TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የሰራተኞችድምጽ " የደመወዝ ጥያቄ እንዳንጠይቅ በፖሊስ መደብደባችንን እና መታሰራችን የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልን !! " - የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች " ከግንቦት ወር ጀምሮ ደመወዝ አልተከፈለንም " ያሉ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች ያሉበትን ችግር እና ቅሬታቸውን ለመግለጽ ወደዞን መምሪያ በመሄድ ላይ ሳሉ በፖሊስ ተደብድበው መመለሳቸውን…
#Update

° " የተቆራረጠ ደሞዝ አንወስድም ምክኒያቱም ካሁን በፊትም እንዲሁ ተደርገናል " - የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች

° " የተፈጠረው የካሽ እጥረት በመሆኑ ወደስራ ተመለሱ " - የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ


የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች " ከግንቦት ወር ጀምሮ ደሞዝ አልተከፈለንም " በሚል ስራ አቁመው ወደ ዞኑ ጤና መምሪያ ጥያቄ ለማቅረብ ለመሄድ ሲሞክሩ በሀድያ ዞን ፖሊስ ተደብድበው ወደ ሆሳዕና ከተማ እንዳይገቡ መደረጋቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።

ጉዳዩን ከምን ደረሰ ? ስንል ጥያቄ ያቀረብንላችሁ ሰራተኞቹ አሁንም ስራ እንዳቆሙ መሆኑን በመግለጽ የተፈቀደውን የአንድ ወር ደሞዝ እንዳይወስዱ በ2015 ዓ/ም በዚህ መልኩ እንደተቃጠለው ገንዘባቸው እንዳይሆን ስጋት እንደገባቸው ገልጸዋል።

ሰራተኞቹ አሁን ላይ ውይይት አድርገዉ አንዳች ውሳኔ ላይ ለመድረስ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን በመግለጽ በቅርቡ አቋማቸውን እንደሚገልጹ ነግረዉናል።

የሰራተኞቹን ስራ ማቆም ተከትሎ በስራ ላይ  ችግር አልተፈጠረም ወይ ? ስንል ጥያቄ ያቀረብንላቸው የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ  አብርሀም ሎምቤ ፥ " ስራ ያላቆሙ ሰራተኞች በጫና ውስጥ ሆነው እየሰሩ ቢሆንም ስራ ያቆሙ ሰራተኞች ወደስራ ገበታቸው ተመልሰው ብንነጋገር የተሻለ ነው " ብለዋል።

ለምን የሰሩበትን ክፍያ አትሰጧቸውም ? በሚል ላነሳነው ጥያቄ " የካሽ እጥረት ነው የተፈጠረው ፤ የካሽ እጥረት እንደሀገር የሚገጥም በመሆኑ ክፍያቸው አይቀርባቸውም " ሲሉ መልሰዋል።

በሌላ በኩል ስራቸውን ያቆሙ ሰራተኞች ወደስራ መመለሳቸውን በደብዳቤ እየገለጹ የአንድ ወር ደሞዝ ይውሰዱ ስለተባለው ጉዳይ የጠየቅናቸው አቶ አብርሀም " ዋናው ወደስራ መመለሳቸው በመሆኑ በቃልም ቢሆን ከሰው ሀብት ጋር ተነጋግረን ስራ መጀመር ይችላሉ " ብለዋል።

ሰራተኞች ግን ባለሙያ ሆስፒታል ውስጥ እንደሌለ እየታወቀ ማስታወቂያው የተነገረው ብለዋል።

" ሲጀመር የሰኔዉ ላይ ለመወያየት ቀድሞ የግንቦት የት ነዉ ያለዉ ስላልን ነዉ ይሄ ሁሉ በደል የደረሰብን። " ሲሉ ገልጸዋል።

" አሁንም የግንቦት ላባችን እንዳይበላ ሁሉም ይወቅልን " ብለዋል።

ሰራተኞቹ አስገዳጅ ሁኔታ ተፈጥሮ የሰኔ ላይ እንዲፈርሙ ከተደረጉ በኃላ የግንቦቱ ክፍያቸው ተበልቶ ሊቀር ይችላል ሚል ስጋት እንዳላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጎፋ 🕯 በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የሞቱ ወገኖች አስከሬን ፍለጋ እንደቀጠለ ነው። እስከአሁን በሰው ኃይል በተደረገ ቁፋሮ የ157 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል። እስከአሁን ህፃናትን ጨምሮ 105 ወንዶች እና 52 ሴቶች በአደጋው መሞታቸው ተረጋግጧል። የተረፉ የቤተሰብ አባላትን ወደ አንድ ቦታ የማሰባሰብ ስራም እየተሰራ ነው። የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ…
Tassa Tassa Tassa 😭

“ ማሽን መግባት የማይችልበት ተዳፋት ቦታ ስለሆነ በሰው ኃይል ቁፋሮ እየተደረገ እየተፈለገ ነው ያለው ” - ዞኑ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ትላንት በደረሰው የመሬት ናዳ የሞቱት አብዛኛዎቹ ነፍስ ለማዳን የገቡ እንዲሁም ችግሩን ለማዬት የተሰበሰቡ ሰዎች መሆናቸውን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ዳይሬክቶሬት አቶ ገነነ እንዳሻው በሰጡት ቃል፣ “ ችግሩን ለማዬት የተሰበሰቡ ሰዎችን ነው ሙሉ በሙሉ ናዳው ያጠቃቸው ” ብለዋል።

ናዳው የተከሰተው መንደር ላይ ነው ? እንዴት ይህ ሁሉ ሰው አደጋው ደረሰበት ? ሲል ቲክቫህ ላቀረበው ጥያቄ፣ “ አንድ አካባቢ ነው። መንደር ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ሌሊት የሆነ አደጋ ተከሰተ ያን አደጋ ተከትሎ ነፍስ ለማዳን የገቡ፣ አካባቢው ላይ ችግሩ ሲፈጠር የተሰበሰቡ ሰዎችን ነው ናዳው ያጠቃቸው ” ሟቾቹ የአንድ ቤተሰብ ወይም የአንድ መንደር ሰዎች ብቻ እንዳልሆኑ ገልጸዋል።

በብዛት በናዳው ህይወታቸው ያለፈው ነፍስ ለማዳን የገቡ ሰዎች እንደሆኑ አስረድተዋል።

በአደጋው ተጠቅተው ገና ያልወጡ ሰዎች ስንት እንደሆኑ ማወቅ ተችሏል ? ሲል ቲክቫህ የጠየቃቸው አቶ ገነነ፣ እየተፈለገ አስከሬን ሲገኝ እንጂ ናዳው ያጠቃቸው ሰዎችን ቀድሞ ማወቅ እንደማይቻል ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት በአካባቢው ተመሳሳይ አደጋ ተከስቶ ነበር ? ለሚለው ጥያቄም፣ “ አዎ በወረዳው አንድ፣ ሁለት ቦታዎች ላይ አጋጥሟል አምና እና ካቻአምና ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ግን እንደ አሁኑ የከፋ አይደለም መለስተኛ ነው የነበረው። የአሁኑ ግን በጣም የከፋ ነው ” ሲሉ አክለዋል።

“ ተፈናቃይ እጅግ በርካታ አለ። የሟቾችም ቁጥር ከዚህ በላይ እንደሚጨምር ይገመታል። አሁንም እዛው ቦታው ላይ ነው ያለነው። አሁንም የመፈለግ ስራው እየተካሄደ ነው ” ነው ያሉት።

“ ማሽን መግባት የማይችልበት ተዳፋት ቦታ ስለሆነ በሰው ኃይል ቁፋሮ እየተደረገ እየተፈለገ ነው ያለው ” ሲሉ ሁነቱን አስረድተዋል።

የሟቾች ቁጥር ትላንት ማታ 55 እንደነበር ዛሬ ደግሞ ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ የሟቾች ብዛት 157 እንደደረሰ ተገልጿል።

በአደጋው ሳቢያ ተፈናቃዮች ስንት ናቸው ? መጠለያና እርዳታስ አግኝተዋል ? ለሚለው ጥያቄ አቶ ገነነ በምላሻቸው፣ “ ቁጥራቸውን ግን ማወቅ አይቻልም። ድጋፉ እየተደረገ ነው ” ብለዋል። 

“ አካባቢው ላይ ድንኳን ተተክሎ ጊዜያዊ መጠለያ ተዘጋጅቶላቸው ምግብና አንዳንድ እርዳታዎች ከዞኑ መንግስት፣ ከሌሎች ዞኖችም እየገዛ ነው ” ተብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#TeleTV

በድርጊት እና በአስፈሪ ዘውግ የተሞሉ የሃገራችን ድንቅ ፊልሞች "6 ሰአት ከለሊቱ" እና "ትዝታ" በቴሌቲቪ መተግበሪያ ብቻ!!

ዛሬዉኑ የቴሌቲቪን መተግበሪያ ከ Playstore ወይም ከ Appstore https://teletv.et/download በማውረድ አልያም በ ድህረ-ገጽ https://www.teletv.et  ላይ በመግባት መመዝገብ ይችላል።

👉ቴሊቲቪ ላይ የሚገኙ ፊልሞችን መመልከት የሚቻለው መተግበሪያው ላይ ብቻ ነው!!

ቴሌቲቪ! ሲኒማ በስልክዎ !

#TeleTV #Tizita and #KeLelitu6Seat  #Tiztamovie #6seatkelelit #Staytuned #Launch
#Update

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሀዘናቸውን ገለጹ።

ጠ/ሚኒስትሩ ፥ " በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ  ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ  ዜጎቻችንን ሕይወት ቀጥፏል " ብለዋል።

" በደረሰው አስከፊ ጉዳት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እገልጻለሁ " ብለዋል።

" አደጋውን ተከትሎ የፌዴራል የአደጋ መከላከል ግብረ-ሀይል በአካባቢው ተሰማርቶ የአደጋውን ጉዳት ለመቀነስ ርብርብ እያደረገ ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Tassa Tassa Tassa 😭 “ ማሽን መግባት የማይችልበት ተዳፋት ቦታ ስለሆነ በሰው ኃይል ቁፋሮ እየተደረገ እየተፈለገ ነው ያለው ” - ዞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ትላንት በደረሰው የመሬት ናዳ የሞቱት አብዛኛዎቹ ነፍስ ለማዳን የገቡ እንዲሁም ችግሩን ለማዬት የተሰበሰቡ ሰዎች መሆናቸውን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ዳይሬክቶሬት…
#Update

የሟቾች ቁጥር 229 ደረሰ።

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የሞቱ ወገኖች ቁጥር 229 ደርሷል።

ከወረዳው አስተዳዳር በተገኘ መረጃ የሟቾች ቁጥር ወንድ 148 ሴት 81 በድምሩ 229 መድረሱ ተሰምቷል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበል ትላንት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ መድረሱ ይታወሳል።

አስክሬን የማፈላለጉ ስራ አሁንም ቀጥሏል።

የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ ይችላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሟቾች ቁጥር 229 ደረሰ። በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የሞቱ ወገኖች ቁጥር 229 ደርሷል። ከወረዳው አስተዳዳር በተገኘ መረጃ የሟቾች ቁጥር ወንድ 148 ሴት 81 በድምሩ 229 መድረሱ ተሰምቷል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበል ትላንት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ መድረሱ…
#ጎፋ 🕯

" በመጀመሪያው ናዳ የተጎዱትን ለማዉጣት ርብርብ ውስጥ የነበረው ማህበረሰብ በአደጋው አልቋል ! " - የጎፋ ዞን ፖሊስ

በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ በደረሰው የመሬት ናዳ አሁን ላይ የሟቾች ቁጥር እጅግ በጣም እየጨመረ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጎፋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታረቀኝ አጥናፉን አግኝቷቸዋል።

" ሁኔታዉ እጅግ አሳዛኝ ነው " ብለዋል።

በመጀመሪያው ናዳ የተጎዱትን ለማዉጣት ርብርብ ውስጥ የነበረው ማህበረሰብ በአደጋው ማለቁን ገልጸዋል።

አዛዡ ከነሱ አባላት ውስጥ የወንጀል መከላከል ኃላፊው ጓዳኛቸው ወጣቶችን እያስተባበረ የመጀመሪያ ተጎጅዎችን ለማዉጣት ሲጥር አብረዉት ከነበሩት ጋር ቀድሞ መሰዋቱን ተናግረዋል።

እኛ እሳቸውን በስልክ ስናገኛቸው 160  አስከሬን እንደተቆጠረና አሁንም ሟቾች እየተገኙ እንደሆነ ገልጸው ነበር።

በኃላ በተገኘው መረጃ የሟቾች ቁጥር 229 ደርሷል።

የፖሊስ አዛዡ ፥ ጉዳት ደርሶባቸዉ ወደህክምና የተወሰዱትን ቁጥር ማወቅ አለመቻሉን ገልጸዋል።

አሁን ላይ ትልቅ ችግር የተፈጠረዉ በህይወት የተረፉትን ወደአንድ ቦታ ካሰባሰብናቸዉ በኋላ የአልባሳትና ምግብ እጥረት በመፈጠሩ ነዉ በማለት ማህበረሰቡ እገዛ እንዲያደርግ ተማጽነዋል።

አደጋዉ የደረሰበት አካባቢ የመንገድ ችግር ያለበት በመሆኑ ሟቾችንም ሆነ ተጎጅዎችን ከቦታዉ የማዉጣቱና ወደህክምና የመዉሰዱም ሆነ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን የማመላለሱ ስራ በሰዉ ሀይል መሆኑ ሁኔታዉን  ከባድ እንዳደረግ አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጎፋ 🕯 " በመጀመሪያው ናዳ የተጎዱትን ለማዉጣት ርብርብ ውስጥ የነበረው ማህበረሰብ በአደጋው አልቋል ! " - የጎፋ ዞን ፖሊስ በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ በደረሰው የመሬት ናዳ አሁን ላይ የሟቾች ቁጥር እጅግ በጣም እየጨመረ ይገኛል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጎፋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታረቀኝ አጥናፉን አግኝቷቸዋል። " ሁኔታዉ እጅግ አሳዛኝ ነው " ብለዋል። በመጀመሪያው ናዳ የተጎዱትን ለማዉጣት…
#Urgent🚨

የጎፋ ዞን ፖሊስ የሟቾች ቁጥር ከ200 በላይ የደረሰ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

" የሰው ኃይል በጣም ተዳክሟልም " ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በጎ ፈቃደኞች በጉልበትም ፣ በምግብ እና በአልባሳት አቅርቦት እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

በተለይ ወደቦታዉ ማቅናት የሚችሉ በጎ ፈቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ቢኖሩ ብዙ ሊያግዙ ይችላሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን እጅግ በጣም አሰቃቂ የሆነ የመሬት ናዳ አደጋ በተመለከተ ከስፍራው የሚያገኛቸውን መረጀዎች እና መልዕክቶች ያደርሳችኋል።

@tikvahethiopia
#ጀስቲሺያ! የቅድስት ይልማ ፊልም ከሀምሌ 5 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በአለም ሲኒማ በመታየት ላይ ነው
 
አዲስ ልብ አንጠልጣይ ፊልም “ጀስቲሺያ”፥ በአዜብ ወርቁና በቅድስት ይልማ ተጽፎ ይሁን ኢንተርቴይንመንት ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር እና ከዴቪድና ሉሲል ፓካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ቀርቧል።

የሁሉንም ቤት የጋራ የሆነውን ጉዳይ የያዘ ፥ እድለወርቅ ጣሰው፤ ድርብወርቅ ሰይፉ እና የሌሎችም አንጋፋና ወጣት ተዋንያን ድንቅ ብቃት የታየበት ፊልም፤ ከሀምሌ 5 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በአለም ሲኒማ መታየት ጀምሯል፡
 
ለሴት የቤት ውስጥ ሰራተኞች ምቹ የስራ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ጫና ለማድረግ በማለም ተዘጋጅቶ የተመረቀው “ጀስቲሺያ” የተሰኘው ፊልም ይሁን ኢንተርቴይንመንት ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር እና ከዴቪድና ሉሲል ፓካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ያቀረበው የቀረበ ነው።

ፊልሙን ተጋበዙ፤ ሁላችሁም እራሳችሁን ታዩበታላችሁ!
#SafaricomEthiopia

ከ07 መስመር ወደ 09 መስመር የሚያስደውሉ የድምፅ ጥቅሎች ተጠቅመን በጉርሻ በሽ በሽ ብለን  እንደዋወል! 0️⃣7️⃣👉🏼0️⃣9️⃣ ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.
mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
“ ድርጊቱ ተፈጽሟል። ድርጊቱ የተፈጸመባቸው ግን የኛ አባላት አይደሉም ” - የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል

የኃይማኖት አባቶች፣ ትልልቅ እናቶች፣ በእድሜ የበሰሉ አባቶች በጉልበታቸው ተንበርክከው እንዲሄዱ እንደተገደዱ የሚያሳይ ቪዲዮ በማኀበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ ተስተውሏል።

ተንበርክከው እንዲሄዱ የተገደዱትም ሰዎችም በቅርቡ የተቋቋመው “ የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል አባላት ” እንደሆኑ ተደርጎ ነው በማኀበራዊ ሚዲያው ወሬው የተራወጠው።

ድርጊቱን ፈጻሚዎቹ፣ “ የ‘ፋኖ’ ታጣቂዎች ናቸው ” የተባለ ሲሆን፣ ድርጊቱ የተፈጸመበት ቦታ ደግሞ በጎጃም መሆኑ ተመላክቷል።

ይህንኑ ቪዲዮ የተመለከቱ ሰዎችም፣ በእናቶችና በኃይማኖት አባቶች ላይ በተፈጸመው ድርጊት ብስጭትና በሀዘን የተቀላቀለበት አስተያየት እየሰጡ ናቸው።

የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል ስለጉዳዩ ምን አለ ?

ድርጊቱ ሲፈጸምባቸው የተስተዋሉት እንደተባለው እውነትም አባሎቻችሁ ናቸው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቀው የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል፣ “ ድርጊቱ ተፈጽሟል። ድርጊቱ የተፈጸመባቸው ግን የኛ አባላት አይደሉም ” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

“ የካውንስሉ ሰዎች አይደሉም ” ያሉት  የካውንስሉ የህዝብ ግንኙነት አቶ እያቸው ተሻለ፣ “ ሲጀመር ደቡብ ሜጫ ላይ ነው ድርጊቱ የተፈጸመው " ብለዋል።

“ ደቡብ ሜጫ ደግሞ በ ‘ፋኖ’ እጅ ስላለ፣ ገና በቀጣይ ከፋኖ ጋር ተነጋግረን ነው ካውንስል ልናቋቁም እያስብን ነበር እንጂ የሰላም ካውንስል አልተቋቋመም እዛ ቦታ ” ነው ያሉት።

“ ስለዚህ ባለን መረጃ የሆነ የጤና ፓኬጅ NGO ውስጥ ያለ ተቋም ስብሰብ ጠርቷቸው እንደነበር ነው። እንጅ ገና ካውንስል እዛ ወረዳ አልተቋቋመም። እኛም አልጠራንም የኛ አባልም አይደሉም ” ነው ያሉት።

“ ቪዲዮውን ለሌላ ሽፋን ነው የተጠቀሙት፤ እንደተሳሳቱ ስላወቁት ነው ‘የሰላም ካውንስሉ’ ያሉት እንጂ አልተቋቋመም ሲጀመር ገና ከ ‘ፋኖ’ ጋር ተነጋግረን ነው በቀጣይ ልናቋቁም ያሰብነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

የተሰራጨው ቪዲዮ የሰዎችን ማንነት በግልጽ ያሳያል ቪዲዮውን አይታችሁት ነበር ? ሲል ቲክቫህ ላቀረበው ጥያቄ አቶ እያቸው፣ “ አይቸዋለሁ። ግን የኛ አባል አይደሉም ” የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፤ ድርጊቱ የተፈጸመባቸው ሰዎች እነማን እንደሆኑስ ካውንስሉ ያውቃል? የሚል ጥያቄ አቅርቧል።

አቶ እያቸው በሰጡት ምላሽ፣ " አያውቅም። እነርሱ ራሳቸው ፋኖዎቹ ምላሽ ይስጡበት። እኛ አናውቅም እነማን እንደሆኑ " ነው ያሉት።

በሌላ በኩል ፥ አማራ ክልል በሰጠው መግለጫ በቪድዮ የሚታዩት የሰሜን ጎጃም ዞን፣ በደቡብ ሜጫ ወረዳ ልዩ ስሙ ገርጨጭ በሚባል አካባቢ ነዋሪ ናቸው ብሏል።

ለተለያዩ ስራዎች ባህር ዳር ከተማ ደርሰው ሲመለሱ ' የሰላም ኮሚቴ አባላት ለመሆን ነው ' በሚል ምክንያት መያዛቸውን ፣ በእንብርክክ እንዲሄዱ መደረጋቸውን፣ እከተያዙት ውስጥም የተገደሉ እንዳሉ አመልክቷል።

ከተገደሉት ውስጥ የወረዳ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጁ መርጌታ ግሩም፣ የሀገር ሽማግሌ አቶ አዘነ አድማሱ፣ የሀገር ሽማግሌ አቶ አስማማው አቤ፣ ወ/ሮ የኔአየሁ ዳኛው የተባሉ የከተማው ነዋሪ ይገኙባቸዋል ብሏል።

ሌሎች 13 አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia