" የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በተለይ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ (ዶላር እና ሌሎች ምንዛሬዎች መውጣት መውረድ) ገበያውን እንደሚያናጋው የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እየገለጹ ይገኛሉ።
በተለይም ሁኔታው በዝቅተኛ ማህበረሰብ ክፍል / ዝቅተኛ የወር ገቢ ያለው ዜጋ ላይ የሚያሳድረው ጫና ከፍተኛ እንደሚሆን ለማንም ግልጽ ነው።
ነገር ግን የአንዳንድ ነጋዴዎች ተግባር ብዙዎችን ያበሳጨ ፣ ያስቆጣ ሆኗል።
' የማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ተደርጓል ' ከመባሉ ከወራት በፊት ያስገቡትን ምርት ፣ ቁሳቁስ በተለይ የምግብ ግብዓት ላይ ጭማሪ ለማድረግ ሲጥሩ ተስተውሏል።
እነዚህ ነጋዴዎች እዚሁ ከማህበረሰቡ ጋር አብረው የማይኖሩ ይመስል ያለ አንዳች ምክንያት በዚህ ልክ ራሳቸውን ክፉኛ ወደው ወገናቸውን ለመጉዳት የሚሄዱበት ርቀት አሳፋሪም ጭምር ነው።
አንዳንዶቹ ምርት ደብቀው " የለም " ማለትም ጀምረዋል።
ለመሆኑ ማሻሻያ ሳይደረግ በፊት ያስገቡት እና መጋዘን ውስጥ ያስቀመጡትን ምርት፣ ቁሳቁስ ላይ " ዶላር ጨምሯል " በማለት ፦
° በምን አግባብ ነው ዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉት ?
° ለምንስ ነው ከገዛ ወገናቸው ምርት የሚደብቁት ?
° እነሱስ የሚኖሩት ከህብረተሰቡ ጋር አይደለም ?
° አብረው ደስታንና ሀዘንን ችግርን የሚጋሩት ከዚሁ ህዝብ ጋር አይደለም ? ፤
° ነገ አንድ ነገር ቢሆኑ የሚደርስላቸው ይኸው ዛሬ ዋጋ እየጨመሩ የሚያሰቃዩት ህዝብ አይደል ?
ህዝቡ ከዛሬ ነገ ምን ይጠብቀኛል ፤ ኑሮው እንዴት ልገፋው ነው ብሎ በተጨነቀበት በዚህ ወቅት መሰረታዊ አቅርቦትን መደበቅ እና ዋጋ መጨመር ምን አይነት የጭካኔ ተግባር ነው ? ምን አይነት ስግብግብነትስ ነው ?
ይህ የነጋዴዎች ተግባር ጭንቀት ላይ ጭንቀት የሚጨምር እጅግ የሚያስተዛዝብ ነው። እንዲህ ያለ ወቅት መረዳዳት እና መተዛዘን ሲገባ ትርፍ ለመሰብሰብ መሮጥ አሳፋሪ ነው።
ከምንም በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው ነዋሪ ጫናው እንደሚበረታበት እየታወቀ ፣ እንደሚያሰቃየው እየታወቀ መቶ አመት ለማይኖር ህይወት በወገን ላይ እንዲህ መጨከን ተገቢ አይደለም።
ከላይ የሚወርደውን ሁሉ በማይችል ጫንቃው የሚሸከመው በዝቅተኛ ገቢ የሚኖረው የሀገሬው ህዝብ ነው። "
(በናውስ የሐሳብ መድረክ)
የሐሳብ መድረኩን ይቀላቀሉ : https://t.iss.one/NousEthiopia/36
Via @nousethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " ጉባኤ በማካሄድ የሚፈጠር ግጭት አይኖርም " - የህወሓት ሊቀመንበር የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) ዛሬ ሀምሌ 20/2016 ዓ.ም በክልሉ ለሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህም ፥ ከ2 ቀናት በፊት አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር…
#Tigray #TPLF
" እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ? " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክተው ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ቃለመጠይቅ ሰጥተው ነበር።
አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?
- የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የትግራይ ህዝብ እና ህልውና ያዳነና ያስቀጠለ ነው።
- ሁሉም የትግራይ ችግሮች ከውጭ ተፅእኖ ነፃ ናቸው ባይባልም በአመዛኝ ውስጣዊ ፓለቲካዊ ችግሮች ናቸው ያሉት። ውስጣዊ ችግሮቻችን ባይጠልፉን የፕሪቶሪያው ስምምነት በፈጠረው እድል በርካታ ለውጦች ይታዩ ነበር።
- ውስጣዊ ፓለቲካዊ ድክመታችን ሰከን ብለን መመርመር አለብን፤ ከጥፋት ለጥቂት ያመለጠ ህዝብ መልሰን ወደ ጦርነት እንዳናስገባው በሃላፊነት መንፈስ መንቀሳቀስ አለብን።
- ጉባኤ መካሄድ የለበትም ያለ የለም ፤ አሁን ያለው ሩጫ ግን ስልጣን ለመቆጣጠርና ከተጠያቂነት ለማምለጥ ያለመ ነው።
- ህወሓት መዳን የሚችለው በጭቅጭቅ ሳይሆን በሳልና ተራማጅ ሃሳብ በማመንጨት ነው።
- እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30/2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር ቢሆንም ፍትህ ሚንስቴር በደብዳቤ አስቀርቶታል። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ?
- " ከፌደራል መንግስት ጥሩ መግባባት ደርሰናል ተስማምተናል " ይባላል እንጂ መሬት ላይ ጠብ የሚል ነገር የለም። አዲስ አበባ በመሄድ የሚስማሙትና እዚህ የሚነገረን የተለያየ ነው፤ ይህ ካድሬው ሊያውቀው ይገባል።
- የተጀመረው ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የመመለስ ተግባር ከተጨማሪ ግጭት ቂምና ቁርሾ በፀዳ መልኩ እንዲፈፀም እየሰራን ነው።
- በእርስ በርስ ሽኩቻ ባሳለፍናቸው ጊዚያቶች ፀፀት ተስምቶን ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ለመመለስና የፕሪቶሪያው ስምምነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈፀም በተቀናጀ የአመራር ጥበብ መስራት ይጠበቅብናል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

" ተማሪዎችን አወዳድሬ ነው የምቀበለው " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
የራስ-ገዝ ዩኒቨርሰቲ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በራሱ ፖሊሲና መስፈርት ፤ ምዘናና የክፍያ ስርዓት ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል አሳውቋል።
በመደበኛ፣ በማታና በርቀት በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ አመልካቾች በቅርቡ ዝርዝር ማስታወቂያ እንደሚያወጣ ገልጿል።
ዝርዝር ማስታወቂያውን ተከታትለን እናሳውቃለን።
@tikvahethiopia
የራስ-ገዝ ዩኒቨርሰቲ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በራሱ ፖሊሲና መስፈርት ፤ ምዘናና የክፍያ ስርዓት ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል አሳውቋል።
በመደበኛ፣ በማታና በርቀት በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ አመልካቾች በቅርቡ ዝርዝር ማስታወቂያ እንደሚያወጣ ገልጿል።
ዝርዝር ማስታወቂያውን ተከታትለን እናሳውቃለን።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #TPLF " እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ? " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክተው ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ቃለመጠይቅ ሰጥተው ነበር። አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ? - የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት…
#Tigray
" ትግራይ በሁለት ቡድን በተከፈለ ገዢ መታመስ ይበቃት !! " - ሦስት የትግራይ ፓርቲዎች
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) ፣ ውድብ ናፅነት ትግራይ (ውናት) ፣ባይቶና ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) ወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ አስመልክተው በጋራ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚህም " ስልጣኑ ከመጠበቅ አልፎ አርቆ ማሰብ የማይችለው ስርዓት ችግሮቹ ወደ ህዝብ ለማላከክ የሚያደርገው ሸፍጥ በጊዜው መታረም አለበት " ብለዋል።
" የትግራይ ችግር መፍትሄ የሚያገኘው ተጠያቂነት ያለው የመንግስት ስርዓት ሲኖር ነው " ያሉት ፓርቲዎቹ " ይህ የሚሆነው ደግሞ ሁሉን አቀፍ ምክር ቤት ሲቋቋም ብቻ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ፓርቲዎቹ በስም ያልጠቀሱትና " ፀረ ህዝብ " ያሉት ሃይል ችግሮቹን ወደ ህዝብ ለማጋባት የሚያደርገው ሸፍጥና አስመሳይነት ተቀባይነት የለውም መታረም አለበት በማለት አስጠንቅቀዋል።
" የትግራይ ህዝብ ለስልጣናቸው ህልውና በማሰብ ብቻ ወደ አደገኛ እልህ ከገቡት ገዢ ቡድኖች ራሱ በማራቅ አድነቱ ጠብቆ ሊታገላቸው ይገባል " ብለዋል።
" ትግራይ በሁለት ቡድን በተከፈለ ገዢ መታመስ ይበቃት ! " ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
" ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ የቅድምያ ቅድምያ መታየት ያለበት አጀንዳ መሆን ይገባዋል " ያሉት ፓርቲዎቹ " የተጀመረው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት " ሲሉ አሳስበዋል።
#TikvahEthiopiaMekelle

#Ethiopia #Italy
ኢትዮጵያ ዛሬ ከጣሊያን ጋር የ25 ሚሊዮን ዩሮ የፋይናንስ ስምምነት እንደተፈራረመች ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።
13 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ በድጋፍ መልክ ሲሆን 11 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ብድር ነው፤ ይህም ለአካባቢና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ይውላል ተብሏል።
በተጨማሪም ስምምነቱ የ ' ገበታ ለትውልድ ' ን እንደሚደግፍ ገንዘብ ሚኒስቴር አመልክቷል።

#Ethiopia
" ... የመንግስት መገናኛ ብዙኃን የአንድን ወገን ሀሳብ ብቻ ወደ ሕዝብ ከማድረስ አልፈው ይኽን ከፍተኛ የዋጋ ንረትን ሊያስከትል የሚችል ውሳኔ እንደ ምስራች በ ' እንኳን ደስ አላችሁ ! ' አጅበው ማቅረባቸው ለሕዝብ ያላቸውን ንቀት ያሳዩበት ፤ አሁንም ከገዢው ፓርቲ ጥገኝነት ወጥተው ሙያቸውን የሚያስከብሩ የመረጃ ብዝሃነትን እና ፍትሃዊነት የሚያረጋግጡ ዘገባዎችን ለመሥራት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላቸው ያረጋገጡበት ነው። " - የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ)
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ " ፖሊሲ የማውጣት ሉዓላዊነትን የሚገድብ ማሻሻያ ውጤቱ ቀውስ ጋባዥ ትርፉም ሀገራዊ ዕዳ ነው " በሚል የላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል። #EZEMA

“ በሁለቱ ክሶች ትላንት ነፃ ተብያለሁ ” - ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ “ የእድሜ ልክ እስራት ያስፈርድበታል ” ሲባሉበት ከነበረው ክስ ጭምር ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነጻ ተብሏል።
ጋዜጠኛው፣ በሐምሌ 2014 ዓ/ም ላይ “ ጥብቅ የመከላከያ ሠራዊትን ምስጢር ማባከን ፤ መከላከያ ሠራዊቱን መከፋፈል ፤ የመከላከያ ሠራዊቱን ስም ማጥፋት ” የሚሉ ሦስት ክሶች ተመስርቶበት ነበር።
በ3ኛው ክስ የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ/ም አንቀጽ ተቀይሮ እንዲከላከል ተወስኖ ነጻ እንደተባለ አስታውሶ ትላንት ደግሞ ሲከራከርባቸው በነበሩ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ክሶች ነፃ መባሉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
“ በሁለቱ ክሶች ትላንት ነፃ ተብያለሁ ” ነው ያለው።
‘ ነጻ ’ የተባለባቸው ክሶች የእድሜ ልክ እና ከ10 እስከ 15 ዓመታት እስራት ያስፈርድባቸዋል ተብሎ በነበሩት ክሶች ነው።
ጋዜጠኛ ተመስገን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ መጀመሪያውንም ስከሰስ መከላከያ 'ምስጢር አወጣ፤ ሠራዊቱን ከፋፈለው' ብሎ ነበር የከሰሰኝ ” ብሏል።
“ ያ ግን ውሸት ነው። መከላከያ ውስጥ ራሱ የነበሩ ችግሮችን በምክንያት አስደግፈን ይፋ ስላደረግን ነው ” ሲል አክሏል።
ክሶቹ ነጻ የሚያስብሉ ሆነው ሲገኙ ብዙ ውጣ ወረድ እንደማሳለፈህ መጠን የካሳ ክፍያ ታስቦልሃል ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ በሰጠው ምላሽ፣ “ እስካሁን ድረስ የተባለ ነገር የለም። ግን ጠበቆችን አማክራለሁ ” ብሏል።
“ ምክንያቱም መንግስት ሰፊ ተቋም ነው። ንጹሐን ሰው እያነሱ እያሰሩ ፣ እያሰቃዩ፣ ሚዲያ እያስቆሙ መጨረሻ ላይ በፍርድ ቤት ነጻ ሲባል ለዚህ ሁሉ መጎሳቆልና ኪሳራ ምክንያት የሆነው መንግስት ደግሞ ካሳ ሊከፍል ይገባል ብዬ አስባለሁ ” ሲል አክሏል።
ጋዜጠኛው ተመስገን ደሳለኝ ተከሶበት የነበረው ክስ እና የፍርድ ሂደቱ ምን ይመስል ነበር ? በዚህ ያንብቡ : https://telegra.ph/TikvahEthiopia-07-31
#TikvahEthiopiaFamilyAA

“ በሁለቱ ክሶች ትላንት ነፃ ተብያለሁ ” - ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ “ የእድሜ ልክ እስራት ያስፈርድበታል ” ሲባሉበት ከነበረው ክስ ጭምር ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነጻ ተብሏል። ጋዜጠኛው፣ በሐምሌ 2014 ዓ/ም ላይ “ ጥብቅ የመከላከያ ሠራዊትን ምስጢር ማባከን ፤ መከላከያ ሠራዊቱን መከፋፈል ፤ የመከላከያ ሠራዊቱን ስም ማጥፋት ” የሚሉ ሦስት ክሶች…
#Ethiopia
ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበረው ቆይታ ምን መልዕክት አስተላለፈ ?
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፦
" እስር ቤት በነበርኩበት ጊዜ በማዕከላዊ፣ ቂሊንጦ አያያዙ ጥሩ አልነበረም። ብዙ ችግሮችም ነበሩ። ሰው ሊታሰርባቸው የማይችሉ ፤ ዋጋ የሚያስከፍሉ የሰቆቃ ቦታዎች ናቸው።
እኛ ጋዜጠኞች ነን። ሚዲያን በተመለከተ ለሚፈጠሩ ጥፋቶች አገሪቷ የራሷ የፕሬስ ህግ አላት፤ 2001 ዓ/ም የወጣ ፤ ከዚያ በኋላም ከ2010 ዓ/ም በኋላ አዲሱ መንግስት ሲመጣ ያንን ህግ አሻሽሎ አውጥቶታል።
ግን ህጉ ምንም ሥራ ላይ አይውለም። Even ጥፋት ሰርተን ቢሆን ኖሮ ራሱ መጠየቅ የነበረብንም በፕሬስ ህጉ ነበረ።
ትልቁ ችግር መንግስት ህግን አለማክበሩ ነው።
ኢህአዲግ እያለ ህጎቹ በጣም አፋኝ ነበሩ ፤ ነገር ግን ከህጉ ወጥቶ ሌላ ጥፋት አይሰራም ነበር።
በእነዛው አፋኝ ህጎቹ ነው ሲያግድ የነበረው። የአሁኑ መንግስት ደግሞ በጣም የተስፋፉ ህጎች አውጦቷል፤ ህጉን ግን አይጠቀምበትም።
ከህግ ውጪ እየሄደ ነው። ከህግ ውጪ ባይሄድ መልካም ነው። "
ፎቶ ፦ ፋይል

Photo
#Update
10 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል !
የመመረቂያ ጽሁፍ በማቅረብ ላይ የነበረችን ተማሪ በጥይትና በስለት ለመግደል የሞከረው ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጥቷል።
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመመረቂያ ጽሁፍ በማቅረብ ላይ የነበረችን ተማሪን ከጀርባዋ ሆኖ በጥይት ተኩሶ በመምታትና በስለት ደጋግሞ በመዉጋት ለመግደል የሞከረ ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱ ፖሊስ ገለፀ።
ተከሳሽ ፦ አማኑኤል እንድርያስ
ነዋሪነቱ ፦ በጉራጌ ዞን አብሽጌ ወረዳ ቁሊት ሁለት ቀበሌ
የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው ፦ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ
የክሱ ዝርዝር ፦ ግለሰቡ የግል ተበዳይን ለመግደል በማሰብ ወልቂጤ ዩንቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ የጦር መሳሪያና ስለት ይዞ ይገባል።
የመመረቂያ ምርምር ጥናታዊ ፅሁፍ በምታቀርብበት ክፍል ውስጥ ከጀርባዋ ሆኖ በመቀመጥ በያዘው ሽጉጥ ተኩሶ ትከሻዋን መቷታል።
በኋላም ደንግጣ ለመሮጥ ስትሞክር ተከታትሎ ጉሮሮዋን አንቆ በመያዝ አስቀድሞ ባዘጋጀዉ ስለታም ቢላዋ ጭንቅላቷን 6 ጊዜ ያህል ደጋግሞ በመዉጋት የመግደል ሙከራ ወንጀል በመፈጸሙ ነው የተከሰሰው።
ተከሳሹ የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ተማሪ ነው። ከዚህ በፊት ተጎጂዋ እና የግል ተበዳይን በመደብደቡ በዲሲፕሊን ተከሶ በዩንቨርስቲዉ አመራሮች ለሁለት አመት ከትምህርት ገበታዉ እንዲታገድ በመወሰኑ ወንጀሉን በዚህ ቂም ተነሳስቶ እንደፈፀመ የተከሳሹ የክስ መዝገብ ያስረዳል።
የጉራጌ ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤትም ተከሳሹ የጦር መሳርያና ጥይቶችን የመያዝ የፀና ፍቃድ ሳይኖረው በተከለከለ ስፍራ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘቱ እና በፈፀመዉ የመግደል ሙከራ ወንጀል የቀረበበትን ክስ ማስተባበል ባለመቻሉ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
በጥይትና በስለት ጉዳት የደረሰባት የግል ተበዳይ ህክምና ተከታትላ አሁን ላይ በመልካም ጤንነት ላይ ትገኛለች።
ለማስታወሻ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/88024?single
#CentralEthiopiaRegionPolice #WolkiteUniversity

ተጨማሪ በጀት ለፓርላማ ሊቀርብ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ያገኘውን ድጋፍ እና ብድር የያዘ ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ለፓርላማ አቅርቦ እንደሚያስጸድቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል። ይህ የተናገሩት ዛሬ በነበረው የምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ ወቅት ነው። ተጨማሪ በጀቱ ፦ ➡️ ለዝቅተኛ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች ለሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ፣ ➡️ ለነዳጅ…
#Ethiopia : " የዋጋ ንረት (inflation) ጫና እንዳለ በተደጋጋሚ ተነስቷል።
ይሄ ሪፎርም (የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ማለታቸው ነው) በመጀመሪያዎቹ #ወራት ወይም #ዓመት ጫና የሚያመጣ መሆኑ ይታወቃል።
በዘላቂነት የዋጋ ንረትን (inflation) ለመቆጣጠር ግን ከዚህ ውጭ አማራጭ የለንም። " - የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ (ለህ/ተ/ም/ቤት የተናገሩት)
ገና በመጀመሪያዎቹ ቀናት " ዶላር ጨምሯል " በሚል የታዩት መሰረታዊ ነገሮች ላይ ዋጋን የመጨመር አዝማሚያዎች ዜጎችን በተለይ ደግሞ በዝቅተኛ ገቢ ሚኖሩትን እጅግ በጣም ከፍተኛ ጭንቀት ላይ የጣለ ሆኗል።
ከዛሬ ነገስ ምን ይፈጠር ይሆን ? በሚልም እንቅልፍ ነስቷቸዋል።
#TikvahEthiopia

#DStvEthiopia
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ሊመለሱ ነው!
አዳዲሱ ተጫዋቾች ያስፈረሙት ቡድኖች ሊጉን ለመጀመር ዝግጁነታችውን አሳውቀዋል!
እናንተስ የአዲሱ ዓመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ማን የሚሆን ይመስላችኋል?
ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/dg1
#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia

" ልጄን አድኑልኝ " - መምህርቷ እናት መምህርት አልሻምጌጥ ንጉስ ፤ ልጇ የአብቃል በተወለደ በሀያ አንድ ቀኑ ነው የልብ ህመም እንዳለበት ያወቀችው። ላለፉት 5 አመታት የህጻናት የልብ ቀዶ ጥገና መዕከል አስመዝባ ብጠብቅም ወረፋ ሊደርሳት አልቻለም። " አሁን ልጄ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደረሰ " ስትል ገልጻለች። ከሀያ አንድ ቀኑ ጀምሮ ከሀዋሳ አዲስ አበባ እየተመላለሰች ሰርጀሪውን ስትጠብቅና ማስታገሻ…
#Update
" የተሰበሰበልንን 300 ሽህ ብር ከፍለን ወረፋ ብናስይዝም ገንዘቡ ሊሞላልን ባለመቻሉ ህክምናዉ ሊያልፈን ነው " - ወላጆች
ከዚህ ቀደም በልብ ክፍተት ህመም እየተሰቃየ የሚገኘዉን ህጻን ህክምና በተመለከተ ለኢትዮጵያ ህዝብ የድጋፍ ጥሪ መድረሱን ተከትሎ አንዲት ልበ ቀና እህት 200 ሺህ ብር እንዲሁም ከህዝቡ በተሰበሰበ 100 ሽህ ብር በድምሩ 300 ሺህ ብር ተከፍሎ ወረፋ ተይዞለት ነበር።
ይሁንና አሁን ላይ ወረፋዉ ቢደርስም ቀሪዉ ገንዘብ መሰብሰብ ባለመቻሉ የህጻኑ ወላጆች በከባድ ጭንቀት ዉስጥ የወደቁ ሲሆን የህጻኑ ስቃይም ከጊዜዉ መሄድ ጋር ተባብሶ ቀጥሎ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል።
" እባካችሁ የሆስፒታሉ ወረፋ ሳያልፈን ልጃችንም ሳያመልጠን ድረሱልን " የሚሉት የህጻኑ ወላጆች መምህርት ወ/ሮ አልሻምጌጥ ንጉሴ እና አቶ አንተነህ ደፈርሻ " አቅም ያላችሁ በገንዘባችሁ አቅም የሌላችሁ ደግሞ በጸሎት አግዙን " ብለዋል።
በልብ ክፍተት ችግር እየተሰቃዩ ያለዉንና በተያዘለት ቀጠሮ የልብ ክፍተቱ የማይስተካከል ከሆነ ለከፋ ችግር ይወድቃል የተባለዉን ህጻን ለመርዳት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000243926053 አልሻምጌጥ ንጉሴ መኮንን መጠቀም እንደሚቻል መምህርቷ እናት ተናግረዋል።
በስልክ ቁጥር 0916155490 በመደወል ደግሞ አስገላጊ ማስረጃ እና ጥያቄ ቤተሰቡን መጠየቅ ይቻላል።

#ዕለታዊ : የዶላር ዋጋ ጨምሯል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዱ የአሜሪካ ዶላር በ77 ብር ከ1280 ሳንቲም እየተገዛ በ78 ብር ከ6706 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል። ፓውንድ ስተርሊንግ በተመሳሳይ ጨምሯል። አንዱ በፓውንድ በ94 ብር ከ3071 ሳንቲም እየተገዛ በ96 ብር ከ1932 ሳንቲም እየተሸጠ ነው። ትላንት መጠነኛ መውረድ አሳይቶ የነበረው ዩሮ ዛሬ ጨምሮ አድሯል። አንዱ ዩሮ በ83 ብር ከ3754…
#ዕለታዊ : ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ/ም በግል ባንኮች ያለው የውጭ ምንዛሬ ምን ይመስላል ?
ዶላር አሁንም መጨመሩን ቀጥሏል።
ትላንት አንዱን ዶላር በ74 ብር ከ7382 ሳንቲም እየገዛ በ76 ብር ከ2329 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረው ኦሮሚያ ባንክ ዛሬ መግዣውን ወደ 79 ብር ከ9448 ሳንቲም መሸጫውን ወደ 82 ብር ከ3431 ሳንቲም ጨምሮታል።
ዩሮ ትላንት በባንኩ 81 ብር ከ0386 ሳንቲም ሲገዛ ፤ 82 ብር ከ6593 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር ዛሬ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ 86 ብር ከ4363 ሳንቲም መግዣ 89 ብር ከ0294 ሳንቲም መሸጫ ተቆርጦለታል።
እጅግ ከፍተኛ ጭማሪ ከታየው የውጭ ምንዛሬ ሌላኛው የፓውንድ ስተርሊንግ ነው በባንኩ ዛሬ አንዱ ፓውንድ ስተርሊንግ 102 ብር ከ6171 ሳንቲም መግዣ 105 ብር 6956 ሳንቲም መሸጫ ተቆርጦለታል።
የUAE ድርሃምም ጨምሮ 21 ብር ከ7637 ሳንቲም መግዣ 22 ብር ከ4166 መሸጫ ተቆርጦለታል።
ሌሎች ባንኮችን ስንመለከት።
ወጋገን ባንክ ትላንት 1 ዶላር መግዣው 77 ብር ከ7401 ሳንቲም ፤ መሸጫው 79 ብር ከ2949 ሳንቲም ነበር ዛሬ ጨምሮ መግዣው 83 ብር ከ4681 ሳንቲም መሸጫው 85 ብር ከ1374 ሳንቲም ገብቷል።
ትላንት 1 ፓውንድ መግዣው 93 ብር ከ6991 ሳንቲም ፤ መሸጫው 95 ብር ከ5731 ሳንቲም ነበር ዛሬ ጨምሮ መግዣው 99 ብር ከ1057 ሳንቲም መሸጫው 101 ብር ከ0878 ሳንቲም ገብቷል።
ዩሮም በጣም ከፍ ብሏል። የዛሬ መግዣው 87 ብር ከ6115 ሳንቲም መሸጫው 89 ብር ከ3637 ሳንቲም ሆኗል።
ሌላኛውን ባንክ ዳሽንን እንመልከት።
ባንኩ ትላንት 1 ዶላር መግዣው 74 ብር ከ7394 ሳንቲም ፤ መሸጫው 76 ብር ከ2342 ሳንቲም ነበር ፤ በዛሬው ዕለት 80 ብር ከ9518 ሳንቲም እየገዛ በ84 ብር ከ9994 ለመሸጥ ቆርጧል።
ፓውድንም እጅግ ጨምሯል ትላንት መግዣው 91 ብር ከ8825 ሳንቲም ፤ መሸጫው 93 ብር ከ7201 ሳንቲም ነበር ዛሬ ግን መግዣው 99 ብር ከ5199 ሳንቲም፤ መሸጫው ደግሞ 104 ብር ከ4959 ሆኗል።
ዩሮ የትላንት መግዣ 81 ብር ከ0400 ሳንቲም ፤ መሸጫ 82 ብር ከ6608 ሳንቲም ነበር ዛሬ ጨምሮ መግዣው 87 ብር ከ7761 ሳንቲም ፤ መሸጫው 92 ብር ከ1649 ሳንቲም ተቆርጦለታል።
#TikvahEthiopia #Floatingexchangerate