TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia

እስካሁን በፓሪስ ኦሎምፒክ ያለን ሜዳሊያ ሁለት ብቻ ነው።

አንዱ ብር በበሪሁ አረጋዊ አንዱ ደግሞ በፅጌ ዱጉማ ነው የተገኘው።

አለቀ ! እስካሁን ወርቅ የለም። ነሃስ የለም።

በአጠቃላይ 68 ሀገራት በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት ሲችሉ ኢትዮጵያ 52ኛ ደረጃን ይዛ ትገኛለች።

በአፍሪካ ከኬንያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ዩጋንዳ ፣ አልጄሪያ ቀጥለን ነው የምንገኘው።

ቀጣይ የፍጻሜ ውድድሮችን በተስፋ መጠበቅ ነው።

@tikvahethiopia
🔈 #የተማሪዎችድምጽ

° " ብዙ ልጆች ተቸግረዋል፡፡ የምግብ አገልግሎት ተከልክለናል " - የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንትርን ሀኪሞች

° " ጥያቄያቸው ይቅረብና ፍትሃዊ ከሆነ እናያለን፡፡ የሚመለከተው አካል ለምን እንዳላስተናገደም የምቀጣ ይሆናል " - ዩኒቨርሲቲው

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 6ኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎች፣ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የምግብ አገልግሎት የሚሰጥ ሆኖ ሳለ እነርሱ ግን ምግብ መከልከላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

ቅሬታቸውን ለተማሪዎች አገልግሎት ቢያቀርቡም መፍትሄ በማግኘት ፋንታ " እናባርራችኋለን " የሚል ዛቻ እንደደረሰባቸው አስረድተው፣ "  ብዙ ልጆች ተቸግረዋል፡፡ የምግብ አገልግሎት ተከልክለናል " ነው ያሉት።

ዩኒቨርሲቲውን የተቀላቀሉት 2010 ዓ.ም እንደሆነ ፤ በተለያዩ ችግሮች ሁለት ዓመታት የሚጠጋ ጊዜ እንደባከነባቸውና እንዳልተካካሰላቸው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ ተማሪዎች ነጻ የህክምና አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ ሆኖ ሳለ እነርሱ ህክምና መከልካላቸውን አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የተማሪዎቹን ቅሬታ ይዞ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚደንት ዶክተር መንገሻ አየነን አናግሯል።

ዶክተር እሳቸው ጋር ምንም አይነት የቀረበላቸው ቅሬታ እንደሌለ ገልጸው፣ ለማን ቅሬታ እንዳቀረቡ ኢንተርን ሀኪሞቹ በድጋሚ እንዲጠየቁ አሳስበዋል፡፡

እሽ በማለት ቅሬታ አቅራቢዎቹን ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አሳውቃችሁ ነበር ? ስንል ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽ፣ "ለዶክተር መንገሻ አልደረሰም። ለተማሪዎች አገልግሎት አቅርበናል። ለዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ጉዳዮች ቢሮ አቅርበናል" ብለዋል።

ለምን ለዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አካላት እንዳላቀረቡ ሲያስረዱም፣ " የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ጉዳዮች ቢሮ 'ይሄ ጉዳይ ከእኔ አልፎ ወደ ላይ ቢሄድ አውቶማቲካሊ ሴኔት ሰብስቤ ፈርሜ  አባርራችኋለሁ' አለን " ብለዋል።

" ቅሬታችንን ለዶክተር መንገሻም አላሳወቁትም ከታች ነው ያስቀሩት " ሲሉም አክለዋል፡፡

ቅሬታው ደርሷቸዋል የተባሉት አካላት ለጊዜ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑ ሲሆን፣ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ቅሬታ ያቀረቡበትን ክፍል በመግለጽ በድጋሚ ስለጉዳዩ ጠይቀናቸዋል፡፡

ፕሬዚደንቱ መንገሻ (ዶ/ር)፣ የኢንተርን ሀኪሞቹ ቅሬታ ዩኒቨርሲቲው ያላወቀው ቅሬታ እንደሆነ አስረድተው፣ ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

" ፕሮፌሰር የሺጌታ የሚባል ሲኢድ አለን ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅን ሙሉውን የሚመራ የፕሬዚዳንቱ ተወካይ ነው እዚያ ግቢ " ያሉት መንገሻ (ዶ/ር)፣ ' ፕሮፌሰሩን ይጠይቁ፡፡ እሱ ካልፈታላቸው ወደ እኔ ይመጣሉ ወይም ደብዳቤ ካላቸው ያምጡ " ብለዋል፡፡

" ጥያቄያቸው ይቅረብና ፍትሃዊ ከሆነ እናያለን፡፡ የሚመለከተው አካል ለምን እንዳላስተናገደም የምቀጣ ይሆናል " ሲሉ አክለዋል፡፡

(ጉዳዩ ከምን እንደደረሰ ተከታትለን መረጃ የምናቀርብ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Alert🚨 " እስካሁን የ11 ሰዎች አክስሬን ተገኝቷል " - የካዎ ኮይሻ ወረዳ በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ ዛሬ ረፋድ 5 ሠዓት አካባቢ በተከሰተ የመሬት ናዳ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡ በተከሰተው አደጋ እስካሁን በተደረገ ፍለጋ የ11 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል። የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የካዎ ኮይሻ ወረዳ አስተዳደር አሳውቋል። ከቀናት በፊት በዚሁ አካባቢ…
#ወላይታ🕯

" 5 አስክሬን የቀረ ስላለ እየተፈለገ ነው " - ዞኑ

በወላይታ ዞን በካኦ ኮይሻ እና ክንደ ኮይሻ የመሬት ናዳ መድረሱ ይታወቃል።

በካኦ ኮይሻ በደረሰው አደጋ የሁሉም ሰዎች አስከሬን ስላልተገኘ ፍለጋው እንደቀጠለ መሆኑን የዞኑ ኮሚኒኬሽን መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡

" እስካሁን ድረስ 6 አስክሬን ወጥቶ 5 የቀረ ስላለ እየተፈለገ ነው " ብሏል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ መስፍን ቶማስ ምን አሉ ?

- ዛሬም አስክሬን ሲፈለግ ነው የዋለው።

- እንደ ዞን በአጠቃላይ የ13 ሰዎች ሕይወት ነው በናዳ አደጋ ምክንያት ያለፈው።

- ተከታታይነት ያለውን ድጋፍ የሚፈልግ ስለሆነ ውይይት እየተደረገ ነው።

- ከስጋት አካባቢዎች ነዋሪዎችን አሽሽተን ጊዜያዊ መጠለያ ነው ያሉት። አስፈላጊ የሆነ ምግብ ነክና የቁሳቁስ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ አደጋው የደረሰው መንደር ላይ ነው ? በሚል ጠይቋል። " አርሶ አደር መንደር ላይ ነው፡፡ ከላይ ተራራ ጫፍ ላይ ተናደና ተንሸራቶ ወረደ " ሲል ዞኑ ገልጿል።

ቤት ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት አለ ? በቁጥር ምን ያክል ነው ? ለሚለው ጥያቄያችን " አለ እንጂ በጣም ብዙ አለ፡፡ ቤቶች ላይ፣ በንብረት ላይም የደረሰ ጉዳት አለ፡፡ በእርሻ ማሳዎችም በተመሳሳይ " ነው ብሏል።

የተደራጀ አሀዛዊ መረጃ በቀጣይ እንሰጣችኋለን ሲል ገልጿል።

ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ችግር በአካባቢው ተከስቶ ያውቃል እንዴ ? ለሚለው ጥያቄያችን " ይቀያየራል፡፡ አንድ ጊዜ በዚህ ሲከሰት ሌላ ጊዜ ሌላ ቦታ ነው፡፡ አሁን የተከሰተበት አካባቢ ላይ ካሁኑ ቀደም አላጋጠማቸውም ነበር " ብሏል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ጾመፍልሰታ

ጾመ ፍልሰታ ረቡዕ ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ይጀምራል።

ጾሙን አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከቅዱስነታቸው መልዕክት ፦

" የተወደዳችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ልጆቻችን !

ጾም ፈቃደ ሥጋን በማድከምና ፈቃደ ነፍስን በማጎልበት ምሕረተ እግዚአብሔር መሻታችንን የምናሳይበት መንፈሳዊ ማመልከቻ ነው ፤ ጾም ከጥንት ጀምሮ የነበረ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ነው።

ቀደምት አበው በጾም ምክንያት ፦
° ከጥፋት ድነዋል፤
° የለመኑትንም አግኝተዋል፤
° ምስጢርም ተገልጾላቸዋል፤
° ዲያብሎስንም ድል አድርገውበታል፡፡

እኛም ዛሬ ጾምን ስንጾም በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን ብሎም በዓለም ዙሪያ ሁሉ ስጋትን እየጫረ ያለው የጥፋት እንቅስቃሴ እግዚአብሔር እንዲያስቆምልን ከልብ በመጸለይ ሊሆን ይገባል።

ይህንንም ስናደርግ በጸሎት ብቻ ሳይሆን ንስሐ በመግባት እና ቅዱስ ቁርባንን በመቀበል እንደዚሁም የሰላም የፍቅርና የዕርቅ ሰው ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት በመቆም ሊሆን ይገባል፡፡

ችግሮችንና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በምክክር ለመፍታት የሚደረገው ጥረትም በእጅጉ ሊደገፍ ይገባል፤ ግጭትና ጦርነት ከሚያጠፋን በቀር ሊያተርፍልን የሚችል አንዳች ጥቅም የለም፡፡

በመሆኑም በየትኛውም የሀገራችን አካባቢ
ላይ ያላችሁ ልጆቻችን እባካችሁ ፦

ለሰላም ለውይይት እና ለሰው ልጆች መብት መከበር ቅድሚያ ስጡ፤

ግድያ ፣ ዕገታ ፣ አብያተ ሃይማኖትን መዳፈር ፣ ዘረፋና ቅሚያ ፣ የሴት ልጅን መድፈርና ሰውን ማንገላታት አቁሙ፤

እነዚህ ድርጊቶች ሰብአዊነትን ዝቅ የሚያደርጉ ፣ እግዚብሔርን የሚያስቆጡ፣ በታሪክም የሚያሳፍሩ ናቸውእነዚህን ሳናርም የምንጾመው ጾም ትርጉም ስለሌለው ንስሐ ገብተን ከእንደዚህ ያለው ድርጊት ርቀን ጾሙን መጾም ይገባል፤ ይህን ስናደርግ ጾማችን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ ይኖረዋል፡፡ "

(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በሙሉ መልካም የፍልሰታ ጾም ይሁንላችሁ !


@tikvahethiopia
#ዮናታን_ቢቲ_ፈርኒቸር
Yonatan BT Furniture

የውበት እና የጥራት ዳር ድንበር!


አድራሻችን፦
1.ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251995272727
2.ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251957868686
3.ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251993828282

👉 Telegram:  https://t.iss.one/yonatanbt_furniture
👉 Facebook:  https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
👉 TikTok: https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture

#yonatanbtfurniture #furniture #modernfurniture #kitchen #kitchencabinet
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዕለታዊ : ንግድ ባንክ ዛሬ ለ4ኛ ተከታታይ ቀን የውጭ ምንዛሬው ላይ ምንም የተለየ ለውጥ ሳያደርግ ቀርቧል።

ዶላር እንደትላንቱ 95.6931 ይገዛል ፣ 101.4347 ይሸጣል።

በአብዛኛዎቹ የግል ባንኮች ላይም ከሰሞኑን የተለየ ጭማሪ የታየበት የውጭ ምንዛሬ ዋጋ አልወጣም።

በተለያዩ ባንኮች ያለው የዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia