TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥቆማ #ጥንቃቄ 🚨

ይህ የተንጋደደና ለመውደቅ ጫፍ የደረሰ የመንገድ መብራት ምሰሶ ወድቆ በአስፓልቱ ላይ በሚተላለፍ ተሽከርካሪ እና በሰው ላይ ጉዳት ከማድረሱ በፊት መፍትሄ ይፈለግለት።

ይነሳ አልያም በአግባቡ ይጠገን።

ቦታው አዲስ አበባ ፣ ከአትላስ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን መሄጃ የትራፊክ መብራቱ ጋር ነው።

እንዲሁ ሊወድቅ እንዳለና እንደተንጋደደ በርካታ ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን የሚያነሳው እና የሚያስተካክለው አልመጣም።

ከከባዱ የክረምት ወቅት ጋር ተያይዞ ወድቆ ጉዳት ሳይደርስ በፊት አስቸኳይ መፍትሄ ይሰጠው።

👉 ለአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ
👉 ትራፊክ ማኔጅመንት

#TikvahEthiopiaAddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

" በችግር ላይ ሌላ ችግር  በህዝቡ ላይ የመጫን ፍላጎት የለንም ፤ አሁን የገጠመን ፈተና እናልፈዋለን። አባቶች በፀሎትና ምክር አግዙን !! " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)

የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) ነሃሴ 24 ቀን 2016 ዓ/ም ከአበው ጳጳሳት እና የአገር ሽማግሌዎች ጋር በኣክሱም ከተማ መወያየታቸውን የሚገልጽና አንድ ንግግር ሲያደርጉ የሚታይበት ቪድዮ ተሰራጭቷል።

ቪድዮው በትግራይ ፐብሊክ ሚዲያ (TPM) የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ነው የተሰራጨው።

ሊቀመንበሩ የ5 ደቂቃ ርዝማኔ ባለው ንግግራቸው  ፥ " እኔ ለድርጅትና ለህዝብ ደህንነት ስል ብዙ ታግሻለሁ ፤ ትዕግስትና ዝምታዬ ግን መልካም ነገር ሳይሆን አደጋ ነው ያስከተለው ፤ ስለሆነም ከአሁን በኋላ መታገስ ሳይሆን ተመጣጣኝ ሰላማዊ ትግል ነው የሚያዋጣው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" እኛ የውጭ ጠላት አለብን የውስጥ ጉዳይ አናቆየው በማለታችን በውስጣችን ብዙ ችግሮች እንዲፈጠሩ ሆኗል " ያሉት ደብረፅዮን (ዶ/ር) ፥ " ከአሁን በኋላ የጎራ መደበላለቅ አይኖርም አቋማችን በግልፅ በማንፀባረቅ ሰላማዊ ትግል ማካሄዳችን እንቀጥላለን " ብለዋል።

" በሃይል ፍላጎቴን አሳካለሁ የሚል አካል ሃይ ሊባል ይገባዋል ፥ በትግራይ በጉልበት እሰራለሁ ማለት አያዋጣም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከአሁን በኋላ ከህዝብ የሚደበቅ ሚስጥር አይኖርም " በማለትም ተናግረዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ " የተፈጠረውን ልዩነት በሰላም እንጨርሰው ፤ የማይሳካ ከሆነ ግን ሉአላዊነታችንን አሳልፈን አንሰጥም ፤ አቋማችን ግልፅ በማድረግ እንታገላለን " ብለዋል።

" አንድ በማያደርገን አንድ ሁኑ አትበሉን  በፓለቲካ አንድ በማያደርግህ አቋም አንድ መሆን አይቻልም ፤ ተከባብሮ በሰላም መስራት ግን ይቻላል ፤ ትግራይ ለሁሉም በቂ ናት " ሲሉም ደብረጽዮን (ዶ/ር) አክለዋል።

ህዝቡ ላይ በችግር ላይ ሌላ ችግር መጫን  እንደማይፈልጉ የተናገሩት ሊቀመንበሩ ፥ የተፈጠረው ሁኔታ ተስፋ የሚያስቆርጥ እንዳልሆነና በሰላማዊ አግባብ እንደሚፈታ በማመላከት የሃይማኖት አባቶች በፀሎትና በምክር እንዲረዱዋቸው ጠይቀዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያመቐለ #TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
Bethlehem Ghiday, a Jasiri fellow of the 5th cohort, says that Jasiri gave her the foundational skills needed to become entrepreneur. Through Jasiri, she was able to become the co-founder of Baobab Superfoods.

If you wish to establish your own venture like Bethlehem, Join the next cohort. Apply now!

👉🏾 https://bit.ly/3A8rxtV

For more information, Join our telegram channel 👉🏾 @Jasiri4africa
🔈#የሠራተኞችድምጽ

“ በ2500 ብር ደመወዝ ቤተሰብ ማስተዳደር፣ ምሳ እንኳ መመገብ አልቻልንም፡፡ በጣም ተጨቁነናል ” - የጥበቃ ሠራተኞች

የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ጭምር የባንክ ቤት ጥበቃ ሠራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዛቸው እጅግ አነስተኛ በመሆኑ መመገብ እንኳ እንዳልቻሉ፣ ቀጣሪ ተቋማትም መፍትሄ እየሰጧቸው እንዳልሆነ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እሮሮ አሰምተዋል፡፡

ከሠራተኞቹ መካከል አንዱ፤ “ እኔ አሁን በፐብሊክ አድሚኒስትሬሽንና ዲቨሎፕመንት ማኔጅመነት ድግሪ አለኝ፡፡ 2015 ዓ/ም ነው የተመረኩት፡፡ የደረጃ እድገት አግኝቼ ወደ ባንክ ሥራ የምገባ መስሎኝ ነበር ጥበቃ የገባሁት፡፡ ግን ካለው ትንሽ ደመወዝ እንኳ ይቆርጡብናል ” ብሏል።

ቤተሰብ ጭምር የሚያስተዳድሩ የጥበቃ ሠራተኞች የሚከፈለው ደመወዝ እንኳን ቤተሰብ ለማስተዳደር ለአንድ ሰውም እንደማይበቃ ገልጸው፣ ወዴት ሂደን እንኑር ? ወደ ማንስ እንጩህ ? ሲሉ ጠይቀዋል።

ሠራተኞቹ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ ደማታአ ጥበቃና ንግድ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማ በሚባለው ኤጀንሲ አማካኝነት ነው ወደ ባንክ ቤት ጥበቃ ሥራ የገባነው፡፡

በደብዳቤ ፣ በውል ነው የገባነው ግን የሆነ ሰበብ ፈልገው ውጣ ነው እያሉን ነው፡፡ ሲፈልጉ ' ግቡ ' ይላሉ ሲፈልጉ ደግሞ ' ውጡ ' ይላሉ፡፡

ሰዎች ነን የሆነ ችግር ሊገጥመን ይችላል፡፡ የጥበቃ መሳሪያ፣ መጸዳጃ ቤት የለንም፡፡ አሁን ደግሞ ከባንክ ቤት ቅጥር ግቢ ውጪ አስወጡን፡፡ በፊት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነበር የምናድረው አሁን ውጪ አደረጉት፡፡

የጥበቃ መሳሪያ እንዲሰጠን ደብዳቤ ብንጽፍ 'እናንተ ደብዳቤ መጻፍ አትችሉም ' አሉና ጭራሽ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ ጻፉልን፡፡ በዚሁ ሳቢያ ሁለት ጓደኞቻችን ተባረዋል፡፡

በ2,500 ብር ደመወዝ ቤተሰብ ማስተዳደር፣ ምሳ እንኳ መመገብ አልቻልንም፡፡ በጣም ተጨቁነናል፡፡ ቢሮ ስንሄድ ጉዳያችንን አጣጥለው ይወነጅሉናል፡፡

በተለይ ደብዳቤ ከጻፍንላቸው ወዲህ እንደሰው አይደለም የሚቆጥሩንም፡፡ ለማን እንደሚጮህም ግራ ገባን፡፡

በውስጥ ሂደን ስናመለክት እኛኑ ነው የሚወነጅሉንና የሚያባርሩን፡፡ ይቺ 2,500 ብር ደመወዝ ለቤት ኪራይ እንኳ መሆን አትችልም።

አንድ ሰው ባንክ ቤት ጥበቃ ሲሰራ 24 በ 48 የሚባል አለ፡፡

5,000 ብር ተከፍሎን አንድ ባንክ ላይ በጥበቃ እንደምንሰራ ነው ባንኮች የሚውቁት (ዋናዎቹ ማለትነው)፡፡ ከታች ያሉት ግን በ2,500፣ በ2500 ከፋፍለው ሁለት ቅርንጫፍ ላይ ነው የሚያሰሩን፡፡

የባንክ ቤት ማናጀሮችን ስናናግር ' እኛ ምን እናድረግ የቀጠራችሁን ኤጀንሲ ጠይቁ ' እያሉ ዝም አሉን፡፡ የሚያስቡን መረጃ አጠያየቅ /አካሄድ አይችሉም ብለው ነው
" ብለዋል።

ሠራተኞቹ የቀጠራቸው ኤጀንሲ ከባንክ ቤት ጋር ተነጋግሮ ችግራቸውን እንዲፈታላቸው በአንክሮ ጠይቀዋል፡፡

ለቅሬታው ምላሽ ለማግኘት ወደ ድርጅቱ ያደረግነው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለጊዜው አልተሳካም፡፡

በድጋሚ የምንጠይቃቸው ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

" ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ የተቋቋሙበት መንደር አይደሉም " - ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የ33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ " ፍትሃዊ እና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ! " በሚል ጭብት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ተካሒዷል።

ጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ፥ በትምህርት ዘርፍ ላይ ያሉ አመራሮች የትምህርት ሥራን ከፖለቲካ መለየት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

" ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ የተቋቋሙበት መንደር አይደሉም " ብለዋል ሚኒስትሩ።

" ከዚህ በኋላ በምንም ዓይነት ሁኔታ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በአካባቢ የሚመደብበት ሁኔታ እንደማይኖር " ገልፀዋል።

" የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ምደባ በውድድር እና በብቃት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንዲሆን ይሠራል " ብለዋል።

Via @tikvahuniversity
#ETHIOPIA🇪🇹

ከሰሞኑን በፔሩ፣ ሊማ ሲካሄድ በቆየ የዓለም ከ20 ዓመት በታች ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአሜሪካ በመቀጠል ከዓለም ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ:- 
6️⃣ የወርቅ፣
2️⃣ የብር
2️⃣ የነሀስ ሜዳሊያ በማግኘት ነው ከዓለም ሁለተኛ ከአፍሪካ ደግሞ #አንደኛ በመሆን ያጠናቀቀችው።

Via @tikvahethsport   
#ExamResult : የ12ኛ ክፍል ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የ2016 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል ? ሲል አንድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከፍተኛ አመራርን ጠይቋል።

እኚሁ ከፍተኛ ኃላፊ ፤ የፈተናው እርማት በጥንቃቄ እየተከናወነ እንደሆነ ገልጸው እርማቱ እንደተጠናቀቀ በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

" እርማቱ በጥንቃቄ እና በፍጥነት እየተሠራ ነው። በቅርቡ ውጤቱ ይፋ ይደረጋል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia

የውጪ ምንዛሪ ቢሮ ፍቃድ መስጠት የሚያስችለውን ሂደት መጨረሱን የብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።

ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም መደበኛ ባልሆነ መንገድ የውጪ ምንዛሪ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ህጋዊ ሆነዉ ፍቃድ አውጥተዉ መስራት እንዲችሉ መፍቀዱን ተከትሎ ከወዲሁ ብዙ ሰዎችና ኩባንያዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ ገልጿል።

የውጪ ምንዛሪ ገበያ ውስጥ የሚሳተፉ በፊት ባንኮች ብቻ የነበሩ ቢሆንም አሁን ግን ከባንኮች በተጨማሪ ሌሎች በግላቸው በዘርፉ ላይ ለመሰማራት የሚፈልጉ አካላት እንዲሰሩ ተደርጓል።

ባንኩ የውጭ ምንዛሪ ክትትልና መጠባበቂያ አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር አቶ አበባየሁ ዱፈራ በሰጡት ቃል ፥ የውጪ ምንዛሪ ቢሮ ለመክፈት ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ባንኩ ተቀብሏል።

" ከንግድ ሚኒስትር ጋር ያለው ጉዳይ ከተፈታ ወዲያው ፍቃድ መስጠት እንጀምራለን በእኛ በኩል ሁሉም ነገር አልቋል " ብለዋል።

" ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የውጪ ሀገር ዜጎችም አካዉንት ከፍተዉ ሲፈልጉ ብቻ ወደ ብር ቀይረዉ እንዲጠቀሙ ተፈቅዷል ፤ ይህም በድፍረት የተደረገ ነው ማለት ይቻላል " ሲሉ እርምጃውን አድንቀውታል።

ሀገር ዉስጥ ያሉ ማንኛውም የዉጪ ምንዛሪ የሚያገኙ ግለሰቦች በትንሹ በ100 ዶላር የውጪ ምንዛሪ አካዉንት መክፈት እንደሚችሉ የጠቆሙት አበባየሁ ዱፈራ ይህ ጥቅሙ ለግለሰቦች ሳይሆን ሀገርም ጭምር ተጠቃሚ ይሆናል ብለዋል።

Credit : Capital Newspaper

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

⚽️አጓጊው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት የእለቱ ጨዋታዎች!

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ወደ ሜዳ ያሳድጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት #DstvEthiopia

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
🔈 #የነዋሪዎድምጽ

• " ቤንዝል ሙሉ በሙሉ  ከጠፋ 4 ቀናት መሆኑን ተከትሎ ከስራ ውጭ ሆነናል " - በሀዋሳ ከተማና አካባቢዉ የሚገኙ አሽከርካሪዎች

• " ከጅቡቲ የተነሱ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች እስኪደርሱ በትእግስት ጠብቁ " - የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ

ከሰሞኑ በነዳጅ እጥረት ምክኒያት አልፎ አልፎ የነዳጅ ፕሮግራም ሲወጣ ቢቆይም ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ ግን ሙሉ በሙሉ ድልድል ባለመውጣቱና በከተማው ውስጥ ያሉ ሁሉም ማደያዎች " ቤንዝል  የለም " በማለታቸው በከፍተኛ ሁኔታ ችግር ውስጥ ገብተናል ያሉ የሀዋሳና አካባቢው አሽከርካሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አሁን ላይ በህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ አሽከርካሪዎች ስራ መፍታታቸዉን ሲገልጹ አንዳንዶች ደግሞ እጅን አጣጥፎ ላለመቀመጥ ከህገወጥ ቤንዝል ሻጮች አንድን ሊትር እስከ ከመቶ ሀምሳ ብር በላይ እየገዙ መሆኑን ይናገራሉ።

በዚህ ደረጃ ቤንዝል መጥፋቱ ግራ አጋብቶናል የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ አሁን ላይ አሽከርካሪዉም ማህበረሰቡም ችግር ላይ ነው ብለዋል።

የአሽከርካሪዎቹን ቅሬታ ይዘን ያነጋገርናቸው የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ኃላፊዉ አቶ ተመስገን ችሎት " ላለፉት ሶስት ቀናት ድልድል ያልነበረው ከተማ ውስጥ የሚገኙ ማደያዎች ቤንዝል በመጨረሳቸዉ ነው " ብለዋል።

በዚህ ሰአት መንገድ የጀመሩ ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ከጅቡቲ መነሳታቸውን የሚገልጽ መረጃ አለን የሚሉት ኃላፊዉ እነዚህ ቦቴዎች እስኪደርሱ  ሁለት ሶስት ቀናት መታገስ ይኖርብናል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የነዋሪዎድምጽ • " ቤንዝል ሙሉ በሙሉ  ከጠፋ 4 ቀናት መሆኑን ተከትሎ ከስራ ውጭ ሆነናል " - በሀዋሳ ከተማና አካባቢዉ የሚገኙ አሽከርካሪዎች • " ከጅቡቲ የተነሱ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች እስኪደርሱ በትእግስት ጠብቁ " - የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከሰሞኑ በነዳጅ እጥረት ምክኒያት አልፎ አልፎ የነዳጅ ፕሮግራም ሲወጣ ቢቆይም ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ ግን ሙሉ በሙሉ ድልድል ባለመውጣቱና…
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

ነዳጅ (ቤንዚን) በክልሎች ላይ ችግር ከሆነ እጅግ በርካታ ጊዜያት ያስቆጠረ ነው።

ከአዲስ አበባ ውጭ ነዳጅ እንደልብ ማግኘት አዳጋች ነው።

ለተለያዩ ጉዞ ወደ ክልሎች የሚወጡ መንገደኞች ይህንን ነገር ያውቁታል።

በአንድ በኩል ነዳጅ የለም እየተባለ በጥቁር ገበያ እስከ 150 ብር ከዛም ከፍ ብሎ ለጉድ ይቸበቸባል።

ይህንን ችግር ማስተካከል ፤ ጥቁር ገበያውን መቆጣጠር ለምን አልተቻለም ? የብዙሃን ጥያቄ ነው።

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች ነዳጅ ለማግኘት ሰዓታትን መሰለፍ ግድይላቸዋል ፤ ጾማቸው ላለማደር ልጆቻቸውን ላለማስራብ የዕለት ጉርሳቸውን ይዘው ለመግባት ከማደያ ውጭ ይገዛሉ።

በየጊዜው በየማደያው " የለም " ይባላል ውጭ ላይ ለጉድ ይሸጣል። ይህ ሰንሰለት ከላይ እስከ ታች መሆኑ እሙን ነው። ዘላቂ መፍትሄ ያስፈልጋል።

ነዳጅ በአግባቡ ለተጠቃሚው እንዲደርስ ያሉት ችግሮች ተፈትሸው መታረም ግድ ይላለቸዋል።

በየጊዜው በነዳጅ ጉዳይ ዜጎች መማረር የለባቸው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia " ሌሎች ተዋናዮች የአፍሪካ ቀንድ ክልልን ለማተራመስ እርምጃ ሲወስዱ በዝምታ አንመለከትም " - ኢትዮጵያ @tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹

" #ኢትዮጵያ ሶማሊያ እንደ አገር ትቆም ዘንድ ብዙ መስዋዕትነትን ከፍላለች፡፡ ብዙ ሺሕ የሚቆጣጠሩ ወንዶችና ሴቶች መስዕዋት አድርገናል ገብረናል፡፡

የቆጠብነው ነገር የለም ሕይወት ሰጥተናል፣ ደም ሰጥተናል፣ ላብ ሰጥተናል፣ ጉልበት ሰጥተናል፡፡ ነገር ግን በሶማሊያ በኩል ይህንን አስተዋጽኦ ከቁብ ላለመቁጠርና ውለታ ለማስቀረት የሚደረግ መግለጫ መስማት እንደ ኢትዮጵያዊ ይኮሰኩሳል።

እንደ አፍሪካዊና ሰላም ወዳድ እንደሆነው የሶማሊያ ሕዝብ ደግሞ ያማል።

በሶማሊያ በኩል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ያደረገውን ተጋድሎ በማንኳሰስ፣ የወሬያቸውና የንግግራቸው ሁሉ ማዋዣ ብቻ ሳይሆን ማዕከል እያደረጉት ነው ፤ ይህ ነውር ነው !!

ኢትዮጵያ ለዘመናት ያደረገችውን አስተዋጽኦ እና የከፈለችውን ዋጋ በማጣጣል፣ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚፃረሩ ኃይሎችን ሶማሊያ መጋበዟን ልታቆም ይገባል።

ኢትዮጵያ የደኅንነት ሥጋት የሚፈጥርባትን አካል ዝም ብላ አትመለከትም። " - አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ (የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር)

#Ethiopia #Reporter
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD🇪🇹 ይህ የኢትዮጵያ ህዝብ የላብና ደም አሻራ ያረፈበት የኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ የአይን ብሌኑም ጭምር ነው። ተማሪው ፣ ሰራተኛው ፣ ወጣቱ ፣ አዛውንቱ ለዚህ ግድብ ካለው ላይ ፤ ከሚበለው ቀንሶ ሰጥቶ ያሰራው ለትውልድ የሚያወርሰው ሀብቱና ቅርሱ ነው። ይህ ግድብ ሀገር ውስጥ በየጊዜው በሚፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት ሀዘን፣ መከፋት፣ መበደል ሲመጣ እንኳን ሁሉም…
የግብፅ ነገር ?

ሀገራችን ኢትዮጵያ " እኔ ማንንም ሳልጎዳ የራሴን ሃብት እጠቀማለሁ " ብላ በራሷ የዓባይ ወንዝ ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ለመገንባት መሰረት ከጣለችበት ጊዜ አንስቶ ስትጮህ ፣ ስትዝት፣ ለማስፈራራት ስትሞክር የነበረችው ግብፅ ዛሬም ግድቡ ወደ መጠናቀቁ ደርሶም ዛቻና ቀረርቶዋን አላቆመችም።

ዛሬ ወደ ተመድ ፀጥታው ምክር ቤት አንድ ደብዳቤ ልካለች።

ሀገሪቱ በቅርቡ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ግድቡን ከጎበኙና ተጨማሪ ተርባይኖች ወደ ስራ መግባታቸውን ካበሰሩ በኃላ ስለ ግድቡ ውሃ መያዝ እና ከሞላ ጎደል የሲቪል እና ኤሌክትሮ መካኒካል ስራ ወደ መጠናቀቁ መድረሱን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ እጅግ አናዷታል፤ አንጨርጭሯታል።

ለጸጥታው ም/ቤት በጻፈችው ደብዳቤ ላይም " በግብፅ መንግሥት ዘንድ ተቀባይነት የለውም " ብላለች።

ሀገሪቱ ግድቡን ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያን ጎረቤቶቿን ተንኳሽ አድርጋ ለማቅረብም ሞክራለች።

ኢትዮጵያ ስንት አመት ሙሉ ለሁሉም ጠቃሚ በሆነ መንገድ መፍትሄ ለማምጣት እንነጋገር እንስማማ ፤ መፍትሄ እንዲመጣ ቁርጠኛ ነኝ ስትል እንዳልከረመች ግብፅ እንደሁል ጊዜ ክሷ " ኢትዮጵያ ሌሎችን አግልላ የአንድ ወገን ፖሊሲ ታራምዳለች፣ መፍትሄ እንዲመጣም አትፈልግም " ብላለች።

ግብፅ ለጸጥታው ምክር ቤት በጻፈችው በዚህ ደብዳቤ ፤ " ኢትዮጵያ እየተከተለች ነው ያለችው ህገወጥ ፖሊሲ በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ማለትም በግብፅ እና በሱዳን ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል " የሚል የተለመደውን ክሷን አቅርባለች።

" ጥቅሜን ለማስጠበቅ ሁሉንም አይነት ህጋዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ ተዘጋጅቻለሁ " ስትልም ዛቻዋን ገልጻለች።

" ሁኔታዎችን በቅርብ እየተከታተልኩ ነው " ያለችው ሀገሪቱ " ህልውናዬን እና የህዝቤን ጥቅም ለማረጋገጥ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር የተረጋገጡ ሁሉንም አይነት እርምጃዎችን ለመውሰድ ተዘጋጅቻለሁ ነው " ያለችው።

ግብፅ እንዲህ አይነት ዛቻ ስታሰማ ይህ የመጀመሪያ አይደለም። ገና ግድቡ መገንባት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እንዲሁ ስትል ነው የኖረችው።

ምንም እንኳን በቀጥታ ሞክራው ባታውቅም ኢትዮጵያን ይጠላሉ፣ ወይም ያዳክሙልኛል የምትላቸውን ኃይሎች በግልፅና በህቡ ስትደግፍ ፤ የግድቡን ስራም ለማደናቀፍ ስትሰራ ነው የኖረችው።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ላይ ዓለም አቅፍ ጫና ለማሳደር ሁሌም እንደተሯሯጠች ነው ፤ ግድቡ ግን ኃይል ማመንጨት ጀምሯል። አሁን ላይም ወደመጠናቀቁ ነው። ግብፅ ዛቻዋን አላቆመችም፤ አርፋም አልተቀመጠችም። በምንም አይነት መንገድ ለኢትዮጵያ የምትተኛም አይመስልም። " ኢትዮጵያን ይጎዳል " የምትለውን ክፍተት ሁሉ ከመጠቀም ወደኃላ የምትመለስም አይደለችም።

የፈለገችውን ብትሞክር ፣ ብትዝት፣ ብታወራ በተግባርና በቀጥታ ግን ኢትዮጵያን መንካት ፈጽሞ አትችልም።

#TikvahEthiopia
#ቲክቫህኢትዮጵያ
#GERD🇪🇹

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሶማሊያ ? ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ #ሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች ወዲህ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት አሻክራለች። የሀገሪቱ ፕሬዜዳንትም በየጊዜው በተለይ ወደ ግብፅ ሲመላለሱ ነው የከረሙት። በቅርብ ደግሞ ግብፅ ሄደው ከፕሬዜዳንት አልሲሲ ጋር ወታደራዊ ስምምነት ፈጽመው ነው የመጡት። ትላንት ደግሞ የጦር መሳሪያዎችን የጫኑ ሁለት የግብጽ የጦር አውሮፕላኖች በሞቃዲሾ ገብተዋል።…
የግብፅ ነገር #2 ?

ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር በባህር በር ጉዳይ የመግባቢያ ስምምነት በተፈራረመች ወቅት ሰዓታት ሳይቆጠር ተቃውሞ ያሰማችው ግብፅ ነበረች።

ከሶማሊያ ጋር ተደዋውላም  " አይዞሽ እኔ አለሁልሽ፤ በማንኛውም መንገድ አብሬሽ ቆማለሁ " ብላት ነበር።

ባለስልጣናቶቿም ኢትዮጵያ ለሶማሊያን ስንትና ስንት የደም ዋጋ እንዳልከፈለች ዛሬ ደፍረው " ኢትዮጵያን እንዳለመረጋጋት ምንጭ " አድርገው ለመሳልም ሞክረዋል።

የኢትዮጵያን ስም እያነሱ ሲለፈልፉ ከርመዋል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ከኢትዮጵያ ጋር መቃቃር ውስጥ ገብተው ወደ ግብፅ ሲመላለሱ ነው የከረሙት።

በቅርብ ደግሞ " ከግብፅ ጋር ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረምን " ብለው ብቅ ብለዋል።

ይህ ተሰምቶ ብዙ ሳይቆይ የተለያዩ የጦር መሳሪያ ቁሳቁሶችን የያዙ የግብፅ ፕሌኖች ሞቃዲሾ ሲያርፉ እና ቁሳቁስ ሲያራግፉ ነው የከረሙት።

ሶማሊያ ደም አፍስሶ ዋጋ የከፈለላትን የኢትዮጵያ መከላከያ በATMIS እንዲቀጥል አልፈልግም ማለቷ ፤ ግብፅ ደግሞ በሶማሊያ ወታደሮቼን ማሰማራት ፈልጋለሁ ማለቷ አስገራሚ ነገር ሆኗል።

" እኛ የግብፅ ወታደር እንዲመጣ አንፈልግም፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች ዋጋ ከፍለውልናል ፤ እንዳይወጡ " ያሉ የሶማሊያ የምክር ቤት ሰዎች እና ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተው ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ፕሬዝዳንቱ " ኢትዮጵያን በአቋማችሁ ደገፋችኋል " ያላቿውን ሰዎችን ከስራ ማባረር እንደተያያዙ ተሰምቷል።

ይኸው ቀጠናዊ ጉዳይ እንዳለ ደግሞ ግብፅ ሆዬ የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብን ጉዳይ በማንሳት " ማንኛውም አይነት እርምጃ ውስዳለሁ " ብላ ዛቻ ማሰማት ጀምራለች ፤ ምንም እንኳን የግብፅ ዛቻ አዲስ ባይሆንም።

እዛው ባለችበት በርቀት ሆና መዛት ፤ መጮህ ፣ ማውራት መብቷ ነው ኢትዮጵያን መንካት ግን ፈጽሞ አትችልም።

#TikvahEthiopia
#GERD🇪🇹

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA🇪🇹

" ልንከተለው የሚገባው ፖሊሲ አለመፍራት ነው ፤ ... አለመፍራት ሲባል ማንቀላፋት ማለት አይደለም " - አቶ መልስ ዜናዊ (የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ)

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ ሲሰጡ በግብፅ ጉዳይ ተናግረው ነበር። ንግግራቸው የፓርላማ አባላትን ፈገግ ያሰኘ ደግሞም ጠንከር ያለ ነበር።

ምን ነበር ያሉት ?

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ፦

" ... የግብፅ መንግሥት #የጥፋት_መንገድ ለማንም እንደማይጠቅም ፤ ተከባብሮ እና ተጠቃቅሞ መኖር እንደሚቻል እንዲገነዘብ ማድረግ ነው ዋናው ስትራቴጂያችን።

አንዱ የግብፅ ስትራቴጂ ትልቅ ወታደር አስቀምጦ ማስፈራራት ነው ፤ ይሄን በተመለከተ ልንከተለው የሚገባው ፖሊሲ አለመፍራት ነው የሚሆነው ማለት ነው።

አለመፍራት ሲባል የቀረርቶ ጋጋታ ማስቀመጥ ማለት አይደለም፤ አለመፍራት ሲባል ማንቀላፋት ማለት አይደለም፤ አለመፍራት ሲባል በተጨባጭ በሀገራችን ላይ ሊቃጣ የሚችለው ወረራ ምን ያህል ነው ? ብሎ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መፈተሽ ማለት ነው።

ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ሲፈተሽ የግብፅ ወረራ አደጋ በኢትዮጵያ ላይ በጣም ትንሽ ነው። ዜሮ ነው ማለት ግን አይቻልም። ነገር ግን በጣም ትንሽ ነው።

ስለዚህም በዚህ በጣም ትንሽ በሆነ አደጋ ምክንያት እንቅልፍ የምናጣበት ምክንያት የለም። ይሄ ማለት ዜሮ ሳላልሆነ ያቺ ትንሿን አደጋ ለመቋቋም ተጨማሪ የአቅማችንን ያህል ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል።

ይሄን የምናደርገው ግብፅ ይወረናል ብለን ቡራ ከረዮ ለማለት አይደለም። አደጋው በጣም ትንሽ ነው መፍትሄው በጣም ቀላል ነው ፤ መፍትሄው ተደጋግፎ መኖር ነው።

ዋናው ስትራቴጂያችን ላይ እየተረባረብን ምናልባት 5በመቶ እድልም ቢሆን 5በመቶ ትኩረት ሰጥቶ ለዚህ ጉዳይ የመከላከል አቅማችንን መገንባት ነው። "

#ETHIOPIA
#GERD🇪🇹

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

🎤 ጎበዝ እየዘፈንን እንጂ! ሰዉ ጥሎን ሊሸለም ነው እኮ! 🏃🏼 አሁኑኑ ወደ TikTok ሄደን ተሰጥዖአችንን እናሳይ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፡
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳንረሳ
📲የTikTok ደረገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ  እንዝፈን! እንላክ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit #FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge