TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.5K photos
1.59K videos
216 files
4.34K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈 #የመምህራንድምጽ

" መምህራን እየተራቡ ስለትምህርት ጥራት ማዉራት አግባብ አይደለም " - የደቡብ ኦሞ ዞን መምህራን

" በዚህ ደረጃ ክፍያ ይዘገያል ብለን ባናስብም ችግሩ ካለ በቅርብ ይፈታል " - የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ

ከሰሞኑ በተደጋጋሚ በደረሰን የቅሬታ መልእክት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል የደቡብ ኦሞ ዞን መምህራን ላለፉት ሁለት ወራት ደሞዝ እንዳልተከፈላቸዉ በመግለጽ በተለያዩ ፕሮግራሞች ውስጥ መሳተፍ እንዳልቻሉ ነግረዉናል።

መምህራኑ እንደሚሉት አሁን ላይ ከፊሉ በመንግስት አቅም ማሻሻያ ፕሮግራሞች ግማሹ ደግሞ በራሱ ፍላጎት ወደተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ቢያቀናም ደሞዝ አለመለቀቁን ተከትሎ ግን ችግር ላይ ወድቀዋል።

አሁን ላይ በገቡባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ አላማቸዉን ካለማሳካታቸዉ ባለፈ ጥለዋቸዉ የመጡ ቤተሰቦቻቼዉ ረሀብ ላይ መዉደቃቸዉን ተከትሎ የሄዱበትን የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች ጥለዉ ለቀን ስራ መዳረጋቸዉን ይገልጻሉ።

ከዚህ በተጨማሪ በትራንስፖርት ችግር ምክኒያት ብዙ መምህራን በሚያስተምርበት አካባቢ ቢቀሩም በእንቅርት ላይ እንዲሉ ባሉበት አካባቢም የወባ ወረሽኝ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል።

ችግሩን የመንግስት አካላት ያዉቁታል የሚሉት የጎሪጌሻ የሜኒት ማጅና ቱም የጎልዲያና ሻሻ እንዲሁም የጋቺት እና ሱርማ ወረዳ  ቅሬታ አቅራቢዎች " መምህራን እየተራቡ ስለትምህርት ጥራት ማዉራት አግባብ አይደለም " ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ ከቀናት በፊት ያነጋገርናቸዉ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊዉ አቶ  በበኩላቸዉ በዚህ ደረጃ ክፍያ ይዘገያል ብለን ባናስብም ችግሩ ካለ በቅርብ ይፈታል ብለዋል።

ሀላፊዉ አክለዉም ምናልባትም ችግሩ የበጀት ከሆነ አሁን ላይ በየወረዳዉ ግብር እየተሰበሰበ በመሆኑ በተቻለ ፍጥነት ችግሩ  ይፈታል በማለት የደሞዝ ችግሮ በቅርቡ እንደሚፈታ ገልጸዉልናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
263😭100👏31😢19😡15🙏10🥰9🤔5🕊4
#Ethiopia

ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ዕቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትን በተመለከተ የገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሽንና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ሰርኩላር አስተላልፏል።

በዚህም ሰርኩላር ፥ መንግሥት በቅርቡ ተግባራዊ ባደረገው የተሟላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ምንዛሬ በገበያው አማካኝነት እንዲወስን ማድረጉ እና ይኸው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተግባራዊ መደረጉን አስታውሷል።

ማሻሻያው የገቢ ንግዱን በይበልጥ እንዲያሳልጥ ወደ አገር እንዳይገቡ በሕግ ክልከላ ከተደረገባቸው ዕቃዎች፣ የነዳጅ አውቶሞቢሎች እና ከፀጥታና ከደህንነት ዕቃዎች ውጪ ሌሎች ዕቃዎች ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ወደ አገር እንዲገቡ በመንግሥት የተወሰነ መሆኑና ይኸው ተግባራዊ እንዲደረግ አሳስቧል።

#MinistryofFinance

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
579👏139🙏55😭48😡44😱26😢21🥰19🕊16🤔13
TIKVAH-ETHIOPIA
ትግራይን ዳግም ወደ ጦርነት የሚያስገባ ተጨባጭ ስጋት አለ ? " ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው። ወደ ጦርነት የሚያስገባ ምንም ነገር የለም " - አቶ አማኑኤል አሰፋ በሊቀ - መንበሩ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የ14ኛው የህወሓት ጉባኤ ቃል አቀባይ አማኑኤል አሰፋ ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ጦርነት የሚያስገባ ነገር የለም ብለዋል። አቶ አማኑኤል ፥ " በአንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ…
#TPLF

በሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ አቶ ጌታቸው ረዳን ከምክትል ሊቀመንበርነት አነሳ።

ዶ/ር ደብረጽዮን በድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ተነግሯል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

ሌሎች የስራ አስፈጻሚና የማእከላይ ኮሚቴ ሆነው የተመረጡ የድርጅቱ አባላት ከላይ ስማቸው ተያይዟል።

ምርጫ ቦርድ ከጉባኤው ቀደም ብሎ የቦርዱን አሰራር ያልተከተለ ጠቅላላ ጉባኤ እና በጉባኤው የሚተላለፉ ማንኛውም ውሳኔዎች ተቀባይነት እንደማይኖረው አሳውቆ ነበር።

@tikvahethiopia
🤔1.68K👏391330😡280🕊151🙏82😢70😭68😱50🥰38
Greetings. Here’s another opportunity to learn about the incredible fully funded entrepreneurship program from Jasiri, designed to help you turn your idea into a successful venture.

Join us on Wednesday, August 21st, at 6 PM EAT. Feel free to share this information and invite a friend or two. You can find the registration link below.

https://us02web.zoom.us/meeting/register/tZ0vf-CopjwvE9Eeu1517JJ48kcLAra36Qp5#/registration

Jasiri Recruitment Team.
jasiri.org
58😱4👏3🥰2😢1😭1
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF በሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ አቶ ጌታቸው ረዳን ከምክትል ሊቀመንበርነት አነሳ። ዶ/ር ደብረጽዮን በድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ተነግሯል። በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊመንበር ሆነው ተመርጠዋል። ሌሎች የስራ አስፈጻሚና የማእከላይ ኮሚቴ ሆነው የተመረጡ የድርጅቱ አባላት ከላይ ስማቸው ተያይዟል። ምርጫ ቦርድ ከጉባኤው ቀደም…
#TPLF

በሊቀ-መንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በተመራውና ለ7 ቀናት በቆየው የህወሓት 14ኛው ጉባኤ አዳዲስ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ተመርጠዋል።

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር እና ጉባኤውን ሲቃወሙ የቆዩትን አቶ ተኽለብርሃን ኣርኣያ ተነስተው አቶ ገብረ ካሕሳይ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

አሁን ከሊቀመንበር ቦታቸው ተነስተው በአቶ ገብረ የተተኩት አቶ ተኽለብርሃን ይመሩት የነበረው የቁጥጥር ኮሚሽን ፤ የቁጥጥር ኮሚሽን ፥ " ጤናማ ያልሆነ ሂደት ውጤታማና መልካም ጉባኤ መፍጠር ስለማይችል የሚያስከትለው አደጋ የከፋ ነው " በማለት ከጉባኤው ራሱን ማግለሉን ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፥ በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ ፤ በጉባኤው ላይ ያልተሳተፉ አባላትን አግዷል።

" ጉባኤው እንዳይካሄድ እንቅፋት ፈጥሯል " ያለውን ቡድን ነው ያገደው።

ያታገዱት አባላት ጥያቄቸውን በጹሁፍ የሚያቀርቡ ከሆነ ወደ አባልነታቸው ሊመለሱ ይችላሉ ብሏል።

ቀደም ብሎ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ያሉበት 14 የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጉባኤውን እንደማይሳተፉ ማሳወቃቸው ፤ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላትም ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
🤔196137😡42👏40🕊35😭12🥰6😱5🙏5😢4
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የአርሶአደሮችድምጽ ° " ' እኛ ያቀረብነውን ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ አትወስዱም ' በመባላችን የእርሻ ወቅት እንዳያልፍብን እስከ 8 ሺህ ብር ማዳበሪያ ለመግዛት ተገደናል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ከተማና አካባቢው አርሶአደሮች ° " ያቀረብነውን ምርጥ ዘር ካልወሰዳችሁ ብሎ ያስገደደ የለም ማዳበሪያ ብቻ የሚፈልግ መውሰድ ይችላል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ…
🔈 #የአርሶአደሮችድምጽ

ሲዳማ !

" የማዳበሪያ ችግር የለም ተብሎ በሚዲያ ቢነገርም በቂ ማዳበሪያ እየደረሰን አይደለም " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች

ከሰሞኑ " ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ አይሰጣችሁም ተባልን " ያሉ የሀዋሳ ዙሪያ አርሶ አደሮች ቅሬታ ማቅረባቸዉን ዘግበን ነበር።

በወቅቱ  የማዳበሪያ ችግር እንደሌለና ወደግብርና ቢሮ በመምጣት መዉሰድ እንደሚቻል ከምርጥ ዘር ጋር በተያያዘ አርሶአደሩን የሚጠቅም አካሄድ መሆኑን ይሁንና ገበሬዉ የራሱ ዘር ካለዉ እንደማይገደደ ተገልጾም ነበር።

ይሁንና ከመረጃዉ በኋላ " የማዳበሪያ ችግር የለም " ተብሎ በሚዲያ ምላሽ ከመሰጠቱ በላይ በስብሰባ ወቅት " መጋዝናችን ሙሉ ነዉ " ብንባልም በአግባቡ እየተሰጠን አይደለም ሲሉ በድጋሜ የአካባቢዉ አርሶአደሮች ቅሬታ አቅርበዉልናል።

" አሁን ላይ የዘር ወቅት እያለፈ በመሆኑ ከፍተኛ ስጋት ዉስጥ ገብተናል " የሚሉት አርሶ አደሮቹ " አራትና አምስት  ኩንታል ለሚያስፈልገዉ አምስት ሄክታር የለሰለሰ ማሳ አንድ ኩንታል ብቻ ስለምን እንደሚሰጠን አይገባንም " በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

" ማዳበሪያዉ በቂ አለመሆኑን የአካባቢዉ የግብርና ባለሙያዎች ያውቃሉ። እንደኛ ከማዘን ዉጭ መፍትሄ መስጠት አልቻሉም " ሲሉ ገልጸዉ ጉዳዩ በአመራሩ እጅ መያዙን አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፥ " ቀኑን ሙሉ ስራ በመፍታት መጋዝን በር ላይ የሚዉለዉ አርሶ አደር ሀያ ሰላሳ ሰዎች ከተስተናገዱ በኋላ ወደቤታችሁ ሂዱ ይባላል በማለት መጋዝኑን የሞላዉ ማዳበሪያ ለማን ነዉ ? " በማለት ጠይቀዋል።

ከሳምንት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ " የማዳበሪያ ችግር የለም ከአካባቢዉ አርሶ አደር ጋርም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል " ያሉት የወረዳዉ አስተዳዳሪ  " መሬቱን ያዘጋጀ ገበሬ የፈለገዉን ያክል ማዳበሪያ መዉስድ ይችላል " በማለት አንዳች ቅሬታ ያለበት አርሶ አደር ካለ ሊያናግረን ይችላል ማለታቸዉ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭26985😱13🙏12👏11🤔11😡10🕊9🥰5😢5
#ደመወዝ

" ለግል ድርጅቶች ሠራተኞችም የደመወዝ ማስተካከያ የሚደረግበት አቅጣጫ እንዲሰጥ ለመንግስት ጥያቄ ቀርቧል " - ኢሠማኮ

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መንግሥት ይፋ ያደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ተከትሎ ለመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ ይደረጋል በተባለው ልክ፣ ለግል ድርጅቶች ሠራተኞችም ማስተካከያ የሚደረግበት አቅጣጫ እንዲሰጥ ጥያቄ አቅርቧል።

የኢሠማኮ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው አህመድ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፤  " በመንግሥት በጀት ለሚተዳደሩት የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ እንደሚደረግ ቢገለጽም፣ የግል ድርጅቶችና ተቋማት በራሳቸው በጀትና ትርፍ የሚንቀሳቀሱ በመሆኑናቸው፣ በትርፋቸው ላይ ተመሥርተው ለሠራተኛ የደመወዝ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ከመንግሥት አቅጣጫ እየተጠበቀ ነው " ብለዋል።

" የሠራተኞችና የደመወዝ ዝቅተኛው ወለል እንዲወጣ እየወተወትን ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

የመንግሥት እና የግል ሠራተኞች አንዱ የተሻለ አንዱ የወደቀ የሚባል ክፍያ ሊኖር አይገባም ሲሉ አክለዋል።

" መንግሥት ይህን ጉዳይ ሊዘነጋው አይችልም የሚል እምነት ቢኖረንም፣ መሰል አገራዊ አጋጣሚዎችና ቀውሶች በሚኖሩበት ጊዜ ባለሀብቶችንና ተቋማትን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች በማድረግና ውይይቶች በማካሄድ አቅጣጫዎች ሊሰጡበት ይገባል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ለአገርም አይጠቅምም፣ የኢንዱስትሪ ሰላም አይኖርም፣ ሠራተኛውም ተረጋግቶ ሥራውን ማከናወን አይችልም " ብለዋል።

አቶ አያሌው፣ " ጉዳዩ እጅግ በጣም አሳሳቢ ስለሆነ መንግሥት አቅጣጫ የማይሰጥበት ከሆነ ኢሠማኮ ጥያቄውን በጽሑፍ ለመንግሥት ያቀርባል " በማለት አስረድተዋል፡፡

" ሠራተኛው በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ምክንያት በልቶ ማደር አልቻለም፣ የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻለም፣ ይህን ማንም ያውቀዋል ሚስጥር አይደለም፣ አሠሪዎቹ ለሚያሠሯቸው ዜጎች ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ መክፈል አለባቸው " ብለዋል፡፡

የሠራተኛ መብት መከበር እንዳለበት " የሚያረጋግጥ ወጥ የሆነ ሕግ ያስፈልጋል " ያሉት አቶ አያሌው፣ " የሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልና ሌሎች የሠራተኞች መብቶችና ጥቅማ ጥቅሞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን መንግሥት ለምን እንዳዘገያቸው አልገባኝም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ጉዳይ ላይ አሁንም መንግሥት የዘነጋው ይመስላል " ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ኢሠማኮ ተጨማሪ ጥያቄ ሊያቀርብ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

አክለው ፥ ከመንግሥት ተቋማት በተሻለ የሚያተርፉት የግል ተቋማት፣ ከመንግሥት የደመወዝ ጭማሪ ጋር እኩል ላለመጨመር ትልቁ ችግር የአስተሳሰብ ጉዳይ እንጂ፣ የገንዘብ እጥረት አይደለም በማለት ለዜጎች ማዘን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ለራስ ብቻ ከማግበስበስ ዕሳቤ በመውጣት ምርታማ ሠራተኛን ለማፍራት፣ አሁን  ተመጣጣኝ የደመወዝ ጭማሪ ማድረግ ብዙ ነው የሚያሰኝ አለመሆኑን ገልጸዋል።

#EthiopianReporter #Salary #Ethiopia

@tikvahethiopia
🙏2.35K504👏228🥰115🕊64🤔52😭51😡51😱45😢42
#አቢሲንያ_ባንክ

ካርድዎን POS ላይ በማስጠጋት ጊዜ ሳይፈጁ ይክፈሉ።
አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth

#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ዘህራ #የሴቶችቁጠባ #አቢሲንያአሚን
91🙏9🥰6😭5😢4👏2🤔2
🛠 የንግድ ሃሳብዎን ወደ ተግባር ለመቀየር እና ስኬታማ ለማድረግ ዝግጁ ነዎት? 🚀

የመስራት ስራ ፈጠራ ፕሮግራም ያዘጋጀውን ልዩ የኦንላይን የንግድ ወርክሾፕ ይቀላቀሉ!

📅 ቀን፡ ነሃሴ 17, 2016 ዓ.ም
🕑 ሰዓት: ከቀኑ 8:00 - 10:30

አሁኑኑ በ https://forms.gle/rmE3eg82aAAvnxoM9 ይመዝገቡ!

#MesiratEthiopia #Entrepreneurship #BusinessGrowth #GigEconomy #Workshops #Mesirat
33😱8😡3🤔1
ኢትዮ ቴሌኮም ከቪዛ ጋር በመተባበር በሀገራችን የመጀመሪያውን የዋሌት ቨርችዋል ቪዛ ካርድ እንዲሁም ሀዋላን በእጅጉ የሚያዘምኑ ቪዛ ዳይሬክት እና ቴሌብር ሬሚት የተሰኙ አገልግሎቶችን በይፋ አስጀምሯል፡፡

የቪዛ ዳይሬክት አገልግሎት ከ190 በላይ ሀገሮች የሚኖሩ የቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች በሀገራችን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የቴሌብር ቨርችዋል ቪዛ ካርድ ቁጥር በመጠቀም ገንዘብ ወደ ሀገርቤት በምቾት፣ በቅልጥፍና እና በቅናሽ መላክ ያስችላቸዋል፡፡

ደንበኞች በቪዛ ዳይሬክት አገልግሎት ገንዘብ ለመቀበል በቅድሚያ የዘመነውን ቴሌብር ሱፐርአፕ በመጫን ከዚያም ለአገልግሎቱ በመመዝገብ ባለ16 አሀዝ የቨርችዋል ቪዛ ካርድ ቁጥር ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የቴሌብር ሬሚት አገልግሎት ደግሞ ተጠቃሚዎች ከአሜሪካ፣ ካናዳ፣ እስራኤል፣ ሳኡዲአረቢያ፣ ዩናይትድ አረብኢምሬትስ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጣሊያን እና ስዊድን ለዚሁ አገልግሎት በኩባንያችን የበለጸገውን ዘመናዊ የቴሌብር ሬሚት መተግበሪያ በመጫን ገንዘብ ለቴሌብር ደንበኞች በቀጥታ መላክ ይችላሉ፡፡ 

ይህን ከቪዛ ኩባንያ ጋር የተፈጸመው ስትራቴጂያዊ የአጋርነት ስምምነት በማሳደግ በቀጣይ ከ47.55 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑት የቴሌብር ደንበኞቻችን ድንበር ተሻጋሪ አስተማማኝ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ጥሬ ገንዘብ የማይጠቀም ዘመናዊ ማህበረሰብ (cashless society) ለመገንባት የሚደረገውን ጉዞ የሚያፋጥን ነው።

የዘመነውን ቴሌብር ሱፐርአፕ በመጫን “VISA” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም ለቨርቿል ቪዛ ካርድ እንዲያመለክቱ በደስታ እንጋብዝዎታለን!

🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕን ከ onelink.to/fpgu4m ይጫኑ!

ለተጨማሪ፡ https://bit.ly/4fQbrFC ይጠቀሙ፡፡
310👏75😡26🙏23😢17🤔12🥰7😱2