TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አማራ #ጎንደር🕯 በአማራ፣ ሰሜን ጎንደር ዞን 3 ወረዳዎች በመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ እና የተጎዱ ሰዎች ቁጥር በዛሬው ዕለት ጨምሯል። ሟች ወገኖቻችን 23 ደርሰዋል። የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖቻችን ደግሞ  8 መድረሳቸው ተነግሯል። ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወገኖቻችን አጠቃላይ ከ2 ሺህ 700 በላይ ናቸው። አደጋው የደረሰው በዞኑ በጠለምት፣ በጃናሞራ፣ በአዲአርቃይና በየዳ ወረዳዎች በሚገኙ…
#ትኩረት🚨

" የመሬት መንሸራተቱ እየጨመረ ነው፡፡ በዞኑ ከ50 ሺሕ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል " - ዞኑ


በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በተከሰተው የመሬት መንሸራተት ከ50 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንና እስካሁን የ5 ሰዎች አስከሬን እንዳልተገኘ ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰላምይሁን ሙላት በሰጡት ቃል፤ " የመሬት መንሸራተቱ እየጨመረ ነው፡፡ በዞኑ ከ50 ሺሕ በላይ ሰዎች ተፈናቅላዋል " ብለዋል።

የመሬት መንሸራተቱ ከዚህ ቀደም ካደረሰው ውጪ በሰዎች ሕይወት ላይ ተጨማሪ ጉዳት ባያደርስም በተለይ ጠለምት ወረዳ ላይ እንደቀጠለ መሆኑን አሰድተዋል።

ችግሩ የከፋ ከመሆኑ በሻገር ሊቆም ባለመቻሉ ለአደጋው ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን በዘላቂነት ከችግሩ ለማውጣት፣ አደጋው የደረሰባቸውን ወገኖች ለመርዳት የሌሎች ድጋፍ እንደሚያሻው ዞኑ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጥሪ አቅርቧል፡፡

" ከመንግስት ውጪ ያሉ አካውንቶች ተገቢ አይደሉም፡፡ ግልጽነት የጎደላቸው ናቸው፡፡ የጣምራ አካውንት የተከፈተ አለ " ያሉት ኃላፊው፣ ተከታዩን አካውንት ልከዋል፡።

ድጋፍ ማድረግ የሚሹ በውጪም በውስጥም ያሉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000647478453 ወይም በአማራ ባንክ አካውንት ቁጥር 9900028121157 ድጋፍ እንዲያደርጉ ነው ጥሪ ያቀረቡት።

በመሬት መንሸራተት አደጋው 23 ሰዎች እንደሞቱ፣ 8 ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ 318 የቤት እንስሳት የጉዳቱ ሰለባ እንደሆኑ፣ 1,775 ሄክታር ማሳና 48 ቤቶቾ እንደወደሙ ዞኑ አስረድቷል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#MesiratEthiopia

💵 የኢንቬስትመንት ውል እና ድርድር ምን መምሰል አለበት? 📝

በዚህ ሃሳብ ዙሪያ ለምንሰጠው ስልጠና ይመዝገቡ 👇
📅 አርብ፣ ነሐሴ 24, 2016 ዓ.ም
🕑 ከቀኑ 8:00 - 11:00 ሰዓት
🔗 https://forms.gle/GnvR5rE7DRGXtfaP8

ቀድመው ይመዝገቡ ቦታዎን ያሲዙ!

#መስራት #ስራፈጠራ #MesiratEthiopia #Investment #Entrepreneurship #MesiratTraining
#Tigray

በትግራይ የክረምቱ ሃይለኛ ዝናብ ባስከተለው አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አልፋዋል።

በበርካታ የክልሉ አከባቢዎችም ከአሁን በፊት ታይቶ በማያውቅ መልኩ የመሬት መደርምስ አደጋ እየተከሰተ ነው።

ነሃሴ 17 እና 19/2016 ዓ.ም በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የሓውዜንና ብዘት ወረዳዎች የጣለ ሃይለኛ ዝናብና በጥልቅ ጉድጓድ በተጠራቀመ ውሃ የ7 እና 9 ዓመት እድሜ ህፃናት የሚገኙባቸው 4 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

የሓውዜን ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ህፃናቱ በአከባቢያቸው በሚገኘው በጥልቅ ጉድጓድ በተጠራቀመ የዝናብ ውሃ ሊዋኙ ሲሉ ነው ለህልፈት የተዳረጉት። 

በዞኑ ብዘት ወረዳ ነዋሪ የሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባላት በሃይለኛ ዝናብ ምክንያት ቤታቸው በላያቸው ላይ ፈርሶ የ5 ልጆች አሳዳሪ የሆኑ ባልና ሚስት ወድያውኑ ህይወታቸው አልፏል።

ልጆቻቸው እቤት ስላልነበሩ የሟቾች ቁጥር ሊቀንስ እንደቻለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከወረዳው ያጋኘው መረጃ ያሳያል።

ልጆቹ ወላጅ እናት አባታቸውን አጥተው በፈረሰ ቤት ሜዳ ላይ መውደቃቸው ተገልጿል።

ከአሁን በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች የመሬት መደርመስ አደጋ ተከስቷል።

በአላጀና ሰለዋ ወረዳዎች በሚገኙ አራት የቀበሌ ገበሬ ማህበራት ፣ በእንደርታና ሕንጣሎ ወረዳዋች ፣ በዓዴትና ፀለምቲ ወረዳዎች የመሬት መደርመስ አደጋ መከሰቱ ከአከባቢዎቹ የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ🚨

“ በተለይ እንቅስቃሴያቸውንና ኑራቸውን አፋፍ ሥር ያደረጉ ነዋሪዎች ጥንቃቄ ያድርጉ " - ኮሚሽኑ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 በተለምዶ ሰላም ሰፈር አካባቢ 4 ሜትር ከሚገመት ከፍተኛ ቦታ በተከሰተ የአለት ናዳ 3 ሰዎች መሞታቸውን የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።

አደጋው የደረሰው ዛሬ ነው።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ባደረጉት ጥረት የ8 ሰዎች ሕይወት ማትረፍ ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
- የአደጋው ምንስኤ ምንድን ነው ?
- ይህ አደጋ በከተማዋ ሲከሰት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ?
- ማህበረሰቡ ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ አለበት? የሚሉ ጥያቄዎችን ለኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ አቅርቧል፡፡

አቶ ንጋቱ ምን ምላሽ ሰጡ ?

“ እንዲህ አይነት አደጋዎች በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እያጋጠሙ መሆኑ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ሜትሮሎጅ ኢንስቲትዩትም የመሬት መንሸራተት፣ ጎርፍ አደጋ ሊያጋጥም ስለሚችል ጥንቃቄ ይደረግ የሚል መረጃ ሲያስተላልፍ ነበር፡፡

ያልተጠበቀ ዝናብ ያጋጥማቸዋል የተባሉ ከተሞችን ሲጠቅስም አዲስ አበባም እዛ ውስጥ ተጠቅሳለች፡፡

በእርጥበት ምክንያት ናዳ፣ የአፈር መደርመስ ሊኖር ስለሚችል በተለይ እንቅስቃሴያቸውንና ኑራቸውን አፋፍ ሥር ያደረጉ ነዋሪዎች ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ መፍትሄ ለመስጠት በሚደረገው ጥረትም የመፍትሄው አካል መሆን ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ሰዎችን ከቦታው ማንሳት ሊያስፈልግ ይችላል።

አዲስ አበባ ላይ የአለት ናዳ አደጋ አጋጥሞ አያውቅም፣ አላስታውስም፡፡ በእርግጥ ደረጃቸውን ያልጠበቁ፣ የአደጋ ደህንነት መስፈርት ሳይጠብቁ አፋፍ ላይ የተሰሩ ቤቶች ተንደው የሰው ሕይወት ጠፍቶ ያውቃል።

ጠሮ መስጂድ የሚባለው (አዲስ ከተማ ፍለ ከተማ ውስጥ) ሰባት ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈበት ሁኔታ ነበር ከኮንስትራክሽን ጥራት ጋር በተያያዘ፡፡

ይሄኛው (የአሁኑ የአለት አደጋ) እዛው መሬቱ ጋር ተያይዞ የበቀለው አለት ከዝናብ ብዛት በመሬት መሸርሸር የሚያጋጥም ነው፡፡

የአለት አደጋውን መስንስኤ ማጣራት የሚጠይቅ ነው ግን ከክረምቱ ወቅት ጋር የሚያያዝ ሊሆን ይችላል ብለን እንገምታለን፡፡ አደጋ የደረሰባቸው መኖሪያ ቤቶቹ ከታች ነው ያሉት፤ አለቱ ደግሞ አፋፍ ላይ ነው ያለው፡፡ በግምት ወደ 4 ሜትር ከፍታ አለው፡፡

ብዙ ጊዜ አፋፍ ላይ ተንጠልጥለው ያሉ ቤቶች ላይ የመውደቅ እድልም አለው፡፡ የሰዎቹም የአኗኗር ሁኔታ፣ የቤቱ አቀማመጥና ደረጃ አስተዋጽኦ አድርጓል። ”


#TikvaEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Urgent🚨

በአማራ ክልል፣ በሰሜን ጎንደር ዞን ፣ ጠለምት ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት አልፏል።

በርካቶችም ችግር ላይ ወድቀዋል፤ ተፈናቅለዋል።

ለተፈናቃዮቹ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋል።

ደጋግ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ወረዳው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጥሪ አቅርቧል።

የወረዳው አስተዳደሪ አቶ ጋሻው እንግዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ቃል ፦

“ አካባቢው ከዚህ ቀደም በድርቅ የተጠቃ ነው፡፡ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ለተፈናቀሉት ነዋሪዎች ደግሞ ከ14, 400 በላይ እህል ያስፈልገናል።

የእርዳታ ምግብ ድጋፍ ፤ 480 ድንኳን / ሸራ ፣ እንደ ብረት ድስት፣ ሳፋ አይነት የቤት ቁሳቁሶች በአስቸኳይ የሚያስፈልጉ ናቸው። ”

#TikvahEthiopiaFamyAA

@tikvahethiopia
❤️

ከአሜሪካ ሃገር በመጡ ሐኪሞች የልብ ሕክምና ተልዕኮ (Mission) አገልግሎት እየተሰጠ ነው።

በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ የልብ ማዕከል-ኢትዮጵያ ውስጥ " ሃርት አታክ ኢትዮጵያ ' በተሰኘ በአሜሪካን ሃገር በሚገኝ በዶ/ር ተስፋዬ ተሊላ እና ዶ/ር ኦብሲኔት መርዕድ የተመሰረተ የግብረ ሰናይ ድርጅት የነጻ የልብ ሕክምና ተልዕኮ አገልግሎት ከነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እየሰጠ ነው።

ይህ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀ የሕክምና ተልዕኮ መርሐግብር ነው።

የሕክምና አገልግሎቱ ከማዕከሉ በተጨማሪም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ100 በላይ በልብ ሕመም የሚሰቃዩ ታካሚዎች ተጠቃሚ ለማድረግ ያቀደ ነው።

የሕክምና አገልግሎቱን ለመስጠት ከ17 በላይ የልብ ሕክምና ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የጤና ባለሞያዎች እየተሳተፉ ነው።

ሃርት አታክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኦብሲኔት ፥ " በዚህ ዙር ደረት ሳይከፈት ከሚሰሩ ሕክምናዎች በተጨማሪ የልብ ቀዶ ሕክምና እና የልብ ምት ችግር ላለባቸው ሕሙማን የሚሰጡ ሕክምናዎች ተካተዋል " ብለዋል።

ድርጅቱ ለሕክምና ተልዕኮው ከ1.4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን ለሕክምና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን አሰባስቦ ነው ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ ነው የጠቆሙት።

ወደፊት ተጨማሪ ተልዕኮዎችን እንደሚያካሂድ አመልክተዋል።

የልብ ማዕከል ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኅሩይ ዓሊ ፥ " በዚህ የሕክምና ተልዕኮ ላይ በርካታ ወረፋ በመጠበቅ ላይ የሚገኙ ሕሙማን ተጠቃሚ ናቸው። " ያሉ ሲሆን " ተልዕኮው ስኬታማ እንዲሆን ማዕከሉ ከዝግጅት ጊዜ ጀምሮ አስፈላጊ ሥራዎችን ሲሰራ ነበር ቆይቷል " ነው ያሉት።

#Ethiopia

@tikvahethiopia @thechfe
@heyonlinemarket

•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 37,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 25,000 Birr
•Meta Quest 2, 45,000 Birr
•Meta Quest 3, 73,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket