TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጎፋ 🕯️ “ ህብረተሰቡ እየተረባረበ አስከሬኖችን በቻሉት ልክ እያወጡ ነው። ቁፋሮው እንደቀጠለ ነው ” - ጎፋ ዞን በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ከቀናት በፊት በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ የሟቾችን አስክሬን በቁፋሮ የማውጣቱ ስራው እንደቀጠለ መሆኑን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል። ቃላቸውን የሰጡት የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ዳይሬክቶሬት አቶ ገነነ እንዳሻው፣ ቁፋሮው እንደቀጠለ መሆኑን…
#Update

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ ተገኝተዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፣ ከቀድሞ ጠ/ሚ አቶ ኃለማርያም ደሳለኝ ፣ ከፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በማሆን በገዜ ጎፋ ወረዳ ተገኝተው በመሬት ናዳ የተጎዱ ወገኖችን እያጽናኑ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንትና ወደ ስፍራው ሊያቀኑ የነበረ ቢሆንም አጋጣሚ አየሩ ዳመናማና ለጉዞ አመቺ ባለመሆኑ ምክንያት እንደቀሩ ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

° " የከተማዉ ከንቲባ ሙሉ ደሞዛችን በሂደት እንደሚከፈለን ቃል ገብተው ወደስራ ብንመለስም ፈርማችሁ ስራ ጀምሩ መባላችን አስፈርቶናል " - ሰራተኞች

° " ህጋዊ ደብዳቤ አስገብተው እንደወጡ ህጋዊ ደብዳቤ  አስገብተው ሊመለሱ ይገባል " - የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ


ከሰሞኑ " የሶስት ወር ደሞዝ ዘግይቶብናል " ያሉ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች ስራ ማቆማቸውን ይህን ለማሳወቅም ወደዞኑ ዋና ከተማ ሲያቀኑ ፖሊስ " ሆሳዕና አትገቡም " ብሎ ከከተማው መግቢያ እንዳስመለሳቸው መዘገባችን ይታወሳል።

ሰራተኞቹ ምንም እንኳን ወደዞኑ አመራሮች ቀርበው አቤቱታቸውን ባያቀርቡም ስራ አቁመው መሰንበታቸዉን ተከትሎ የሾኔ ከተማ ከንቲባና ሌሎች ባለስልጣናት አወያይተዋቸው ነበር።

በውይይቱም የአንድ ወር ደሞዛቸዉን ማለትም የሰኔን ቅድሚያ  እንዲወስዱና ቀሪውን የግንቦት ወር ደግሞ በሂደት እንደሚያገኙ ከንቲባው ቃል ገብተውላቸው ወደስራ ቢመለሱም እስካሁን ስራ በማቋረጣችሁ የይቅርታ ደብዳቤ አስገቡ መባሉን ተከትሎ ስራውን መጀመር አለመቻላቸውንና መፈረም የሚለዉ ሀሳብ እንዳስፈራቸው ገልጸዉልናል።

ጉዳዩን በተመለከተ ከቀናት በፊት ወደስራ ከገቡ በቃል ሪፖርት አድርገው ስራቸዉን መጀመር ይችላሉ ያሉን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሀም ሎምቤ ምን ሀሳባችሁን ቀየራችሁ ? ስንል ላቀረብንላቸዉ ጥያቄ " ሀሳብ መቀየር ሳይሆን የድርጅቱ አሰራር ስለሆነ ነው " ሲሉ መልሰውልናል።

" ሰራተኞቹ ፍርሀት ሊሰማቸው አይገባም " ያሉት ስራ አስኪያጁ " ህጋዊ ደብዳቤ አስገብተዉ እንደወጡ ሁሉ ህጋዊ ደብዳቤ  አስገብተው ሊመለሱ ይገባል ይህ ደግሞ ሊያስፈራቸዉ አይገባም ብ ጉዳዩ ችግር የለውም ብለን አስረድተናቸዋል " ሲሉም ገልጸዉልናል።

አሁን ላይ የተወሰኑ ሰራተኞች ፈርመዉ ስራ ሲጀምሩ  የተወሰኑት ፊርማዉን ባለመፈረማቸው ምክኒያት ወደስራ አለመመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ሰራተኞቹ ያለፈው የደከሙበት ደመወዛቸውን ተብልቶ ይቀራል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ሳይናገሩ አላለፉም።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
መቐለ እና የወንጀል የተግባር መስፋፋት !

" ፀጥታ እና ሰላም ከሌለ ሁሉም የለም "
- የመቐለ ከንቲባ

በመቐለ ከተማ በያዝነው ዓመት ከአምናው በ1,841 በመቶኛ ሲሰላ 68 ፐርሰንት / የሚበልጥ የወንጀል ተግባር መፈፀሙ የከተማዋ የሰላምና የፀጥታ ዘርፍ አስታውቋል።

በ2015 ዓ/ም ላይ የተፈፀሙት የወንጀል ተግባራት 2,895 ሲሆኑ በያዝነው 2016 ዓ/ም 4,735 የወንጀል ተግባራት ተፈፅሟል።

ይህ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዘንድሮ የ1,841 የወንጀል ተግባራት መጨመር አሳይቷል።

" ፀጥታ እና ሰላም ከሌለ ሁሉም የለም " ያሉት የከተማዋ ከንቲባ ይትባረኽ ኣምሃ " ለፀጥታና ሰላም መጠበቅና የወንጀል ተግባር ለመቆጣጠር የሚያግዙ የድህንነት ካሜራዎች በተለያዩ የከተማ አከባቢዎች በመገጠም ላይ ናቸው " ብለዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በህገ-ወጦች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ " በከተማዋ የሚካሄደው ህግ የማስከበር ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል " ያሉት ከንቲባው እስካሁን በምን የወንጀል ተግባር የተሳተፉ ፣ ምን ያህል ፣ እነማን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ በይፋ አልገለፁም። 

መቐለን ጨምሮ ሌሎችም ከተሞች ከደም አፋሳሹ ጦርነቱ በፊት በዚህ ልክ ወንጀል ተስፋፍቶባቸው አያውቅም።

በተለይም መቐለ ከተማ በደህንነት እና በጸጥታ ረገድ አንጻር ቀንም ማታም መንቀሳቀስ የሚቻልባት ነበረች። ወንጀልም በዚህ ልክ የተስፋፋባት ከተማ አልነበረችም።

#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia            
" ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የምሽት በረራ እንጀምራለን " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ እንዲሁም ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ የምሽት በረራ የሚጀምር መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ TPLF ምን አሉ ? ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦ " የምርጫ ቦርድ ' ምርጫ አራዝማለሁ ' ሲል ብዙዎቻችን ስንስማማ TPLF አልስማማም ብሎ የገባንበት ቀውስ ይታወሳል። ምን ያክል ሰው እንደወደመ፣ ምን ያክል ሃብት እንደወደመ መገመት ይቻላል። ያ የወደመ የሰው ህይወት እና የወደመ ሃብት በትክክል ሳይገመገም እንዴት ጠፋ ሳይባል ሌላ ጥፋት ማምጣት ጥሩ አይደለም። ህዝቡ ይጎዳል።…
#TPLF

" ጉባኤ በማካሄድ የሚፈጠር ግጭት አይኖርም  " - የህወሓት ሊቀመንበር

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) ዛሬ ሀምሌ 20/2016 ዓ.ም በክልሉ ለሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር። 

በዚህም ፥ ከ2 ቀናት በፊት አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማካሄዳቸውን ነው ገልጸዋል።

በውይይቱ ላይ ድርጅታቸው ህወሓት በሁለት ሳምንት ውስጥ እውቅና እንዲሰጠው የፌዴራል መንግሥትን መጠየቃቸውን አመልክተዋል።

" ጉባኤ በማካሄድ የሚፈጠር አንዳች ግጭት የለም " ያሉ ሲሆን " በአዲስ አበባ በነበረን ውይይትም ጥሩ መግባባት ላይ ደርሰናል " ሲሉ አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyaMK

@tikvahethiopia            
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#CHAPA

ደስተኛ ደንበኛ ፤ አዋጭ ንግድ!💫💸

በቻፓ ደንበኞት በመረጡት የክፍያ አማራጭ እንደ ቴሌ ብር፣ አሞሌ፣ ሲቢኢ ብር፣ ወጋገን ሄሎ ካሽ፣ ኩፕ ፔይ ኢ - ብር፣ አዋሽ ብር፣ አቢሲኒያ ኤቲኤም ካርድ፣ እናት ባንክ፣ ቪዛ፣ ማስተር ካርድ፣ ፔይ ፓል እና ሌሎች ክፍያን በፍጥነት መቀበል ይችላሉ። ለየት የሚያደርገው እርሶ ከሁሉም ወደአንድ ቦታ በቻፓ አማካኝነት መቀበል መቻሎ ነው።

ለደንበኞችዎ አማራጭን በማፋት ግብይትን ያቅልሉ።

ቻፓ ኢትዮጽያ ውስጥ ላሉ ንግዶች ሁሉ!
እርስዎ ንግድዎ ላይ ያተኩሩ ፣ ቻፓ ክፍያዎችዎን ይቆጣጠራል። ንግድዎን ዛሬውኑ ቻፓ ላይ በማስመዝገብ ክፍያዎትን ያዘምኑ!

🌐ለበለጠ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ፡ https://chapa.co/ ወይንም ዛሬውኑ በ 8911 ይደውሉልን።

Telegram | Website | Instagram | Facebook |LinkedIn |X
#SafaricomEthiopia

ካሁን በኋላ ለመብራት ልጅ መላክ ቀረ! የመብራት ክፍያችንን በM-PESA በመክፈል ለመጀመሪያዎቹ 5 ክፍያዎች የ10% ተመላሽ እናግኝ ፤ በM-PESA አሁንም ቅናሽ አለ!

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጎፋ 🕯️ “ ህብረተሰቡ እየተረባረበ አስከሬኖችን በቻሉት ልክ እያወጡ ነው። ቁፋሮው እንደቀጠለ ነው ” - ጎፋ ዞን በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ከቀናት በፊት በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ የሟቾችን አስክሬን በቁፋሮ የማውጣቱ ስራው እንደቀጠለ መሆኑን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል። ቃላቸውን የሰጡት የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ዳይሬክቶሬት አቶ ገነነ እንዳሻው፣ ቁፋሮው እንደቀጠለ መሆኑን…
" አካባቢው በጣም የስጋት ቀጠና እየሆነ በመምጣቱ ሌላ አደጋ ከመፈጠሩ በፊት ሕዝቡን የማውጣት ስራ ይሰራ " -  የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጭ

በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተው የመሬት ናዳ በርካታ ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ አስክሬን የማውጣት ስራው በመቀጠሉ የሟቾች ቁጥር እንደሚያሻቅብ በተደጋጋሚ እየተየገረ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገረው ዞኑ፣ ዛሬም ማህበረሰቡ ርብርብ በማድረግ አስከሬን የማውጣት ስራውን እንደቀጠለ መግለጹ አይዘነጋም።

አሁንም የተለያዩ ቦታዎች ተመሳሳይ ችግር እየተፈጠረ መሆኑ የአካባቢውን ሰዎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ከቷል ተብሏል።

ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው ለጊዜው ስሜ ከመገለጽ ይቆይ ያሉ አንድ ባለድርሻ አካል፣ " በተለያዩ ቦታዎች መሬቱ እየተሰነጠቀና እየተናደ ነው " ብለዋል።

" ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው በጣም ብዙ ናቸው። በየቀኑ እየጨመረ ስለሆነ በቁጥር አይታወቅም " ሲሉ አክለዋል።

" እስካሁን በጣም ደስ የሚል ትብብር ነው እየተደረገ ያለው " ያሉት እኝሁ አካል፣ " ሆኖም ግን በዘላቂነት መፍትሄ መበጀት ስላለበት ከዚህም በላይ ብዙ ድጋፍ ያስፈልጋል " ነው ያሉት።

" በናዳው ብዙ ቤቶች እየወደሙ ነው። ምክንያቱም በተለያዩ ቦታዎች ናዳው እንደቀጠለ ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

" ክረምት በመሆኑ በተለያዩ ቦታዎች መሬቱ እየተሰነጠቀና እየተናደ ነው " በማለት የአደጋውን አሳሳቢነት ገልጸዋል።

አካባቢው በጣም የስጋት ቀጠና እየሆነ በመምጣቱ ሌላ አደጋ ከመፈጠሩ በፊት ህዝቡን የማውጣት ሥራ እንዲሰራ አሳስበዋል።

ባስተላለፉት መልዕክትም፣ " ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ቢበጅለት የተሻለ ስለሆለ አሁንም ጉዳት ላይ ላለው ህብረተሰብ በደምብ ትኩረት ይሰጥ " ብለዋል።

ከጎፋው አደጋ በተጨማሪ በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የመሬት ናዳ ተከስቶ 3 ሰዎች፣ በካፋ ዞን በዴቻ ወረዳ በተከሰተ ተመሳሳይ አደጋ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት መሞታቸው አይዘነጋም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ከተማና ወምበራ ወረዳ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ ችግር ላይ መውደቃቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

በተለይም በወምበራ ወረዳ አገልግሎቱ ከተቋረጠ አራት ወራት እንዳስቆጠረ ገልጸው፣ እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ) መፍትሄ እንዳልተገኙ ተናግረዋል።

ሞባይል በጀነሬተር ቻርጅ ለማድረግ እንኳ በየቀኑ 20 ብር እንደሚያወጡ አስረድተው፣ " ይህ ማለት አንድ ሰው በ4 ወራት ከ2,000 ብር በላይ ላልተፈለገ ወጪ ተዳርጓል ማለት ነው " ሲሉ የችግሩን አስከፊነት ገልጸዋል።

በተለይ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የሚሰሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ችግሩ የከፋ አሉታዊ የሆነ ተፅዕኖ እንዳሳደረባቸው፣ የውሃ አገልግሎትም እንደተቋረጠ አክለው ገልጸዋል።

በወረዳው መብራት ከተቋረጠ ከሶስት ወራት በላይ እንዳስቆጠረ ባሳለፍነው ወር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከዚያ ወዲህ አንድም ቀን መብራት እንዳልበራ ተናግረው፣ ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው  ፤ በከተማው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተቋረጠ አንድ ሳምንት በማስቆጠሩ እየተቸገሩ መሆኑን ተናግረዋል።

አገልግሎቱ ከዚህ ቀደምም ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁንም መጥቶ ትንሽ ከቆዬ በኋላ ተመልሶ በመጥፋቱ የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

አንድ የአሶሳ ነዋሪ የሆነ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፥ " የአሶሳ ማብራት ይኸው አሁንም መፍትሄ አላገኘም። በመሃል ለትንሽ ቀናት መጥቶ መልሶ ጠፍቷል " ብለዋል።

የሚመለከታቸው አካላት በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኞች ያልሆኑ ሲሆን፣ በቀጣይ ፈቃደኞች ከሆኑ ምላሻቸውን የምናቀርብ ይሆናል።

ከዚህ ቀደም ስለወንበራ ወረዳ ቅሬታ የጠየቅነው የኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ዘይት ማዕከል፣ "እንደ ወንበራ ደብረ ዘይት ቅድሚያ የቡለን ማዕከል ራሱን የቻለ አለ። እሱ ከበራ በኋላ ነው እኛ ማብራት የምንችለው" ብሎ ነበር።

ችግሩን ለመቅረፍም፣ " ከወረዳው መንግስት ጋር እየተየጋገርን ነው፤ በቅርቡ እንሰራዋለን " ነበር ያለው።

በወቅቱ ስለጉዳዩ የጠየቅነው የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ፣ "የተቋረጠው ኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቀጠል እየተከታተልን ነው" ማለቱ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ክረምቱን ከአስደሳች ዜና ጋር... በቅርብ ቀን!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው
#Amhara #Bahirdar

በአማራ ክልል መዲና ባሕር ዳር ክልከላ ተጣለ።

ክልከላው የተጣለው በከተማው የጸጥታ ምክር ቤት ነው።

ከክልከላዎቹ ምንድናቸው ?

-  የቤት መኪና ፣ ታክሲ ፣ የመንግሥት መኪና ፣ ማንኛውም የጭነት መኪና ተሽከርካሪ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኃላ እንዳይንቀሳቀሱ ክልከላ ተጥሏል። ከተፈቀደው ሰዓት እላፊ ሲያሽከረክሩ መገኘት በሕግ ያስቀጣል።

- ከምሽቱ 3 ሰዓት በኃላ ማንኛውም የሰው እንቅስቃሴ ተከልክሏል።

- ማንኛውም ተሽከርካሪ ታርጋ ሳይኖረው ወይም ሳያስር መንቀሣቀሥ አይችልም።

- ከተፈቀደላቸው ተሽከርካሪዎች ውጭ ስቲከር መለጠፍ ተከልክሏል።

-  ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ባጃጅ መጋረጃ እና የግራ ጎን ሸራን ሳያነሱ ማሽከርከር ተከልክሏል።

- የባጃጅ ተሽከርካሪ ማኀበራት ከተሰጣችው የሥምሪት ቦታ ውጭ ማሽከርከር አይችሉም።

- በማኀበራት ተደራጅተው ስምሪት ከተሰጣቸው ባጃጆች ውጭ ማሽከርከር ተከልክሏል።

- የባጃጅ ተሸከርካሪዎች የባሕር ዳር አስተዳደር ትራንስፖርት ጽ/ቤት በአዲስ የሚሰጠውን መለያ ወይም ባር ኮድ ግልጽ እና በሚታይ መንገድ የመለጠፍ ግዴታ አለባችው።

- የባጃጅ ባለ ንብረቶች ለቀን ገቢ ወይም ለተለያዩ የጊዜ ገደብ ለሚያከራዮቸው ግለሰቦች የውል ስምምነት በመያዝ ለፓሊስ እና ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ማሳወቅ አለባቸው።

- ባጃጆች ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ማሽከርከር ተከልክሏል።

- ባለ 2 እግር ሞተር ተሽከርካሪ ላልተወሰነ ጊዜ ማሽከርከር ተከልክሏል።

ክልከላው የማይመለከታቸው እነማንን ነው ?

ክልከላ የማይመለከታቸው ተሽከርካሪዎች ፦
° በጸጥታ ሥምሪት ላይ የሚገኙ፣
° አንቡላሶች፣
° የእሳት አደጋ መኪናዎች ናቸው። ነገር ግን በማንኛውም ሰዓት በአንቡላንስም ኾነ በሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ ፍተሻ ይደረጋል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ከጸጥታ መዋቅሩ አባላት እና ለጸጥታ ሥራ ተሰማርተው የመንቀሣቀሻ ፈቃድ ከተሰጣቸው ሰዎች ውጭ የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሣቀሥ ተከልክሏል።

ማንኛውም የጸጥታ አባል ከተሰጠው ስምሪት ውጭ በሚሆንበት ጊዜ ሲቪል ለብሶ የጦር መሣሪያ ይዞ መንሳቀስ እንዳይችል ክልከላ ተጥሏል።

#AmharaRegion

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ፖሊሲን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ አውጥተዋል።

ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።


@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ፖሊሲን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ አውጥተዋል። ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል። @tikvahethiopia
#Ethiopia : ከማከሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎቹ ዋና ዋና የፖሊሲ ርምጃዎች መካከል አንዱ በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓትን የሚመለከት ነው።

ይህ የውጭ ምንዛሬ ግብይት በገበያው አማካኝነት እንዲበየን የማድረግ ሂደት እንደሆነ ተገልጿል።

መንግሥት " በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመንን ማረጋገጥ በአቅርቦት እና በፍላጎት መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሪ መዛባት ለማስተካከል ይረዳል " ብሏል።

ከዚህ ባለፈ "ገቢና ወጪ ሸቀጦችንና አገልግሎቶችን ዋጋ ከገበያ እውነታዎች ጋር እንዲጣጣም ያስችላል ፤ በክፍያ ሚዛን ላይ ያለውን አለመመጣጠን ለማስተካከል ይረዳል " ሲል ጠቁሟል።

ሌላው ፥ በወለድ ተመን ላይ የተመሠረተ የገንዘብ ፖሊሲ ሥርዓት ነው።

ርምጃው የገንዘብ ፖሊሲ ማሕቀፉን ማዘመን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል።

" የሦስት ዓመት የብሔራዊ ባንከ ስትራቴጂክ ዕቅድ ዝቅተኛ እና የተረጋጋ የዋጋ ንረት መኖሩን ማረጋገጥ " መሆኑ የገለጸው መንግሥት " ባንኩ ከንግድ ባንኮች ጋር በሚያደርገው የንግድ ግብይት በወለድ ተመን ላይ የተመሠረተ የገንዘብ ፖሊሲ ሥርዓት እንዲፈጠር ቅድሚያ ይሰጣል " ብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይህንን የፖሊሲ ማሻሻያ ትግበራ እንደጀመረ በይፋ አሳውቋል።

የፊስካል ፖሊሲ ማሻሻያው ሌላኛው ሲሆን ዋና ትኩረቱ ፦
- የመንግሥት ገቢን ማሳደግ፤
- የመንግሥት ወጪንና የድጎማ ሥርዓትን ውጤታማ ማድረግ፣
- በጡረታ ፈንድ ሥርዓቶች ላይ መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን መተግበር፣
- የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ውጤታማና ተወዳዳሪ ማድረግ እና የመንግሥት ብድር አስተዳደር ውጤታማና አዛላቂ እንዲሆን ማረጋገጥ ናቸው ተብሏል።

" ርምጃዎቹ የበጀት አስተዳደር ውጤታማነትን እና የመንግሥት ዕዳ ተጋላጭነትን ያሻሽላሉ " ሲል የገለጸው መንግሥት ፥ " በዚህ የተነሣ የልማት ፋይናንስ አማራጮቻችን ይሰፋሉ። ሀገራዊ የልማት ፍላጎቶቻችንን በሀገር ውስጥ ዐቅም ለማሳካት ምቹ መደላድል ይፈጥራሉ " ብሏል።

ሌላው እርምጃ የልማት ፋይናንስ ዕድሎች እና የመንግሥት ዕዳ አስታዳደር ማሻሻያ ነው።

መንግሥት " ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ጋር በተደረገው የመግባቢያ ስምምነት መሠረት ከተለያዩ አበዳሪዎች ጋር በመነጋገር ከፍተኛ የዕዳ ማሻሻያ ርምጃዎችን ለመውሰድ እየተሠራ ነው " ብሏል።

" በሌላ በኩል ይህ የፖሊሲ ማሻሻያ ፕሮግራም ኢትዮጵያ አዳዲስ የልማት ፋይናንስ አቅርቦት በተለይም ከዓለም ባንከ፣ ከሌሎች የልማት ፋይናንስ አቅራቢ ባንኮች እና ከሁለትዮሽ አበዳሪ ድርጅቶች እንድታገኝ መንገድ ይከፍታል " ሲል ገልጿል።

" በዚህም በአጠቃላይ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ ትግበራ መሠረት በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ብዙ ቢልዮን ዶላር ኢትዮጵያ ታገኛለች " ሲል አክሏል።

ሙሉ መግለጫው 👇
https://t.iss.one/tikvahethiopia/89204?single

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : ከማከሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎቹ ዋና ዋና የፖሊሲ ርምጃዎች መካከል አንዱ በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓትን የሚመለከት ነው። ይህ የውጭ ምንዛሬ ግብይት በገበያው አማካኝነት እንዲበየን የማድረግ ሂደት እንደሆነ ተገልጿል። መንግሥት " በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመንን ማረጋገጥ በአቅርቦት እና በፍላጎት መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሪ መዛባት ለማስተካከል…
#ETHIOPIA

መንግስት " በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት " ተግባራዊ ሊያደርግ እንደሆነ አስታውቋል።

ውሳኔው በመንግስት ቁጥጥር ሲከናወን የቆየውን የውጭ ምንዛሬ ግብይት " በገበያው አማካኝነት እንዲበየን " የሚያደርግ ነው።

ውሳኔው ተግባራዊ ሲሆን ብር፤ ዶላር እና ፓውንድን ከመሳሰሉ ዋና ዋና የመገበያያ ገንዘቦች አኳያ ያለው የምንዛሬ ተመን ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል።

አሁን በስራ ላይ በሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ተመን ስርዓት፤ ባንኮች አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ54 ብር ከ50 ሳንቲም ገደማ ገዝተው በ58 ብር ከ64 ሳንቲም ገደማ ይሸጣሉ።

በተለምዶ " ጥቁር " እየተባለ በሚጠራው ትይዩ ገበያ በአንጻሩ፤ ይህ የምንዛሪ ተመን ከእጥፍ በላይ ልዩነት አለው።

የውጭ ምንዛሬ ግብይት ስርዓትን ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ በሚያደርጋቸው የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች እና እርምጃዎች " ተጋላጭ " የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚያስችሉ ተግባራት እንደሚከናወኑ መንግስት ገልጿል።

ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች የማክሮ ኤኮኖሚ ማሻሻያዎቹ ሊያስከትሉ ከሚችሉት የአጭር ጊዜ አሉታዊ ተጽዕኖዎች ለመጠበቅ አስፈላጊ የደመወዝ ድጎማ እና ማሻሻያዎች ለተወሰኑ ጊዜያት ይደረጋሉ ተብሏል።

በነዳጅ ዋጋ ላይ የሚከተለውን ጭማሪም መንግስት በከፊል #እንደሚደጉም አሳውቋል።

#EthiopiaInsider #Ethiopia #MacroEconomicReform

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA መንግስት " በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት " ተግባራዊ ሊያደርግ እንደሆነ አስታውቋል። ውሳኔው በመንግስት ቁጥጥር ሲከናወን የቆየውን የውጭ ምንዛሬ ግብይት " በገበያው አማካኝነት እንዲበየን " የሚያደርግ ነው። ውሳኔው ተግባራዊ ሲሆን ብር፤ ዶላር እና ፓውንድን ከመሳሰሉ ዋና ዋና የመገበያያ ገንዘቦች አኳያ ያለው የምንዛሬ ተመን ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል። አሁን…
#Ethiopia

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ የኢትዮጵያ መንግሥት " በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት " ማስተዋወቁን ይፋ አድርገዋል።

ገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓትን ጨምሮ ሌሎቹንም የኢኮኖሚ ሪፎርምን በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮች በገንዘብ ሚኒስቴር እና በብሔራዊ ባንክ በኩል በየጊዜው ይገለጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ የኢትዮጵያ መንግሥት " በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት " ማስተዋወቁን ይፋ አድርገዋል። ገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓትን ጨምሮ ሌሎቹንም የኢኮኖሚ ሪፎርምን በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮች በገንዘብ ሚኒስቴር እና በብሔራዊ ባንክ በኩል በየጊዜው ይገለጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። @tikvahethiopia
#IMF : የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ኢትዮጵያ በጠየቀችው ብድር ላይ ለመወያየት ነገ ሰኞ ሐምሌ 22 / 2016 ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ብሎምበርግ ድረገጽ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የመረጃ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ጋር የምታደርገው ድርድር ከተሳካ በቀጣይ አመታት 10.5 ቢሊዮን ዶላር ልታገኝ እንደምትችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በፓርላማ ቀርበው በነበረበት ወቅት መናገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia