TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ይመለሳሉ💥

🔴 አርሰናል ሁለተኛውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በቪላ ስታዲዮም ከአስቶን ቪላ ጋር ቅዳሜ ነሐሴ 18 ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት በSS Premier League እና SS Liyu ቻናል በሜዳ ፓኬጅ በቀጥታ ይከታተሉ!

🤔አርሰናል የዓምናውን ሽንፈት መበቀል ይችላል? አርቴታ እምሪይን ማሸነፍ ይችላል?

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ወደ ሜዳ ያሳድጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#SafaricomEthiopia

🤩🎧 ማነው አሪፍ ድምጽ አለኝ የሚለው? እስቲ ቲክቶክ ላይ ፖስት ይደረግና ችሎታ ይታይ! ብዙ የሚታዩት ቪዲዮዎች የገንዘብ ሽልማት እና በታዋቂ አርቲስቶች የመሰልጠን እድል ያስገኛሉ! 

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፡
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳንረሳ
📲የTikTok ደረገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ  እንዝፈን! እንላክ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
#Ethiopia : ነገ በመላ ሀገሪቱ በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ዘመቻ ይካሄዳል ተብሏል።

ለዚህም ዘመቻ በፌዴራል፣ በክልል ፣ በዞን ፣ በወረዳ እንዲሁም በቀበሌ የተለያዩ መዋቅሮች ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል።

የችግኝ ተከላውን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) " አዋቂዎች ከ20 በላይ ፣ ታዳጊወች ከ10 በላይ ችግኝ በመትከል ለሀገር ያለንን ፍቅር፣ ለትውልድ ያለንን ስጦታ በተገቢው ስፍራ እንግለጥ " ሲሉ ጥሪ አቅርበው ነበር።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

“ አዋጅ ተጥሶ ነው ጋዜጠኞቹ እስር ቤት እንዲገቡ የተደረገው ” - ማኀበሩ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኀበር በአዲስ አበባ ከተማ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ስንት ጋዜጠኞች በእስር ላይ ይገኛሉ? ስለታሰሩ ጋዜጠኞች የፍርድ ሂደቱ በአዋጁ መሠረት ምን መሆን ነበረበት/አለበት? ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ የታሰሩ ጋዜጠኞች አሉ? ጋዜጠኝነት ላይ የሚስተዋለውን ጫና ምን ይመስላል? ሲል ማኀበሩን ጠይቋል፡፡

የማኀበሩ ፕሬዚደንት እታገኘሁ መኮንን ምን ምላሽ ሰጡ ?

“ በአዲስ አበባ በእስር ላይ ያገኘናቸው በቃሊቲ ሁለት ሴቶችን ፣ በቂሊንጦ ደግሞ አራት ወንዶችን ነው፡፡ ከታሰሩ ሁለት ዓመት አልፏቸዋል፡፡ ሁለት አመት ከ4 ወራት አካባቢ ሆኗቸዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ ጋዜጠኞች ታስረው እንደሆን አጣርተናል፡፡ ግን ለጊዜው በቂ መረጃም አላገኘንም፡፡ ወደ ፊት የምናየው ይሆናል፡፡

የመገናኛ ብዙኃን አዋጁ፣ ጋዜጠኛ ሚዲያ ላይ በሰራው ሥራ ጥፋተኛ ተብሎ የሚጠየቅ ከሆነ ጉዳዩን ከማረሚያ ቤት ውጭ ሆኖ እንዲከታተል ይፈቅዳል፡፡

ነገር ግን ይሄ አዋጅ ተጥሶ ነው ጋዜጠኞቹ እስር ቤት እንዲገቡ የተደረገው፡፡ ከሁለት አመት በላይ በማረሚያ ቤት እንዲቀመጡ የተደረገው፡፡ ስለዚህ በመጀመሪያ ደረጃም መያዛቸውና መታሰራቸው አግባብ አይደለም፡፡

ያም ከሆነ በኋላ ደግሞ ፍርድ ቤት (ለምሳሌ የጋዜጠኛ የዳዊት በጋሻውን ጉዳይ ብናነሳ በዋስትና እንዲወጣ ከተፈቀደለት በኋላ ነው በድጋሚ በሽብርተኝነት ክስ ስለሚከሰስ ተብሎ ዋስትናው ውድቅ ተደርጎ እዚያው እንዲቆይ የተደገው፡፡)

የሎሌቹም ተመሳሳይ ኬዝ ነው፡፡በሚዲያ ላይ በሰሩት ሥራ በጋዜጠኝነታቸው ተይዘው በኋላ ላይ ሌሎች ክሶች እየቀረቡ ነው፡፡ ለእሱም እካሁን ማስረጃ ሳይቀርብ ነው ፍርድ ቤት እየተመላለሱ ያሉት፡፡

እነርሱም ያነሱት ቅሬታ ይሄው ነው፡፡ ሚዲያ በሚሰራው ሥራ ሲጠየቅ ፅሑፉ ማስረጃው ነውና የሚደበቅ ማስረጃ አይኖርም፡፡ ስለዚህ ጉዳያቸውን ከእስር ቤት ውጭ ሆነው መካታተል ይችሉ ነበር፡፡

ሌላኛው ቅሬታቸው፣ 'ፍርድ ቤት ያለ አግባብ እየተመላለስን ነው፤ በሽብርተኝነት ክስ ተከሰዋል ማስረጃ አቀርባለሁ ብሏል መንግስት ግን እየቀረበ አይደለም በዚህ ምክንያት እየተጉላላን ነው' የሚል ነው፡፡

የእኛም (የማኀበሩ) አቋምም ይሄው ነው፡፡ ይሄ መብት መከበር አለበት። ለጋዜጠኝነት የሚዲያ ነጻነት አለማግኘት፣ የጋዜጠኞች እስር፣ መሰደድ፣ አጠቃላይ የፖለቲካው አሉታዊ ተፅዕኖ ሚዲያው ላይ ትልቅ ጉዳት እያስከተለ ነው።

ነጻ ሚዲያ እንዲኖር፣ ሚዲያው ከፖለቲካ አተያይ ነጻ በሆነ መንገድ እንዲዳይ ነው የምንጠይቀው ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" የሃሳብ ልዩነቱ ወደ ግጭት አያመራም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ዓመታዊው የ2016 ዓ/ም የአሸንዳ በዓል ዛሬ ነሃሴ 16/2016 ዓ/ም በመላ ትግራይ መከበር ጀምሯል።

በዓሉ እስከ ነሃሴ 24/2016 ዓ.ም አንደሚቀጥል የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል።

በሌላ በኩል ፕሬዜዳንት ጌታቸው በ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የተገነባ የ10.2 ኪሎ ሜትር  የአስፋልት መንገድ ሲመርቁ ፤ የአሸንዳ አደባባይ ግንባታ መሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ዳግም የህወሓት ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል የተባሉት ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) በተምቤን በመገኘት የቀለም ፋብሪካ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አኑረዋል።

በመቐለ ትንሹ ስታድዮም በተከናወነው ይፋዊ የአሸንዳ ስነ-ሰርዓት ተገኝተው ፥ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፉት አቶ ጌታቸው ረዳ " የተፈጠረው የሃሳብ ልዩነት ወደ ግጭት አይሸጋገርም "በማለት ታዳሚውን አረጋግተዋል።  

ዓመታዊ የአሸንዳ የሴት ልጃገረዶች በዓል በሽረ-እንዳስላሰ ፣ በአክሱም ፣ በዓድዋ ፣ በዓዲግራት ፣ በተምቤን ፣ በመቐለ ፣ በማይጨውና በሌሎች ከተሞች በድምቀት መከበር ጀምሯል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia  
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : ነገ በመላ ሀገሪቱ በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ዘመቻ ይካሄዳል ተብሏል። ለዚህም ዘመቻ በፌዴራል፣ በክልል ፣ በዞን ፣ በወረዳ እንዲሁም በቀበሌ የተለያዩ መዋቅሮች ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል። የችግኝ ተከላውን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) " አዋቂዎች ከ20 በላይ ፣ ታዳጊወች ከ10 በላይ ችግኝ በመትከል ለሀገር ያለንን ፍቅር፣…
ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የችግኝ ተከላ ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ከተማ ተገኝተው ችግኝ ተክለዋል።

" በዛሬው ሁነት መጨረሻ በመላው ሀገራችን ባለፉት አምስት አመታት የተከልናቸው ችግኞች ወደ 40 ቢሊዮን ይደርሳሉ። " ብለዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ " ባለፈው አመት ከተተከሉት ችግኞች 50 ከመቶው በምግብ ዋስትና፣ አፈር ጥበቃ እና የመሬት መራቆት ላይ አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ የተተከሉ ነበሩ። " ሲሉ ገልጸዋል።

በቀጣይም እንደ አባይ ተፋሰስ ባሉ አካባቢዋች ችግኞችን በመትከል የውሃ ጥበቃ ሥራን ልንደግፍ ይገባል " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#አቶለማበቀለ👏

አቶ ለማ በቀለ አለሙ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በሴኪዩሪቲ ክፍል ውስጥ ነው የሚሰሩት።

በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና ሲቀጠሩ በገቡት ቃል መሰረት አየር መንገዱ የሚመራበትን መርህና ሥነ ምግባር እንዲሁም ሙያዊ ታማኝነታቸውን በብቃት በመወጣት ማስመስከራቸውን አየር መንገዱ ገልጿል።

አቶ ለማ በሥራ ገበታቸው ላይ በነበሩበት ወቅት አንድ መንገደኛ ረስተዉ የሄዱትን የእጅ ቦርሳ ውስጡ ከነበረው 71 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ጋር ምንም ሳያጎድሉ በሙሉ ለሚመለከተው የአየር መንገድ ቢሮ ያስረከቡ ሲሆን፤ አየር መንገዱም አስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ በኋላ ንብረቱ ለባለቤቱ እንዲመለስ ተደርጓል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" አገሮች የአስተናጋጅ አገርን ሕግ አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ይጠበቃል " - ገንዘብ ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ከአሁን በኃባ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ብቻ እንዲያስገቡ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ገንዘብ ሚኒስቴር ፥ የዲፕሎማሲና የቆንስላ አገልግሎት የሚሰጡ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት፣ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቧቸው ተሽከርካራች የኤሌክትሪክ ብቻ መሆን እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመታገል በምታደርገው ቁርጠኝነት በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ማስገባት የተከለከለ እንደሆነ ነው ሚኒስቴሩ ያሳውቀው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ምን አሉ ?

" ይህንን ውሳኔ በርካታ የአውሮፓ አገሮች የሚደግፉት ሐሳብ ነው።

አገሮች የአስተናጋጅ አገርን ሕግ አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ይጠበቃል።

ውሳኔው የዲፕሎማሲ ሥራን ለመሥራት የሚያውክና የአገሮችን ሉዓላዊነትን የሚጥስ ባለመሆኑ፣ እንደ እነዚህ ዓይነት ሕጎች ሲወጡ ዲፕሎማቶች ያንን ሕግ አክብረው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ "

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ 38 የገቢ ንግድ ምርቶች ዕግድ እንዲነሳላቸው ባሳለፈው ውሳኔ ቢያሳውቅም የገንዘብ ሚኒስቴር ግን በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ላይ ዕግዱ እንደማይነሳ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ #EthiopianReporter

@tikvahethiopia
🔈#የመምህራንድምጽ

“ ምንም እንቅስቃሴ ያላደረጉ አካቢዎች አሉ፡፡ ግን በአንዴ 700 ሺሕ መምህር አይዳረስም ” - ማኀበሩ

የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን የቤትና የደመወዝ ችግር እየተፈታላቸው እንዳልሆነ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ አቅርበዋል፡፡

መምህራኑ የገለጹት፣ ቤት የተሰጣቸው መምህራን ቢኖሩም ያልተሰጣቸውም እንዳሉ፣ ይህ ደግሞ በተለይ ከዝቅተኛ ደመወዝ ጋር ተዳብሎ ኑሮውን በእጅጉ እንዳከበደባቸው ነው፡፡

ቅሬታውን ያቀረቡት በተለይ በሶማሌ እና በአፋር ክልሎ የሚገኙ መምህራን፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር የመኖሪያ ቤት ችግር እንዲቀረፍ፣ ደመወዝ ማሻሻያ እንዲደረግ የራሱን አስተዋጽዖ እንዲያደርግ ጠይቃዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመምህራኑን ቅሬታ ይዞ የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር (ኢመማ)ን ማብራሪያ ጠይቋል፡፡

የማኀበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አበበ ምን አሉ ?

“ ሶማሌ ክልል አካባቢ ላይ ምንም አይነት መሬት አልሰጡም፡፡ ምንም እንቅስቃሴ ያላደረጉ አካቢዎች አሉ፡፡ በሶማሌና አፋር ክልሎች፡፡ ግን በአንዴ 700 ሺሕ መምህር አይዳረስም፡፡

ድሬዳዋ በጣም ብዙ መምህራን ተሰጥተዋል፡፡ ሀረሪ ላይ በዚህ ዓመት ብቻ ለ34 መምህራን አንድ ሙሉ ኮንዶሚኒየም ተሰጥቷል፡፡ የአጠቃለይ ትምህርት ላይ ያለው የመኖሪያ ቤት ጉዳይ እተሰጠ ነው፡፡ አልተቋረጠም፡፡

ደብረ ብርሃን ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ኦሮሚያ ክልል ለምሳሌ በትምህርት
ቤት ጭምር መኖሪያ ቤት እየተሰራ ነው ለመምህራን፡፡

አዲስ አበባ ላይ በዚህ አመት ብቻ ከ400 በላይ ቤቶች ተሰጥተዋል፡፡ አሁን ደግሞ ቦታ ለመስጠት ተደራጁ ተብሎ በመደራጀት ላይ ናቸው፡፡

ለእያንዳንዱ ለ700 ሺሕ መምህር በአንድ ጊዜ መስጠት አይቻልም፡፡ ሁላችንም በአንዴ ቸኩለን የቤት ባለቤት እንሁን ቢባል አይቻልም፡፡ ችግሮች አሉ፡፡ በሂደት የአባሎቻችን ጥያቄ እየተመለሰ መሄድ አለበት ትክክል ነው፡፡

ከደመወዝ ጋር በተያያዘ የሥራ ክብደት ምዘና ተሰጥቷል፡፡

ደፍሬ ነው የምናገረው በሥራ ክብደት ምዘናው መምህራን የተቀመጡበት ቦታ ትክክለኛ ቦታ ላይ ነው፡፡ ኢንፈሌሽኑ ኢንፈሌትድ ሆኗል፡፡

እሱን ጥያቄ ለጠ/ሚ አቢይ አህመድ (ዶ/ር) አንስተናል፡፡ ከደመወዝ ጋር በአጠቃለይ የተያያዘው ምናልባት እንደ መንግስት አሁን ከከረንሲ ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚጨመር ነገር አለ ሚባል ነገር አለ፡፡ አጠቃላይ ሆነውን ነገር የምናየው ነው የሚሆነው፡፡

የዩኒቨርሲቲ መምህራን ቅሬታ ግን አልተፈታም፡፡

የእነርሱ በተለዬ መንገድ መፈታት ነበረበት እየተፈታ አይደለም፡፡

ለጠ/ሚ አቢይ አህመድ (ዶ/ር)ም አንስተናል፡፡ አሁንም በሂደት ላይ ነው፡፡ ዛሬ ተጠይቆ ነገ መልስ ይገኛል የሚል እምነት የለንም እናም የሂደት ውጤት ነው። ”

የማኀበሩ ፕሬዚዳን ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፦

“ ስታክ አድጎ የነበረው የዩኒቨርሲቲዎች እንጂ 1ኛና 2ኛ ደረጃ ላይ ችግር የለም፡፡ ግን አንዳንድ ክልሎች አካባቢዎች የመሬት አቅርቦት ችግርም አለባቸው፡፡ ግን ያልሄዱባቸው ደግሞ እንዳለ ሪፖርት አለ፡፡

አይሆናችሁም የሚል ሳይሆን ከቢሮክራሲ ጋር የሚያያዝ  ነገር ነው ችግሩ፡፡ የእኛም አመራር በቅርበት ክትትል አድረጎ ከሚመለከታቸው ጋር ሆኖ ማስፈጸም፣ መምህራንም በማኀበር መደራጀት አለባቸው፡፡ ያልተሟሉ ነገሮች ካሉ እነርሱን ማሟላት የሚያፈልግ ይመስለኛል። ” የሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
Lecturers Claims and questions -.pdf
1.3 MB
🔈 #የመምህራንድምጽ

የዩኒቨርስቲ መምህራን ጉዳይ በጣም አሳሳቢ እንደሆነ መምህራኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ መልዕክት የላከ መምህር ፥ " የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ሆነንም መሆን የፈለግነውን ሆነናል ነገር ግን እንኳ ቤተሰብ ልናስተዳድር እራሳችንን እንኳ መመገብ አልቻንም ልጅ ወልድን እንዳናሳድግ ሆነናል " ብሏል።

" የከፍተኛ ትምህርት መምህራን ሆነን ጎዳና ልንወጣ ነው " ያሉት መምህሩ " ምንም ጥርጥር የለውም የምሠማንም የለም። ድምጻችን ግን ይሰማ " ብለዋል።

መምህራንና የቴክኒክ ረዳቶች ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተዳምሮ የሚከፈላቸው ክፍያ አይደለም ህይወትን ለመቀየር ከወር ወር ለመድረስ ፈተና እንደሆነባቸው አመልክተዋል።

የዩኒቨርሲቲ መምህራን የሚጠይቁት ምንድነው ? ከላይ በፋይል ተይይዟል።

@tikvahethiopia