TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF
" ጠቅላላ ጉባኤው ከቦርዱ ፍቃድ ውጭ ከተካሄደ ቦርዱ ለዚህ ጉባኤም ሆነ በጉባኤዎቹ ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ዕውቅና አይሰጥም "- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከህወሓት ጉባኤ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለድርጅቱ ደብዳቤ ጽፏል።
ቦርዱ ፥ ነሐሴ 3/2016 ዓ/ም ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ ፖርቲው በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን እና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትም እንደሰጠው አስታውሷል።
ፓርቲው የቦርዱ ደብዳቤ እና የምስክር ወረቀት ከደረሰው ቀን ጀምሮ የሚተዳደረው የኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011ና ይህን አዋጅ ባሻሻለው አዋጅ ቁጥር 1332/2016 እንዲሁም እነዚህን አዋጆች መሰረት ተደርገው በወጡ መመሪያዎችና የቦርዱ ውሳኔዎች መሰረት እንደሆነ አስገንዝቧል።
ቦርዱ ውሳኔ የሰጠባቸውና በደብዳቤ ከገለፃቸው በፓርቲው መተግበር ካለባቸው ተግባራት መካከል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ከማድረጉ ከ21 ቀን በፊት ለቦርዱ ማሳወቅና ፖርቲው በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባኤ የቦርዱ ታዛቢዎች መገኘት በዋናነት የተገለፁ ግዴታዎች እንደሆኑ አመልክቷል።
ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት ፖርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ሊያደርግ መሆኑን ቦርዱ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን እየተዘገበ መሆኑ መመልከቱን ገልጿል።
በዚህም ቦርዱ " ለአንድ ጠቅላላ ጉባኤ መደረግ አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እንዲያውቅ ባልተደረገበት፣ ባልተከታተለበትና ባላረጋገጠበት እንዲሁም የቦርዱ ታዛቢዎች ባልተገኙበት ተጠራ የተባለው ጠቅላላ ጉባኤ ሊካሄድ አይችልም " ሲል አሳውቋል።
ጠቅላላ ጉባኤው ከቦርዱ ፍቃድ ውጭ ከተካሄደ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዚህ ጉባኤም ሆነ በጉባኤዎቹ ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ዕውቅና የማይሰጥ መሆኑን ለህወሓት በጻፈው ደብዳቤ ላይ ገልጿል።
#TPLF #NEBE
@tikvahethiopia

#እንድታውቁት
" ከዛሬ ጀምሮ ከአያት አደባባይ ወደ መገናኛ ፤ ከመገናኛ ወደ አያት አደባባይ የተቃራኒ ጉዞ ተከልክሏል " - የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ
በአዲስ አበባ፣ ከአያት አደባባይ ወደ መገናኛ ፤ ከመገናኛ ወደ አያት አደባባይ ድረስ በስራ የመውጫ እና የመግቢያ ሰዓቶች ላይ ይፈጠር የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ በሚል በጊዜያዊ መፍትሄነት ከአያት አደባባይ እስከ ሴንቸሪ ሞል በሁለቱም መስመሮች የተቃራኒ ጉዞ ተፈቅዶ ነበር።
ነገር ግን መጨናነቁን ይፈጥር የነበረው የሳዕሊተ ምህረት አደባባይ በመቀየሩ ከዛሬ ነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በሁለቱም መስመሮች የተቃራኒ ጉዞ መከልከሉን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳውቋል።
አሽከርካሪዎች ይሄን ተገንዝበው የመደበኛ የጉዞ መስመሮችን ብቻ እንዲጠቀሙ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
#AddisAbaba #TMA
#TikvahEthiopia
@TikvahEthiopia

#Infinix_Note40_Pro_Plus
የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ካሜራ 108 ሜጋ ፒክስል ጥራት ያለው የካሜራ ቴክኖሎጂ ይዞ የመጣ ሲሆን የ 100 ዋት ፋስት ቻርጀር እና ባለ 20 ዋት ያለገመድ ዋየር ለስ ቻርጅ ማድረግ የሚችል ነው፡፡ በተጨማሪም የዘመኑ የመጨረሻ ቴክኖሊጂ የሆነውን 5G ኔትወርክን ማስጠቀም የሚያስችል ድንቅ አቅም ያለው ስልክ ነው፡፡
#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt

ህወሓት ጉባኤውን ለማድረግ መዘጋጀቱ ታውቋል።
የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የሚገኙባቸው በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተቃውሞ እና በሌሎችም ምክንያቶች የማይሳተፉበት ፤ የድርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና የነፈጉት 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ዛሬ ማክሰኞ ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በይፋዊ የመክፈቻ ስነ-ሰርዓት በመቐለ መካሄድ እንዲጀምር ቀን፣ ቦታና ሰዓት ተቆርጦለታል።
ጉባኤውን አስመልክቶ የተሰራጨው መርሃ ግብር እንደሚጠቁመው ከዛሬ ነሀሴ 7 እስከ 12 / 2016 ዓ.ም ባሉት 6 ቀናት ይከናወናል።
የህወሓት ፅህፈት ቤት እና ማህተም የተቆጣጠረውና በሊቀመንበሩ ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመራው ሃይል ጉባኤውን በመቐለ በሰማእታት የሓወልቲ አዳራሽ " ጉባኤ ድሕነት!" ማለትም " የመዳን ጉባኤ! " በሚል መሪ ቃል ነው የሚያካሂደው።
በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንትና በድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ የሚመሩት 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ደግሞ " ጉባኤው ህወሓት የሚያጠፋ ፣ ለትግራይ ህዝብ ሌላ ችግርና የእርስ በርስ ግጭት የሚጋብዝ አደገኛ ጉባኤ " በማለት በይፋ ባወጡት መግለጫ ተቃውሞውታል።
በእነ ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ክንፍ ግን በከፍተኛ ተቃውሞ ታጅቦ ከነሀሴ 7 - 12/2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በሚቀጥሉት 6 ተከታታይ ቀናት ጉባኤውን ማካሄድ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፍቃዱ ውጭ ለሚካሄድ ለዚህ ጉባኤ ምንም አይነት እውቅና እንደማይሰጥ አሳውቋል።
ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-08-13

Telegraph
Tikvah Ethiopia
የህወሓት ወዴት ያመራል ? የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የሚገኙባቸው በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተቃውሞና በሌሎች ምክንያቶች የማይሳተፉበት ፤ የድርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና የነፈጉት 14 ኛው የህወሓት ጉባኤ ዛሬ ማክሰኞ ነሀሴ 7 / 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በይፋዊ የመክፈቻ ስነ-ሰርዓት በመቐለ መካሄድ እንዲጀምር ቀን፣ ቦታና ሰዓት ተቆርጦለታል።…
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዕለታዊ : የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ጨመረ።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል። የሌሎችም ምንዛሬ ዋጋ ጨምሯል።
(ንግድ ባንክ)
💵 አንድ የአሜሪካ ዶላር መግዣ 102.9899 ፤ መሸጫ 113.2889
💷 ስተርሊግ መግዣ ው125.5507 ፤ መሸጫው 138.7004
💶 ዩሮ መግዣ 112.5577 ፤ መሸጫ 123. 8134
🇰🇼 የኩዌት ዲናር መግዣው 321.2233 መግዣ ፤ መሸጫው 354.8592
🇦🇪 የUAE ድርሃ መግዣ 28.0428 ፤ መሸጫው 30.8471
በግል ባንኮች ደግሞ የአንዱ የአሜሪካ ዶላር መግዣ ከ103 ብር አንስቶ እስከ 119 ብር ደርሷል።
(ዕለታዊ የባንክ ምዛሬ ከላይ ተያይዟል)
(ነሐሴ 7/2016 ዓ/ም

የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ጉዳይ !
🔵 " ተመዝግበን አሻረ ከሰጠን አመት ሊንሞላ ነው እስካሁን ምንም የለም " - በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች
🟢 " አንድ ሰው ስለተመዘገበ ብቻ ይሄዳል ማለት አይደለም ፤ ለጉዳዩ ተፈላጊ የሆኑ መስፈርቶች ማሟላት ያስፈልጋል " - ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በመዘዋወር በጎ ተግበራት ሲያከናውኑ የቆዩ ብሔራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንዳሉ ይታወቃል።
እነዚህ ወጣቶች ከዚህ ቀደም የውጪ የሥራ እድል በሚኖርበት ወቅት ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ተነግሯቸው እንደነበር አስታውሰዋል።
ይሁን እንጂ ወደ ወጪ ለመሄድ ተመዝግበው አሻራ ቢሰጡም እስካሁን የተባሉት ነገር እንደሌለ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ባቀረቡት ቅሬታ፣ " ተመዝግበን አሻረ ከሰጠን አመት ሊንሞላ ነው እስካሁን ምንም የለም " ብለዋል።
" ' ቅድሚያ ለብሄራዊ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰልጣኞች ተብለን ' ከተመዘገብን ቆየን። እናም ከስራ እድል አኳያ የመኖር ያለመኖር ጉዳይ በብዙ የሀገራችን ወጣቶች ላይ እየተሰተዋለ ይገኛል እባካችሁ በፍጥነት መፍትሄ ስጡን " ሲሉ ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል ፤ " ምዝገባ ይደረጋል ማስታወቂያ እየወጣ በተለያየ የስራ መስክ። ታዲያ እንዴት ነው ወደ ውጭ የሚኬደው ? የተመዘገበ ሁሉ ይሄዳል ? ውድድር አለው ? " የሚሉ ጥያቄዎችን አቅርበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህንን የወጣቶቹን ጥያቄ በቀጥታ ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አቅርቧል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ምን ምላሽ ሰጡ ?
(ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል)
➡ ኮሚዩኒኬሽኑ ላይ ያልነው ቃል በቃል እደዛ ባይሆንም እንደዛ እንደሚሉ እኛም እናውቃለን፡፡
➡ በሰዓቱ በነበረን ስምሪት የሰጠነው መረጃ ማንም ሰው ሰልጥኖ ብቁ ሆኖ በፍቅር አገሩን አገልግሎ እስከተገኘ ጊዜ ድረስ እንደሚሆን ነው።
➡ ሰው ስለተመዘገበ ብቻ ይሄዳል ማለትም አይደለም፡፡ ለጉዳዩ ተፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችን ማሟላት ያስፈልጋል፡፡
ለምስሌም ፦ ' የሰለጠነ የሰው ኃይል እንልካለን ' ስንስል አገራቱ በሚፈልጓቸው የሙያ መስኮች የሚላኩ ወጣቶችን ሰርቲፋይ የሚያደርጓቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት መኖር አለባቸው፡፡ ዘንድሮ ይህንን ከሚመለከታቸው ጋር ሆነን ማሳካት ተችሏል።
ስለዚህ አንዳንዶቹ የሙያ መስኮች ላይ በዬጊዜው ይፋ እያደረግን ነው ያለው። በቅርብ የሱዊድንና የኖርዌይ ገበያ ጭምሮ ይፋ አድረገናልል፡፡ በርካታ የሙያ መስኮች ላይ የሰለጠኑ ሰዎች ይፈለጋሉ።
➡ የተመዘገቡ ሰዎች ራሳቸውን አዘጋጅተው በደብን (ኦንላይን የምናዘጋጃቸውን ይዞቶች አሉ፡፡ ተመዝግበው ደግሞ ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶች አሉ መውሰድ ያለባቸው የሥልጠና የፈተና አይነት) ያሟላ ሰው መሄድ ይችላል።
➡ ስርዓት አልምተናል ፤ ይህም ስርዓት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ማስተናገድ የሚችል በቴክኖሎጅ የታገዘ ነው፡፡ የሰው ጣልቃ ገብነት የለውም፡፡ የአክስቴ የአጎቴ የሚባል ነገር የለም። ሪኳየርመንት ያሟላ በሙሉ ይህንን እድል ማግኘት ይችላል፡፡ ከዚህ ውስጥ አንዱ የብሔራዊ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ናቸው ማለት ነው፡፡
➡ በ2014 ዓ/ም ላይ 40 ሺሕ ገደማ ሰው ነው የተላከው። የሥራው ባህሪ የሚጋብዝ አልነበረም፣ ምሩቃን ለሆኑ ሴትና ወንድ ወጣቶች፡፡ ቢያንስ እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ የተማሩ ሴት ወጣቶችን በአመዛኙ የሚጋብዝ ነው የነበረው።
ሙሉ ንግግራቸውን ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-08-13-2
🌐 lmis.gov.et🌐
#TikvahEthiopiaFamilyAA

🌐 lmis.gov.et
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ህወሓት ጉባኤውን ለማድረግ መዘጋጀቱ ታውቋል። የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የሚገኙባቸው በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተቃውሞ እና በሌሎችም ምክንያቶች የማይሳተፉበት ፤ የድርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና የነፈጉት 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ዛሬ ማክሰኞ ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በይፋዊ የመክፈቻ ስነ-ሰርዓት በመቐለ…
#TPLF : ህወሓት የጉባኤ መክፈቻ እያደረገ ይገኛል።
ድርጅቱ " 14ኛው ጉባኤ መክፈቻ እየተካሄደ ነው " ብሏል።
በሊቀመንበሩ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ቡድን ነው ጉባኤውን በመቐለ በሰማእታት የሓወልቲ አዳራሽ " ጉባኤ ድሕነት ! / የመዳን ጉባኤ ! " በሚል መሪ ቃል የጀመረው።
እንደወጣው መርሀ ግብር ጉባኤው ከነሀሴ 7 - 12/2016 ዓ.ም እንደሚቆይ ነው የተነገረው።
የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተቃውሞና በሌሎችም ምክንያቶች አይሳተፉም።
የድርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና ነፍገዋል።
በተለይ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉና ከቦርዱ ፍቃድ ውጭ በሚደረግ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ዕውቅና የማይሰጥ መሆኑን ለህወሓት በጻፈው ደብዳቤ ቀድሞ አሳውቋል።
#TikvahEthiopiaMekelle
ፎቶ፦ TPLF

#Update
" ይህ ጉባኤ ትግራይን እና ህዝቡን ወደ አደጋ ከመክተት የዘለለ እርባና የለውም " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ አውጥተዋል።
ጉባኤው " በችኮላና የጋራ መግባባት ሳይደረስበት ፤ በማደናገርና በአቋም አልባነት አሰባስበናቸዋል በሚሉት ኔትወርክ ' ይቃወሙናል ' የሚሉዋቸው የተወሰኑ #አመራሮች_ለማስወገድ በማለም የሚካሄድ ጉባኤ ነው " ብለውታል።
" ይህ ጉባኤ ትግራይን እና ህዝቡን ወደ አደጋ ከመክተት የዘለለ እርባና የለውም " ሲሉ ገልጸዋል።
ምክትል ሊቀመንበሩ ፤ " የተሻሻለው የፓለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ ህወሓት እንደ አዲስ እንደሚዘገብ የሚያደርግ ፣ ወርቃዊው የትግራይ ህዝብ ትግል የሚያጎድፍ በቀጣይ ቅርቃር ውስጥ የሚከት መሆኑን በመገንዘብ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ በማእከላዊ ኮሚቴ አባላት መግባባት ተደርሶ ነበር " ብለዋል።
" ይሁን እንጂ የተደረሰው መግባባትና መተማመን ወደ ጎን በመተው ' ከፌደራል መንግስት ተማምነናል ' በሚል ማደናገሪያ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመነጋገር ከማእከላዊ ኮሚቴ እና ካድሬ በመደበቅ የተሄዴበት ሂደት ወዳልተፈለገ ወጥመድ እንድንገባ ተደርገናል " ብለዋል።
" በዚህ ምክንያት የሚፈጠር ማንኛውም ጥፋት ተጠያቂው ለጠባብ ቡድናዊ ፍላጎቱ ብቻ የሚንቀሳቀሰው ቡድን ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
አቶ ጌታቸው ፥ " የህዝቡ ሰላም እንዳይደፈርስና እንዳይረበሽ ከህዝባችንና ከመላ አባላችን በመሆን እንታገላለን " ብለዋል።
" ሁሉም የትግራይ አቅሞች በማቀናጀት በተደራጀ ትግል ከፍተኛ ፓለቲካዊ ድርድር በማካሄድ የህወሓት ህጋዊነት በመመለስ ካጠላብን ዙርያ መለስ ፈተና በመውጣት የትግራይ የተሟላ ደህንነትና እድገት እንደሚረጋገጥ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ " ብለዋል።