TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar #Tigray ትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው በኩል ባደረጉት ይፋዊ ግንኙነት የሁለቱም ህዝቦች አብሮነት የሚጎዱ ወንጀለኞች ተላለፈው እንዲሰጣጡ ተሰማሙ። በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ በዓፋር ክልል ሰመራ ከተማ ያደረገው የአንድ ቀን ምክክር አድርጓል። ምክክሩ ውጤታማ እንደነበር ተገልጿል። የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ልኡክ አባል የዓፋር ክልል…
#Afar #Tigray

" የትግራይ ክልል ሰላም ለክልላችን ሰላም ወሳኝ ነው " - ሀጂ አወል አርባ

የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት ሀጂ አወል አርባ ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ከፍተኛ አመራርን ላካተተዉ ሉዑካን ቡድን ምን አሉ ?

" የአፋርና ትግራይ ህዝቦች መካከል የሰላምና ፀጥታ ችግሮችን መፍታት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር አስፈላጊ ነው።

በሁለቱ ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰላምን ማስፈን አስፈላጊ ነው።

የትግራይ ክልል ሰላም ለክልላችን ሰላም ወሳኝ በመሆኑ በክልሉ መረጋጋትን ለመፍጠር የሁሉንም ተሳትፎ ይጠይቃል።

ለክልሉ ሰላምና መረጋገት የድርሻችንን እንወጣለን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
" የጥገና ሥራው ከ20 ቀን ያላነሰ ጊዜ ሊወስድ ይችላል " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ከቆቃ-ሁርሶ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈፀመ ስርቆት ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።

ኃይል የተቋረጠው በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በንቲ ቀበሌ ልዩ ስሙ አዋሽ ፓርክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ላይ በተፈፀመ ስርቆት ምክንያት ነው።

የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ፦
- በምስራቅ የሃገሪቱ ክፍል ለሚገኙ ከተሞችና አካባቢዎች፣
- ለአዲስ አበባ- ጅቡቲ የባቡር መስመር
- ለጅቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበ ነበር።

በደረሰው ጉዳት ምክንያት በተጠቀሱት ቦታዎች የኃይል አቅርቦት መቋረጡ ተገልጿል።

በስርቆት ምክንያት ከወደቀው አንድ ምሰሶ በተጨማሪ ሰባት የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

ጉዳት የደረሰበትን የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ለመቀየር የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን ተዋቅሮ ወደ ሥራ መግባቱ ተገልጿል።

ስርቆት የተፈፀመበት የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ጥምር የኤሌክትሪክ መስመሮችን የያዘ በመሆኑ የጥገና ሥራው ከ20 ቀን ያላነሰ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተመላክቷል።

የጥገና ሥራው ሙሉ በሙሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስም ከመስመሩ ኃይል ሲያገኙ ለነበሩ ከተሞችና አካባቢዎች በፈረቃ ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ ጥረቶች ይደረጋሉ ተብሏል።

ህብረተሰቡ የተፈጠረውን ችግር ተረድቶ በትዕግስት እንዲጠብቅ ተቋሙ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ፥ ከመተሃራ - አዋሽ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የባቡር መስመር ላይ በሚገኙ 9 የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

የጥገና ሥራዎችን ለማከናወን ርብርብ እየተደረገ ነው ተብሏል።

በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በኃይል ማስተላለፊያ ተሸካሚ ምሰሶ አካላት ላይ እየተፈፀሙ የሚገኙ የስርቆት ወንጀሎች መበራከታቸው የገለጸው ተቋሙ ፦
- የአካባቢው ማህበረሰብ፣
- የመስተዳድር
- የፀጥታ አካላት ለኃይል መሰረተ ልማቶቹ ተገቢውን ጥበቃና ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DV2026 የ2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ማመልከቻ ከነገ ጀምሮ ክፍት ይደረጋል። ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) አዘጋጅታለች። ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም። አሜሪካ በየዓመቱ ከኢትዮጵያ ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) አማካኝነት እንደምትቀበል ይታወቃል። በነገው ዕለት ዝርዝር መረጃ የምንልክላችሁ…
#DV2026

የ2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ማመልከቻ ከዛሬ ጀምሮ ክፍት ተደርጓል።

ለ2026 DV ለማመልከት https://dvprogram.state.gov/ ይጠቀሙ።

ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም።

ማመልከቻው እስከ ህዳር 5 /2024 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ከፍተኛ የመሙላት ፍላጎቶች ድረገጹ ላይ መዘግየቶችን ሊያስከትል ስለሚችል ለመሙላት እስከ የምዝገባው ጊዜ የመጨረሻ ሳምንት ድረስ ባይጠብቁ ይመከራል።

ዘግይተው የሚገቡ ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

ህጉ ለአንድ ሰው አንድ ጊዜ ብቻ እንዲያመለክት ነው የሚፈቅደው። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የሚጠቀመው የተራቀቀ ቴክኖሎጂ ደጋግሞ የሚገቡ ማመልከቻዎችን የሚለይ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ አንድ ሰው ካመለከተ ሁሉንም የዛን ሰዎች ማመልከቻዎች ይሰርዛል።

ያልተሟላ ማመልከቻም ተቀባይነት የለውም።

ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ከቪዛ አማካሪዎች ፣ ' እንሞላለን ' ከሚሉ ወኪሎችና ከሌሎች አካላት እገዛ ሳይጠይቁ ራስዎ እንዲሞሉ ይመከራል።

ማመልከቻውን እንዲሞላሎት የሰው እርዳታ ካስፈለገ ጥያቄዎችን በትክክል ለመመለስ በሚሞላበት ስፍራ መገኘት ያስፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪም የ ' ልዩ ማረጋገጫ ቁጥሩ ' ን ለመያዝ በስፍራው መገኝት ያስፈልጋል።

አንዳንድ የሚሞሉ ሰዎች ይህን ቁጥር ይዘው በመቀየር ተጨማሪ ብር የሚጠይቁ ስላሉ እንዳይታለሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

የማረጋገጫ ቁጥሩ እጅግ ወሳኝ በመሆኑ በጥንቃቄ መያዝ አለበት።

ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የሚደርስ የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ተዘጋጅቷል። ይህ ቁጥር ብቁ የሆኑ ሀገራት ሁሉ የሚጠቃልል ነው።

ኢትዮጵያውያንም ለማመልከት ብቁ ናቸው።

አሜሪካ በየዓመቱ ከኢትዮጵያ ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) አማካኝነት እንደምትቀበል ይታወቃል።

🇺🇸 ለአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ 2026 ለማመልከት ይህንን dvprogram.state.gov ሊንክ ይጠቀሙ !🇺🇸

(ተጨማሪ ማብራሪያ እና እንዴት መሙላት እንደሚቻል የሚገልጽ መመሪያ በቀጣይ እናያይዛለን)

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#MesiratEthiopia

📢 በሐዋሳ እና በድሬዳዋ ለምትገኙ ወጣቶች በሙሉ!

የመስራት የወጣቶች መማክርት ቡድን (M-YAG) አባል በመሆን ለለውጥ ድምጽ ሁኑ !

M-YAG ከቡድን በላይ ነው፤ በመስራት ፕሮግራም ውስጥ የወጣቶችን ድምጽ ለማሰማት የተዘጋጀ እንቅስቃሴ ነው።
ከ 15 እስከ 35 እድሜ የሆኑ ለመምራት፣ ለማነሳሳት እና በማህበረሰቦቻቸው ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለማሳደር ዝግጁ የሆኑ ወጣቶችን እየፈለግን ነው። በM-YAG በኩል በዋጋ ሊተመን የማይችል የግል እና ሙያዊ ክህሎቶችን ታገኛላችሁ፣ ጠንካራ አመራር ላይ ቁርጠኛ የሆነ ቡድን አካል ትሆናላችሁ።

ተጽዕኖ ለማሳደር ዝግጁ ከሆናችሁ እዚህ ተመዝገቡ፥ https://forms.gle/pd3JLtHM1u1fDD4D6

#MYAG #መስራት #Hawassa #ሐዋሳ #DireDawa #ድሬዳዋ
#ባይቶና

" በትግራይ ያጋጠመው ፓለቲካዊ ብልሽት የሚያጠራ ብሄራዊ እርቅ ያስፈልጋል " - ባይቶና ፓርቲ 

ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) የፓለቲካ ፓርቲ በክልሉ ወቅታዊ የፓለቲካ ሁኔታ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ " በትግራይ ያጋጠመው ፓለቲካዊ ብልሽት የሚፈታ ብሄራዊ የእርቅ ምክር ቤት ያስፈልጋል " ብሏል።

ብሄራዊ የዕርቅ ምክር ቤት በአስቸኳይ እንዲቋቋም የጠየቁት የባይቶና ፓርቲ ሊቀመንበር ክብሮም በርሀ ፥ ምክር ቤቱን የማቋቋም ሃላፊነት ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ይሰጥ ብሏል። 

የትግራይ ጥቅም የሚያረጋግጥ ብሄራዊ ዕርቅ ማካሄድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ የገለፁት ሊቀመንበሩ እርቅ ሲባል በልሂቃን መካከል የሚፈፀም እንደሆነ  አብራርተዋል። 

" የተፈጠረው መገፋፋት የትግራይ ብሄራዊ ጥቅም ወደ አደጋ እያስገባው ነው " ያሉት አቶ ክብሮም " ከመጠፋፋት ፓለቲካ ወጥተን የሰለጠነ ፓለቲካ ማራመድ አለብን " በማለት ተናግረዋል። 

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ የአንድ ቡድን ሳይሆን የጀግኖች ደም ባረጋገጠው የፕሪቶሪያ ስምምነት እውቅና ያለው ነው " ያሉት አቶ ክብሮም " ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንዳሻን የምንገነባውና የምናፈርሰው ሳይሆን ፀጋዎቹን አሟጠን በመጠቀም የህዝባችን ድህንነት ማረጋገጠረ አለብን ' ማለታቸው ቲክሻህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል። 

@tikvahethiopia 
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል።

ከኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ጋር በተያያዘ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል መስከረም 25/ 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይከበራል ፤ ይህን ተከትሎ የሚከተሉት መንገዶች ይዘጋሉ።

- ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ፤

- ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፤

- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ፤

- ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)፤

- ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ፤

- ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፤

- ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ፤

- ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ፤

- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ፤

- ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ ሼል አጠገብ፤

- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ፤


ከመስከረም 24/ 2017 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል።

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ መስጠት ይችላል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

💥ማን ዩናይትድ ከ ቶተንሃም 0-3 ሸንፈት በኋካ ዛሬ ምሽት ወደ ፖርቹጋል ተጉዞ ከፖርቶ ጋር ይጫወታል!

ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት መንገድ ይመለሳል?

👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሜዳ ፕላስ ፓኬጅ ይከታተሉ!

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#ChampionsLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvSelfServiceET
“ለፒኤችዲ የሚመጡት ተማሪዎች የኑሮ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው ለብቻው ሶልቭ የሚያደርገው አይደለም፡፡ አጠቃላይ የአገሪቷ ችግር ነው ” - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

በአንጋፋውና ራስ ገዙ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፒኤችዲ ትምህርታቸውን የሚማሩ ቤተሰብ ጭምር የሚያስተዳድሩ ተማሪዎች ኑሮው እጅግ ፈታኝ እንደሆነባቸው በምሬት ሲገልጹ ተስትውለዋል፡፡

ትምህርትቻውን የሚከታተሉት ለዛውም ሲያገኙ ሻይ በዳቦ እየተመገቡ፣ መቀየሪያ አጥተው ለበርካታ ጊዜ አንድ ልብስ ለብሰውና አንድ ጫማ ተጫምተው እንደሆነ ያነሳሉ።

በዚህም ሃፍረትና የዝቅተኝነት ስሜት አሸማቋቸው የሚያውቋቸውን ሰዎች ሲያዩ መንገድ ቀይሰው ለመሄድ፣ ቤተሰብ ላለመጠየቅ እንደተገደዱ በተሰበረ ድምጽ እሮሮ እያቀረቡ ነው፡፡ 

ይህንኑ ቅሬታ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምን አስተያየት እንዳለው ተጠይቆ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ምን አለ ?

“ ችግሩ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ብቻ አይደለም፡፡ አጠቃላይ ችግር ነው፡፡

ነገር ግን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለይ ለድኀረ ምረቃ ፕሮግራም በተቻለ አቅም ለመፍታት ካደረጋቸው አንዱ ጥረት በአነስተኛ ኪራይ የመኖሪያ ክፍሎችን (ዶርሚተሪ) ማዘጋጀት ነው፡፡

በግል በከተማ ውስጥ እንከራይ ቢባል ክራይስ እንደሚያመጣ ማንም ሰው መገመት የሚያቅተው አይደለምና አንዱ የዩቨርሲቲው ኮንትሪቢሽን በቀላሉ የፒኤችዲ ተማሪዎች ዶርም እንዲይዙ ማድረግ ነው፡፡

በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሚኖሩት የጥናትና ምርምር ሥራዎችም እንዲሳተፉ እያደረገም ነው ያደርጋልም፡፡

የፒኤችዲ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ፕሮግራም ውስጥ መማር ማስተማር በተወሰነ ደረጃ እስከ 3 ክሬዲት ሊሆን የሚችል ሎድ እንዲይዝ ነው የተደረገው፡፡ ይሄም ከመደገፍ አንጻር ሊታይ ይገባል፡፡

እንደ አጠቃላይ ለፒኤችዲ የሚመጡት ተማሪዎች የኑሮ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው ለብቻው ሶልቭ የሚያደርገው አይደለም፡፡ አጠቃላይ የአገሪቷ ችግር ነው፡፡

ከዛ ውጪ ዩኒቨርሲቲው ባለው አቅም ለመደገፍና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ፋላጎትና አቅም ኖሮት የያዘው አይደለም። ማድረግ የሚችለውን እያጣረ፣ መደገፍ የሚችለውን እያደገ ነው ያለው”
ብሏል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Djibouti 45 ስደተኞች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። ከየመን 310 ስደተኞችን በመጫን በጉዞ ላይ የነበሩ ሁለት ጀልባዎች ሰጥመው እስካሁን ባለው 45 ሰዎች መሞታቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል። የጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጠባቂ እንዳስታወቀው አደጋው በሰሜናዊ ምዕራብ ሖር አንጋር አካባቢ ካለው የባህር ዳርቻ 150 ሜትሮች ርቆ ነው የተከሰተው። ከሰኞ ጀምሮ በተደረገው ፍለጋ…
" የሞቱት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው " - በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ሰሞኑን በጅቡቲ የባህር ዳርቻ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ በአደጋው የሞቱት ዜጎች በሙሉ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው መረጋጋገጡን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም ማምሻውን ከየመን ወደ ጅቡቲ 320 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች ይዘው የተነሱት ሁለት የስደተኞች ጀልባዎች በጅቡቲ ባህር ዳርቻ አከባቢ ሲደርሱ በደረሰው አደጋ የበርካቶች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

አደጋውን ተከትሎ 48 ፍልሰተኞች ህይወታቸው ሲያልፍ፣ 197 ፍልሰተኞች ከአደጋው ተርፈው ኦቦክ የሚገኘው ዓለም አቀፉ የስደተኞች ካምፕ መድረሳቸው ተጠቅሷል።

የተቀሩት 75 ፍልሰተኞችን አካል የማፈላለጉ ስራ በነፍስ አድን ሠራተኞች መቀጠሉ ተጠቁሟል። 

እስከአሁን በስፍራው በተደረገው የዜጎች ማጣራት ሂደት ሁሉም ፍልሰተኞች ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ከሚመለከተው አካላት በተገኘው መረጃ ማወቅ መቻሉን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia " ማንኛውም ማሻሻያ ወይም የደመወዝ ስኬል ለውጥ ካለ ሕጋዊ ሰውነት ባላቸው እና በሚመለከታቸው አካላት ይፋ ይደረጋል " ሲል የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አሳውቋል። ውሳኔዎቹ ሲኖሩ በዝርዝር ጥናቶችና የበጀት አጸዳደቅ ሥርዓትን ተከትለው የሚካሄዱ እንደሆኑ ገልጿል። የትኛውንም አይነት መረጃ ሁልጊዜም በቀጥታ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ማጣራት እና ማገናዘብ ከስህተት ይታደጋልም ብሏል። የትላንትናው…
የመንግሥት_ሰራተኞች_የደመወዝ_ጭማሪ_1.pdf
14.9 MB
#ደመወዝ ፦ ይህ ስለ መንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ ጭማሪ የሚያትት ዶክመንት ባለፈው ዓመት ነሃሴ ወር ላይ ሲዘዋወር የነበር ነው።

ዶክመንቱ ከየትኛው አካል የወጣ እንደሆነ በግልጽ አይታወቅም።

በእርግጥም ከዚህ ወር ጀምሮ ወደ ትግበራ የሚገባው የመንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ ጭማሪ ይኸው ይሁን ወይስ ሌላ ስለሚለው ጉዳይ ወይም ደግሞ ስለዚህ ዶክመንት ትክክለኝነት ወይም ትክክል አለመሆን በግልጽ ወጥቶ ምላሽ የሰጠ አንድም አካል የለም።

ይህ ዶክመንት ወጥቶ ከመሰራጨቱ በፊት አንድ ስለ ደመወዝ ጭማሪ የሚያትት ምስል ተሰራጭቶ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ' ሀሰት ' ነው ማለቱ አይዘነጋም።

ስለዚህ የደመወዝ ጭማሪ ዶክመንት ግን ወጥቶ ያስተባበለ ሆነ ማረጋገጫ የሰጠ አካል የለም።

ይህ ጉዳይ በቀጥታ ይመለከታቸዋል የተባሉ አካላትን በማነጋገር ምላሽ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም አልተሳካም።

NB. ከላይ በፋይል የተያያዘው ስለ ደመወዝ ጭማሪ የሚያትተው ዶክመት በቀጥታ ጉዳዩ በሚመላከታቸው የትኛውም አካላት ያልተረጋገጠ ነገር ግን ደግሞ በይፋ ትክክል አይደለም ተብሎ ማስተባበያ ሆነ አስተያየት ያልተሰጠበት ነው።

#Ethiopia

@tikvahethiopia
#ደመወዝ

" የደመወዝ ጭማሪ ዝርዝሩ በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ይፋ ይደረጋል " - የገንዘብ ሚኒስቴር

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ፤ ከመስከረም ወር 2017 ጀምሮ የሚጨመር ደመወዝ በካቢኔ መፅደቁን አሳውቀዋል።

ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ትኩረት ያደረገ የተወሰነ የደመወዝ ጭማሪ መደረጉን አመልክተዋል።

አቶ አህመድ " የተወሰነ የደመወዝ ጭማሪ ለኑሮ ድጎማ ጭምር እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ በካቢኔ ፀድቋል ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ ይደረጋል። የደመወዝ ጭማሪው ከ91 እስከ 92 ቢሊዮን ብር መካከል ተጨማሪ በጀት የሚጠይቅ ይሆናል " ብለዋል።

በነባሩ በጀት የተወሰነ መግባቱን ፤ በተጨማሪ በጀትነትም የሚታወጅ መኖሩን ጠቁመዋል።

" ሲቪል ሰርቫንቱ አጠቃላይ የመንግሥት ሰራተኛው በሁሉም መስክ በፀጥታም በሌሎችም ዘርፍ ያሉትን የኑሮ ጫና ለመቋቋም የሚያስችለውን ድጋፍ ለማድረግ መንግሥት በከፍተኛ ቁርጠኝነት ተገባበት ነው " ሲሉ አቶ አህመድ ተናግረዋል።

" የባለፉት ሁለት ወራት የኢንፍሌሽን አፈጻጸም በሚታይበት ጊዜ እንደተሰጋው አይደለም። የተረጋጋ የዋጋ ሁኔታ ነው ያለው። የተወስነ ጭማሪ በአንዳንድ እቃዎች ላይ እንጂ በአብዛኛው የተረጋጋ ሁኔታ ነው ያለው። " ብለዋል።

" እንደዛም ሆኖ የደመወዝ ጭማሪው እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ የሰራተኛውን ቋሚ ደመወዝተኛ ገቢ ያለውን ዝቅተኛውን ትኩረት አድርገን የዝቅተኛውን በጣም ከፍተኛ ጭማሪ አድርገናል የላይኛውን ዝቅተኛ ጭማሪ አድርገን ነው የተሰራው ዝርዝሩ በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ይፋ ይደረጋል " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
" የ5 ተማሪዎቻችን ህይወት አልፏል " - መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ

በቀን 22/01/2017 በግምት ከጥዋቱ 4:00 ገደማ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ በተለምዶ " አባዱላ " የሚባለው መኪና ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል።

እንደ አማራ ፖሊስ መረጃ ፤ አደጋው የደረሰው በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ 015 ቀበሌ ደቦት ልዩ ቦታው እቧዮች ኪዳነምህረት አካባቢ ነው። መኪናው ከባህር ዳር ወደ ወልድያ መስመር ወደ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ ነበር።

መኪናው በወቅቱ 21 ሰው ጭኖ ሲጓዝ እንደነበር ተነግሯል።

ከተሳፋሪዎቹ 7 ሰዎች ሲሞቱ 14 ሰዎች ላይ ጉዳት አጋጥሟል።

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ 5 ተማሪዎቹ በአደጋው እንደሞቱበትና በ13 ተማሪዎቹ ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰ አሳውቋል።

ህይወታቸው ያለፈው ተማሪዎች ፥ አሜሪካ ሙሉ፣ ይርጋ ወርቁ፣ ሰናይታ ካሳ፣ አቤል ግደይ ፣ በላይነሽ ሽፈራው እንደሆነ ገልጿል።

ነፍስ ይማር !

@tikvahethiopia
🎉🎉ኢትዮ 130 lucky slot አሸናፊዎች ሽልማታቸው እየወሰዱ ነው!!

🔥3ቱ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎች ገና አልተነኩም

በቴሌብር ሲገበያዩ፣ የአየር ሰዓት ወይም ጥቅል ሲሞሉ፣ ገንዘብ ገቢ ሲያደርጉ፣ ሲያወጡ ወይም ሲላላኩ፣ የአገልግሎት ክፍያ ሲፈጽሙ በሚሰበስቧቸው ሲልቨር/ጎልድ ሳንቲሞች በመጠቀም የዕድል ጨዋታ እና የማስታወስ ጨዋታ በመመለስ ሽልማቶችን ያግኙ!

🚘 3 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖች
🛺 3 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች
💰 በየቀኑ የ20 ሺህ እና በየሳምንቱ የ50 ሺህ ኢ-የገንዘብ ሽልማቶች በቴሌብር
📱 70 ዘመናዊ ስማርት ስልኮች
🎁 130 ሺህ የሞባይል ጥቅሎች

💁‍♂️ ከእርስዎ የሚጠበቀው አገልግሎቶቻችን እየተጠቀሙ በ131 ጨዋታዎች እየተዝናኑ ዕድልዎን መሞከር ብቻ ነው!
በቴሌብር ሱፐርአፕ ኢትዮ 130 ላኪ ስሎትን (Ethio 130 lucky slot) በመምረጥ ወይም ወደ 131 ok ብለው በመላክ ይመዝገቡ፡፡

ደንብና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት አላቸው

ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/4dckxdb
🎉የአሸናፊዎችን ዝርዝር ለመመልከት 👇🏼

#130_ዓመታትን_በጽናት_ታላቅ_አገርና_ሕዝብ_በማገልገል_ላይ

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " ህጋዊ እና ትክክለኛ 14ኛ ጉባኤ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን " - በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት   " ህዝብ እና ህወሓት በማዳን የትግራይ ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ " በሚል መሪ ቃል ሰብሰባ የተቀመጠው በምክትል ሊቀመንበር  አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት  ሰብሰባውን ቀጥሏል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት እና ከፍተኛ ካድሬዎች " ህዝብ እና ህወሓት በማዳን የትግራይ…
#Tigray

" የህወሓትን ህጋዊነት መመለስ አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የሚወያይ ልኡክ እንደ አዲስ ይደራጃል ሲል " በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ገለጸ።

በህወሓት ምክትል ሊቀመንበር የሚመራው ህወሓት ከመስከረም 20 አስከ 22 /2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ያካሄደውን የማእከላዊ ኮሚቴ እና የከፍተኛ ካድሬዎች ስብሰባ ማጠቃለሉ በማስመልከት የአቋም መግለጫ አውጥቷል። 

በዚህም ፥ " የህወሓት ህጋዊነት ለመመለስ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የተጀመረው ውይይት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል " ገልጿል።

" ውይይቱን የሚያስቀጥል የትግራይ የሰላም ልኡክ አንደ አዲስ እንዲደራጅና በሰው ሃይል እንዲጠናከር ይደረጋል " ብሏል።

" ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየው የሪፎርም እቅድ በተጠናከረ መንገድ ይቀጥላል " ሲልም ገልጿል።

አቶ ጌታቸው የሚመሩት ህወሓት " ድርጅቱን በማጠናከር የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ እንሰራለን " ብሏል። 

በትግራይ የሚታየው ቀላል የማይባል የህግ ጥሰት ስርዓት ለማስያዝና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ በመግለፅም የፀጥታ መዋቅርና የህዝብ ድጋፍ ጠይቋል።

በአቶ ጌታቸው የሚማራው ህወሓት " ከጎረቤቶች ጋር የሚደረግ ግንኙነት ለማሻሻል ሰላማዊ ዝምድና ለማጠናከር ከሁሉም ጎረቤቶች በጋራ እንሰራለን " ብሏል።

ቡድኑ ባካሄዘው የ3 ቀን ውይይት በሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ባካሄደው 14ኛው ጉባኤ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ያልሆኑ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ከሰባቱ  የትግራይ ዞኖች የተወጣጡ ከፍተኛ ካድሬዎች መገኘታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

@tikvahethiopia