TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

በምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " አስቸኳይ " ያለውን ሰብሰባ ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።

ዛሬ መሰከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በመቐለ በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅ/ቤት አዳራሽ መካሄድ በጀመረው ስብሰባ በሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን ህወሓት በይፋ የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ከፍተኛ ካድሬዎች ተገኝተዋል። 

አቶ ጌታቸው በሰብሰባው መክፈቻ " ፓለቲካዊና ሰላማዊ ትግል በማጠንከር በብቃት በመምራት ወደፊት የሚያራምድ አመራር መፍጠር ልዩ ትኩረት  ያሻዋል " ብለዋል። 

ህወሓት ያጋጠመው ችግርና መፍትሄዎቹ አልሞ መካሄድ በጀመረው ስብሰባ በድርጅቱ ወስጥ የተፈጠረው ችግር ተገንዝቦ ውስብስቡን በማቅለል ተገቢ የፓለቲካ መፍትሄና አቅጣጫ የሚሰጥ አመራር የሚያስፈልግበት ወቅት አሁን ነው ተብሏል። 

" የፕሪቶሪ ስምምነት ህዝብን ከተጨማሪ እልቂት የታደገ ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " ስምምነቱ ያሰገኘው ሰላም ማስቀጠል ቁልፍ ጉዳይ ነው " ብለዋል።

" በምክትል ሊቀመንበር የተመራው ማእከላይ ኮሚቴና የከፍተኛ ካድሬዎች ስበሰባ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል " ሲል ድምፂ ወያነ ጠቅሶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#VisitAmhara

ግሸን ደብረ ከርቤ !

ግሸን ደብረ ከርቤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በአንጋፋነታቸው ከሚታወቁት ቅዱሳን ሥፍራዎች አንዷ ናት፡፡

የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ሌሎች የገዳሟን ታሪክ ማወቅ የሚፈልጉ ሰዎች በየጊዜው ወደ ግሸን ይጓዛሉ፡፡

በተለይ ከመስቀል በዓል እስከ መስከረም 21፣ ጥር 21 እንዲሁም መጋቢት 10 ወደ ግሸን የሚጓዘው ሕዝብ በመቶ ሽዎች ይቆጠራል፡፡

በረከት ለማግኘት፣ ታሪክ ለማወቅ እና ለመፈወስ ግሸን ለእምነቱ ተከታዮች ቀዳሚ መዳረሻ ናት፡፡

በኢትዮጵያ የሀይማኖት ቱሪዝም ታሪክ ብዙ እንግዶችን በማስተናገድ ግሸን ከቀዳሚዎች መካከል ትገኛለች፡፡

ነገ መስከረም 21 ታላቁ የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ክብረ በዓል ይከበራል፡፡

እንኳን አደረሳችሁ !

(Vist Amhara)

#TourismAndPeace  #GishenDebreKerbe #SouthWollo #ReligiousFestival #Ethiopia #LandOfOrigins

@tikvahethiopia
" ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥምቅት 30/2017 ወደ ቤታችሁ ግቡ ፤ ይህ ካልሆነ የሽያጭ ውሉ እንዲቋረጥ ተደርጎ ቤቱን ለሌላ ዕድለኛ እናስተላልፋለን " - የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየገነባ ለቤት ተጠቃሚዎች በዕጣና በጨረታ የሚያስተላልፈው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን " በሽያጭ ከተላለፉና ውል ከተፈጸመባቸው ቤቶች መካከል የቤት ባለቤቶች ወደ ቤታቸው ገብተው እየኖሩ አለመሆኑን አረጋግጫለሁ " ብሏል።

" በህጋዊ መንገድ ውል የተያዘባቸው ቤቶች ለህገወጥ ተግባር እየዋሉ ነው " ያለው ኮርፖሬሽኑ ፥ የቤት ባለቤቶች ከኮርፖሬሽኑ ጋር በያዙት የሽያጭ ውል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ አስጠንቅቋል።

" በተባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ቤቱ የማይገባ የቤት ባለቤት የሽያጭ ውሉ በህግ አግባብ እንዲቋረጥ ተደርጎ ቤቱን ለሌላ ዕድለኛ እናስተላልፋለን " ሲልም ገልጿል።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
#CBE🚨

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ ተጨመረ።

መንግስት በቅርቡ ባወጣው አዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕግ መስረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚያቀርባቸው ምርት እና አገልግሎቶች ላይ በነበረው የአገልግሎት ክፍያ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲከፈልባቸው መወሰኑን ገልጿል።

በዚህም ከነገ መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ. ም ጀምሮ የባንኩ ምርትና የአገልግሎት ዓይነቶች ላይ በሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ የተጨመረባቸው መሆኑን ባንኩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
ዋሪት ፈርኒቸር !

የቤትዎን ምቾትና ውበት የሚያስናፍቁ  የዋሪት ምርቶች በሁሉም ማሳያ ሱቆቻችን ያገኛሉ ። ከእርሶ ሚጠበቀው ጎራ ማለት ብቻ ነው። በሚወዱት የቀለም  ምርጫ ይሸምቱ!!
ዋሪት ፈርኒቸር
ትክክለኛ ምርጫ!!
* 22- ዋሪት ህንፃ
* ጉርድ ሾላ- ሴንቸሪ ሞል
* ለቡ- ቫርኔሮ ፊት ለፊት
* ፒያሳ- ፍርዱ ኮሜርሻል
* ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት
* አዳማ- ሶረቲ ሞል
📞0911210706 | 07
www.warytze.com
ፌስቡክ፡ www.fb.com/WARYTZE
ቴሌግራም፡ https://t.iss.one/warytfurniture
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/warytfurniture/
ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/@warytzefurniture
🇪🇹በኢትዮጵያ የተመረተ 🇪🇹
ስለ ሲፒ ጉዳተኛ ህጻናት ይመለከተኛል !!

' እዝነት አካል ጉዳተኛ ህፃናትና ወላጆች መርጃ ድርጅት ' የዓለም አቀፍ የሲፒ ጉዳተኞች ቀን አስመልክቶ የእግር ጉዞ ማዘጋጀቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ድርጅቱ  የእግር ጉዞውን አዘጋጅቶ ነበረው በኢትዮጵያ መስረም 26 / 2017 የነበረ ቢሆን በዚህ ሰሞን ከሚከበረው ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ እንዲሁም በምልእተ ህዝብ የሚከበር አመታዊ ክብረ በአል (ኢሬቻ) ጋር ስለተገጣጠመበት መርሃግብሩን እንደቀየረ አመልክቷል።

የእግር ጉዞው የሚያረደርግበት ቀንም ጥቅምት 03 / 2017 መሆኑን ገልጿል።

ድርጅቱ  በሃገራችን ያለው የሲፒ ጉዳተኞች ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን በማመልከት የድጋፍ ስራው ማህበረሰቡን ያሳተፈ እንዲሆን፣ ግንዛቤ ለማስጨበጥና የድርጅቱን ተደራሽነት ከፍ እንዲል ለማድረግ ነው የዓለም አቀፍ የሲፒ ጉዳተኞች ቀን በማሰብ ይህን መርሃ ግብር ያዘጋጀው፡፡

የድርጅቱ መሰራች እና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዘቢባ አህመድ " ቀን ለውጡን ያረግንበት ዋና አላማ የህዝቡን ትኩረት እና ድጋፍ በይበልጥ ለማግኘት ፣ እንደ እቅዳችን ብዙ ህዝብ ያካተተ ሆኖ ተደራሽነቱ ከፍ እንዲል ነው " ብለዋል።

ድርጅቱ ቀኑን የቀየረው አምኖበት ቢሆንም ቀደመው ቲሸርት ለገዙ ተሳታፊዎች ይቅርታ ጠይቋል።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የዓለም የሰረብራል ፓልሲ ጉዳተኞች ቀንን ተንተርሶ የሚዘጋጀው መርሃግብር በአዲስ አበባ ከተማ ጥቅምት 03 / 2017 ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 7፡00 ድረስ መነሻውን አድዋ ዐዐ መዳረሻውን ኩባ ፓርክ ያደርጋል።

@tikvahethiopia
" ህጋዊ ሰውነት ያለው ማህበር ለመመስረት አስበናል " - የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 31ኛ ዙር የህክምና ምሩቃን

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 31ኛ ዙር የህክምና ምሩቃን የነበሩ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎችና ከሀገር ውጭ በህክምናው ዘርፍ ሙያዊ ግዴታቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ።

ሀኪሞቹ የ10ኛ ዓመት የምረቃ በዓላቸውን ለማክበር በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

እነዚህ ተመራቂዎች በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ በነበሩበት ወቅት በሚያደርጉት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና በነበረው ጠንካራ የተማሪዎች ህብረት በስኬታማ ስራዎች ይታወቁ ነበር።

ሀኪሞች በህክምናው መስክ በተናጠል እያደረጉ ያሉት አስተዋፅኦ ይበልጥ ፍሬያማ እንዲሆን እና ለመደጋገፍ እንዲያመች ጥቅምት 9/ 2017 ዓ.ም ሁሉም ከያሉበት በመሰባሰብ ምክክር ለማድረግ እንዲሁም ህጋዊ ሰውነት ያለው ማህበር ለመመስረት እንዳሰቡ ገልጸዋል።

ህብረቱ ዩኒቨርሲቲውን ለማገዝ እንዲሁም የጤና ዘርፉን ለመደገፍ ላሰበው በጎ ተግባር በኢትዮጲያ ውስጥና  ከኢትዮጵያ ዉጭ ያሉ ሃኪሞች ' ሸራተን አዲስ ' በመገኘት በመርሀግብሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ሲል ' የጎልደን ባች ሪዩኒየን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ' ጥሪውን አስተላልፏል።

@tikvahethiopia