TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዕለታዊ  : ዛሬ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም በተለያዩ የግል ባንኮች ያለው የዛሬው ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ከላይ ተያይዟል።

(ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ/ም)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፣ በአትሌት ዴሬሳ ገለታ ፣ በአትሌት ታምራት ቶላ የተወከለችበት የፓሪስ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር እየተካሄደ ይገኛል። Via @tikvahethsport @tikvahethiopia
#Ethiopia የወንዶች ማራቶን ሊጠናቀቅ 9 ኪሎ ሜትር ይቀረዋል።

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ታምራት ቶላ እና ደሬሳ ገለታ ውድድሩን ከፊት ሆነው በመምራት ላይ ይገኛሉ።

ወቅታዊ ደረጃቸው 1ኛ ታምራት ቶላ ደሬሳ ገለታ 2ኛ ናቸው።

ታምራት በርቀት እየመራ ነው። ጥሩ ጥንካሬና ጉልበት ያለውም ይመስላል።

መጨረሻውን ያሳምረው። ውድድሩ በዚህ ካለቀ የወርቅ ሜዳሊያ ልናገኝ እንችላለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ 🥇 ወርቅ አገኘች !! @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ወርቅ አገኘች።

ሀገራችን በኦሎምፒኩ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ በማራቶን በጀግናው አትሌትላችን ታምራት ቶላ አማካኝነት አግኝታለች።

ምንም እንኳን በፓሪስ እየተመዘገበ ያለው ውጤት አንገት የሚያስደፋ ቢሆንም ዛሬ በወንዶች ማራቶን የተገኘው ውጤት የሚያኮራ ነው።

አትሌት ታምራት እጅግ በሚደንቅ ብቃት ነው ወርቁን ወደ ኢትዮጵያ እጅ ያስገባው።

አትሌት ታምራት ተጠባባቂ የነበረ ሲሆን የአትሌት ሲሳይ ለማን መጎዳት ተከትሎ ነው በውድድሩ ሊሳተፍ የቻለው።

@tikvahethiopia @tikvahethsport
#Ethiopia

በማራቶን ውድድር ላይ " ተጠባባቂ ነህ " ተብሎ የተያዘውና ለውድድሩ የተመረጠ ሌላ አትሌት መጎዳቱን ተከትሎ ሀገሩን ወክሎ የተሳተፈው ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ ለሀገሩ ኢትዮጵያ ወርቅ ማምጣት ብቻ ሳይሆን በሚደንቅ ብቃት የኦሎምፒክ ሪከርድም ጭምር ነው የሰበረው።

ጀግናው አትሌት ታምራት ከአትሌት ገዛኸኝ አበራ በኋላ (ከ24 ዓመታት በኃላ) ነው የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ለሀገራችን ያስገኘው።

ሌላው አንጋፋው ኢትዮጵያ ሁል ጊዜ በስራው የምታመሰግነው የ42 ዓመቱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 39ኛ ደረጃ ይዞ እጅግ ከባድ የነበረውን የፓሪስ ማራቶን አጠናቋል።

አትሌት ደሬሳ ገለታም 5ተኛ ደረጃ በመውጣት እጅግ በጣም አበረታችና ተስፋ ሰጪ ውጤት አስመዝግቧል።

ምንም እንኳን ዛሬ በወንዶች ማራቶን የተገኘው ውጤት አስደሳችንና የሚያኮራ ቢሆንም በፓሪስ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ኢትዮጵያን የሚመጥናት አይደለም።

በጭቅጭቅና ንትርክ በተሞላው በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ ያገኘችው እስካሁን 3 ሜዳሊያ ብቻ ነው። 1 ወርቅ እና 2 ብር ብቻ።

የአትሌቲክሱ ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ ያሉ ችግሮች እና ኢትዮጵያን ዝቅ ያደረጉ ነገሮች ሁሉ ተፈትሸው መለወጥ እንዳለባቸው የፓሪስ ኦሎምፒክ በግልጽ አመላክቷል።

ከሚዲያ በዘለለ ስለዚህ ሀገር አትሌቲክስ ሁሉም " የሀገር ክብር ያሳስበኛል " የሚል ቁጭ ብሎ ተነጋግሮ በአስቸኳይ ለውጥ ማምጣት አለበት። እንዲህ ከቀጠለ በዓለም ደረጃ የነበረን ክብር የማናጣበት ምክንያት የለም።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

" የተወሰኑ ግለሰቦች ከድርጅቱ አሰራር ውጪ በቡድን የላኩት ማስረጃ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( #ህወሓት ) ምክትል ሊቀመንበርና  የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅሬታ ደብደቤ አቀረቡ።

ምክትል ሊቀ-መንበሩ ነሀሴ 4/2016 ዓ.ም በህወሓት " በልዩ ሁኔታ " የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ዙሪያ ነው ለቦርዱ ቅሬታቸውን ያቀረቡት።

" በህወሓት የምዝገባ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተላከው ደብዳቤ ማእከላዊ ኮሚቴ የማያውቀው በግለሰቦች የተላከ ነው " ብለዋል።

ም/ ሊቀ መንበሩ አቶ ጌታቸው ፥ " የተወሰኑ ግለሰቦች ከድርጅቱ አሰራር ውጪ በቡድን በመሆን የፈረሙት እንጂ እኛ ለምዝገባ ብለን የፈረምነው ማንኛውም ሰነድ የለም " ሲሉ አክለዋል።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት አስመልክቶ ለተወሰኑ ግለሰቦች የሰጠው እውቅና የተጭበረበረ በመሆኑ ዳግም ሊያጤነው ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የአንዲት ታዳጊ ህይወት አልፏል !

በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የሐዋሳ ቅርንጫፍ በመደበኛው የፓይለት ስልጠና ልምምድ ላይ የነበረ ቀላል የተማሪዎች መለማመጃ አውሮፕላን (Dimond DA40NG) አየር ላይ ሳለ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አርሲ ነጌሌ አካባቢ ለማረፍ መገደዱን የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ ገልጿል።

" ይህንን ተከትሎ በመደበኛ ስልጠናው ላይ የነበሩት አስተማሪውና ተማሪው የመለማመጃ አውሮፕላኑ ሕብረተሰቡ ላይ አደጋ በማያደርስ ሁኔታ ለማሳረፍ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም ለማረፍ በተደረገው ጥረት መሬት ላይ በነበረች አንዲት ታዳጊ ላይ ጉዳት ደርሷል " ብሏል።

በዚህም የታዳጊዋ ህይወት አልፏል።

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ፥ የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ በሚመለከታቸው አካላት በመጣራት ላይ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
Within the Jasiri Talent Investor Program, you’ll meet like-minded individuals and potential co-founders from diverse backgrounds, and together, you will form a co-founding team to build high growth venture from scratch. 🤝🚀

Apply today to join cohort 7 at https://jasiri.org/jasiri-talent-investor/.

Follow our telegram channel @Jasiri4Africa
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF : ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተሰጥቶታል። @tikvahethiopia
#TPLF

" አልቀበልም ! " - ህወሓት

ህወሓት የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ የሰጠውን የምዝገባ ውሳኔ አልቀበልም አለ።

ድርጅቱ " የተሰጠኝ የምዝገባ ውሳኔ ከተካሄዱት የሁለትዮሽ ወይይቶችና መግባባት ወጪ ነው፤ ስለሆነም ወደ ነባሩ እውቅናዬ የማይመልስ ውሳኔ አልቀበልም " ብሏል ዛሬ ነሀሴ 4/2016 ዓ.ም ባወጣው ባለ ሁለት ገፅ የፅሑፍ መግለጫ።

ህወሓት ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዞ ቀርቧል።

ትላንትና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፓርቲዎች " በልዩ " ሁኔታ ሲመዘገቡ የሚሰጥ ሕጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠቱ ይታወሳል።

ይህን ውሳኔ ነው ህወሓት " አልቀበልም " ብሎ መግለጫ ያወጣው። " እኛ የምፈልገው የተሰረዘው ህጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስልን ብቻ ነው " ብሏል።

@tikvahethiopia