TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
⚫️ #ኢትዮጵያ ⚫️

ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ምን ያልተፈጸም ፤ ምንስ ያልተደረገ ግፍ አለ ?

እጅግ በጣም ሚያስደነግጠው እንዲሁም ፍጹም ከሰውነት ተራ እየተወጣ መሆኑን የሚያሳየው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ልክ ጀግንነት ፣ በጎ ተግባር፣ ፍቅርን ለትውልድ የሚያስተላልፉ ይመስል ግፍና ጭካኔያቸውን በቪድዮ ማስረጃ እራሳቸው ቀርጸው ለትውልድ እያስቀመጡ መሆናቸው ነው።

በእርግጥም እንዲህ እየቀረጹ ማስቀመጣቸው ህዝቡን ለሚፈልጉት ዓላማ ለማነሳሳትና እርስ በርስ ለማባላት፣ ህዝቡን ወደ ግጭት ለማስገባት ሊሆን ይችላል።

በጥላቻ የሚፈጽሙት የግፍ ተግባራቸው አላረካ ብሏቸው ፣ " እዩልን ምን ያህል አውሬ እንደሆንን " የሚለውን ለማሳየትም ይሆናል።

በሀገራችን ፦
🔴 ሰው ከነህይወቱ ሲቃጠል
🔴 በድንጋይ ተወግሮ ሲገደል
🔴 በጅምላ በጥይት ተደብድቦ ወደ ገደል ሲከተት
🔴 አስክሬን ሲጎተት
🔴 አስክሬን አደባባይ ላይ ሲጣል
🔴 ተዘቅዝቆ ሲሰቀል
🔴 በስለት ተቀልቶ ሲገደል
🔴 የጥይት በረዶ ሲዘንብበት ... ኧረ ብዙ ብዙ በቪድዮ ተቀርጾ አይተናል።

ይኸው ዛሬ የሰው ልጅ ልክ እንደ ዶሮ " በስመአብ " ተብሎ ሲታረድ በቁማችን አየን።

ይህ ጭካኔ በማስረጃ በቪድዮ ተቀርጾ የወጣ ነው ለመሆኑ ስንት በቪድዮ ያልተቀረጸ ፣ በየአካባቢው የተፈጸመ ግፍ ይኖር ይሆን ?

እነዚህ ግፍ ፈጻሚ ሰዎች ሰይጣናዊ ስራቸውን በቪድዮ ቀርጸው ማስቀረታቸው በቤተሰብ ፣ በህዝብ ላይ የማይረሳ ቂም፣ ቁርሾና ቁስል ለማኖር ይመስላል።

የትም ይሁን ማንኛውም የግፍ ድርጊት ሲፈጸም ግን የሚቀድመው ድርጊቱን ከልብ አዝኖ ማውገዝ  ነው። ፍትህ ተጠያቂነት እንዲሰፍን መጠየቅ ፤ ለፍትህ መታገል ነው።

ልክ ሰው በሞተ ቁጥር ያለ አንዳች ሀዘን እና መከፋት ወደ ፖለቲካ ንትርክ መግባትና የሰው ደም ፈሶ እንዲቀር ለማድረግ መሯሯጥ የግፍ ግፍ ነው።

ከዚህ ቀደም ብዙ ታዝበናል።

ሰው በግፍ ይገደላል ከዛም ሰዎች በየማህበራዊ ሚዲያ ይመጡና " የኔ ወገን ሰው አይገድልም፤ ፍጹም ነው ፣ ፃድቅ ነው ፣ እንዲህ እንዲያደርግ ተፈጥሮው አይፈቅድለትም " እያሉ ድርጊቱ ያራክሱታል።

ሌላው ወገን ይመጣና በሞተው ንጹህ ሰው ደም ፖለቲካ ይሰራል። በጅምላ ጥላቻውን ይተፋል። በዚህ መንገድ የስንት ሰው ደም ፈሶ ቀረ ?

ላለፉት ዓመታት ሰው በግፍ ይገደላል ከዛ የቀናት የማህበራዊ ሚዲያ አጀንዳ ሆኖ ያልፋል፤ ይረሳል። ከዛ ሌላ ግፍ ሌላ ግድያ ይፈጸማል።

አንዳንዱ እውነት ከልቡ አዝኖ ፤ አንዳንዱ ደግሞ የይስሙላ ያዘነ ይመስል ሸፋፍኖ በማህበራዊ ሚዲያው ይጽፋል ፤ ይለፍፋል። ከሰዓታት በኃላ ሁሉም ረስቶት ምንም እንዳልተፈጠረ ወደ ህይወቱ ይመለሳል። ማህበራዊ ሚዲያ ሲገባ ትዝ ሲለው ለቀናት ስሜቱን ይፅፍ ይሆናል።

እስከ ህይወት ፍጻሜ ድረስ በሀዘን የሚቃጠሉትና ልጃቸውን የማይረሱት እናት አባት፣ ወንድም ፣ እህት ቤተሰብ፣ ዘመዶች ናቸው።

በተለይ እናት እና አባት ሲያለቅሱ ነው የሚኖሩት።

ይህ አዙሪት መቆም አለበት። ደመ በፈሰሰ ቁጥር ቁርሾ ቂም እየተወለደ እንጂ ፍቅር አንድነት አይመጣም።

ልጆቹን የተነጠቀ ቤተሰብና አካባቢ እንደሌላው የማህበራዊ ሚዲያ አርበኛ የአንድ ቀን ሀዘን አድርጎ አያልፈውም። የተፈጸመበትን ግፍና በደል መቼም አይረሳውም ! ቂም በውስጡ ያድራል። ይህ በሀገር ህዝብ ትስስር ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ ከባድ ነው።

ከምንም በላይ ለተጎዱ ወገኖች ፍትህ በማስፈን ፣ ሌላ የአንድ ሰው ደም እንዳይፈስ በማድረግ አዙሪቱን ማቆም ካልተቻለ የከፋ ነገር መምጣቱ አይቀርም።

እዚህች ምድር ላይ ነገ ሳይሆን ዛሬ የሰው ልጅ ደም መፍሰስ እንዲቆም ማድረግ ይገባል።

ፍትህ ሊሰፍን ፤ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል።

ታጣቂም ሆነ አልሆነ ፤ የአካባቢው ፣ የክልሉ የመንግሥት አካል ሆነ አልሆነ ሁሉም በየድርሻው በየደረጃው ሊጠየቅ ይገባል።

እጅግ በጣም አስገራሚው ነገር በምንም አይነት መንገድና ሁኔታ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ቀዳሚ ስራው ሊሆን የሚገባው እና ችግርም ሲፈጠር ለህዝብ የማሳወቅ ኃላፊነት ያለበት መንግሥት የሚፈጸሙ ድርጊቶችን ከማህበራዊ ሚዲያው ጩኸት በኃላ ለመናገር ሲወጣ መታየቱ ነው።

ለመሆኑ የሚፈጸመውን የሚሰማው ከህዝብ ጋር በሚዲያ ነው ? ነዋሪው በሚዲያ ባይጮህ ላያወግዝ ነው ?

ቆይ ልክ እንደማንኛውም ሌላ አካል " አወገዝኩ " ብቻ ነው የሚባለው  ወይስ ስለተፈጸመ ግፍ በዝርዝር አጣርቶ ለህዝብ ወጥቶ መረጃ መስጠት ነው የሚገባው ? የመንግሥት ስራ ድርሻው ምንድነው ? ለስንቱ ፍትህ ለተነፈገ እያነባ ላለ ወገን ፍትህ ሰጠ ? ተጠያቂነትን አሰፈነ ? በደል የደረሰባቸውን ካሰ ? ዳግም ደም እንዳይፈስ ተከላከል ? እኚህ ሁሉ ጥያቄዎች መልስ ይሻሉ።

ህዝብ በሀገሩ የሚሆነውን ሁሉ ያያል ፣ ይታዘባል፣ ይገመግማል ፣ ነጥብም ይይዛል።

በምንም አይነት ሁኔታ የሰው ደም አይፈስስ ፤ ደም ሲፈስ ቂምና ቁርሾ እንጂ ፍቅርና አንድነት አይወለድም።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#TikvahEthiopia
#ናውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
⚫️ #ኢትዮጵያ ⚫️ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ምን ያልተፈጸም ፤ ምንስ ያልተደረገ ግፍ አለ ? እጅግ በጣም ሚያስደነግጠው እንዲሁም ፍጹም ከሰውነት ተራ እየተወጣ መሆኑን የሚያሳየው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ልክ ጀግንነት ፣ በጎ ተግባር፣ ፍቅርን ለትውልድ የሚያስተላልፉ ይመስል ግፍና ጭካኔያቸውን በቪድዮ ማስረጃ እራሳቸው ቀርጸው ለትውልድ እያስቀመጡ መሆናቸው ነው። በእርግጥም እንዲህ እየቀረጹ ማስቀመጣቸው…
የእውነት ያለቀስነው መቼ ነው ?

አሁን ላይ ጨምሮ ባለፉት ዓመታት ምን ያህል ግፍ ምን ያህል ጭካኔ ሀገራችን ውስጥ እንደተፈጸመ መናገር መቼም ለቀባሪው ማርዳት ነው።

ግን ግን እውነት አብረን ያለቀስንበት ቀን መቼ ነው ? ትዝ የሚለውስ አለ ?

አንዱ በሀዘን ተሰብሮ ሲያለቅስ አንዱ ይስቃል  ይደሰታል ፤ አንዱ ሲደሰት አንዱ ያለቅሳል። ሁሉንም አንድ የሚያደርገው የሰብዓዊነት ስሜትም እየታየ ጠፍቷል ፤ ሞቶ አፈር ለብሷል።

ለማዘን ቅድሚያ ጥያቄው " ማነው ? የትኛው ወገን ነው ? " ብሎ መጠየቅ ተለማምደነዋል። " የኔ " የምንለው ሲሆን ማልቀስ " የሌላው ነው " ብለን ስናስብ ምንም እንዳልተፈጠረ ማለፍ ከዛም ከፍ ሲል ግፉን ኖርማል ለማድረግ መሮጥ ስራችን ሆኗል።

ሌላው ይቅር ግፍና መጥፎ ተግባር ማውገዝ እንኳን ሂሳብ ተሰልቶ ጥቅምና ጉዳቱ ታይቶ፣ ጩኸቱንና የህዝቡን ቁጣ ተመልክቶ ሆኗል።

ከምንም በላይ የሚስፈራው ጭካኔና ግፍ ለሚፈጽሙ ግለሰቦች ያውም ከነማስረስረጃቸው ለሚታዩ ሰዎች ጥብቅና መቆም ለነሱ መከራከር ልምድ እየሆነ መምጣቱ ነው።

" እባካችሁ ነገሩ በደንብ ይጣራ " ማለት አንድ ነገር ሆኖ ሳለ ሰው የግፍ ፈጻሚዎቹ ማንነት የኔ ወገን ነው ብሎ ካሰበ " በፍጹም እንዲህ አያደርጉም ፤ የተፈጠሩበት ተፈጥሮና ስነልቦና አይፈቅድም " ብሎ ድምዳሜ በመስጠት ሌላ ግፍ መፈጸም ተለምዷል።

በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በአማራ ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ... በሌሎችም ክልሎች በመንግሥት ታጣቂዎች፣ መንግሥትን እንፋለማለን ብለው በወጡ ታጣቂዎች ፣ ፓለቲከኞች በሚሰሩት ጥላቻ የተመረዙ ከማህበረሰቡ በወጡ ሰዎች ለማየት የሚከብድ ብዙ ግፍ ተሰርቶ ያውም በቪድዮ ተቀርጾ ታይቷል ዛሬም እዚሁ መንደር አለ።

ድርጊቶቹ ይፋ ሲወጡ አብሮ በጋራ ከማዘን ፍትህን ከመጠየቀ ይልቅ የፈጻሚዎቹ ደጋፊ ሆነው የሚቀርቡ ሰዎች በዘመቻ ነገሩን ለማራከስ እና እንዳልተፈጸመ ለማሳየት የሚሄዱበት ርቀት እውን ነገ ለወጥ ይመጣል ? የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

በሌላኛው ጎራ በንጹህ ሰው ደም ጥቅም ያስገኝልኛል ያለውን ፖለቲካ ይጫወታል። ከበፊትም እጠላዋለሁ የሚለውን አካል መርጦ ሌላ እልቂት ይቀሰቅሳል።

በዚህም መሃል በርካቶች እንደወጡ ቀርተው ፍትህ አላገኙም።

ለማህበራዊ ሚዲያ ሰዎች እና ሰላም ያለበት ከተማ ለሚኖሩ ነገሩ የሁለት ቀን ግፋ ቢል የሶስት ቀን አጀንዳ ሆኖ ያልፋል። ከዛ ሌላ ግፍ ይፈጸማል።

እናት አምጣ የወለደችውን ፤ ለፍታ ያሳደገችውን ልጅ እያሰበች ዘላለም በለቅሶ ትኖራለች። ወዳጅ ዘመድ ግፉን እያሰበ አመለካከቱ ተቀይሮና በመጥፎ ስሜት ተሞልቶ ለሌላው እንዳያዝን ሆኖ ይኖራል።

የስንቱ ቤት በሀዘን ፣ የስንቱ ሰው ልብ በቂምና ቁርሾ ፤ ሳይወድ በግዱ በመጥፎ አመለካከት ተሞልቶ ይሆን ?

ይህ ነገር ማብቃት አለበት። ተስፋ የሚሰጥ ትንሽ ሰብዓዊነት ሊኖር ይገባል። ማንም ይሁን ማን ተጠያቂነት ሊፈጠር፣ ፍትህ ሊሰፍን ይገባል።

እናቶች የሞተው ልጆቻቸውን ባይመልስላቸውም ፍትህ ሲያገኙ ቢያንስ እንባቸው ይታበስ ተስፋቸው ይለመልም ይሆናል።

ፍትህ ሲገኝ ዜጎች በሀገራቸው ተስፋቸው ያብባል።

በምንም አይነት ሁኔታ በግጭት ፣ በጦርነት ሆነ በምንም መንገድ በምድሪቱ ደም አይፈሰስ ፣ ሰው አይበደል ፤ የሰው ደም በፈሰሰ ቁጥር ፤ በደል በተፈጸመ ቁጥር ቂም ጥላቻ፣ አለመተዛዘን እየተወለደ እየተስፋፋ ይመጣል።

ደስታውስ ይቅር እውነት አብረን መቼ ነው በጋራ ያለቀስነው ? ብለን እንጠይቅ። ከልብ እንኮንን፣ ሂሳብ አንስራ ፤ የሰው ደም ላይ ፖለቲካ አንቆምር ፤ ለፍትህ እንታገል ! ካልሆነ የሁላችን እጣ ፋንታ እንደወጡ መቅረት ፍትህ አለማግኘት ይሆናል።

#TikvahEthiopia
#ቲክቫህኢትዮጵያ
#ናውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ የዘንድሮው በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት የአጠቃላይ በጀት 1.5 ትሪሊየን ብር ሆኗል። ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 582 ቢሊየን ብር ተጨማሪ የፌደራል መንግስት በጀት አፅድቋል። ለ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ ሆኖ የፀደቀው በጀት ፦ - ለውጭ እና ለሀገር ውስጥ ዕዳ ክፍያ፣ - ለማህበራዊ በጀት ድጎማ (ለነዳጅ፣ ለማዳበሪያ፣ ለመድሐኒት፣ ለምግብ ዘይትና ሌሎች)፣ - ለካፒታል ፕሮጀክቶች…
#ኢትዮጵያ

" ... የውጭ ምንዛሬ ለውጡ in in terms of Dollar ያመጣውን ለውጥ ሊያካክስ የሚችል የደመወዝ ጭማሪ መጨመር ነበረበት " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

🔴 " አንድ ደመወዝተኛ በውጭ ምንዛሬ ስናሰላው ያገኝ የነበረው ገቢ በዶላር ከ50% በላይ እንዲቀነስ ተደርጓል !! "


የህ/ተ/ም/ቤት አባሉና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካዩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በተጨማሪ በጀቱ ዙሪያ ስጋቶች እንዳላቸው ገልጸዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፍ ማሻሻያው ሀገራዊ ውጥቅጥ ውስጥ እንዳስገባን በግልጽ እንደሚታይ ተናግረው ይሄ በጀት እሱን ምን ያህል አ
ተደራሽ ያደርጋል ? ሲሉ ጠይቀዋል።

ከዚህ ባለፈም ደሳለኝ (ዶ/ር) ፤ ስለ ኑሮ ውድነት ፣ ስለሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ፣ በጀቱን ለመሸፈን ስለሚጣል ግብር አንስተው ጠይቀዋል ፤ ሃሳባቸውን አካፍለዋል።

ምን አሉ ?

" በኑሮ ውድነት ላይ / ቋሚ ደመወዝተኛ በሆነው አካል ላይ የውጭ ምንዛሬው (Foreign exchange) ለውጡ የፈጠረው ጫና አለ።

አንድ ደመወዝተኛ በውጭ ምንዛሬ ስናሰላው ያገኝ የነበረው ገቢ በዶላር ከ50% በላይ እንዲቀነስ ተደርጓል ፤ በውጭ ምንዛሬው ለውጥ ምክንያት።

መንግሥት የደመወዝ ማሻሻያ በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ተቀጣሪዎችን ደመወዝ ማሻሻያ አድርጊያለሁ ቢልም አብዛኛው ደመወዝተኛ ከ1 ሺህ ብር እና ከ2 ሺህ ብር በላይ ጭማሪ አልተደረገለትም። ስለዚህ እነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች ኑሯቸውን እንዴት እንዲመሩ ታስቦ ነው ?

በእኔ በኩል ቢያንስ መንግሥት ሌሎች የmarket variables ትቶ የውጭ ምንዛሬ ለውጡ in in terms of Dollar ያመጣውን ለውጥ ሊያካክስ የሚችል ጭማሪ መጨመር ነበረበት።

አንድ የ12 ሺህ ብር ደመወዝተኛ ከምንዛሬ ለውጡ በፊት ወደ 300 እስከ 350 ዶላር አካባቢ ያገኝ ነበር አሁን መንግሥት ጨመርኩ ያለው 1 ሺህ ብር ነው ወደ ዶላር ሲቀየር ደመወዙ የሚወድቀው ወደ 150 ዶላር አካባቢ ነው።

ይህ ከፍተኛ ጫና፣ የመንግሥት ሰራተኛውን ወደ ልመና፣ ወደ ጎዳና እያስወጣው እንደሆነ  መሸፈን በማንችልበት ሁኔታ ዘገባዎች እየወጡ ነው።

ስለዚህ ይህን በስነስርዓት address በሚያደርግ መንገድ የደመወዝ ማስተካከያው መስተካከል ነበረበት። ጭማሪውም ለዛ ትኩረት መስጠት ነበረበት።

ሌላው የ281.5 ቢሊዮን ተጨማሪ ታክስ raise በማድረግ ይሄን 532 ቢሊዮን ተጨማሪ በጀት ለመሸፈን ከሚደረገው ውስጥ አንደኛው ታክሱ ነው።

ይህ ከፍተኛ የታክስ ጫና (burden) ነጋዴው ላይ የሚጭን ነው። ነጋዴው ላይ ከፍተኛ የታክስ ጫና እየፈጠረ ነው። የንግዱ ማህበረሰብን ከፍተኛ confusion (መደናገር) ውስጥ እየተከተተው ነው።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር ተያይዞ ቀድሞውኑ shock ውስጥ ነው ቢዝነሱ ፤ ብዙ ነጋዴዎች confusion ውስጥ እንደገቡ ይናገራሉ ከዛ ላይ ተጨማሪ confusion እና ተጨማሪ መደናገጥ እንዲሁም shock የሚፈጥር ነው ይሄ እንዴት ታስቦ ነው ?

መንግሥት fair በሆነ መንገድ ከከፍተኛ ታክስ ከፋዩ ላይ ከሚደበቁትን፣ የታክስ ሆሎችን ተጠቅመው የሚሰወሩትን እሱን መሰብሰብ አለበት በእርግጠኝነት ፤ ግን ደግሞ ከአቅም በላይ የሆነውን የመንግሥት spending compensate ለማድረግ ሲባል የታክስ ጫናውን ከአቅም በላይ መለጠጥ በንግድ እንቅስቃሴው ላይ በተለይ በሀገር ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ያለው ችግር በደንብ ተገምግሟል ? የሚኒስትሮች ም/ቤት ይሄን እንዴት አይቶት ነው ?

ሌው ጭማሪው 532 ቢሊዮኑ በዋነኝነት ለዕዳ ክፍያ፣ ለማህበራዊ ድጎማ ፣ ለደመወዝ ጭማሪ እንደሚውል ነው የተገለጸው።

ባለፈው 971 ቢሊዮኑ በጀቱ ሲፀድቅ አሁንም የካፒታል ፕሮጀክቶችን ጉዳይ አንስቼ ነበር። መንግሥት literally ትቶታል።
- አዲስ መንገድ
- አዲስ ግድብ
- አዲስ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ ሆስፒታል ... አዳዲስ መሰረተ ልማቶችን መተው የሚታየው አሁን በተጨመረው 582 ቢሊዮን ውስጥ 90 ቢሊዮን ብቻ የካፒታል ፕሮጀክት ማሻሻያ ብቻ ነው የተካተተው።

ሌላው ነገር የለም። already እያልን ያለነው ኮሪደር ልማት ብቻ እንስራ ነው። እንደዚህ ሆኖ ሀገር እንዴት ሊለማ ይችላል ? መሰረታዊ የሚባሉ የ irrigation development ፣ ግድቦች ላይ ፣ አገር አቋራጭ መንገዶች ላይ፣ ፈጣን መንገዶች ላይ ፣ የኃይል ተቋማት ላይ፣ ሆስፒታሎች ፣ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ እንዲህ አይነት critical የሆኑ የህዝብ መሰረተ ልማቶች ላይ በጀታችንን ካላዋልነው አሁንም ዞሮ ዞሮ የማብለጭለጭ አይነት ልማት structurally ምንም ለውጥ የማያመጣ ልማት ላይ ነው እንዳለ ገንዘባችንን ፈሰስ እያደረግን ያለነው። እዚህ ላይ ስጋት አለኝ።

መሰረታዊ የሚባሉ investment ላይ መንግሥት ውጪውን ቅድሚያ መስጠት አለበት። "

#TikvahEthiopia #ደመወዝ #ዶክተርደሳለኝጫኔ

@tikvahethiopia
" ዋና ኃላፊዋ በሀገር ውስጥ የሉም። ነገር ግን ደብዳቤያችን ከደረሳቸው በኃላ ነው የወጡት " - የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ2015 /2016 በጀት አመት የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና ውጤታማነትን በተመለከተ የተከናወነ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት እንዲሁም የ2015 የሂሳብ ኦዲት ሪፖርት ላይ ለመወያየት ስብሰባ ጠርቶ ነበር።

ነገር ግን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ስብሰባው ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው ቁጣን ፈጥሯል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሺእመቤት ደምሴ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" በመሰረቱ ምክር ቤቱ ተመርምረው የቀረቡለትን የዋና ኦዲት ሪፖርቶችን ይፋዊ ውይይት የሚያደርግባቸው የመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ነው።

እኔ የመጣችሁትን የተመርማሪ መ/ቤት ኃላፊዎች ኃላፊነታችሁን አከብራለሁ ነገር ግን ዋና ኃላፊ በኦዲት ሪፖርት ምርመራ ላይ መገኘት ግዴታ ነው።

ዋና ኃላፊዋ በሀገር ውስጥ የሉም። ነገር ግን ደብዳቤያችን ከደረሳቸው በኃላ ነው የወጡት። ይህ ድርጊት ተገቢ አይደለም።

እኛ ከ10 ቀን በፊት ነው የምናሳውቀው ከ10 ቀን በፊት የምናሳውቅበት የራሱ ምክንያት አለው። መገኘት የማይችሉ ከሆነ reschedule መደረግ ካለበት reschedule መደረግ አለበት አለበለዚህ ግን ችግር የለውም ባላቹ ሰዎች መካሄድ ይችላል ተብሎ ወደ ጎን የሚተው ተግባር አይደለም።

ይሄ እኮ የመ/ቤቱ ቁልፍ ተግባር ነው።

ምክር ቤቱ ሃብት ነው የሚሰጠው፣ ይህ ሃብት በአግባቡ፣ በህግ እና በስርዓት መዋሉን ማረጋገጥ መቆጣጠር ይፈልጋል በዛ በሚቆጣጠርበት ሰዓት ኃላፊነት የሰጣቸው አካል አለመገኘት ተገቢ አይደለም።

በርካታ ስራዎች ሊኖሩ ይችላሉ ግን ከበርካታ ስራዎች የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው (በኦዲት ምርመራ ሪፖርቱ ላይ መገኘት)።

ይህ የሚያመላክተው ለኦዲቱ የሰጣችሁትን ትኩረት ነው። ትኩረት መስጠታችሁ አንዱ ማሳያ ተገኝቶ ይሄን ተምሪያለሁ፣ ፈጽሚያለሁ፣ ይሄን አልፈጸኩም ብሎ ፊት ለፊት ያልፈጸመበትን ምክንያት ማስረዳት ከአንድ ኃላፊ የሚጠበቅ ነው።

ለወደፊቱ እንዳይደገም አሳስባለሁ " ብለዋል።

ምንም እንኳን ዋና ኃላፊዋ ባይገኙም ስብሰባው ምክትል ዋና ዳይሬክተሮቹ ቢቂላ መዝገቡ እና ጎሳ ደምሴን ጨምሮ ሌሎችም አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሮቹ በተፈጠረው ነገር ይቅርታ ጠይቀው " ድጋሚ አይደገምም " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

ዋና ኃላፊዋ መገኘት የማይችሉ ከሆነው ቀድመው መናገር ነበረባቸው ተብሏል።

በዚህ አይነት መንገድ (ዋና ኃላፊዋ በሌሉበት) ሰብሰባውን ማድረግ የማይገባ ቢሆንም ከዋና ኦዲተር ጀምሮ፣ ከጠ/ሚ ፅ/ቤት ፣ ከተለያዩ ተቋማትም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጊዜያቸውን መስዕዋት አድርገው " ዋና ተግባራችን ነው " ብለው ስለተገኙ ብቻ ስብሰባው መደረጉ ተገልጿል።

በዛሬው ስብሰባ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2015/2016 በጀት ዓመት የክዋኔ እና ሂሳብ ኦዲት ሲመረመር በርካታ ገድለቶች መገኘታቸው ተገልጿል።

ከሪፖርቱ በመነሳት ቋሚ ኮሚቴው በርካታ ጥያቄዎችን አቅርቧል። በጥያቄዎቹ ላይም የአገልግሎቱ ኃላፊዎች ምላሽ ያሉትን ሰጥተዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዋና ኃላፊዋ በሀገር ውስጥ የሉም። ነገር ግን ደብዳቤያችን ከደረሳቸው በኃላ ነው የወጡት " - የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ2015 /2016 በጀት አመት የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና ውጤታማነትን በተመለከተ የተከናወነ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት…
" ዜጎች ምን ያህል እንደሚንገላቱ የአይን ምስክር ነኝ !! " - የሺእመቤት ደምሴ (ዶ/ር)

ዛሬ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት #የፓስፖርት_አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ በተካሄደው የ2015/2016 የክዋኔ እና ኦዲት ሪፖርት ስብሰባ ላይ በመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኩል ስለ ሰራተኞች ስነምግባር ፤ ስለ ዜጎች እንግልት ተነስቷል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሺእመቤት ደምሴ (ዶ/ር) መ/ቤቱን " ሁላችንም የምንረግጠው በር ነው ያላችሁ " ሲሉ ገልጸዋል።

" ነገር ግን ሁላችንም ተጠቂ / Victim የሆንበት ጉዳይ ነው እውነቱን ለመናገር " ሲሉ ተናግረዋል። ይህንን ያሉት ስለ ሰራተኞች ስነምግባር እና ስለ ተገልጋይ እንግልት ባነሱት ሃሳብ ነው።

በጉዳዩ ላይ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ኃላፊዎች ለምክር ቤቱ " አጃቢዎቻቸው ፣ በቋንቋ ፣ ቦታ ባለማወቅ ... በተለያዩ ምክንያቶች አጅበዋቸው የሚመጡት እንጂ አገልግሎት ፈላጊዎቻችን አይደለም የሚንገላቱት " ብለዋል።

የምክር ቤት አባልና የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ ግን " እኔ ምስክር ነኝ እኔ ተንገላትቻለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

" እኔ ተንገላትቻለሁ ፤ እኔ ተገፍቼ ወጥቻለሁ ያውም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መታወቂያ እያሳየሁ ፤ ተጎትቼ ወጥቻለሁ ይህንን ከማንም አይን እማኝ አይደለም እኔ ላይ የደረሰ ነው። እኔ ይሄንን የምለው እኔ ተበድያለሁና እኔ ለምን ተበደልኩ ብዬ አይደለም " ብለዋል።

" እኔ ይህን ሃሳብ እያቀረብኩ ያለሁት ከኃላዬ ያለው ዜጋ ምን ያህል እንደሚንገላታ የአይን ምስክር ነኝ ለማለት ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

" ይህንን ፈትሹት ፤ ሩቅ አይደለም የሩቅ ጊዜ ትዝታ አይደለም እየናገርኳችሁ ያለሁት ዛሬ ላይ እየተፈጸመ ያለ ነው " ብለዋል።

" አገልግሎት ፈላጊው ወረቀት ይዞ ፣ የሞላውን ፕሪንት አድርጎ ይዞ በጣም እየተንገላታ ፤ እየተገፋ ያለበት ሰዓት ነው ያ መሆን የለበትም " ሲሉም አሳስበዋል።

አክለው " ለዜጎቻችን መስጠት የምንችለውን አቅማችን የፈቀደውን አገልግሎት በአግባቡና በስርዓት ልንሰጥ ይገባል እንጂ ከዛም አልፎ መንገላታትን ልንጨምርበት አይገባም " ብለዋል።

መ/ቤቱ ያሉትን ቅርንጫፎች አቅም እንዲያጠናክር እና ዜጎችን ከሚያንገላታ አሰራር እንዲታረም በጥብቅ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopia
#Passport

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

እስከ 1 ሚሊዮን ፓውንድ ሽልማት የሚያስገኘውን የ " The Earthshot Prize 2025 " ኢትዮጵያውያን እንዲወዳደሩ ጥሪ ቀረበ።

በእንግሊዝ ልዑል ዊሊያምና ሮያል ፋውንዴሽን በፈረንጆቹ 2020 የተቋቋመውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአካባቢና አየር ብክለት የፀዳ፣ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ የሚያበረክትና ለተፈጥሮ ተስማሚ የሆነ ስራ እየሰሩ ያሉ ተቋማትን ፣ የቢዝነስ ፈጠራ ባለሙያዎችን (ኢንተርፕረነሮችን) ወይም ግለሰቦችን የሚሸልመው " The Earthshot Prize 2025 " የዘንድሮ እጩ ተወዳዳሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

በአፍሪካ የውድድሩ ዋና አጋር መልቲቾይስ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎች እንዲወዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

በ5 የተለያዩ ምድቦች የሚካሄደው ይህ ዓመታዊ ሽልማት ላይ በተለይ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑና ተፈጥሮን የማይበክሉ ቢዝነሶችን የሚያንቀሳቅሱ ኢትዮጵያውያን  መሳተፍ ይችላኩ።

ውድድሩ እስከ 1 ሚሊዮን ፓውንድ ሽልማት የሚያስገኝ ነው ተብሏል።

ፕሮጀክቶቻቸውን ለማስፋፋትና እየተባባሰ ለመጣው የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ እንዲያበረክቱም ያግዛል።

መልቲቾይስ አፍሪካ ፤ በደቡብ አፍሪካ በተከናወነው የ2024 ውድድር ከጋና " ግሪን አፍሪካ ዩዝ ኦርጋናዜሽን " እንዲሁም ከኬንያ " ኪፕ ኢት ኩል" የተሰኙ የአረንጓዴ ጉዳይ አቀንቃኞችና የሥራ ፈጣሪዎች አሸናፊ እንደሆኑ አስታውሷል።

ለዚህ ዓመቱ ሽልማት ማመልከት የሚቻለው እስከ ፈረንጆቹ ዲሴምበር 04 / 2024  ሲሆን ኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎች እና ተቋማት  በ https://www.multichoice.com/earthshot-nomination.php#prId=324466  እንዲያመለክቱ ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahEthiopia

Via @TikvahethMagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሽርካ " በየቤቱ ይዘው በማገት ወደ ወንዝ አካባቢ ወስደዋቸው፤ አሰልፈው ነው የገደሏቸው " - ነዋሪዎች በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ትላንት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች 9 ሰዎችን ከቤታቸው በመውሰድ መግደላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች እና ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ግድያው የተፈጸመው ሐሙስ ኅዳር 19/ 2017 ዓ.ም. ከሌሊቱ 6፡00 አካባቢ መሆኑን ቤተሰቦች ገልጸዋል።…
የሽርካ ወረዳ ነዋሪዎች ምን አሉ ?

" ከዚህ ቀደም ሰዎች ይታገታሉ የሆነ ብር ተከፍሎ ይለቀቁ ነበር። አሁን የተፈጸመው ግን እጅግ አስከፊ ነው " - ነዋሪዎች

የሽርካ ወረዳ፣ ፈረቀሳ ነዋሪዎች ትላንት ለሊት 9 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪዎች ምን አሉ ?

" በዚህ ሳምንት ሞት አላቋረጠም፤ ቢያንስ ላለፉት ሦስት ቀናት በአከባቢው በተለያዩ ቀበሌያት የሞት አላቋረጠም።

ትላንት ደግሞ በእኛ ቀበሌ ፈረቀሳ የእነዚህ 9 ሰዎች ተገድለዋል። እጅግ አሳዛኝ ነው።

5 ሰዓት ላይ ተኩስ ተጀመረ ግድያው ለሊት 8:00 ገደማ ነው የተፈጸመው።

በየቤታቸው በመሄድ ለቅመው አንድ ላይ ካከማቿቸው በኋላ ነው ጅምላ ጭፍጨፋ ያደረጉባቸው።

ከዚህ ቀደም ሰዎች ይታገታሉ የሆነ ብር ተከፍሎ ይለቀቁ ነበር። አሁን የተፈጸመው ግን እጅግ አስከፊ ነው።

ሰዎቹ ምንም አይነት የሌላ ንክኪ የላቸውም ፤ በሃይማኖት ተለይተው ነው ይህ ጥቃት የተፈጸመባቸው።

ከሞቱት መካከል አባትና ልጅ እንዲሁም ባልና ሚስት ይገኙበታል።

3ቱ አብረው ታግተው ሳለ 9ኙን ሲገድሉ ይኑሩ ይሙቱ አይታወቅም።

ድርጊቱን የፈጸሙት የሸኔ አባላት ናቸው። ሆኖም ግን ምንም እንኳን ስሙ በሸኔ ይነገድ እንጂ በስሩ ሌላ ቡድን የተደራጀ አለ። ሙሉ ለሙሉ ሸኔ ለማለት ያስቸግራል።

በሌላ ቦታ ላይ የሸኔ አድራጎት ሲሰማ ብር ይጠይቃል ሰዎችን ይለቃል ፤ እዚህ ያለው ሃይማኖትን በመቃወም ጥቅም ለማግኘት የሸኔ ስም በመጠቀም የተደራጀ ቡድን አለ ብለን ነው የምናስበው።

የመንግስት አካላት ከዞንም መጥተው ዛሬ ላይ ደርሶ ' አይዟችሁ ነገ ላይ አጸፋውን እንመልሳለን አሳልፋችሁ ከሰጣችሁን ' በሚል የማጽናኛ ተስፋ ሰጥተውናል።

መከላከያውም የመንግስት አመራሩም አለ ገፋ አድርጎ ግን ለህዝብ መፍትሔ የሰጠ የለም።

ጫካውን ደኑን ተገን በማድረግ ግድያ ይፈጸማል።

ባለፈው ዓመት በነሐሴ ወር [2015 ዓ.ም] ነው የተጀመረው አለፍ እያለ እያረሳሱ አሉ የሚባሉ ሰዎች ሽማግሌ አይሉም ወጣት፤ አሉ የተባሉ ሰዎችንዠ ተገድለዋል።

9ኙ የተገደሉት የአንድ ሃይማኖት አባላት ሲሆኑ ቀብራቸውም ዛሬ 9 ሰዓት ነው የተፈጸመው።

ህብረተሰቡ ነግ በኔ ነው እያለ ነው። ከቀብር መልስ የመንግስት አባላት ከዞን መጥተው አጽናንቶ ነው የሄደው።

አዝመራ ልንሰበስብ አንችልም። የቀበሌው አመራር ተደራጅተን አንድ ላይ ሆነን እንሰብስብ እያለን ነው። እንደዚህ በተደራጀ መልኩ የምንቀሳቀስ ከሆነ እንጂ ለዛሬውም አዳር ሰግተን ነው ያለነው።

በተለይ ወጣቱ በአሳዛኝ ሁኔታ ላይ ነው ያለው፤ ይኸው ይሄ ጩኸት 2 ዓመት ያስቆጠረ ነው ምንም የተደረገ ነገር የለም።

ሰርግ ኃዘን አንድ ላይ ነበር ያሳለፍነው [የአከባቢው ማኅበረሰብ] አንድ ቢላ ነበር የሚለየን አሁን ላይ ግን ይሄ ተረስቶ በገቢያም በምንም ያለው ነገር ጎራ መከፈሉን ያሳያል።

በሃይማኖት አባቶች በኩል ህብረተሰቡን ለማቀራረብ ሞክረዋል። በተደጋጋሚ በተደረጉ ስብሰባዎች ግን ስብሰባዎች እየተበተኑ፤ ስብሰባውን ረግጠው እየወጡ ሳይሳካ ቀርቷል።

በድርድሩ ምንም አይነት መፍትሔ የሚመጣ አይመስለኝም የሃይማኖት አባቶች እንዳሉት ከፈጣሪ ከመጠበቅ በቀር ሌላ ምንም ተስፋ የምናደርገው ነገር የለም።

በቀጣይ ቀናትም በተመሳሳይ ጥቃት ይፈጸማል በሚል የአከባቢው ሰው ንብረቱን ትቶ አከባቢውን ለቆ ወደ ቤተክርስቲያንም ወደ ከተማ ቤት ተከራይቶም እየሄደ ነው ያለው።

አሁን ያለው ሁኔታ እንኳን ለወጣቱ ለአዛውንቱም የሚዘገንን ሁኔታ ነው። ምን አይነት ሰዓት ላይ ተፈጠርን በሚል ወጣቱ በኃዘን ተውጦ ነው ያለው።

በአከባቢያችን ካሉ 4 ቀበሌዎች ላይ ካሉ 5 እና 6 ደብሮች አገልግሎት የሚሰጠው አንድ የሚካኤል ደብር ነው። ቀብርም ካለ የሚፈጸመው እዛ ነው። ይህ ከሆነ አንድ አመት አልፎታል።

እንደ ወረዳው ግን ከ35 አብያተ ክርስቲያናት በላይ ተመሳሳይ እጣ ደርሷቸዋል። ሦስት አራት ደብሮች ናቸው አገልግሎት የሚሰጡት። ይህም በጸጥታው ምክንያት ነው።

ከ32 ቀበሌ ከየአቅጣጫው ተመርጦ የሚገደለው ግን የሀገር ሽማግሌ ነው ከዚህ ቀደምም እየተመረጠ አልቋል። ይሄን ያህል ነው ጥቃት የደረሰብን።

የሚመለከተው አካል ከፈጣሪ ጋር የድረሱልን ጥሪ አሰሙልን ወገን ለወገን ደራሽ ነው። "

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Sidama

🔴 " በብልፅግና ፓርቲ መዋጮ ምክንያት አባላትና አመራሮች እየታሰሩብኝ ነው " -የሲዳማ ህዝብ አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ሲህአዲድ)

🔵 " በፓለቲካ አቋሙና አመለካከቱ የታሰረ የፖለቲካ ፓርቲ አባልና አመራር የለም " - የሲዳማ ክልል ፖለቲካ ፖርቲ የጋራ ምክር ቤት

🚨" የታሰርነዉ ለሁለት ፖርቲዎች መዋጮ አናዋጣም ስላልን ነው " - የሲህአዲድ አባላትና አመራሮች


የሲዳማ ህዝብ አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል አቶ ሠለሞን ቡሮዳ የፓርቲያቸው አባላትና አመራሮች " ለብልፅግና  ፖርቲ መዋጮ አናዋጣም " በማለታቸዉ እየታሰሩና በሐሰት እየተወነጀሉ ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቀረቡ።

በክልሉ ከጥቅምት ወር መገባደጃ ጀምሮ በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች አባላትና አመራሮቻቸው ሰበብ እየተፈለገ ሲታሰሩና ሲፈቱ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

አሁን ላይ ደግሞ በአባላቶቻቸው ላይ ሐሰተኛ ክስ እየተፈበረከባቸዉ መሆኑን ጠቁመዋል።

በአንዳንድ ወረዳዎች ማሸማቀቅ ተበራክቷል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ለአብነትም ፦
- ወንሾ፣
- ጠጥቻ፣
- ጎርቼ፣
- ቦና ዙሪያ፣
- ቡርሳ፣
- ጫቤ ጋምቤልቱ፣
- ሸበዲኖ፣
- ጭሬና በንሳ ወረዳዎች አባላትና አመራሮቻቸው " የብልፅግና ፓርቲ መዋጮ ለምን አታዋጡም " በሚል ለእስር ተዳርገዉ እንደነበር አንስተዋል።

አቶ ሠለሞን ፤ " አሸናፊዉ ፓርቲ ብልፅግና ነዉ፤ ሁሉም ለብልፅግና ፓርቲ የህንፃ ግንባታ  መዋጮ የማዋጣት ግዴታ አለበት " የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ በአንዳንድ ወረዳዎች በግልፅ እየተስተዋለ ነው ብለዋል።

" በዚህ ሁኔታ የሚደረጉ ኢ-ሕገ መንግስታዊና የሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች የቃል ኪዳን ሰነድ በሚፃረርር መልኩ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ የሲዳማ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና የኢሶዴፖ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የደቡባዊ ቀጠና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በለጠ ሲጄቦ አነጋግሯል።

ቅሬታ መቅረቡን አልሸሸጉም።

ቅሬታውን ተከትሎ ምክር ቤቱ የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ በማድረግ ኮሚቴ ተሰይሞ የማጣራት ሥራ መስራቱን ገልጸዋል።

በዚህም የታሰሩት ግለሰቦች በደረቅ ወንጀል የተጠረጠሩ አንጂ በፖለቲካ አቋማቸዉና አመለካከታቸዉ ምክንያት እንዳልሆነ መረጋገጡን አሳውቀዋል።

ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ የፓርቲው የወረዳ አባል መሆናቸውን የሚገልጹት የጠጥቻ ወረዳ ነዋሪ አቶ አስራት ወርሶ ግን " ለሁለት ፓርቲ መዋጮ አላዋጣም በማለቴ ታስሬ ነበር " ሲሉ ስለእስራቸው ምክንያት ይገልጻሉ።

ከአንድ ቀን እስር በኋላም የፓርቲው አመራሮች ባቀረቧቸዉ መረጃዎች ምክንያት ከእስር መለለቃቸዉን አስረድተዋል።

የሲዳማ ህዝብ አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የሁላ ወረዳ ስራ አስፈፃሚ መ/ር ሀንሳሶ በበኩላቸው " እኔም አባላቶቻችን ለምን ታሰሩ " በሚል ልንጠይቃቸዉ በሄድንበት ከሁለት አባላት ጋር ታስረን ነበር ሲሉ " ተጨማሪ ምስክርነት ሰጥተዋል።

አክለውም " ለብልፅግና ፓርቲ የሕንፃ መሰሪያ መዋጮ ካላዋጣችሁ በሚል በአባላትና አመራሮቻቸዉ ላይ በበርካታ ወረዳዎች እየደረሰ ያለዉ ጫና ስጋት ዉስጥ ከቶናል " ሲሉ ገልጸዋል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ እና የገዢዉ ብልፅግና ፓርቲ ሃሳብ ለማካተት ያደረግነዉ ሙከራ ያልተሳካ ሲሆን ኃሳባቸውን እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
" ልመና አልነበረም ማለት አይደለም ፤ አሁን ግን እየተባባሰ ሄዷል ! ... የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አቅቶት ህብረተሰቡ መድረሻ እያጣ ነው " - አቶ አበረ አዳሙ

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ 8ኛ መደበኛ ሰብሰባው አድርጎ ነበር።

በዚህም ወቅት ከም/ቤት አባላት ለንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

ሚኒስትሩም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑ አቶ አበረ አዳሙ ምን ጠየቁ ?

" 1. በዓለም አቀፍ ተጨባጭ ሁኔታዎች ምክንያት ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች ዋጋ የኑሮ ውድነቱን እያናረው ከመሆኑንም በላይ በተለይ በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ የሚደረገው ምክንያት የለሽ ጭማሪ የህዝቡን ኑሮ እንዲመሰቃቀል አድርጎታል።

ለምሳሌ ፦
- ጤፍ
- ስንዴ
- ምስር ... ሆነ ሌሎች የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ቢሆኑም በጥራት እና በብዛት ገበያ ላይ አይገኙም ፤ ቢገኙም ዋጋቸው እጅግ የተጋነነ በመሆኑ በቀላሉ የሚቀመስ አይደለም።

የችግሩ ምንጭ ደግሞ ሰው ሰራሽ መሆኑ አይካድም።

ህጋዊ ነጋዴው በኮንትሮባንድ ነጋዴዎች እና ለደላላ እየተጠለፈ መስራት ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

በዚህ የተነሳ ' ልጆቼን የማበላቸው አጣሁ ' የሚሉ አዛውንቶች፣ ' ጋሽዬ ቁራሽ የዳቦ መግዣ ስጠኝ ራበኝ ' የሚሉ አንጀት የሚበሉ በርካታ ህጻናትን ማየት በከተማችን እየተለመደ መጥቷል።

ልመና አልነበረም ማለት አይደለም አሁን ግን እጅግ እየተባባሰ ሄዷል።

ደላላው ዋጋ ይተምናል ፤ ደላላው ዋጋ ይሰቅላል ቢፈልግም ያወርዳል ለዚህም አንድ ወቅት የሱዙኪ መኪና ዋጋን ሰማይ አድርሶ መሬት አስልሶት የነበረበትን አጋጣሚ ማስታወስ ይቻላል።

በአጭር አነጋገር ደላላ የንግዱን ስርዓት /ሲስተም እንደ ተባይ ወሮታል። በዚህም የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አቅቶት ህብረተሰቡ መድረሻ እያጣ ነው።

ጥቅሙን የሚያገኘው  በጋ ከክረምት ደም ታፍቶ ያመረተው አርሶ አደሩ ቢሆን መልካም ነበር።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶ ህገወጥ ነጋዴዎች እና ደላላዎችን ስርዓት ሊያሲዝ የሚችል ዘላቂነት ያለው ስራ ከመስራት ይልቅ አልፎ አልፎ ወይም የሆነ አጋጣሚ ሲፈጠር ' ይሄን ያህል የንግድ ድርጅቶችን አሽኩ / ልናሽግ ነው ' እያሉ በመገናኛ ብዙሃን ማስታወቂያዎችን ከማስተጋባት የዘለለ ፦
° የንግድ ተቋማቱ በምን ምክንያት እንደታሸጉ
° ምን አይነት ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው
° የማሸጉ እርምጃ ምን ውጤት እንዳስገኘ
° የንግድ ድርጅቶቹ ከታሸጉ በኃላ የመጣንው ለውጥ ለህዝቡ ሲያሳውቅ አይታይም።

በኑሮ ላይ ጠብ የሚል ለውጥ አይስተዋልም።

ታዲያ የሀገራችንን ገበያ እየመራ ያለው ንግድ ሚኒስቴር ነው ወይስ ደላላና ህገወጥ ነጋዴ ?

2. ለንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተጠሪ የሆነው የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ከሚቆጣጠራቸው ተቋማት አንዱ መብራት ኃይል ነው። (በየጊዜው የመዋቅር መቀያየር ለውጥ ካለ ይቅርታ ጠይቃለሁ!)

ይሁን እንጂ የመብራት ተደራሽነት እና አግልግሎት አሰጣጥ በእጅጉ የተበላሸ ነው።

👉 ተደራሽነቱ ፍትሃዊነት የጎደለውና ለማዳረስ የተሞከረው ለረጅም አመታት የተተከሉ ፖሎች ሳይቀር ያለ አገልግሎት የቆሙበት፤

👉 ተዳረሰ የተባለውም በኃይል መቆራረጥ ችግር ተጠቃሚውን የሚያሰቃይ፤

👉 አገልግሎቱን ለማግኘት ያለ እፍረት በእጅ መንሻ / ጉባ ካልሆነ በቀር የማይሰራ ሰራተኛ የበዛበት ነው።

የሚያሳዝነው ደግሞ ጉቦ ወንጀል መሆኑ ቀርቶ መብት እስኪመስል ድረስ ዋጋ ተምነው ' ይህን ያህል አምጣ ' የሚሉ ሰራተኞች መብዛታቸው ነው።

በዚህ ከቀጠለ ምናልባትም ፓርላማውን ' የምቀበለው ጉቦ አንሶኛል እና ህግ አውጡልኝ ' ማለት የቀራቸው ይመስላል።

ይህ የእርሶን ተቋም ብቻ የሚመለከት አይደለም በርካታ ተቋማትን የሚያካትት ነው።

ክቡር ሚኒስትር ለመሆኑ ለእርሶ ተጠሪ የሆነው ባለስልጣን መ/ቤት ህዝቡን እያስለቀሰ የሚቀጥለው እስከመቼ ነው ? ይህንን ተቋም መቆጣጠርና ስርዓቱን ማስያዝ ያልተቻለው ለምንድነው ?

3. የኑሮ ውድነቱን ከሚያባብሱ ምክንያቶች አንዱ ነዳጅ ነው።

የዋጋው ማሻቀብ ምክንያቱ የሚታወቅ ቢሆንም ከዋጋው በላይ ሰልፉ ህዝቡን እያማረረ ይገኛል።

ከእጥረቱም በላይ ነዳጅ ለመቅዳት በሚደረግ ረጃጅም ሰልፍ ምክንያት የስራ ሰዓት ያለ አግባብ እየባከነ፣ የትራፊክ ፍሰቱን እያስተጓጎለ፣ እንዲያውም ሲል በህገወጥ መንገድ ነዳጅ ከሀገር እንዲወጣ ሰፊ በር እየከፈተ መሆኑን እማኝ መጥቀስ የሚያስፈልግ አይመስለኝም።

ክቡር ሚኒስትር ይህንን የተበላሸ አሰራር ስርዓት ማስያዝ የማን ኃላፊነት ይመስሎታል ? እባክዎ ለዚህ የተከበረ ም/ቤት እና ለብዙሃኑ የሀገራችን ህዝብ ተገቢውን መልስ ይስጡ። "

ሚኒስትሩ ምን ምላሽ ሰጡ ? ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-03

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " - ማርክ ጉዬ

➡️ የእስልምና እምነት ተከታዩ ሳም ሞርሲም የግብረሰዶማውያንን ምልክት ሳያደርግ ወደ ሜዳ ገብቶ ጨዋታውን አድርጓል !

ማርክ ጉዬ የተባለው እግር ኳስ ተጫዋች በድጋሚ ክንድ ላይ በሚጠለቀው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " የሚል ፅሁፍ በመፃፍ ወደ ሜዳ በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።

ክሪስታል ፓላስ ለተባለው ክለብ የሚጫወተውና የቡድኑ አምበል የሆነው ጉዬ ከቀናት በፊት ኒውካስል ዩናይትድ ከተባለው ቡድን ጋር ሲጫወት ክንዱ ላይ ባጠለቀው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ " ኢየሱስን እወደዋለሁ " ብሎ ፅፎ በመግባቱ የሊጉን አስተዳዳሪዎች አስቆጥቶ ነበር።

ይኸው ተጫዋች ትላንት ምሽት ቡድኑ ኢፒስዊች ታውን ከተባለው ቡድን ጋር ሲጫወት ክንዱ ላይ ባለው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ በድጋሚ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " ብሎ በመፃፍ በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።

ባለፈው ቅዳሜ ከፃፈው " ኢየሱስን እወደዋለሁ ! " ከሚለው ፅሁፍ በኃላ ፉትቦል አሶሲዬሽን የተባለው የሊጉ አስተዳዳሪ " ኃይማኖታዊ ምልክቶች የእግር ኳስ ማሊያ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ላይ መፃፍ ክልክል ነው " ሲል ለክለቡ እና ለአምበሉ ማስጠንቀቂያ ቢልክም ማስጠንቀቂያው ወዲያ በሉት ብሎ ትላንት ምሽት በድጋሚ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " ሲል በመፃፍ ገብቶ ተጫውቷል።

የሊጉ አስተዳዳሪ ቅጣት ሊጥልበት ይችላል እየተባለ ነው።

በሌላ በኩል የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነው ሳም ሞርሲ የተባለው የኢፒስዊች ታውን ተጫዋች ትላንትም የግብረሰዶማውያንን ምልክት ያለበትን የአምበልነት መለያ ሳያደርግ ነው የገባው።

ተጫዋቹ " ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም " በማለት ባለፈው ቅዳሜም ይህንን የግብረሰዶሞች ምልክት ሳያደርግ መግባቱ የሚዘነጋ አይደለም።

' እኩልነት እና ብዝሃነት ' በሚል ሰብሰብ በዓለም ላይ የግብረሰዶማውያንን እንቅስቃሴ ለማስተዋወቅ እና ሰዎች ጋር ለማድረስ የግብረሰዶማውያን ደጋፊዎች ብዙ አይነት መንገድ ይከተላሉ።

አንዱ ግብረሰዶማውያንን ለማስተዋወቅ የሚጠቀሙት በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ በተለይም ወጣት ተመልካቾች ያሉትን የእግር ኳስ ፍልሚያ ነው።

ከነዚህ የእግር ኳስ ፍልሚያዎች አንዱ ደግሞ በኢትዮጵያ / አፍሪካ ሆነ በዓለም ላይ ብዙ ተመልካች ያለውን እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነው።

በዚሁ ሊግ የሊጉ አስተዳዳሪ አካላት በ ' እኩልነት እና ብዝሃነት ' ሰበብ የክለብ አምበሎች ክንዳቸው ላይ የግብረሰዶማውያንን ምልክት እንዲያጠልቁ አድርገው ለግብረሰዶማውያን ማስታወቂያ እንዲሰሩ ያደርጋሉ።

ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ የሊጉ ፍልሚያ በሚጋጋልበት ወቅት ነው።

ግብረሰዶማውያን እና የነሱ ደጋፊዎች እጅግ በጣም ተወዳጁን የእግር ኳስ ፍልሚያን ተጠቅመው ግብረሰዶምን የሚያስተዋውቁት በልጆች ፣ ታዳጊዎች ፣ ወጣቶች ዘንድ ድርጊቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግና እነሱን ለማነሳሳት ነው።

#TikvahEthiopia
#Guehi #Christian  #PremierLeague
#SamMorsy #Muslim

@tikvahethiopia