆኑ አካባቢዎች አዘዋውሯል።
መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ሲሆን ፎቶና ቪድዮ የአብዶ ሀሰን፣ ሱልጣን ከሚል ነው።

የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል። የመስከረም ወር 2017 ዓ/ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ነሃሴ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አሳውቀዋል። ሚኒስትሩ ፥ የነዳጅ ማደያዎች ካልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። @tikvahethiopia
የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።
ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚቆይ የሁሉም የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተሰምቷል።
በዚህ መሰረት፦
➡️ ቤንዚን - ብር 91.14 በሊትር
➡️ ነጭ ናፍጣ - ብር 90.28 በሊትር
➡️ ኬሮሲን - ብር 90.28 በሊትር
➡️ ቀላል ጥቁር ናፍጣ - ብር 100.20 በሊትር
➡️ ከባድ ጥቁር ናፍጣ - ብር 97.67 በሊትር
➡️ የአውሮፕላን ነዳጅ - ብር 77.76 በሊትር ሆኗል።
መረጃው ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው የተገኘው።