TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia

" አዲስ የጨዋታ ሕግ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ እየመጣ ያለው " - ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

መንግሥት አሁን ላይ በኢኮኖሚው ውስጥ ካለው እንቅስቃሴ አንጻር " ገቢ ገና አልሰበሰብኩም ፤ ገና አልጀመርኩ " ብሎ ያስባል።

ይህንን ለማስተካከል እና ሀገራዊ ገቢን ለማሳደግ በአዲሱ ሪፎርም ብዙ ስራዎች ይሰራሉ ብሏል።

ገቢ ለማሳደግ በሚሰራው ስራ ግን ተጨማሪ ታክስ አይጣልም፣ የታክስ መጥናኔም አይጨምርም ሲል ገልጿል።

ታዲያ በምን መንገድ ገቢውን ለማሳደግ ነው ያሰበው ?

የገንዝብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ፦

" በየዓመቱ የገቢ መሰብሰብ አቅማችን እየተሻሻለ መምጣቱ የሚታይ ነው። ግን ኢኮኖሚ ውስጥ ካለው አቅም አንጻር ገቢ ገና አልሰበሰብንም / አልጀመርንም የሚል ድምዳሜ ላይ ነው መንግሥት የደረሰው።

ጎረቤት ሀገር አማካይ 15% እና 14% በመሆነበት ሁኔታ እኛ 7% አካባቢ ከሀገራዊ ምርት አንጻር እየሰበሰብን ገቢ እየሰበሰብን አይደለም።

ይህ ሪፎርም አንዱ አንጓ በፊሲካል ፖሊሲው ስር የተቀመጠው ሀገራዊ ገቢ ማሳደግ ነው።

4% GDP በሚቀጥለው ሶስት ዓመት እንጨምራለን ማለት ቀላል ስራ አይደለም ከባድ ነው። በዚህ ዓመት ሰኔ 30 ላይ 527 ቢሊዮን አካባቢ ገቢ አውጀን ከወር በኋላ 851 ቢሊዮን ማወጅ በጣም ከባድ ነው።

ይህንን ስናደርግ ግን ሌሎች ሀገራት እንዳደረጉት ተጨማሪ ታክስ በመጣል፣ ወይም የታክስ ምንጣኔ በመጨመር አይደለም። ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን distortion በማስተካከል ነው ለመጨመር ያሰብነው።

አንድ ምሳሌ ላንሳ፦ የመኪና አስመጪዎች ጋር ገበያ ተኪዶ መኪና ሲገዛ የመኪና ዋጋው 10 ሚሊዮን ከሆነ ገቢዎች ሄደው ደረሰኝ የሚሰጡት ወይ የ1 ሚሊዮን ወይ 2 ሚሊዮን ነው። ስንት እንደሚሸጥ እየታየ ማንም ሰው ገበያው ላይ የሚያውቀውን። ይሄ መስተካከል አለበት።

ከዚህ በፊት በነበረ ሁኔታ እነሱም ችግር ነበረባቸው (መኪና አስመጭዎች) LC የሚሰጣቸው 1000 ዶላር ይሆናል ፤ ሌላው ብር ከኤክስፖርተር ገዝተው ወይ ከጥቁር ገበያ አሰባስበው መኪና ገዝተው ፣ ጅቡቲ አምጥተው ነው የሚሸጡት ይሄን ችግር በመሰረታዊነት ነው ሪፎርሙ የሚቀይረው።

ሁሉ ነገር ግልጽ ይሆናል። ዋጋ እንዲታወቅ እና ግልጽ በሆነ መንገድ እንዲሆን ይደረጋል ሪፎርሙ።

ይህንን መሰል እና በተለያየ ቦታ ያልሰበሰብናቸው ፦

- መርካቶ አካባቢ ያለው የንግድ እንቅስቃሴ ይታወቃል፣

- የንግድ ሂደት ላይ ደረሰኝ መቁረጥ አለመቁረጥ ችግር ይታወቃል

- ጉምሩክ ላይ የ1 ሚሊዮን አይተም አስገብቶ እዛ ቀረጥ ከፍሎም አስገብቶ ገቢዎች ሄዶ ሪፖርት የሚያደርገው ምናልባት የ100 ሺህ እቃ ይሆናል ... ያንን የሚያስታርቅ ዳታውን reconcile የሚያደርግ ሲስተም እየዘረጋን ነው።

እስካሁን ታክስ ሳይከፍል ይከብር የነበረው ባለሃብት አሁን ቶሎ ወደ መስመር መግባት አለበት። ይሄን የሚፈቅድ ነገር አይኖርም።

ጠንካራ የሆነ የ enforcement ስራ ይካሄዳል። እነዚህ የዳታ ጉዳዮችም አሉ። ታክስ ሳይከፍል ሃብት የሚያፈራውን ደግሞ even ያፈራውን ሃብት መውረስ የሚያስችል ለህግ ድጋፍ ተቀምጧል።

ስለዚህ አዲስ የጨዋታ ሕግ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ የመጣ ያለው። ይሄ የታክስ መሰብሰብ አቅማችንን እንድናሳድግ ትልቅ አቅም ይሆነናል። የልማት ትልማችንን ለማሳካት፣ የራሳችንን ወጪ በራሳችን ገቢ ለመሻፈን ያስቀመጥነውን ራዕይ እንድናሳካ እድል ይፈጥርልናል። "

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#Ethiopia

የ3000 ሜትር የወንዶች መሰናክል የፍጻሜ ውድድር በመካሄድ ላይ ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ፦
🇪🇹 በአትሌት ለሜቻ ግርማ ፣
🇪🇹 በአትሌት ጌትነት ዋሌ
🇪🇹 በአትሌት ሳሙኤል ፍሬው ተወክላለች።

መልካም ዕድል !

Via
@tikvahethsport

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬም ሜዳሊያ ውስጥ አልገባንም። @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Ethiopia

በ3000 ሜትር መሰናክል ፍጻሜ ወደ ማጠናቀቂያው በጥሩ ኃይል ወደፊት እየመጣ የነበረው እና ለኢትዮጵያ ሜዳሊያ ሊያስገኝ ይችላል ተብሎ የተጠበቀው ለሜቻ ግርማ ወድቆ ውድድሩን ማጠናቀቅ አልቻለም።

ጉዳቱ የከፋ እንዳይሆንበትና ጤናው  ደህና እንዲሆን እንመኛለን።

ሳሙኤል ፍሬው 6ኛ ፤ ጌትነት ዋለ ደግሞ 9ኛ ሆነው ነው የጨረሱት።

ሞሮኮ፣ አሜሪካ እና ኬንያ ሜዳሊያዎቹን ወስደዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#LamechaGirma : የ3,000 ሜትር መሰናክል ሪከርድ ባለቤቱ ለሜቻ ግርማ በውድድሩ ወቅት ሲዘል ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በፍጥነት ወደ ሆስፒታል እንደተወሰደ ተነግሯል።

አትሌቱ በደረሰበት ጉዳት ሳቢያ እራሱን እንደሳተ አሁንም ሙሉ በሙሉ እንዳልነቃ ፤ በሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኝ ፤ ያለበት ሁኔታ ግን ለህይወቱ አስጊ የሚባል እንዳልሆነ ተሰምቷል።

ልጃችን ጉዳቱን ክፉ አያድርግበት ፤ ጤናውም አይጓደልበት !

ደህና ሆኖ ዳግም በውድድር መድረክ ላይ ሀገሩን ወክሎ እንድናየው እንመኛለን።

Photo Credit - AFP

@tikvahethsport @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia

" በእግሩ እና በጭንቅላቱ ላይ ጉዳት አልደረሰበትም " - የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ ራሱን ከሳተበት በመንቃት መናገር መጀመሩን ሌኪፕ የተሰኘው ታቃዊው የፈረንሳይ ጋዜጣ አስነብቧል።

በአሁን ሰዓት ተጨማሪ የህክምና ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝም ጋዜጣው ገልጿል።

የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ቃል አቀባይ በበኩላቸው ፤ " አትሌት ለሜቻ ግርማ አስፈላጊ የሆነ አፋጣኝ ህክምና ተደርጎለታል " ብለዋል።

ስለ ጉዳቱ ዝርዝርና የህክምና ውጤቱን በተመለከተ ግን በይፋ ምንም የተባለ ነገር የለም።

በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፥ " አትሌት ለሜቻ ግርማ በውድድሩ ላይ በደረሰበት የመውደቅ አደጋ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ በተደረገለት የሲቲ ስካን ምርመራ በእግሩና በጭንቅላቱ ላይ ጉዳት እንዳልደረሰት ከሆስፒታል የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች አረጋግጠዋል " ሲል በይፋ አሳውቋል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
2 ቀን ቀረው!

🏆 የአንድን ከተማ ሕዝብ በሁለት ጎራ የከፈሉት ማን ዩናይትድ እና ማን ሲቲ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋዜማ በኮሙኒቲ ሺልድ ዋንጫ ተፋጠዋል!

⚽️ ዩናይትድ እና ሲቲ የሚያደርጉትን የዋንጫ ፍልሚያ ቅዳሜ ነሐሴ 4 በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይከታተሉ!

🔥 ዋንጫው የማን ነው? 

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ የኮሙኒቲ ሺልድ ጨዋታ ከትንታኔ እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ልዩ በቀጥታ ይከታተሉ!    

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
#አበሽጌ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ጉራጌ ዞን፣ አበሽጌ ወረዳ ዋልጋና ዳልጌ ከተሞች የሚኖሩ በተለይም የአማራ ወጣቶች ፣ ባለሀብቶችና አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች በጸጥታ ኃይል በአፈሳ እየተያዙ መሆናቸውን ተከትሎ ወጣቶች ከቤት ለመውጣት ፍርሀት ውስጥ መሆናቸው ተሰምቷል።

አካባቢው በተለይ ከኦሮሚያ ጋር የሚዋሰንባቸው መንደሮች ካሁን በፊት ግጭቶች መፈጸማቸውን ተከትሎ በስጋት መቆየታቸውን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ከሰሞኑ እየሆነ ያለው ነገር እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ወጣቱ በፍርሀት ቤቱ ቢቀመጥም አንዳንዶቹ ቤታቸዉ ባሉበት መያዛቸዉን ተከትሎ ፍርሀቱ ከፍ ሊል ችሏል።

ቃላቸውን የሰጡ አንዳድን ነዋሪዎች አፈሳው እየተደረገ ካለባቸው ምክንያቶች አንዳንዶቹ " እናተ ፋኖን ትደግፋላችሁ፤ ከፋኖ ጋርም ግንኙነት አላችሁ " የሚል ነው ብለዋል።

ሁኔታውን በተመለከተ ማን ማንን ነው እየያዘ ያለው ? ስንል የጉራጌ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ገና ደገሞን ጣይቀናል።

እሳቸውም " የተቀናጀ የጸጥታ ኃይል ወንጀለኞችን እየያዙ ነው " ብለዋል።

በተጨማሪም ሰው ፍርሀት ውስጥ ነው ለሚባለው " ወንጀል ውስጥ እጁ ካለበት ሰው ውጭ ንጹሀኑ ፍርሀት ሊገባው አይገባም " ሲሉ መልሰዋል።

" አሁን ላይ የብሄራዊ ደህንነትን ጨምሮ የፌደራል ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት በአካባቢዉ ተሰማርተዉ አሰሳ በማድረግ የጥፋት ኃይሎችን እየያዙ ነው " በማለት አካባቢዉ በፍጥነት ወደነበረ ሰላሙ ይመለሳል ብለዋል።

ዋና ኢንስፔክተሩ አክለዉ " እንቅስቃሴዉ በአበሽጌ ወረዳና በኦሮሚያ ወሰን መካከል መሆኑን በመግለጽ ሰላማዊ ሰዎች ያለስጋት የእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸውን እንዲቀጥሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia ለተከታታይ ቀናት የውጭ ምዛሬ ዋጋ ባለበት እየቀጠለ ነው።

የንግድ ባንክ ዛሬም ለ5ኛ ተከታታይ ቀን የውጭ ምንዛሬው ላይ ምንም የተለየ ለውጥ ሳያደርግ ውሏል። ዶላር 95.6931 ይገዛል፣ 101.4347 ይሸጣል።

በግል ባንኮችም ያን ያህል ጭማሪ አልታየም።

ትላንትና ብሔራዊ ባንክ 27 ባንኮች በተሳተፉበት ባወጣው ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ መሸጡን ይታወሳል።

ይኸው አማካይ ዋጋ የዛሬ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጠቋሚ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ነው ማለቱ አይዘነጋም።

በሌላ በኩል ምንም እንኳን በሀገሪቱ  ውስጥ ያሉት ባንኮች  በየዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ዋጋቸውን እያወጡ ቢሆንም ዶላር እንደልብ ማግኘት ገና አልተጀመረም።

@tikvahethiopia