TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia #Italy

ኢትዮጵያ ዛሬ ከጣሊያን ጋር የ25 ሚሊዮን ዩሮ የፋይናንስ ስምምነት እንደተፈራረመች ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

13 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ በድጋፍ መልክ ሲሆን 11 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ብድር ነው፤ ይህም ለአካባቢና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ይውላል ተብሏል።

በተጨማሪም ስምምነቱ የ ' ገበታ ለትውልድ ' ን እንደሚደግፍ ገንዘብ ሚኒስቴር አመልክቷል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

" ... የመንግስት መገናኛ ብዙኃን የአንድን ወገን ሀሳብ ብቻ ወደ ሕዝብ ከማድረስ አልፈው ይኽን ከፍተኛ የዋጋ ንረትን ሊያስከትል የሚችል ውሳኔ እንደ ምስራች በ ' እንኳን ደስ አላችሁ ! ' አጅበው ማቅረባቸው ለሕዝብ ያላቸውን ንቀት ያሳዩበት ፤ አሁንም ከገዢው ፓርቲ ጥገኝነት ወጥተው ሙያቸውን የሚያስከብሩ የመረጃ ብዝሃነትን እና ፍትሃዊነት የሚያረጋግጡ ዘገባዎችን ለመሥራት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላቸው ያረጋገጡበት ነው። " - የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ)

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ " ፖሊሲ የማውጣት ሉዓላዊነትን የሚገድብ ማሻሻያ ውጤቱ ቀውስ ጋባዥ ትርፉም ሀገራዊ ዕዳ ነው " በሚል የላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል። #EZEMA

@tikvahethiopia
“ በሁለቱ ክሶች ትላንት ነፃ ተብያለሁ ” - ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ “ የእድሜ ልክ እስራት ያስፈርድበታል ” ሲባሉበት ከነበረው ክስ ጭምር ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነጻ ተብሏል።

ጋዜጠኛው፣ በሐምሌ 2014 ዓ/ም ላይ “ ጥብቅ የመከላከያ ሠራዊትን ምስጢር ማባከን ፤ መከላከያ ሠራዊቱን መከፋፈል ፤ የመከላከያ ሠራዊቱን ስም ማጥፋት ” የሚሉ ሦስት ክሶች ተመስርቶበት ነበር።

በ3ኛው ክስ የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ/ም  አንቀጽ ተቀይሮ እንዲከላከል ተወስኖ ነጻ እንደተባለ አስታውሶ ትላንት ደግሞ ሲከራከርባቸው በነበሩ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ክሶች ነፃ መባሉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

“ በሁለቱ ክሶች ትላንት ነፃ ተብያለሁ ” ነው ያለው።

‘ ነጻ ’ የተባለባቸው ክሶች የእድሜ ልክ እና ከ10 እስከ 15 ዓመታት እስራት ያስፈርድባቸዋል ተብሎ በነበሩት ክሶች ነው።

ጋዜጠኛ ተመስገን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ መጀመሪያውንም ስከሰስ መከላከያ 'ምስጢር አወጣ፤ ሠራዊቱን ከፋፈለው'  ብሎ ነበር የከሰሰኝ ” ብሏል።

“ ያ ግን ውሸት ነው። መከላከያ ውስጥ ራሱ የነበሩ ችግሮችን በምክንያት አስደግፈን ይፋ ስላደረግን ነው ” ሲል አክሏል።

ክሶቹ ነጻ የሚያስብሉ ሆነው ሲገኙ ብዙ ውጣ ወረድ እንደማሳለፈህ መጠን የካሳ ክፍያ ታስቦልሃል ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ በሰጠው ምላሽ፣ “ እስካሁን ድረስ የተባለ ነገር የለም። ግን ጠበቆችን አማክራለሁ ” ብሏል።

“ ምክንያቱም መንግስት ሰፊ ተቋም ነው። ንጹሐን ሰው እያነሱ እያሰሩ ፣ እያሰቃዩ፣ ሚዲያ እያስቆሙ መጨረሻ ላይ በፍርድ ቤት ነጻ ሲባል ለዚህ ሁሉ መጎሳቆልና ኪሳራ ምክንያት የሆነው መንግስት ደግሞ ካሳ ሊከፍል ይገባል ብዬ አስባለሁ ” ሲል አክሏል።

ጋዜጠኛው ተመስገን ደሳለኝ ተከሶበት የነበረው ክስ እና የፍርድ ሂደቱ ምን ይመስል ነበር ? በዚህ ያንብቡ : https://telegra.ph/TikvahEthiopia-07-31

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ በሁለቱ ክሶች ትላንት ነፃ ተብያለሁ ” - ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ “ የእድሜ ልክ እስራት ያስፈርድበታል ” ሲባሉበት ከነበረው ክስ ጭምር ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነጻ ተብሏል። ጋዜጠኛው፣ በሐምሌ 2014 ዓ/ም ላይ “ ጥብቅ የመከላከያ ሠራዊትን ምስጢር ማባከን ፤ መከላከያ ሠራዊቱን መከፋፈል ፤ የመከላከያ ሠራዊቱን ስም ማጥፋት ” የሚሉ ሦስት ክሶች…
#Ethiopia

ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ  ጋር በነበረው ቆይታ ምን መልዕክት አስተላለፈ ?

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፦

" እስር ቤት በነበርኩበት ጊዜ በማዕከላዊ፣  ቂሊንጦ አያያዙ ጥሩ አልነበረም። ብዙ ችግሮችም ነበሩ። ሰው ሊታሰርባቸው የማይችሉ ፤ ዋጋ የሚያስከፍሉ የሰቆቃ ቦታዎች ናቸው።

እኛ ጋዜጠኞች ነን። ሚዲያን በተመለከተ ለሚፈጠሩ ጥፋቶች አገሪቷ የራሷ የፕሬስ ህግ አላት፤ 2001 ዓ/ም የወጣ ፤ ከዚያ በኋላም ከ2010 ዓ/ም በኋላ አዲሱ መንግስት ሲመጣ ያንን ህግ አሻሽሎ አውጥቶታል።

ግን ህጉ ምንም ሥራ ላይ አይውለም። Even ጥፋት ሰርተን ቢሆን ኖሮ ራሱ መጠየቅ የነበረብንም በፕሬስ ህጉ  ነበረ።

ትልቁ ችግር መንግስት ህግን አለማክበሩ ነው።

ኢህአዲግ እያለ ህጎቹ በጣም አፋኝ ነበሩ ፤ ነገር ግን ከህጉ ወጥቶ ሌላ ጥፋት አይሰራም ነበር።

በእነዛው አፋኝ ህጎቹ ነው ሲያግድ የነበረው። የአሁኑ መንግስት ደግሞ በጣም የተስፋፉ ህጎች አውጦቷል፤ ህጉን ግን አይጠቀምበትም።

ከህግ ውጪ እየሄደ ነው። ከህግ ውጪ ባይሄድ መልካም ነው። "


ፎቶ ፦ ፋይል

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

10 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል !

የመመረቂያ ጽሁፍ በማቅረብ ላይ የነበረችን  ተማሪ በጥይትና በስለት ለመግደል የሞከረው  ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጥቷል።

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመመረቂያ  ጽሁፍ በማቅረብ ላይ የነበረችን ተማሪን ከጀርባዋ ሆኖ በጥይት ተኩሶ በመምታትና በስለት  ደጋግሞ በመዉጋት ለመግደል የሞከረ  ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱ ፖሊስ ገለፀ።

ተከሳሽ ፦ አማኑኤል እንድርያስ
ነዋሪነቱ ፦ በጉራጌ ዞን አብሽጌ ወረዳ ቁሊት ሁለት ቀበሌ
የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው ፦ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ
የክሱ ዝርዝር ፦ ግለሰቡ የግል ተበዳይን ለመግደል በማሰብ ወልቂጤ ዩንቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ የጦር መሳሪያና ስለት ይዞ ይገባል።

የመመረቂያ ምርምር ጥናታዊ ፅሁፍ በምታቀርብበት ክፍል ውስጥ ከጀርባዋ ሆኖ  በመቀመጥ በያዘው ሽጉጥ ተኩሶ ትከሻዋን  መቷታል።

በኋላም ደንግጣ ለመሮጥ ስትሞክር ተከታትሎ ጉሮሮዋን አንቆ በመያዝ አስቀድሞ ባዘጋጀዉ ስለታም ቢላዋ ጭንቅላቷን 6 ጊዜ ያህል ደጋግሞ በመዉጋት የመግደል ሙከራ ወንጀል በመፈጸሙ ነው የተከሰሰው።

ተከሳሹ የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ተማሪ ነው። ከዚህ በፊት ተጎጂዋ እና የግል ተበዳይን በመደብደቡ በዲሲፕሊን ተከሶ በዩንቨርስቲዉ አመራሮች ለሁለት አመት ከትምህርት ገበታዉ እንዲታገድ በመወሰኑ ወንጀሉን በዚህ ቂም ተነሳስቶ እንደፈፀመ የተከሳሹ የክስ መዝገብ ያስረዳል።

የጉራጌ ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤትም ተከሳሹ  የጦር መሳርያና ጥይቶችን የመያዝ የፀና ፍቃድ ሳይኖረው በተከለከለ ስፍራ የጦር መሳሪያ  ይዞ በመገኘቱ እና በፈፀመዉ የመግደል ሙከራ ወንጀል የቀረበበትን ክስ  ማስተባበል ባለመቻሉ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

በጥይትና በስለት ጉዳት የደረሰባት የግል ተበዳይ ህክምና ተከታትላ አሁን  ላይ በመልካም ጤንነት ላይ ትገኛለች።

ለማስታወሻ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/88024?single

#CentralEthiopiaRegionPolice  #WolkiteUniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ተጨማሪ በጀት ለፓርላማ ሊቀርብ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ያገኘውን ድጋፍ እና ብድር የያዘ ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ለፓርላማ አቅርቦ እንደሚያስጸድቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል። ይህ የተናገሩት ዛሬ በነበረው የምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ ወቅት ነው። ተጨማሪ በጀቱ ፦ ➡️ ለዝቅተኛ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች ለሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ፣ ➡️ ለነዳጅ…
#Ethiopia : " የዋጋ ንረት (inflation) ጫና እንዳለ በተደጋጋሚ ተነስቷል።

ይሄ ሪፎርም (የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ማለታቸው ነው) በመጀመሪያዎቹ
#ወራት ወይም #ዓመት ጫና የሚያመጣ መሆኑ ይታወቃል።

በዘላቂነት የዋጋ ንረትን (inflation) ለመቆጣጠር ግን ከዚህ ውጭ አማራጭ የለንም። " - የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ (ለህ/ተ/ም/ቤት የተናገሩት)

ገና በመጀመሪያዎቹ ቀናት " ዶላር ጨምሯል " በሚል የታዩት መሰረታዊ ነገሮች ላይ ዋጋን የመጨመር አዝማሚያዎች ዜጎችን በተለይ ደግሞ በዝቅተኛ ገቢ ሚኖሩትን እጅግ በጣም ከፍተኛ ጭንቀት ላይ የጣለ ሆኗል።

ከዛሬ ነገስ ምን ይፈጠር ይሆን ? በሚልም እንቅልፍ ነስቷቸዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ሊመለሱ ነው!

አዳዲሱ ተጫዋቾች ያስፈረሙት ቡድኖች ሊጉን ለመጀመር ዝግጁነታችውን አሳውቀዋል!

እናንተስ የአዲሱ ዓመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ማን የሚሆን ይመስላችኋል?

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/dg1

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ልጄን አድኑልኝ " - መምህርቷ እናት መምህርት አልሻምጌጥ ንጉስ ፤ ልጇ የአብቃል በተወለደ በሀያ አንድ ቀኑ ነው የልብ ህመም እንዳለበት ያወቀችው። ላለፉት 5 አመታት የህጻናት የልብ ቀዶ ጥገና መዕከል አስመዝባ ብጠብቅም ወረፋ ሊደርሳት አልቻለም። " አሁን ልጄ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደረሰ " ስትል ገልጻለች። ከሀያ አንድ ቀኑ ጀምሮ ከሀዋሳ አዲስ አበባ እየተመላለሰች ሰርጀሪውን ስትጠብቅና ማስታገሻ…
#Update

" የተሰበሰበልንን 300 ሽህ ብር ከፍለን ወረፋ ብናስይዝም ገንዘቡ ሊሞላልን ባለመቻሉ ህክምናዉ ሊያልፈን ነው " -  ወላጆች

ከዚህ ቀደም በልብ ክፍተት ህመም እየተሰቃየ የሚገኘዉን ህጻን ህክምና በተመለከተ ለኢትዮጵያ ህዝብ የድጋፍ ጥሪ መድረሱን ተከትሎ አንዲት ልበ ቀና እህት 200 ሺህ ብር እንዲሁም ከህዝቡ በተሰበሰበ 100 ሽህ ብር በድምሩ 300 ሺህ ብር ተከፍሎ ወረፋ ተይዞለት ነበር።

ይሁንና አሁን ላይ ወረፋዉ ቢደርስም ቀሪዉ ገንዘብ መሰብሰብ ባለመቻሉ የህጻኑ ወላጆች በከባድ ጭንቀት ዉስጥ የወደቁ ሲሆን የህጻኑ ስቃይም ከጊዜዉ መሄድ ጋር ተባብሶ ቀጥሎ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል።

" እባካችሁ የሆስፒታሉ ወረፋ ሳያልፈን ልጃችንም ሳያመልጠን ድረሱልን " የሚሉት የህጻኑ ወላጆች መምህርት ወ/ሮ አልሻምጌጥ ንጉሴ እና አቶ አንተነህ ደፈርሻ " አቅም ያላችሁ በገንዘባችሁ አቅም የሌላችሁ ደግሞ በጸሎት አግዙን " ብለዋል።

በልብ ክፍተት ችግር እየተሰቃዩ ያለዉንና በተያዘለት ቀጠሮ የልብ ክፍተቱ የማይስተካከል ከሆነ ለከፋ ችግር ይወድቃል የተባለዉን ህጻን ለመርዳት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000243926053 አልሻምጌጥ ንጉሴ መኮንን መጠቀም እንደሚቻል መምህርቷ እናት ተናግረዋል።

በስልክ ቁጥር
0916155490 በመደወል ደግሞ አስገላጊ ማስረጃ እና ጥያቄ ቤተሰቡን መጠየቅ ይቻላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዕለታዊ : የዶላር ዋጋ ጨምሯል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዱ የአሜሪካ ዶላር በ77 ብር ከ1280 ሳንቲም እየተገዛ በ78 ብር ከ6706 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል። ፓውንድ ስተርሊንግ በተመሳሳይ ጨምሯል። አንዱ በፓውንድ በ94 ብር ከ3071 ሳንቲም እየተገዛ በ96 ብር ከ1932 ሳንቲም እየተሸጠ ነው። ትላንት መጠነኛ መውረድ አሳይቶ የነበረው ዩሮ ዛሬ ጨምሮ አድሯል። አንዱ ዩሮ በ83 ብር ከ3754…
#ዕለታዊ : ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ/ም በግል ባንኮች ያለው የውጭ ምንዛሬ ምን ይመስላል ?

ዶላር አሁንም መጨመሩን ቀጥሏል።

ትላንት አንዱን ዶላር በ74 ብር ከ7382 ሳንቲም እየገዛ በ76 ብር ከ2329 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረው ኦሮሚያ ባንክ ዛሬ መግዣውን ወደ 79 ብር ከ9448 ሳንቲም መሸጫውን ወደ 82 ብር ከ3431 ሳንቲም ጨምሮታል።

ዩሮ ትላንት በባንኩ 81 ብር ከ0386 ሳንቲም ሲገዛ ፤ 82 ብር ከ6593 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር ዛሬ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ 86 ብር ከ4363 ሳንቲም መግዣ 89 ብር ከ0294 ሳንቲም መሸጫ ተቆርጦለታል።

እጅግ ከፍተኛ ጭማሪ ከታየው የውጭ ምንዛሬ ሌላኛው የፓውንድ ስተርሊንግ ነው በባንኩ ዛሬ አንዱ ፓውንድ ስተርሊንግ 102 ብር ከ6171 ሳንቲም መግዣ 105 ብር 6956 ሳንቲም መሸጫ ተቆርጦለታል።

የUAE ድርሃምም ጨምሮ 21 ብር ከ7637 ሳንቲም መግዣ 22 ብር ከ4166 መሸጫ ተቆርጦለታል።

ሌሎች ባንኮችን ስንመለከት።

ወጋገን ባንክ ትላንት 1 ዶላር መግዣው 77 ብር ከ7401 ሳንቲም ፤ መሸጫው 79 ብር ከ2949 ሳንቲም ነበር ዛሬ ጨምሮ መግዣው 83 ብር ከ4681 ሳንቲም መሸጫው 85 ብር ከ1374 ሳንቲም ገብቷል።

ትላንት 1 ፓውንድ መግዣው 93 ብር ከ6991 ሳንቲም ፤ መሸጫው 95 ብር ከ5731 ሳንቲም ነበር ዛሬ ጨምሮ መግዣው 99 ብር ከ1057 ሳንቲም መሸጫው 101 ብር ከ0878 ሳንቲም ገብቷል።

ዩሮም በጣም ከፍ ብሏል። የዛሬ መግዣው 87 ብር ከ6115 ሳንቲም መሸጫው 89 ብር ከ3637 ሳንቲም ሆኗል።

ሌላኛውን ባንክ ዳሽንን እንመልከት።

ባንኩ ትላንት 1 ዶላር መግዣው 74 ብር ከ7394 ሳንቲም ፤ መሸጫው 76 ብር ከ2342 ሳንቲም ነበር ፤ በዛሬው ዕለት 80 ብር ከ9518 ሳንቲም እየገዛ በ84 ብር ከ9994 ለመሸጥ ቆርጧል።

ፓውድንም እጅግ ጨምሯል ትላንት መግዣው 91 ብር ከ8825 ሳንቲም  ፤ መሸጫው 93 ብር ከ7201 ሳንቲም ነበር ዛሬ ግን መግዣው 99 ብር ከ5199 ሳንቲም፤ መሸጫው ደግሞ 104 ብር ከ4959 ሆኗል።

ዩሮ የትላንት መግዣ 81 ብር ከ0400 ሳንቲም ፤ መሸጫ 82 ብር ከ6608 ሳንቲም ነበር ዛሬ ጨምሮ መግዣው 87 ብር ከ7761 ሳንቲም ፤ መሸጫው 92 ብር ከ1649 ሳንቲም ተቆርጦለታል።

#TikvahEthiopia #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
#Sidama

በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ  ያሉ የግል ትምህርት ቤቶች የ2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ የሚያከናውኑት ከሐምሌ 25 ቀን 2016 እስከ ነሀሴ 10 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን የከተማው ትምህርት መምሪያ አሳውቋል።

መምሪያው ፤ የመመዝገቢያ ክፍያ ት/ቤቱ በበጋ ወቅት ከሚያስከፍለው የትምህርት አገልግሎት ክፍያ ከ20% መብለጥ አይችልም ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በተጨማሪ ፥ ትምህርት ቤቶች በምዝገባ ወቅት ደስታ ወረቀትንና መሰል ቁሳቁሶችን በየትኛውም የእርከን ደረጃ መጠየቅ እንደማይችሉ አሳውቋል።

ትምህርት መምሪያው በ2017 ዓ.ም መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት የክፍያ ጭማሪ ያደረጉ ት/ቤቶች ዝርዝርም ይፋ አድርጓል።

ከዚህ ውጪ (ከላይ በዝርዝር ከተገለጹት ውጭ) ክፍያ ጨምሮ የተገኘ ት/ቤት እርምጃ ይወሰድበታል ሲል አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ክልል፣ በመቐለ ከተማ የፀጥታና ደህንነት ችግር በሚታይባቸው የከተማዋ አከባቢዎች የደህንነት መከታታያ ካሜራዎች ተገጠሙ።

እንዘህ የደህንነት መከታተያ ካሜራዎች ከ200 ሜትር እስከ አንድ ኪሎ ሜትር ባለው ርቀት የሚፈፀሙ ድርጊቶችን በጥራት የመቅረፅ እና የመከታተል አቅም እንዳላቸው የትግራይ ዲጂታል ኤጄንሲ አሳውቋል።

ቀበሌ 14 ፣ ቀበሌ 16 እና ቀዳማይ ወያነ በተባሉ በዛ ያለ የፀጥታ መደፍረስ በሚታይባቸው የከተማው አከባቢዎች ካሜራዎቹ መተከላቸው ነው የተነገረው።

@tikvahethiopia
#Oromia

የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተና ይፋ ሆነ።

በኦሮሚያ ክልል የ2016 የ6ኛ ክፍል እና 8ኛ ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ትምህርት ቢሮው የማለፊያ ነጥቡንም አሳውቋል።

የማለፊያ ነጥብ ፦
ለወንዶች እና ለሴቶች 50% እና ከዚያ በላይ፣
ለአርሶ አደር አከባቢዎች ለወንዶች 48%፣ ለሴቶች 45% እና ከዚያ በላይ፣
ለአካል ጉዳተኞች ለወንዶች 45% እና ለሴቶች 42% እና ከዚያ በላይ መሆኑን ቢሮው አመልክቷል።

ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን የመለያ ቁጥር እና ስም በማስገባት ውጤት መመልከት ይችላሉ።

የ6ኛ ክፍል፡-
https://oromia6.ministry.et/#result

የ8ኛ ክፍል፡-
https://oromia.ministry.et/#result

በተጨማሪም በቴሌግራም ቦት
@emacs_ministry_result_qmt_bot 'Start' ካሉ በኋላ ክልላቸውን ወይም ኦሮሚያ ክልል የሚለውን በመምረጥ የምዝገባ ቁጥራቸውን እና ስማቸውን በማስገባት ማየት ይችላሉ።

@TikvahEthiopia
#ጥቆማ

43,500 የመስክ መረጃ ሰብሳቢዎች ይፈለጋሉ ፤ ሞክሩት።

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 የበጀት ዓመት ለሚያካሂደው የሁለተኛው ዙር የግብርና ናሙና ቆጠራ 43500 የመስክ መረጃ ሰብሳቢዎች አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

ቅጥሩ 1 ዓመት ነው።

ለሥራው ማመልከት የሚፈልግ ማንኛው ዜጋ በአካል መገኘት ሳይጠበቅበት ይህን የሌበር ማርኬት ፖርታልን
https://lmis.gov.et በመጠቀም ማመልከት ይችላል።

መስፈርቶቹ ምንድናቸው ?

➡️ የትምህርት ደረጃ ፡- በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያለው ሆኖ ፖርታል ላይ በተገላጸው መሠረት፣
➡️ የስራው ቆይታ ፦ 1 ዓመት
➡️ ቋንቋ ፦ ለሥራ የሚመዘገቡበትን አካባቢ ቋንቋ የሚችል
➡️ ፆታ ፦ አይለይም
➡️ የጤና ሁኔታ ፡- በገጠርና በከተማ ቀበሌዎች ተዘዋውሮ መስራት የሚችልና ለዚህም ፍቃደኛ የሆነ

ለመመዝገብ ምን መከተል ይገባል ?

1. በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ የሌበር ማርኬት ፖርታል ላይ ይህን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም መረጃውን
lmis.gov.et መሙላት፣

2. ምዝገባ ካጠናቀቁ በኋላ በስልካችሁ የሰራተኛነት መለያ ቁጥር ይደርሶታል፣

3. የደረሰዎትን የሰራተኛነት መለያ ቁጥር በመያዝ እና አቅራቢያችሁ ወደሚገኝ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ በመሄድ አሻራ መስጠትና ምዝገባውን ማጠናቀቅ።

መረጃው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎትና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ነው።

#Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የወላጆችድምጽ #AddisGlobalAcademy “ ልጆቻችንን የት እናስመዝግባቸው ? ” - ወላጆች በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የሚገኘው “ አዲስ ግሎባል አካዳሚ ‘ለኮሪደር ልማት ያስፈልጋል ’ ” በመባሉ ልጆቻቸውን ሌላ ት/ቤትም ማስመዝገብ እንዳልቻሉ ወላጆችና ትምህርት ቤቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። ሌላ ት/ቤቶች እንዲያስመዘግቡ የተነገራቸው ሰሞኑን እንደሆነ፣ ሌሎች ት/ቤቶች…
#Update

" ለልማት ይፈለጋል ልቀቁ " በመባሉ የተማሪ ወላጆችን ያበሳጨው የአዲስ ግሎባል አካዳሚ ጉዳይ ከምን ደረሰ ?

አዲስ ግሎባል ትምህርት ቤት ያለበት ቦታ " ለልማት ይፈለጋል " በመባሉ የተማሪ ወላጆች ልጆቻችን የት እናስመዝግብ ? ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል መጠየቃቸው ይታወሳል።

ት/ቤቱ በበኩሉ፣ ባይሆን የአንድ አመት ጊዜ እንኳ እንዲሰጠው ነበር የጠየቀው።

ት/ቤቱ ምን አይነት ውሳኔ ላይ ደረሰ ?

ዛሬ ትምህርት ቤቱ አነጋግረን ነበር ፤ የትምህርት ቤቱ ዲን ት/ቤቱ በኪራይ ቤት ለማስተማር መገደዱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በኪራይ በማስተማሩ ለይ ተስማምታችሁ ነው ? ስንል ለጠየቅነው ጥያቄ የትምህርት ቤቱ ዲን ፤ " ምን እናድርግ ! በኪራይ እንድንሰራ መንግስትም ድጋፍ እንደሚያደርግልን ነግሮናል " ብለዋል።

" ልማቱ መቀጠል አለበት " ስለተባለ የመጨረሻው አማራጭ በኪራይ ቤት ተማሪዎቹን ማስተማር መሆኑን አስረድተዋል።

ስለዚህ ተማሪዎቹ አይበተኑም በኪራይ ቤቱ ለማመር ተስማምተዋል ? ለሚለው ጥያቄ፣ " ማስገደድ አንችልም። የሚፈልጉን ነባር ተማሪዎች አብረውን ይቀጥላሉ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" ኪራይም ባይሆን በራሳቸው መንገድ የሚለቁ ይኖራሉ " ያለው ትምህርት ቤቱ፣ " ስለዚህ አዲስም የያዝናቸው አሉ። ነባር ተማሪዎችንና ወላጆቻችንን ይዘን እንቀጥላለን " ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia