TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Infinix_Note40_Pro_Plus

የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G አጅግ ፈጣን እና በአለማችን የመጨረሻው የኔትወርክ ቴክኖሎጂ የሆነውን የ5G ኔትወርክ ማስጠቀም ሲያስችል በተለይም ከፍተኛ አቅም የሚፈልጉ ስራዎችን በስልካቸው በሚከውኑ ሰዎች ተመራጭ የሆነውን የ Mediatek Dimesnty 7020 ፕሮሰሰርን የተገጠመለት ፈጣን ስልክ ነው፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
TIKVAH-ETHIOPIA
የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው ፦ " የመንግስት ኃላፊዎች በተለያየ ጊዜያት በተደጋጋሚ ስለ ሀገራዊ ምክክር እና ስለ ሽግግር ፍትህ ሲያነሱ ይደመጣል። ነገር ግን ከሀገራዊ ምክክር እና ከሽግግር ፍትህ በፊት መቅደም ያለባቸው ነገሮች አሉ። ከነዚህ ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው የእምነት ግንባታ ነው። መንግስት በህዝብ…
" መኖሪያ ቤታቸው የገቡት ትላንት ከምሽቱ 4 ሰዓት ገደማ ነው " - ቤተሰቦች

ከ6 ወራት በፊት " ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታፍነው " መወሰዳቸው የተነገረላቸው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ሀብታሙ በላይነህ ትላንት ተይዘው ከነበረበት መለቀቃቸውን ቤተሰቦቻቸውን ዋቢ በማድረግ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

የአብን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ሀብታሙ፤ ደብዛቸው የጠፋው ከየካቲት 22፤ 2016 ጀምሮ ነበር።

በዕለቱ በአዲስ አበባ 4 ኪሎ አካባቢ " ሰው ላግኝ ብሎ ከቤት እንደወጣ አልተመለሰም ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ለ6 ወራት ያህል ያለበት ሳይታወቅ ቆይተዋል " ሲሉ አንድ የቅርብ ምንጭ  አስረድተዋል።

የአማራ ክልል የምክር ቤት አባሉ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አያት አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው የገቡት ትላንት ከምሽቱ 4 ሰዓት ገደማ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

አቶ ሀብታሙ በላይ እስካሁን ድረስ የት እንደቆዩና የነበሩበትን ሁኔታ በተመለከተ ግን በዚህ ጊዜ መናገር እንደማይፈልጉ ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የአቶ ሀብታሙን መለቀቅ አረጋግጣል።

የቆዩበት እና ሌሎችንም ዝርዝር ጉዳዮች በተመለከተ " ገና ቃላቸውን እንዳልሰጡ " አስረድቷል።

ሰኔ መጨረሻ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ምንም እንኳን ምላሽ ባይሰጥበትም የአቶ ሀብታሙ ጉዳይ በአብን የምክር ቤት ተመራጭ አቶ አበባው ደሳለው ተነስቶ እንደነበር ይታወሳል።  #EthiopiaInsider

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ከእዚህ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ የ '' ቤቲንግ '' ወይም የስፖርት ውርርድ ቤት አይኖርም ሲል የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ማሳወቁን ሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ዘግቧል።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ ፤ " በተጠናቀቀው 2016 የበጀት ዓመት በከተማዋ የሚገኙ 4,118 የቤቲንግ (የስፖርት ውርርድ) ቤቶችን ዘግተናል፤ ከዚህ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ የውርርድ ወይም ቁማር ቤት አይኖርም " ብለዋል፡፡

" የቤቲንግ ቁማር ስራን በዚህ ከተማ ላይ ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም " አስረድተዋል፡፡

" ልጆቻችን አዕምሯቸው በቁማር ምክንያት እየተበላሸ ነው ፤ እቃም ጭምር ከቤት እየተሰረቀ እየተሸጠ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ለትዳር ፊቺ ጭምር መነሻ ሆኗል እየተባለ ቅሬታ ሲነሳ ነበር፤ ምላሽ ተሰጥቶታል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ማሸጉ ግብ አይደለም፤ በዘርፉ ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ ሌላ ስራ ቀይረው እንዲሰሩ ትዕዛዝ ተላልፏል " ብለዋል።

አቶ ሚደቅሳ ከበደ ፥ " ቤት አከራይተው የነበሩ አከራዬችም ለሌላ ንግድ ወይም አገልግሎት በማከራየት አንዲጠቀሙ ተደርጓል " ሲሉ መናገራቸውን ሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የሚሰጠውን አስተያየት ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ' ህወሓት ' ውስጥ እየሆነ ያለው ምንድነው ? ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከትግራዩ ጦርነት በፊት እንደ ህጋዊ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ስር ተመዝግቦ ይንቀሳቀስ ነበር። ነገር ግን  ቦርዱ ፓርቲው " ኃይልን መሰረተ ያደረገ የአመጽ ተግባር ላይ ተሰማርቷል " በሚል ሰርዞታል። የተወካዮች ምክር ቤትም ፓርቲውን " ሽብርተኛ ድርጅት " ሲልም ፈርጆት ነበር። ደም አፋሳሹና አስከፊው…
#TPLF

በአመራሮች መካከል ከፍተኛ ክፍፍል የፈጠረውና በምርጫ ቦርድ እውቅና የተነፈገው የህወሓት ጉባኤ ዛሬ በዝግ ሲመክር ውሏል።

በዛሬ ውሎው የአዘጋጅ ኮሚቴ ሪፓርት አቅርቦ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በሙሉ ድምፅ ማፀደቁ ተሰምቷል። 

ከመላው ትግራይ በድምፅ መሳተፍ ከሚገባቸው 950 ጉባኤተኞች 785 ማለትም 83% ተገኝተዋል ተብሏል።

የተለያዩ ወረዳዎች በድምጽ የሚሳተፍ ሰው እንዳላኩ ተሰምቷል።

ከዛሬው የዝግ ስብሰባ በኃላ ድርጅቱ ባሰራጨው መረጃ ፤ " በጉባኤው አንሳተፍም ያሉ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ስህተታቸው በማረም ወደ ጉባኤው በመግባት ሃሳቦች ለማቅረብ ዝግጁ ከሆኑ በሩ ክፍት ነው " ብሏል።

የህወሓት የ14ኛው ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋይ ገ/እግዚአብሔር  " በኮሚቴው ስራ ውስጥ የሚታዩ ጣልቃ የመግባት ፣ ከፕሮግራም ውጪ ስብሰባ መጥራት፣ ውሳኔዎችን መጠምዘዝ የመሳሳሉ ተግባራት እንዲታረሙ ለመስራት ብሞክርም  አልተሳካም " በማለት ደብዳቤ ፅፈው ከሃላፊነት ራሳቸው ስለማግለላቸው  መዘገባችን ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በዛሬው ዕለት የወጡ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ጉባኤውን የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ቁጥር ጨምሯል ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል የዚን መረጃ ትክክለኝት ለማጣራት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF በአመራሮች መካከል ከፍተኛ ክፍፍል የፈጠረውና በምርጫ ቦርድ እውቅና የተነፈገው የህወሓት ጉባኤ ዛሬ በዝግ ሲመክር ውሏል። በዛሬ ውሎው የአዘጋጅ ኮሚቴ ሪፓርት አቅርቦ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በሙሉ ድምፅ ማፀደቁ ተሰምቷል።  ከመላው ትግራይ በድምፅ መሳተፍ ከሚገባቸው 950 ጉባኤተኞች 785 ማለትም 83% ተገኝተዋል ተብሏል። የተለያዩ ወረዳዎች በድምጽ የሚሳተፍ ሰው እንዳላኩ ተሰምቷል። ከዛሬው…
#TPLF

ከህወሓት ከፍተኛ አመራር አንዱ የሆኑት የማይጨው ከተማ ከንቲባ አቶ የማነ ንጉስ ለዶቼ ቨለ በሰጡት ቃል ፤ " ጉባኤው የተወሰነ ቡድን ለማጥቃት በችኮላ የተጠራ ነው " ብለዋል።

በዚህም እሳቸው ጨምሮ በርካቶች ተቃውሞዋቸውን በመግለፅ ከመድረኩ መቅረታቸውን አመልክተዋል።

የህወሓት ማእከላዊ ቁጥጥር ኮምሽን ሊቀ መንበር አቶ ተክለብርሃን አርአያ ትላንት በሰጡት መግለጫ ፥ " 14ተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተብሎ የተጀመረው ስብሰባ ህወሓትን ወደከፋ ችግር የሚያስገባ ነው " በማለት ጉባኤውን አውግዘዋል።

አቶ ተክለብርሃን ፥ " አንድነታችን ይዘን ፣ የፕሪቶርያው ውል ማእከል አድርገን፣ ለአላዊነታችን አረጋግጠን በተጨማሪም አንድ ላይ በመንቀሳቀስ ሕጋዊ እውቅናችን መልሰን ሊደረግ የሚገባው ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይህ ጉባኤ ግን ወደ ቅርቃር ውስጥ የሚያስገባን ነው " ብለዋል።

" ተግባብተን ወደ አንድ መንገድ መጥተን ልናደርገው ይገባ የነበረ ነው። ላይ ያለው አመራሩ ብቻ ሳይሆን ታች ያለው አባልም ጭምር መግባባት የፈጠረበት ሊሆን ይገባ ነበር " ማለታቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
🔈 #Silte

ስልጤ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ በመከሰቱ በርካታ ወገኖቻችን ለመፈናቀል መገደዳቸውን ነዋሪዎችና ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በተለይ በዞኑ የስልጢ ወረዳ ጎፍለላ ቀበሌ በጎርፍ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

ወገኖቻችን ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ ቤት ንብረታቸውን ትተው ወደ ተለያዩ ስፍራዎች ተፈናቅለዋል።

አደጋው እንስሳትን ጨምሮ በንብረት ላይ ውድመት አስከትሏል ፤ የእለት የሚሆን ምግብ እንኳ እንዳላስቀረ ነው ነዋሪዎች የገለጹት፡፡

በቅጡ መጠለያ ያላገኙም ተፈናቃይ ወገኖች እንዳሉ አስረድተው፣ ፤ ለችግሩ በቂ መፍትሄ እየተሰጠው እንዳልሆነና በዘላቂነት መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

የስልጤ ዞን ኮሚኒኬሽን ፤ በጎፍለላ ቀበሌ ላይ የደረሰው አደጋ ሰፊ እንደሆነ ጠቁሟል። ነዋሪዎች አካቢቢውን ጥለው እንደወጡ አመልክቷል።

" የሚመገቡት እህልም ፣ ልብሳቸውንም… ምንም ይሄ ቀረ የሚባል ነገር የለም ራቁታቸውን ነው "  ሲል የሁኔታውን ክብደት አስረድቷል።

ዛሬ ላይ በተገኘው መረጃም ከ1,650 በላይ ሰዎች ተፈናቅለው በየት/ቤቱ ፣ ዘመድ ቤት እና መንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ተጠልለዋል።

300 ሄክታር መሬት ላይ የለማ ሰብልም ወድሟል።

Read https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-08-14

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Alert🚨

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (MPox) የዓለም አቀፍ አሳሳቢ የህዝብ ጤና ደኅንነት ስጋት (PHEIC) እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ወሰኑ።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) እና በአፍሪካ የሥርጭት መጠኑ እየጨመረ መምጣቱን አሳውቀዋል።

ከዚህ ባለፈ፣ የዝንጀሮ ፈንጣጣን የአፍሪካ ሲዲሲ የህብረተሰብ ጤና አህጉራዊ ደህንነት ስጋት እንደሆነ ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ የተያዘ ሰው #አለመኖሩን የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ አመልክቷል።

በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት እና ሞያሌን ጨምሮ በሌሎች የመግቢያ ቦታ ላይ የቁጥጥርና ማጣራት ስራ እየተሰራ ነው።

በሽታው እስካሁን በ13 የአፍሪካ ሀገራት መከሰቱን እንዲሁም፣ 2,863 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው እና 517 ለህልፈት መዳረጋቸዉ መረጋገጡን የአፍሪካ ሲዲሲ መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Alert🚨 የዝንጀሮ ፈንጣጣ (MPox) የዓለም አቀፍ አሳሳቢ የህዝብ ጤና ደኅንነት ስጋት (PHEIC) እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ወሰኑ። የዝንጀሮ ፈንጣጣ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) እና በአፍሪካ የሥርጭት መጠኑ እየጨመረ መምጣቱን አሳውቀዋል። ከዚህ ባለፈ፣ የዝንጀሮ ፈንጣጣን የአፍሪካ ሲዲሲ የህብረተሰብ ጤና አህጉራዊ ደህንነት ስጋት እንደሆነ…
#Alert🚨

ከተ.መ.ድ የጤና ኤጀንሲ እንደተገኘው መረጃ በቅርቡ ኤምፖክስ (Mpox) ለመጀመሪያ ጊዜ በ4 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም ፦
- በጎረቤታችን ኬንያ ፣
- በቡሩንዲ ፣
- በሩዋንዳ
- በኡጋንዳ ተገኝቷል። ሀገራቱም ሪፖርት አድርገዋል። በነዚህ ሀገራት ውስጥ የታየው በሽታ በኮንጎ ካለው ጋር የተገናኘ ነው።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም Mpox በሽታ የሚከሰተው በቫይረስ አማካኝነት ነው።

ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል። በወሲባዊ ግንኙነት ፣ በቆዳ ንክኪ ፣ በቅርብ ርቀት ሆኖ ማውራት/ መተንፈስ ፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ባለ የቅርብ ግንኙነት ይተላለፋል።

አሁን ላይ #ዋነኛዎቹ ናቸው የሚባሉት ሁለቱ የቫይረሱ ዝርያዎች Clade 1 - በማእከላዊ አፍሪካ ውስጥ ያለ ፤  Clade 1b - እጅግ በጣም አደገኛ የሆነው አዲስ የቫይረሱ ዝርያ ነው።

@tikvahethiopia
🏆የመጀመሪያውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በኦልድትራፎርድ ስታዲዮም ማን ዩናይትድ ከፉልሃም ጋር የሚያደርጉትን ፍልሚያ አርብ ነሐሴ 10 ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በSS Premier League እና SS Liyu ቻናል በሜዳ ፓኬጅ በቀጥታ ይከታተሉ!

⚽️ዩናይትድ ከኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫ ሽንፈት በኋላ የዓመቱን የመጀመሪያ 3 ነጥብ ለማሸነፍ ይጫወታል!

🤔እናንተስ ከሊጉ የትኛውን ተጫዋች ለማየት ጓግታችኋል?

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን  ወደ ሜዳ ያሳድጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
ሴንት ማርክ ኢንተ. ስኩል ለ 2017 ዓ.ም ባካበት ነው የ12 ዓመት በላይ የመማር ማስተማር ልምድ ጥራት ያለውን የት/ት አሰጣጣችንን ተደራሽ ለማድረግ 22 ከሚገኘው ዋና ጊቢ በተጨማሪ በመገናኛ ፣ ጎተራ እና መሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን ጨርሷል።

👉 እንዳያመልጦዎ የቀረን ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድመው ይመዝገቡ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን  0912506470/71 ይደውሉልን

ለልጅዎ የሚገባ ት/ት ቤት
ሴንት ማርክ ኢንተ. ስኩል
Follow us : Telegram - https://t.iss.one/SaintMarkSchool
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዕለታዊ

አንዱ አሜሪካን ዶላር ዛሬ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 103.9699 መግዣው ፤ በ114.6788 መሸጫ ተቆርጦለታል።

በግል ባንኮችም፥ ከ103 ብር አስንቶ (መግዣው) እስከ 117 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው።

(የዛሬ ነሐሴ 9 የውጭ ሀገር ምንዛሬ ዋጋ ዝርዝር ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia " መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ አድርጉልኝ ፤ ፕሬዜዳንታችንንም እዛው ሊወጡ ሲሉ ይቅርታ ጠይቂያለሁ አሁንም ይቅርታ ደግሜ ደጋግሜ ጠይቃለሁ !! " - አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ምን አሉ ? " የብር ጉዳይ አይደለም። ለእኛ (ለአሰልጣኞች) እየተሰጠን ያለው Value የተለያየ ነው። እኔ አስተማሪ ነበርኩ ፤ በአስተማሪነት ለ9 ዓመት አገልግያለሁ የጠላሁት ማንም…
#Update

አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ፣ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ከኢትዮጵያ መንግሥት የተበረከተላቸውን የ2 ሚሊዮን ብር ሽልማት " አልቀበልም " ብለው መልሰው ከመድረክ መውረዳቸው ይታወሳል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር " ገንዘቡ ወደ መንግስት ካዝና ተመላሽ ይሆናል። ምክንያቱም ስጦታ በግድ ውሰዱ ስለማይባል " ሲል ለኤፍ ኤም 97.1 ተናግሯል።

አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ፤ ለሙያውና ለአሰልጣኞች የሚሰጠው ክብር ዝቅ ያለ በመሆኑ በስሜታዊነት ያንን ነገር እንዳደረጉ በዚህም ፕሬዜዳንቷን እና መላው የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል።

አሰልጣኙ ገንዘቡን ካላስተካከሉት እንደማይቀበሉም ለሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ መናገራቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#Gambella

ከ6 አመት በላይ ጋምቤላ ክልልን ሲመሩ የቆዩት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ከስልጣናቸው ተነስተው አዲስ ፕሬዚዳንት ዛሬ ተሹሟል።

የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድን የክልሉ ፕሬዜዳንት አድርጎ ሾሟል።

ወ/ሮ አለሚቱ የዛሬው ሹመት እስኪሰጣቸው በኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን አገልግለዋል።

በክልሉ ም/ቤት " የአመራር ለውጥ ያስፈለገበት ምክንያት በሠላም እና ፀጥታ እንዲሁም በልማት ዘርፍ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም የተቀመጡ አቅጣጫዎች ውስንነቶች በመታየታቸው ነው " ተብሏል።

የቀድሞው ፕሬዜዳንት አቶ ኡመድ ሌላ የፓርቲ ተልዕኮ እንደሚሰጣቸውም ተሰምቷል።

በሌላ በኩል ደግሞ ጋትሏክ ሮን (ዶ/ር) ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል።

@tikvahethiopia