TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" በረራውን ለማቋረጥ የተገደድኩት ገንዘብ እንዳላንቀሳቅስ በመታገዴ ነው " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ከመስከረም 20፣ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቆም የሚያሳውቅ ደብዳቤ ጽፎ እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ አየር መንገዱ በሰጠው መግለጫ ውሳኔው ይሻሻላል በሚል ሲጠብቅ እንደነበር እና የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣንን ለማናገር በተደጋጋሚ ያደረገው ሙከራ አለማሳካቱን አስታውቋል።

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በመግለጫው እንደጠቀሱት በአስመራ የሚገኘው ተወካያቸው ከሽያጭ የተሰበሰበ ገንዘብ ለማስገባት ሲል ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ መላክ እንደማይቻል ተነግሮታል። ይህ የሆነው ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ አማካኝነት ነው።

" ' ከነሐሴ 25/ 2016 ዓ.ም በኋላ ሂሳባችሁ ታግዷል ለሀገር ውስጥ ወጪም (oppration fee) መጠቀም አትችሉም ' መባሉን ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ በረራውን ለማቋረጥ ተገደናል። የበረራ ወጪያችንን መሸፈን ባለመቻላችን ተገደን ወጥተናል " ሲሉ ነው የገለጹት።

አየር መንገዱ እንዳያንቀሳቅስ የታገደበት ገንዘብ መጠን ስንት ነው ?

ይህ ጥያቄ ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚው የገንዘቡን መጠን ከመግለጽ ተቆጥበው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አየር መንገዱ በኤርትራ ሁለት አካውንት እንዳለው የገለጹት አቶ መስፍን፥ አንዱ የናቅፋ አካውንት ሲሆን የቆየ እንዲሁም ወደ ዶላር መቀየር ያልተቻለ የማይንቀሳቀስ የሂሳብ አካውንት መሆኑን ገልጸዋል።

ሌላኛው የባንክ አካውንት ደግሞ የዶላር ሲሆን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ትኬት ሲሸጥ የነበረው በውጭ ምንዛሬ መሆኑን ገልጸው ይህንን ገንዘብም እገዳው እስከተላለፈበት ቀን ድረስ በተለያዩ ጊዜዎች ገንዘቡን ሲያንቀሳቅስ እንደነበረ ገልጸዋል።

" የበረራ እገዳውን ካወጡብን በኋላ ነው Block ያደረጉብን " ሲሉ ነው የገለጹት።

አቶ መስፍን አክለውም ፥ "ለእኛ ገንዘቡ ካልተለቀቀልን ከዚህ በኋላ የሁለቱ ሀገራት ጉዳይ ነው የሚሆነው " ሲሉ ጉዳዩን ለኢትዮጵያ ለሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን እና ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቃቸውን ገልጸዋል።

" አየር መንገዱ ከኤርትራ የወጣው ተገዶ ነው " ያሉት አቶ መስፍን ዋናው ችግሩ ለምን እንደታገድን አለማወቃችን ነው፤ በተጻፈው ደብዳቤም ላይ ምንም የተገለጸ ነገር የለም ብለዋል።

" ከዚህም በተጨማሪ በደብዳቤም በስልክም ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም " ሲሉ ገልጸዋል።

የአየር ቀጠናውን አስመልክቶ ጥያቄ የቀረበላቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚው አሁን ባለው ሁኔታ በኤርትራ የአየር ክልል መብረር እንዳልተከለከሉ ገልጸው የሚያስገድድ ጉዳይ ካለ ግን አማራጭ መጠቀም እንደሚችሉ አንስተዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መግለጫ
TIKVAH-MAGAZINE
" የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ አስመራ የሚደረገውን መደበኛ በረራ ከዛሬ ሴፕቴምበር 3/2024 ጀምሮ አቋርጧል። " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

(ሙሉ መግለጫውን ከድምጽ ቅጂው ያዳምጡ)

@tikvahethiopia
🌟 ዓለም አቀፍ የበረራ ትኬትን ጨምሮ በትላልቅ ሽልማቶች ይንበሽበሹ!!

መጪውን አዲስ ዓመት አስመልክቶ ከባህርማዶ በቴሌብር ሬሚት እና በአጋሮቻችን በኩል በቴሌብር ዓለም አቀፍ ሐዋላ የተላከልዎን ገንዘብ ሲቀበሉ 5% የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ፡፡

በተጨማሪም 5 ሺህ ብር እና ከዛ በላይ ሲቀበሉ አጓጊ ለሆነው ልዩ የዕድል ጨዋታ ብቁ ይሆናሉ!

✈️ ደርሶ መልስ የበረራ ትኬት - እያንዳንዳቸው 480,000 ብር
🏞 ኩሪፍቱ ወተር ፓርክ ቤተሰብ ፓኬጅ - እያንዳንዳቸው 44,000 ብር
🐏 የበግ ስጦታ - እያንዳንዳቸው 20,000 ብር
💰 5 ሺህ ብር - 450 ስጦታዎች
🌐 ወርኃዊ ያልተገደበ ዳታ + ድምጽ - 300 ስጦታዎች

🗓 እስከ መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ የጊግ ኢኮኖሚን ጥቅም ማወቅ ይፈልጋሉ?

በቢዝነስ፣ በህግ እና በፋይናንስ ዙርያ የሚሰጠውን የጊግ ኢኮኖሚ ስልጠና በቴሌግራም ቦት በኩል ይውሰዱ!

🔗https://t.iss.one/mesirat_academy_bot ተመዝግበው ስልጠናውን ይጀምሩ!

ስልጠናውን ሲጨርሱ ሰርተፍኬቶን እንዳይረሱ!

#MesiratEthiopia #Entrepreneurship #BusinessGrowth #GigEconomy #Workshops #Mesirat
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TIGRAY

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በዓዲግራት ምን አሉ ?

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ዓዲግራት ህዝባዊ ውይይት አካሂደዋል።

" ህዝቡ ስጋት ላይ የሚጥል ሁኔታ ለመቅረፍ ከናንተ መሃል ተገናኝተናል " ብለዋል።

" የትግራይ መልሶ ግንባታ ጋሃድ እንዲሆን በመደጋገፍ መስራት ይገባናል " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" በውስጣች በተፈጠረው መፎካከር መስራት የሚገቡን አልሰራንም " ያሉት አቶ ጌታቸው " አብዛኛው ጊዚያችን በጭቅጭቅና በጎሪጥ በመተያየት ነው ያሳለፍነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ በማህበራዊ አገልግሎት መልሶ ግንባታ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገናል ፤ ጅምሮቻችን ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በውስጣችን የታዩ ድክመቶችን ማረምና የጋራ መፍትሄ ለመሻት መስራት ይጠበቅብናል " ብለዋል።

" በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ሁሉም በጠላት ስር የሚገኙ አከባቢዎች  ወደ ነባር አስተዳደራቸው መመለስ አለባቸው ብለን እየሰራን ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " የሰላም ስምምነቱ በተሟላ መልኩ እንዲተገበር እንደ መንግስት ጠንክረን እንሰራለን " ሲሉ ተናግረዋል።

" የህዝባችን ሰላም በማረጋገጥ በኩል ዓለም ከኛ ጋር ናት ይህንን እንዲቀጥል ግን ውስጣዊ አንድነታችን እንዳይላላ ያለማቋረጥ መስራት አለብንም " ብለዋል።

በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ዓዲግራት ሲደርሱ በልዩ አጀብ በፈረሰኞች የተደገፈ አቀባበል ነበር የተደረገላቸው።

በአቀባበሉ የተገኙ የዓዲግራት ከተማ ወጣቶች ፦
👉 የጥይት ድምፅ እንጠየፍ !! 
👉 መሰረታዊ ለውጥ እንፈልጋለን !!" 
👉 ተፈናቃዮች ይመለሱ ግዛታዊ አንድነት ይከበር !!
👉 ትግራይ በሳይንስና ጥበብ እንጂ በጥይት አፈሙዝ አትመራም !!
👉 ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንደግፋለን !!
የሚሉና ልሎች መፈክሮች በመያዝ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በተመራ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ቡድን ምክትል ፕሬዜዳንት ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ ነበሩበት።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የNGAT ፈተና መቼ ይሰጣል ? ትምህርት ሚኒስቴር ፥ የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ እና የፈተና ቀንን አሳውቋል። በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላቸው እና በተለያዩ ምክንያቶች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ያመለጣቸው አመልካቾች እስከ ነሐሴ 26/2016 ዓ.ም ድረሰ በ https://ngat.ethernet.edu.et በኩል…
#NGAT : የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የሚሰጥበት ቀን እና ሰዓት ይፋ ተደርጓል።

ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነውን የትምህርት መስኮችና የመግቢያ ፈተና የሚሰጥባቸውን መርሐግብር ከላይ ይመልከቱ።

ፈተናው ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#NGAT : የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የሚሰጥበት ቀን እና ሰዓት ይፋ ተደርጓል። ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነውን የትምህርት መስኮችና የመግቢያ ፈተና የሚሰጥባቸውን መርሐግብር ከላይ ይመልከቱ። ፈተናው ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል። Via @tikvahuniversity
NGAT_EXAM_SCHEDULE_FFF1.xls
33.5 KB
#NGAT : ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1 / 2016 ዓ.ም የሚሰጠው የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የሚሰጥበት ቀንና ሰዓት፣ የመፈተኛ ማዕከላት እና የትምህርት መስኮች

ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ የመጨረሻ መርሐግብር ከላይ ተያይዟል።

Via @tikvahuniversity
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ ይህ #ድብድብ ከሶማሊያ ተገንጥላ ራሷን በምታስተዳድረው #ሶማሌላንድ ፓርላማ ውስጥ የተከሰተ ነው።

ምንድነው የተፈጠረው ?

ዛሬ የፓርላማ አባላቱ ሞሃመድ አቢብ በተባለ የፓርላማ አባል ያለመከሰስ መብት መነሳት ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ ነበራቸው።

ሞሀመድ አቢብ እጅግ የሚታወቁና አውዳል ላይ ብዙ ተከታይ ያላቸው ፖለቲከኛ ሲሆኑ ገዢዎችን በመኮነን ለውጥ እንዲመጣ የሚታገሉ ናቸው ይባልላቸዋል።

የሶማሌላንድ መንግሥት እኚህን ፖለቲከኛ ከዛሬ 3 ቀን በፊት ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ዱባይ ሲመለሱ ሀርጌሳ ኤርፖርት ላይ ጠብቆ አስሮ እስር ቤት አስገብቷቸዋል።

ያሰራቸው በሀገር ክህደት እና የሶማሌላንድ ሪፐብሊክን ከሚቃወሙ ቡድኖች ጋር አብረዋል በሚል ነው።

ይህ በደጋፊዎቻቸው ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል።

መንግሥት ፓርላማውን አስቸኳይ ስብሰባ አስቀምጦ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በጠቅላይ አቃቤ ሕግ የውሳኔ ሀሳብ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ከተገኙት 57 አባላት ውስጥ 51 አባላት ተቃውመዋል።

ታዲያ በዚህ ጉዳይ ላይ ነው ፓርላማ ውስጥ ክርክር ሲደረግ በሁለት አባላት መካከል የለየለት ድብደብ እና የቡጢ መሰነዛዘር፣ እቃ መወራወር የደረሰ መነጋገሪ ክስተት የተከሰተው።

ተደባዳቢ የፓርላማ አባላቱ መጎዳታቸው ተነግሯል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቱርክ #ኢትዮጵያም ያለችበትን የBRICS ስብሰብ ትቀላቀል ይሆን ? ባለፈው ሳምንት የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን የBRICS አባሏን ቻይናን ጎብኝተው ነበር። በጉብኝታቸው ወቅት ከቻይና ባለስልጣናት ጋር መክረዋል። በወቅቱ ሀገራቸው ቱርክ የBRICS ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ተጠይቀው ፥ " በእርግጥም #እንፈልጋለን። ለምን አንፈልግም ? " ብለዋል። " በእርግጥም ፤ የBRICS…
#BRICS+

የNATO አባል ሀገሯ ቱርክ የBRICS አባል ለመሆን ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች።

ቱርክ የBRICS አባል ለመሆን በይፋ ማመልከቻ ማቅረቧን የቱርክ ገዥ ፓርቲ ቃል አቀባይ ኦመር ሴሊክ አረጋግጠዋል።

ቃል አቀባዩ " ፕሬዝደንታችን የBRICS አባል መሆን እንደምንፈልግ ደጋግመው ተናግረዋል። ጉዳዩ በሂደት ላይ ነው " ብለዋል።

" በአባልነት ሂደት ላይ ያለውን እምርታ ለህዝብ እናሳውቃለን " ሲሉም ተናግረዋል።

ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም የBRICS+ ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ማሳወቋ የሚዘነጋ አይደለም።

ቱርክ የ #NATO አባል ሀገር እንደሆነች ይታወቃል።

#BRICS+ ኢትዮጵያን ጨምሮ የሩስያ ፣ የብራዚል ፣ የቻይና ፣ የህንድ ፣ የደቡብ አፍሪካ ፣ የኢራን ፣ የግብፅ ፣ የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ስብስብ ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia