TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ? " እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ…
#ATTENTION🚨
ድጋሚ ሊከሰት ይችላል ? መደረግ ያለበት ጥንቃቄስ ምንድነው ?
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ምን አሉ ?
" ድጋሚ ሊከሰት ይችላል ወይ ? የሚባለው ሰሞኑን በሙሉ ይሄን አይነት ንዝረቶች ነበሩ።
መሬት መንቀጥቀጥ መተንበይ የሚባል ነገር የለም ፤ የት አካባቢ እንደሆነ እንጂ መቼ ይከሰታል የሚባለውን መተንበይ አይቻልም።
ስለዚህ ሊከሰት ይችላል ሊመጣ ይችላል። ይሄ ሁል ጊዜ በተለይ አዲስ አበባ የምንኖር ሰዎች ነቅተን የምንጠብቀው ነገር መሆን አለበት።
ስምጥ ሸለቆና የስምጥ ሸለቆ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ነቅተን የምንጠብቀው ነገር ነው መሆን ያለበት።
ለጊዜው መናገር የምችለው ከበድ ያለ ነገር ከመጣ አይመጣም ብለን ነው የምንገምተው ከመጣ ግን ምን መደረግ ስለለበት ጥንቃቄ ነው።
➡️ የቤት ቋሚዎች በተለይ ኮንዶሚኒየም ህንጻ ላይ ያሉ ሰዎች ኮለኖች አካባቢ መጠጋት ለምን መውረድ ሊከብድ ይችላል ቁልፍ ማክፈትም ሊከብድ ይችላል። ስለዚህ ኮለኖች አካባቢ መጠጋት።
➡️ ከተቻለ ጠረጴዛ ስር መግባት።
➡️ ሊፍት አትጠቀሙ። ማንም ሰው በሊፍት ለመውረድ እንዳይሞክር። ያን እንዳትጠቀሙ።
ይሄን ይሄን ጥንቃቄ ማደርግ ያስፈልጋል። ነገር ግን አሁን ባለው እዚህ ደረጃ የሚያደርስ ከባድ ነገር አለ ብለን አንገምትም። "
#Ethiopia #AddisAbaba
@tikvahethiopia

Photo
#ለጥንቃቄ🚨
የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብን ?
➡️ ከቤት ውጭ ከሆኑ ፦ ከዛፎች ፣ ከሕንፃዎች ፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።
➡️ በቤት ውስጥ ከሆኑ ፦ በበር መቃኖች ፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።
➡️ በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ ፦ ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር ፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።
➡️ መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ ፦ የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።
#Ethiopia #AddisAbaba #የእሳትናአደጋስራአመራር

#MPESASafaricom
💫ከዳር እስከ ዳር በፈጣኑ የሳፋሪኮም ኢንተርኔት አሁንም አንድ ወደፊት! ባለው የሳፋሪኮም ኔትወርክ አሁንም አንድ ወደፊት እያልን እንገናኝ!✨ የተመቸንን ሼር እናድርግ!👍ከወደድነው ❤️ጋር እንደልብ እንገናኝ!
አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!
የቴሌግራም ቦታችንን https://t.iss.one/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
#SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether

ፎቶ ፦ የአልነጃሺ መስጂድ መልሶ የመጠገን ስራ በመከናወን ላይ እንደሆነ ተገልጿል።
ከትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በተገኘው መረጃ ፥ በትግራይ ጦርነት ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው ቅርሶች አንዱ የሆነው ቅዱሱ መስጂድ አልነጃሺን መልሶ የመጠገን እና የማልማት ስራ ከያዝነው ወር መጀመሪያ ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።
ጥገናው የመስጂዱን ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ይዘት በጠበቀ መልኩ በመከናወን ላይ ነው ተብሏል።
በሚቀጥሉት 8 ወራት ጥገናው ተጠናቅቆ ክፍት እንደሚደረግ ተመላክቷል።
የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የአልነጃሺ ቅዱስ መስጂድን መልሶ ለመጠገን ከቱርክ ልማት ኤጀንሲ (ቲካ) ጋር መፈራረሙ ቢሮው አስታውሷል።

#ኢትዮጵያ
የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ከደቂቃዎች በኃላ መካሄድ ይጀምራል።
የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ከ8 ሰዓት ጀምሮ ነው የሚካሄደው።
በዚህ መክፈቻ ላይ #የሪፐብሊኩ_ፕሬዚዳንት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት ለሁለቱ የፌደራል መንግሥት ምክር ቤቶች ዓመታዊውን ስራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌደራል መንግስትን ዓመታዊ ዕቅድ ያቀርባሉ።

#TPLF " ህዝብ በማደናገር ላይ ይገኛሉ " - በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የማዕከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ክፍፍል ተቀራርቦ ከመፈታት ይልቅ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ እየተካረረ መጥቷል። " ከህወሓት አባልነት የተባረሩ በማንኛውም ቦታና ጊዜ በህወሓት ስም ፓለቲካዊ ስራና እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም " ሲል በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት…
#TPLF
ከዛሬ ጀምሮ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ጨምሮ ሁሉም በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ በጉባኤ ያልተሳተፉ የስራ ሃላፊዎች በጉባኤ በተሳተፉ ሹማምንት መቀየሩን በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት " ወስኛለሁ " ብሏል።
" ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ህወሓት ከሰጣቸው የስራ ሃላፊነት ተነስተዋል እንዴትና በማን እንደሚተኩ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገርኩ ነው " ብሏል በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት።
ከየትኛው የፌዴራል መንግሥት አካል ጋር እየተወያየ እንደሆነ በግልጽ ያለው ነገር የለም።
ስለ ጉዳዩ እስካሁን በምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ከሚመራው ህወሓት በኩል የተሰጠ መልስ የለም።
በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራ ህወሓት ባወጣው የውሳኔ መግለጫ ፥ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔዎች ፣ ቢሮዎች ፣ ኤጀንሲዎች ፣ ኮሚሽኖች የዞን አስተዳደሮች የሚገኙ በጉባኤ ያልተሳተፉ የስራ ሃላፊዎች በማንሳት በጉባኤ በተሳተፉ አባላቱን ሙሉ በሙሉ መተካቱ አስታውቋል።
በዚሁ መሰረት ፦
- አቶ በየነ መክሩ
- ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት
- ዶ/ር ሓጎስ ጎዲፋይ
- ወ/ሮ አልማዝ ገ/ፃዲቕ
ከጊዚያው አስተዳደሩ ካቢኔ በማንሳት በ
- ዶ/ር አብራሃም ተኸስተ
- አቶ አማኒኤል አሰፋ
- ዶ/ር ፍስሃ ሃብተፅዮን
- አቶ ተወልደ ገ/ፃድቃን
- ወ/ሮ ብርኽቲ ገ/መድህን
- አቶ ይትባረክ አምሃ
- ዶ/ር ፀጋይ ብርሃነ መተካቱ ገልጿል።
- አቶ ርስቁ አለማው
- አቶ ሰለሙን መዓሾ
- አቶ ሺሻይ መረሳ
- አቶ ሃፍቱ ኪሮስ ከዞን ዋና አስተዳዳሪነት በማንሳት
- በአቶ ተኽላይ ገ/መድህን
- በአቶ ወልደኣብራሃ ገ/ፃዲቕ
- በአቶ ሺሻይ ግርማይ
- በአቶ ፍስሃ ሃይላይ
- በአቶ ሃይላይ ኣረጋዊ
- በዶ/ር አብራሃም ሓጎስ ተተክተዋል ብሏል።
በተጨማሪ
- አቶ ረዳኢ ሓለፎም
- ወ/ሮ ሰብለ ካሕሳይ
- አቶ ነጋ አሰፋ
- ዶ/ር ገ/ሂወት ገ/ሄር ከኤጀንሲ እና የኮሚሽን የስራ ሃላፊነት ወርደዋል ያለው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራ ህወሓት በእነ ማን እንደተተተኩ ያለው የለም።
ይህ ዘገባ አስከተጠናቀረበት ቀንና ሰዓት
ድረስ በምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ ከሚመራ ህወሓት በኩል የተሰጠ መልስ የለም።
#TikvahEthiopiaMekelleFamily

#BREAKING አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሾሙ በእጩነት ቀረቡ። @tikvahethiopia
#Update
አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡
በዚህም የፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።
አምባሳደር ታዬ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ከመሾማቸው በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡

#Update አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡ በዚህም የፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸው ተገልጿል። አምባሳደር ታዬ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ከመሾማቸው በፊት…
ፎቶ፦ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አዲስ ለተሾሙት ፕሬዜዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ህገመንግስቱን አስረክበዋል።
@tikvahethiopia
@tikvahethiopia