TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
2 ቀን ቀረው!

🏆 የአንድን ከተማ ሕዝብ በሁለት ጎራ የከፈሉት ማን ዩናይትድ እና ማን ሲቲ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋዜማ በኮሙኒቲ ሺልድ ዋንጫ ተፋጠዋል!

⚽️ ዩናይትድ እና ሲቲ የሚያደርጉትን የዋንጫ ፍልሚያ ቅዳሜ ነሐሴ 4 በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይከታተሉ!

🔥 ዋንጫው የማን ነው? 

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ የኮሙኒቲ ሺልድ ጨዋታ ከትንታኔ እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ልዩ በቀጥታ ይከታተሉ!    

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
#አበሽጌ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ጉራጌ ዞን፣ አበሽጌ ወረዳ ዋልጋና ዳልጌ ከተሞች የሚኖሩ ወጣቶች ባለሀብቶችና አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች በጸጥታ ኃይል በአፈሳ እየተያዙ መሆናቸውን ተከትሎ ወጣቶች ከቤት ለመውጣት ፍርሀት ውስጥ መሆናቸው ተሰምቷል።

አካባቢው በተለይ ከኦሮሚያ ጋር የሚዋሰንባቸው መንደሮች ካሁን በፊት ግጭቶች መፈጸማቸውን ተከትሎ በስጋት መቆየታቸውን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ከሰሞኑ እየሆነ ያለው ነገር እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ወጣቱ በፍርሀት ቤቱ ቢቀመጥም አንዳንዶቹ ቤታቸዉ ባሉበት መያዛቸዉን ተከትሎ ፍርሀቱ ከፍ ሊል ችሏል።

ሁኔታውን በተመለከተ ማን ማንን ነው እየያዘ ያለው ? ስንል የጉራጌ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ገና ደገሞን ጣይቀናል።

እሳቸውም " የተቀናጀ የጸጥታ ኃይል ወንጀለኞችን እየያዙ ነው " ብለዋል።

በተጨማሪም ሰው ፍርሀት ውስጥ ነው ለሚባለው " ወንጀል ውስጥ እጁ ካለበት ሰው ውጭ ንጹሀኑ ፍርሀት ሊገባው አይገባም " ሲሉ መልሰዋል።

" አሁን ላይ የብሄራዊ ደህንነትን ጨምሮ የፌደራል ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት በአካባቢዉ ተሰማርተዉ አሰሳ በማድረግ የጥፋት ኃይሎችን እየያዙ ነው " በማለት አካባቢዉ በፍጥነት ወደነበረ ሰላሙ ይመለሳል ብለዋል።

ዋና ኢንስፔክተሩ አክለዉ " እንቅስቃሴዉ በአበሽጌ ወረዳና በኦሮሚያ ወሰን መካከል መሆኑን በመግለጽ ሰላማዊ ሰዎች ያለስጋት የእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸውን እንዲቀጥሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia ለተከታታይ ቀናት የውጭ ምዛሬ ዋጋ ባለበት እየቀጠለ ነው።

የንግድ ባንክ ዛሬም ለ5ኛ ተከታታይ ቀን የውጭ ምንዛሬው ላይ ምንም የተለየ ለውጥ ሳያደርግ ውሏል። ዶላር 95.6931 ይገዛል፣ 101.4347 ይሸጣል።

በግል ባንኮችም ያን ያህል ጭማሪ አልታየም።

ትላንትና ብሔራዊ ባንክ 27 ባንኮች በተሳተፉበት ባወጣው ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ መሸጡን ይታወሳል።

ይኸው አማካይ ዋጋ የዛሬ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጠቋሚ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ነው ማለቱ አይዘነጋም።

በሌላ በኩል ምንም እንኳን በሀገሪቱ  ውስጥ ያሉት ባንኮች  በየዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ዋጋቸውን እያወጡ ቢሆንም ዶላር እንደልብ ማግኘት ገና አልተጀመረም።

@tikvahethiopia
#ለመረጃ_እንዲሆኖት

ከቀረጥ ነፃ ወደ አገር ስለሚገቡ ተሸከርካሪዎች !

የልማት ፕሮጀክቶች እንዲውሉ ተሸከርካሪዎችን ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ የማስገባት ማበረታቻ የሚሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች የትኞቹ ናቸው ?

ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው ለልማት ፕሮጀክቶች እንዲውሉ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የሚፈቀዱ ተሸከርካሪዎችን ዓይነትና ብዛት ለመወሰን እንደገና ተሻሽሎ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ የወጣ መመሪያ ቁጥር 942/2015 ነው።

ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ የማበረታቻ ተጠቃሚ የኢንቨትመንት መስኮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

➡️ በማምረቻ ኢንዱስትሪ፣
➡️ በኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት፣
➡️ በግብርና፣
➡️ በሎጂስቲክስ፣
➡️ በኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭነት፣
➡️ የኮከብ ደረጃ ላላቸው ሆቴሎች(የሪሶርት ሆቴሎችን ጨምሮ)፣
➡️ ሞቴሎች፣
➡️ ሬስቶራንቶችና ሎጆች፣
➡️ በባቡር መሰረተ ልማት ለመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ (ICT) ልማት ለአስጎብኝነት ስራ፣
➡️ በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫና ማሰራጫ፣
➡️ በትምህርትና ስልጠና፣
➡️ የጤና አገልግሎት፣
➡️ የአርኪቴክቸር እና ኢንጂነሪንግ ስራዎች የቴክኒክ ምርመራና ትንተና አገልግሎት
➡️ የንግድ የሥራ መስኮች አዳዲስ ፕሮጀክትን ለሚያቋቁሙ ወይም ነባር ድርጅታቸውን ለሚያስፋፉ ብቻ ነው።

#MinistryofRevenuesofEthiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችን ለመክፈት የሥራ ፈቃድ ማመልከቻዎችን መቀበል ጀመረ።

ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ጀምሮ ሥራ ላይ በዋለው የውጭ ምንዛሪ መመሪያ ቁ.01/2016 መሠረት የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮ ለመከፈት የሚፈልጉ የሥራ ፈቃድ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ብሔራዊ ባንክ ጥሪ አቅርቧል።

በገበያ ላይ ተመሥርተው የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ መሸጥና መግዛት የሚፈልጉ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች እንዲቋቋሙ በተፈቀደው መሠረት የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚኖሩ እንዲሁም የሌላ ሀገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ምንዛሪ ቢሮ መስፈርቱን አሟልተው ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ሲያገኙ መክፈት ይችላሉ፡፡

የውጭ ምንዛሪ ቢሮ ለመክፈት የሚያስፈልገው የካፒታል መጠን እንዲሁም ሌሎች ለሥራው የሚያስፈልጉ መስፈርቶች ከላይ ተያይዟል።

ካፒታልን በተመለከተ በመመሪያው ላይ የሰፈረው ይህ ነው ፦

Fulfills the minimum capital requirement of Birr 15 million and is able to provide a Security Deposit of Birr 30 million to be placed in a blocked account (which can be interest-earning) at any bank:


ዝቅተኛ 15 ሚሊዮን ብር ካፒታል እና በዝግ በየትኛውም ባንክ የተቀመጠ 30 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል።

ባንኩ " የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች መቋቋም የውጭ ምንዛሪ ገበያን መሠረት ለማስፋትና ለማጠናከር እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ ለመሸጥም ሆነ ለመግዛት የሚሹ ደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት እንደሚረዳ እሙን ነው " ብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ፣ " የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች እንዲከፈቱ የሥራ ፈቃድ መስጠታችን የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ለመክፈትና ዘርፉን በቀጣይ ዓመታት ከዓለም ምርጥ ተሞክሮዎችና አሠራሮች ጋር የተመጣጣነ እና ተወዳዳሪ የሆነ ለማድረግ የጀመርነውን አዲስ ምዕራፍ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የጀመረውን ስትራቴጂካዊ የሆነ ለውጥ ከግብ ለማድረስ በቁርጠኝነት መነሣሣቱን የሚያመለከት ነው " ብለውታል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
የደመወዝ ማሻሻያ / ጭማሪ ይፋ ተደርጓል ?

አጭር መልስ ፦ ሀሰት ነው ! ምንም ይፋ የተደረገ ነገር የለም።

እስካሁን የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ / ጭማሪ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልተደረገም።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በቴሌግራም ፣ በፌስቡክ እየተዘዋወረ ያለው " የፌዴራል መንግሥት ሲቪል ሰርቫንት ደመወዝ ማሻሻያ " የሚለው መረጃ ምንም ምንጩ የማይታወቅ ነው።

የተሰራጨው የደመወዝ ማሻሻያ ሰንጠረዥ ፤ የፅሁፍ ስህተቶች ጎልተው የሚታዩበት፣ የአጻጻፉ ግድፈት ያለበት፣ የድምር ጭምር ግልጽ እና ቀላል ስህተት ያለበት ነው።

ሌላው ማን ይፋ እንዳደረገው አይታወቀም።

ማህተም አላፈረበትም ፤ መረጃውንም ያወጣው መ/ቤትም አይታወቅም።

እስካሁን በይፋ ለህዝብ የተሰራጨ የደመወዝ ጭማሪ ዝርዝር መረጃ የለም።

በመሆኑንም እየተዘዋወረ ያለው የደመወዝ ጭማሪ ሰንጠረዥም ሆነ የደመወዝ ጭማሪ መረጃ ሀሰተኛ ነው።

መንግሥት በቅርቡ የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ ማሳወቁ ይታወሳል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የደመወዝ ማሻሻያ / ጭማሪ ይፋ ተደርጓል ? አጭር መልስ ፦ ሀሰት ነው ! ምንም ይፋ የተደረገ ነገር የለም። እስካሁን የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ / ጭማሪ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልተደረገም። በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በቴሌግራም ፣ በፌስቡክ እየተዘዋወረ ያለው " የፌዴራል መንግሥት ሲቪል ሰርቫንት ደመወዝ ማሻሻያ " የሚለው መረጃ ምንም ምንጩ የማይታወቅ ነው። የተሰራጨው የደመወዝ…
#Ethiopia : ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወር የነበረው የደመወዝ ጭማሪ መረጃ " ሐሰተኛ መረጃ ነው " ሲል የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ማምሻውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል አረጋግጧል።

ዛሬ ከሰዓት አንስቶ ሲዘዋወር የነበረውን ሀሰተኛ መረጃ በርካታ ተከታይ ያላቸው አካላት / ገጾች ጭምር ምንም ሳያረጋግጡ ለህዝብ ሲያሰራጩ ነው የዋሉት።

አንዳንድ ሠራተኞች እንደ ትክክለኛ መረጃ ቆጥረውት ነበር።

ለቲክቫህ ቃላቸውን የሰጡት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ከበደ ደሲሳ ፥ ሲሰራጭ የነበረው መረጃ ፍጹም ከእውነት የራቀ መሆኑን ተናግረዋል።

"ሐሰተኛ መረጃ ነው" ሲሉም አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

" የዋጋ ንረቱ ሰራተኛውን አልፎት ሄዷል! ለዚህም የደመወዝ ማሻሽያው መዘግየት የለበትም " - ኢሠማኮ

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን ስለ ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ምን አለ ?

ምክትል ፕሬዝዳንት አያሌው አህመድ ፦

" መንግስት የደመወዝ ጭማሪ አደርጋለው ቢልም ገበያው በዚሁ ከቀጠለ ከሠራተኛው ከአቅሙ በላይ ሊሆንበት ይችላል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሽያው በታወጀ በማግስቱ ስለሆነ ለመንግስት ሰራተኞች ይደረጋል የተባለው የደመወዝ ማሻሽያ ሊዘገይ አይገባም።

የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሽያ ተከትሎ በገበያ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ  እየታየ ነው።

ይህ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ለመንግስት ሰራተኛው ይደረጋል የተባለው የደመወዝ ማሻሽያ ዋጋ የለውም።

የገበያው ዋጋ ቁጥጥር በሌለበት እና በተለመደው አይነት መልኩ ከተገቢው በላይ ጭማሪ የሚያሳይ ከሆነ ይጨመራል በተባለው ደሞዝ መቋቋም የማይችልበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል።

የነጋዴው ማህበረሰብም መንግስት የሚያወጣውን መመርያ ተክትሎ የማይጎዱበትን ጭማሪ ካልሆነ በስተቀር በዘፈቀድ ምርቶች እየተደበቁ ሰራተኛው ለአላስፈላጊ ወጪ የሚደረግ ከሆነ አሁንም መልሶ ከችግር የሚወጣበት ሁኔታ አይኖርም።

መንግስትም በቂ የደመወዝ ማሻሽያ ፤ ነጋዴውም ምክንያታዊ ጭማሪ ካላደረገ በገበያው ይበልጥ ቀውስ ሊፈጠር ይችላል።

ለዚህ ደግሞ ቁጥጥር ማድረግ ያለበት መንግስት እና ህብረተሰቡ ነው።

በገበያው ላይ ምን እንዳለ መንግስት ያውቀዋል ፤ ምክንያቱም የዋጋ ንረቱ ሰራተኛውን አልፎት ሄዷል ለዚህም የደመወዝ ማሻሽያው መዘግየት የለበትም። "

#Ethiopia #ShegerFMRadio

@tikvahethiopia
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ኪራይ ክፍያዎን በቴሌብር!!

ወርሃዊ የኪራይ ቤቶች ክፍያዎን በቴሌብር ሱፐርአፕ በቀላሉ በመፈጸም ጊዜዎን ቆጥበው ድካምዎን ይቀንሱ!

ቴሌብር ሱፐርአፕን onelink.to/fpgu4m ይጫኑ፤ ሕይወትዎን ያቅልሉ!

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም አስተያየት በ https://t.iss.one/EthiotelecomChatBot 24/7 ያግኙን!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #SmartAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
የቆጣቢዎች ቅሬታ እና የተሰጠ ምላሽ !

• " በ36 ወራት ቤት አስረክባችኋለሁ ብሎን ነበር ግን ሳንረከብ 3 ወር ሆነን " - ቆጣቢዎች

• " ክፍያ በምናሸጋሽግበት ወቅት የፕሮጀክቱን የጊዜ ሰሌዳ ይገፋዋል " - ሐምብራ ቢዝነስ ግሩፕ


የ " ሐምብራ ቢዝነስ ግሩፕ " የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቆጣቢዎች " ድርጅቱ በገባነው ውል መሠረት ቤቱን አላስረከበንም ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረሩ።

የቅሬታ አቅራቢዎች ነን ያሉ ቆጣቢዎች ያጋጠማቸውን ችግር ይዘው ወደ ቲክቫህ ኢትዮጵያ መጥተዋል።

ቆጣቢዎቹ " ድርጅቱ በ36 ወራት ቤቱን አስረክባለሁ ብሎን ነበር ግን እስካሁን አላስረከቡንም። ይኸው 3 ወር ሆነን " ብለዋል።

" በአንዱ ሳይትም ቆፋሮ አልጀመሩም። ካስፈለገ ቦታውን ሂዶ ማዬት ይቻላል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ውላችንን ፤ ገንዘብም የከፈልንበትን ደረሰኝ (ወደ እነርሱ የገባበትን) ማሳየት ይቻላል። ይሄ ሆኖ ሳለ በተደጋጋሚ ደብዳቤ ብንጽፍም አንሰማም አሉ " ያሉት ቆጣቢዎች " እኛ ከፍያ ጨርሰን አስረክበናል። በብራችን እንዲሰሩ ነው የጠበቅነው። ሁለት ብሎኮች አሉ። ብሎክ “ኤ” ሳይት ላይ ትንሽ ከፍ ብሏል። ብሎክ “ቢ” ደግሞ ገና ቁፋሮም አልተጀመረም " ብለዋል።

" ቤታችንን ያስረክቡን ይህ ካልሆነ ደግሞ ይዞታውን ወደ ቤት ገዢዎች ማስተላለፍ ካለባቸው ያስተላልፉ " ሲሉ ጠይቀዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎች ቶሎ ችግሩ ካልተፈታ ወደ ሕግ እንደሚወስዱት አመልክተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቆጣቢዎች የመጣውን ቅሬታ ይዞ የሐምብራ ቢስነስ ግሩፕን ጠይቀዋል።

ድርጅቱም ፥ " ቤት እናስረክባለን ብለን ያሰብነው ጊዜ በ3 አመታና በ3 አመት ተኩል ይጠናቀቃል ብለን ነበር። የማተሪያል ዋጋ ጭማሪዎች ፣ የማተሪያል Avalability ፤ ከባንክ ጋር ተያይዞ ያለ የፋይናስ አቅርቦት ይህንን ነገር ማድረግ እንዳንችል የያዙን ነገሮች ናቸው " ብሏል።

" በተለይ ከዋጋ ጭማሬ ጋር በተያያዘ የማተሪያል ጭማሪ በሚኖር ሰዓት ላይ በውሉ መሠረት ደንበኞች እስከ 10% የሆነውን ድርጅቱ የሚሸከመው ሆኖ ከ10% በላይ ከሆነ ግን ለደንበኞች አሳውቆ ጭማሪ ማድረግ እንዳለባቸው ውሉ ይጠቅሳል " ሲል ገልጿል።

" ያን በምናቀርብ ሰዓት ደንበኞች አቅም ያንን የሚችል ሆኖ አላገኘነውም " ያለው ድርጅቱ " የአብዛኛው ደንበኞቻችን በጭማሪው መሠረት እየጨመሩ የመቀጠል አቅም ስለሌላቸው ከደንበኞች ጋር የደረስነው Individual አግሪመንቶች አሉ " ብሏል።

" ስለዚህ 'ጭማሪ በሚሆን ጊዜ ያለን ብቸኛ አማራጭ ማቆራረጥ ነው' በሚሉ ሰዓት የክፍያ ማሸጋሸጎች እና ክፍያ በምናሸጋሽግበት ወቅት የፕሮጀክቱን የጊዜ ሰሌዳ ይገፋዋል " ሲል አስረድቷል።

" ፕሮጀክቱን ማጠናቀቅ ያልተቻለው በዋጋ ንረት ሳቢያ ነው። የጊዜ ማራዘሚያዎችን አድርገን ከደንበኞቻችን ጋር ግንባታውን እንቀጥላለን " ብሏል።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-08-09