TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ እና የግብረ ሰዶማዊነትን #ኃጢአት በተመለከተ አጀንዳ አድርጎ መወያየቱ ተሰምቷል። በዚህም፥ የቅድስት ቤተ ክርስቲያኗን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ #ዓለም_አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር የሆነ መግለጫ እንዲሰጥ ወስኗል። #EOTCTV @tikvahethiopia
#Update

የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ተሰጥቷል።

በዚሁ መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ " በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ በመሆኑ በእጅጉ እናዝናለን " ብሏል።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በአጽንኦት ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል ቅዱስ ሲኖዶስ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አካሄድ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳለው ገልጿል።

" ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል " ብሏል።

ይሁን እንጅ " ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅር አሰኝቶናል " ብሏል።

በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን አሳውቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ውሳኔ አሳለፈ ?

➡️ በቅድስት ቤተ ክርስቲያኗና በመንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ሰይሟል።

➡️ ቅዱስ ሲኖዶስ የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁም #ከመጽደቁ_በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ሰይሟል፡፡

➡️ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ #የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገልጿል። ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ወስኗል።

➡️ #ከሀገር_ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ ፦
- በሙያ ብቃታቸው፣
- በምግባራቸው
- በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት #በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ወስኗል፡፡

ሙሉ መግለጫ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/88105?single

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ እና የግብረ ሰዶማዊነትን #ኃጢአት በተመለከተ አጀንዳ አድርጎ መወያየቱ ተሰምቷል። በዚህም፥ የቅድስት ቤተ ክርስቲያኗን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ #ዓለም_አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር የሆነ መግለጫ እንዲሰጥ ወስኗል። #EOTCTV @tikvahethiopia
ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ወሰነ ?

ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ፦

➡️ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣

➡️ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ #የተከለከለ

➡️ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣

➡️ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣

➡️ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ #እንደሚያወግዝ ገልጿል።

#የተመሳሳይ_ጾታ_ጋብቻ እና #የግብረ_ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ተሰጥቷል። በዚሁ መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ " በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ በመሆኑ በእጅጉ እናዝናለን " ብሏል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን…
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዓተ ጉባኤው የብፁዕ አቡነ ልቃስን የአውደምህረት ንግግር ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና አስተምህሮት ውጭ የሆነ ፣ ቅዱስ ሲኖዶስንም ሆነ ቤተክርስቲያንን የማይወክል ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ።

ንግግራቸው ቤተክርስቲያንን #ዋጋ_እያስከፈላት መሆኑና በቤተክርስቲያንና መንግሥት መካከል የነበረውን ግንኙነት እንዳሻከረው ተመላክቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ፅ/ቤት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስ ታህሳስ 19 / 2016 ዓ/ም በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሜሪላንድ ከተማ ሐመረብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በዓለ ንግስ ላይ ታቦተ ህጉ በቆመበት እንዲሁም ምእመናን በተሰበሰቡበት ቤተክርስቲያንን የማይመጥንና የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ብሎም የአባትነትን ክብር ዝቅ በሚያደርግ ሁኔታ አንድን ጠቅላይ ሚኒስትር ፦
° " #ግድሉ "
° " #ዘርህ_ይጥፋ "
° " #የአድማ_ብተና_ይበትንህ " በማለት መናገራቸውን ገልጿል።

ይህ ንግግራቸው ፦
➡️ ቤተክርስቲያኒቱን የማይወክል፣
➡️ ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ የሆነ፣
➡️ ቅዱስ ሲኖዶስን የማይወክል፣
➡️ ለዘመናት ጸንቶ የቆየውን የአባቶች ክብር ዝቅ የሚያደርግ፣
➡️ የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ዝቅ የሚያደርግ፣
➡️ ከህገ ኦሪትም ሆነ ከቃለ ወንጌል ያፈነገጠ ንግግር እንደሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል።

የብፁዕ አቡነ ሉቃስን ጨምሮ አንዳንድ አባቶች በተለያየ ቦታ የሚያስተለልፏቸው መልዕክቶች ቤተክርስቲያንን ለትችት እየዳረገ እንዲሁም ዋጋ እያስከፈለ ነው ተብሏል።

በቀጣይ የመግለጫ አሰጣጥ እና የትምህርተ ወንጌል አሰጣጥ ገዢ ህገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለጥቅምት 2017 ዓ/ም ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ ተወስኗል።

ከዛሬ ጀምሮ በመላው ዓለም ያሉ አህጉረ ስብከት ስህተት እንዳይፈጸም ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርጉ ያን ሳያደረጉ ቀርተው የተሳሳቱ እና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ያፈነገጡ ትምህርቶች አውደምህረት ላይ ቢተላለፉ በኃላፊነት እንደሚያስጠይቅ ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍ ተወስኗል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
DStv

✈️ አውሮፓ እንሂድ

🏆የምትወዷቸው የአውሮፓ ታላላቅ ተጫዋቾች ለሃገራችው ዋንጫ ለማሸነፍ ጉዞ ወደ ጀርመን ጀምረዋል!

⚽️በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአውሮፓ ዋንጫ ሊጀመር ነው! በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት በወር 350 ብር በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ ሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#Euro2024 #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዓተ ጉባኤው የብፁዕ አቡነ ልቃስን የአውደምህረት ንግግር ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና አስተምህሮት ውጭ የሆነ ፣ ቅዱስ ሲኖዶስንም ሆነ ቤተክርስቲያንን የማይወክል ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ። ንግግራቸው ቤተክርስቲያንን #ዋጋ_እያስከፈላት መሆኑና በቤተክርስቲያንና መንግሥት መካከል የነበረውን ግንኙነት እንዳሻከረው ተመላክቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ…
#ሙሉ_ቃል

ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ምን አለ ?

" ' ግደሉ ብሎ ' ማወጅ ቤተክርስቲያኒቱን የማይወክል እና ቅዱስ ሲኖዶስን የማይመጥን ንግግር ነው " - ቅዱስ ሲኖዶስ

ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈውን ውሳኔ ያቀረቡት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ናቸው።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በንባብ ያሰሙት ፦

" በአሁኑ ሰዓት ላይ ትልቅ ተግዳሮትና የፈተና ምንጭ በመሆን ቤተክርስቲያናችንን ዋጋ እያስከፈሏት ያሉትን የአንዳንድ አባቶች መግለጫ እና የአውደ ምህረት ትምህርቶች እንደ አብነት በመጥቀስ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሰፊው ተወያይቷል።

በውይይቱ የተለዩ ዋና ዋና ነጥቦች ፦

- አብዛኛው የአውደ ምህረት ስብከቶቻችን ከትምህርተ ወንጌል ይልቅ የነገር እና የደረቅ ትችት መድረክ እየሆኑ መምጣታቸው ፤

- በተለይም በመዋቅር ውስጥ የስራ መደብ የሌላቸው ተዘዋዋሪ " #ሰባኪ_ነን_ባዮች " የወገንተኝነት እና የፖለቲካ ትችትን እንደ ተከታይ ማፍሪያ በመቁጠር በሚዘሩት ፍጹም ከቃለ ወንጌል የራቀ ዘር ቅድስት ቤተክርስቲያንን ዋጋ እያስከፈላት መሆኑ ፤ ይህን ለመከላከል ጥረት በሚያደርጉ አህጉረ ስብከት ላይ ትልቅ የመልካም አስተዳደር ችግር እየተፈጠረ መሆኑ ፤

- በተለይም ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ፅ/ቤት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስ ታህሳስ 19 / 2016 ዓ/ም በሀገረ አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሜሪላንድ ከተማ ሐመረብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በዓለ ንግስ ላይ ታቦተ ህጉ በቆመበትና ምእመናንም በተሰበሰቡበት እንደ ቀኖና ቤተክርስቲያን ዕለቱን አስመልክቶ ተገቢውን ትምህርተ ወንጌል ከመስጠት ይልቅ ቤተክርስቲያንን የማይመጥን እና የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ብሎም የአባትነትን ክብር ዝቅ በሚያደርግ ሁኔታ አንድን የተከበረ ጠቅላይ ሚኒስትር ፦

° " #ግድሉ "
° " #ዘርህ_ይጥፋ "
° " #የአድማ_ብተና_ይበትንህ " የሚሉ ህገወጥ እና ክብረነክ የሆኑ ንግግሮች በመናገር በፈጸሙት ያልተገባ ተግባር በቤተክርስቲያኒቱ እና በመንግስት መካከል የነበረውን ግንኙነት በማሻከር ቤተክርስቲያንን ብዙ ዋጋ እያስከፈላት ከመሆኑ በላይ ለዘመናት ጸንቶ የቆየውን የአባቶችን ክብር እና የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ዝቅ ያደረገ ተገቢነት የሌለው አድርጎት መሆኑን፤

- ክብር ይግባውና ጌታችን፣ አምላካችን መድሃኒታችን ኢያሱስ ክርስቶስ በማትዮስ ወንጌል ምዕራፍ አምስት ቁጥር ሰላሳዘጠኝ ላይ እንደተናገረው " እኔ ግን እላችኋለሁ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግመህ አዙርለት " ብሎ ያስተማረውን አብነት አድርጋ አትግደል የሚለውን ህገ ኦሪት አጽንታ እያስተማረች እስካሁን ድረስ ጸንታ በቆየችው እናት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አውደምህረት ላይ " ግደሉ " ብሎ ማወጅ ቤተክርስቲያኒቱን የማይወክልና ቅዱስ ሲኖዱስን የማይመጥን ንግግር መሆኑን ፤

- ልክ እንደ አቡነ ሉቃስ ፈጽሞ ጫፍ የረገጠ ባይሆንም ሌሎችም #አንዳንድ_አባቶች በተለያዩ ቦታዎች ያስተላለፏቸው መልዕክቶች አግባብነት የሌላቸውና ቤተክርስቲያንን ለትችት የዳረጉ መሆናቸውን ምልዓተ ጉባኤው በዝርዝር ገምግሟል።

ውሳኔ ፦

1ኛ. ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ፅህፈት ቤት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስ ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ/ም በሀገረ አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሜሪላንድ ከተማ ሐመረብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ወ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አውደምህረት ላይ " ግደሉ ፣ ዘርህ ይጥፋ፣ የአድማ ብተና ይበትንህ " ... ሌሎች ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ የሆኑ ንግግሮች ቤተክርስቲያኒቱንም ሆነ ቅዱስ ሲኖዶስን የማይወክል ከቤተክርስቲያኒቱ አስተምህሮ እና ቀኖና ውጭ የሆነ ከህገ ኦሪትም ሆነ ከቃለ ወንጌል ያፈነገጠ ንግግር መሆኑ ፤

2ኛ. በቀጣይም እንዲህ አይነት ተመሳሳይ ስህተት #በብዑጽነታቸው ሆነ በአንዳንድ አባቶች ሰባክያን ወንጌል እንዳይደገም ተፈጽሞም ቢገኝ ተገቢው የእርምት ውሳኔ ለመስጠት ይቻል ዘንድ የመግለጫ አሰጣጥ እና የትምህርተ ወንጌል አሰጣጥ አስመልክቶ ገዢ የሆነ ህገ ደንብ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አገልግሎት መምሪያ እና በሊቃውንት ጉባኤ በኩል ተዘጋጅቶ ለጥቅምት 2017 ዓ/ም ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ ፤

3ኛ. ይህ ውሳኔ ከተወሰነበት ዕለት ጀምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ አህጉረ ስብከት ተመሳሳይ ስህተት እንዳይፈጸም ተገቢውን ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርጉ ፤ ከክትትል እና ከቁጥጥር ጉድለት ምክንያት በየትኛውም የቤተክርስቲያኒቱ አውደምህረት ላይ ለሚተላለፉ የተሳሳቱና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ያፈነገጡ ትምህርቶች እና ንግግሮች በኃላፊነት የሚያስጠይቅ መሆኑን ለሁሉም ሀገረ ስብከት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በኩል ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

ይህ ሙሉ ቃል የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ነው። "

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከ 'አፍሪካ ህብረት' የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ በ6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር የምዝበራ ሙከራ የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ የጠየቁት ዋስትና ውድቅ ተደርጓል። ጥያቄውን ውድቅ ያደረገው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። ከምዝበራ መኩራው ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ፦ 1ኛ. ቀሲስ በላይ መኮንን፣ 2ኛ. በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ…
#Update

እነ ቀሲስ በላይ ማረሚያ እንዲወርዱ ታዘዘ።

ከአፍሪካ ሕብረት ሒሳብ የ6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር የምዝበራ ሙከራ ጋር ተያይዞ የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ መኮንን ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ፍርድ ቤት አዟል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ተከሳሾች ማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ አዟል።

ዛሬ ፦
1ኛ ቄስ በላይ መኮንን፣
2ኛ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው ኢያሱ እንዳለ ወ/መስቀል፣
3ኛ በኮሚሽን ሥራ ላይ የተሰማራው በረከት ሙላቱ ጃፋር ችሎት ቀርበው ነበር።

4ኛ አለምገና ሳሙኤል ዲንሳ
5ኛ የኒሞና ንግድ ሥራ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አበራ መርጋ ተስፋዬ ዛሬም ፍርድ ችሎት #አልቀረቡም

ችሎት የቀረቡ ከ1ኛ - 3ኛ ተከሳሾች የወንጀል ድርጊት መፈጸማቸውንና አለመፈጸማቸውን የማረጋገጫ ጥያቄ በፍ/ ቤት ተጠይቀው " ወንጀሉን አልፈጸምንም " ሲሉ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዐቃቤ ሕግ ምስክሮች እንዲሰሙለት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ፍ/ቤቱ የምስክሮችን ቃል ለመስማት ለሰኔ 26 እና 27/2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት ፖሊስ ፦
° 4ኛ ተከሳሽ ይኖሩበታል የተባለው ቦታ የፀጥታ ችግር እንዳለ ገልጾ፤
° 5ኛ ተከሳሽ በአድራሻቸው አለመገኘታቸውን ገልጾ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው በጽሑፍ ጠይቋል።

ፍርድ ቤትም ፖሊስ 4ኛው ተከሳሽ ያሉበት ቦታ የፀጥታ ችግር ስለመኖሩ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ አዟል።

5ኛው ተከሳሽ የወረዳው ነዋሪ መሆናቸው ወይም አለመሆናቸውን ከወረዳው ማረጋጋጫ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

#FBC

@tikvahethiopia
የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል እሁድ ሰኔ 9 ይከበራል።

በዛሬው ዕለት ጨረቃ #በመታየቷ የዙልሒጃ ወር ነገ አንድ ብሎ ይጀምራል።

የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል እሁድ ሰኔ 9 ይከበራል።

#Haramain

@tikvahethiopia
#ሬሜዲያል

" በበዓል ቀናት ሆነ ማግስት የሚወጣ የፈተና ሰሌዳ አግባብነት የለውም " - የፌዴራል መጅሊስ

የሬሜዲያል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ቅሬታ አስነስቷል።

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የሪሚዲያል ተማሪዎች የፈተና መርግብር፤ ፈተናው ከሰኔ 3-10/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ያሳያል።

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 3 እስከ 6/2016 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 6-10/2016 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

ይህ የፈተና ፕሮግራም ግን ከ #ኢድ_አል_አድሃ (አረፋ) በዓል ጋር የሚጋጭ በመሆኑ በእስልምና እምነት የከታዮች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል።

እንዲህ ያለ ቅሬታ ሲፈጥር ይህ የመጀመሪያ አይደለም ። ከዚህ ቀደም መሰል ሁኔታዎች ተፈጥረው እንደነበር አይዘነጋም።

የዘንድሮ የሬሜዲያል ፈተና ቀንን በተመለከተ የፌዴራል መጅሊስ ለሃሩን ሚዲያ በሰጠው ቃል ፤ " በበዓል ቀናት ሆነ ማግስት የሚወጣ የፈተና ሰሌዳ አግባብነት የለውም " ሲል ተቃውሟል።

የመጅሊሱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ከማል ሀሩን ፥ " የተማሪዎች የመፈተኛ የጊዜ ሰሌዳ የሙስሊሙን በዓላት ታሳቢ አድርገው መውጣት አለባቸው " ያሉ ሲሆን "  የበዓል ቀናትን ታሳቢ ያላደረገ የፈተና የጊዜ ሰሌዳ አወጣጥ አግባብነት የሌለውና በተማሪዎች የስነልቦና አልፎም የፈተና ውጤታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

#ኢትዮጵያ
#ሬሜዲያልፈተና
#ሀሩን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ ተገደሉ። በወረዳው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ አልብስ አደፍራሽን ትለንትና በምሽት በመግባት እንደገደሏቸው ተሰምቷል። ወረዳው ባወጣው የሀዘን መግለጫው ፥ " አቶ አልብስ ለዓመታት በቀውስ ነጋዴዎች ለችግር ተጋልጦ የሴራ ፖለቲካ መሸቀጫ የተደረገውን የጀውሃና አካባቢው ማህበረሰብ ቀርቦ በማወያየት መተማመን ፈጥሮና አደራጅቶ ወደ ቀደመ…
#AmharaRegion

ወ/ሮ ሚሊሹ በቀለ ተገደሉ።

የቀወት ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሚሊሹ በቀለ ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ።

ወ/ሮ ሚሊሹ በዛሬው እለት ነው የተገደሉት።

እንደ ወረዳው መረጃ ፥ የመንግስታዊ አገልግሎት ላይ ውለው ከተማ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ ነው ጥቃት ተሰንዝሮባቸው የተገደሉት።

ግድያ የተፈጸመባቸው አመራሯ በእናትነት ላይ ነፍሰ ጡርነትን ይዘው እንደነበር ተገልጿል።

የወረዳው አስተዳደር ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ " ግድያው የተፈጸመው በጽንፈኛ አካላት #በተተኮሰ ጥይት ነው "  ብሏል።

ከቀናት በፊት የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪው አቶ አልብስ አደፍራሽ #በታጣቂዎች_መገደላቸው ይታወሳል።

በሌላ በኩል ከሰሞኑን በወልዲያ ከተማ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተቋምን ዒላማ ያደረጉ #የቦምብ ጥቃቶች ተፈጽመው እንደነበር ነዋሪዎች ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል ተናግረዋል።

ጥቃቶቹ በዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤትና በመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መኖሪያ ቤት ላይ እንደተፈጸሙ ነው የተሰማው።

ጥቃቱ አነጣጥሮባቸው ነበር ከተባሉት ውስጥ፦

➡️ የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ

➡️ የወልዲያ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ኃላፊ ይገኙበታል።

መኖሪያ ቤታቸው ላይ ነበር ጥቃት የተፈጸመው።

ከዚህም ባለፈ የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ቅጥር ግቢም የጥቃት ኢላማ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል።

" #ባልታወቁ_አካላት " ተፈጽሟል በተባሉት ጥቃቶች በባለስልጣናቱ ላይ ሳይሆን በሌሎች ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ እንዲሁም ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።

በቅርቡ የጉባ ላፍቶ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት እና በፖሊስ ጣቢያ ላይ ተመሳሳይ ጥቃቶች ተፈጽመው እንደነበር ተነግሯል።

ባለፈው #ሚያዚያ ወር የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው የጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ከስብሰባ ሲመለሱ በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸው አይዘነጋም።

#TikvahEthiopia
#BBCAmharic

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ ከተማ የወጣው የመሬት ሊዝ  ጨረታ ተራዘመ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ  ፤ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ በሌሎችም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል። በዚህም ከሚያዚያ 10 ቀን 2016…
#አዲስአበባ #ሊዝ

የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር ይፋ ሆኗል።

• በአንድ ካሬ ሜትር አሸናፊ የሆነው ከፍተኛ ዋጋ 470 ሺህ ብር ሲሆን ዝቅተኛ 20 ሺህ 100 ብር ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የ2ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ ተሰራጭቷል።

በጨረታው ዝቅተኛ ዋጋ የተመዘገበው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሲሆን ይህም በካሬ ሜትር 20 ሺህ 100 ብር ነው።

ከፍተኛው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በካሬ ሜትር 470 ሺህ ብር እንደሆነ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በካሬ ሜትር 470 ሺህ ብር ያቀረበው " ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ት/ቤት " መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአሸናፊዎች ዝርዝር ላይ ተመልክቷል።

በአጠቃላይ 4 ሺህ 201 ተጫራቾች የጨረታ ሰንድ በኦንላን መግዛታቸው ተነግሯል። ከነዚህ ውስጥ 2 ሺ 972 ሰነዶች ተሟልተው ተመላሽ እንደተደረጉ ተገልጿል።

1ኛ የወጡ አሸናፊ ተጫራቾች በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ኤም.ኤ ህንጻ  ላይ የአዲስ አበባ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ የሊዝ ውል እንዲፈጽሙ ጥሪ ቀርቧል።

1ኛ የወጡ ተጫራቾች ውል የማይፈጽሙ ከሆነ ዕድሉ 2ኛ ለወጡት ተጫራቾች ተላልፎ ይሰጣል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አዲስአበባ #ሊዝ የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር ይፋ ሆኗል። • በአንድ ካሬ ሜትር አሸናፊ የሆነው ከፍተኛ ዋጋ 470 ሺህ ብር ሲሆን ዝቅተኛ 20 ሺህ 100 ብር ነው። የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የ2ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ ተሰራጭቷል። በጨረታው ዝቅተኛ ዋጋ የተመዘገበው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሲሆን ይህም…
Addis Lissan Ginbot 27-2016.pdf
7.2 MB
#AddisAbaba

የ2ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ #አሸናፊዎች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

በጋዜጣው ላይ በካሬ ሜትር የቀረበው ከፍተኛው ገንዘብ 478 ሺህ ብር ተብሎ ተገልጿል።

ከታች ዝርዝሩ ላይ ደግሞ ከፍተኛው 470 ሺህ ብር እንደሆነ ሰፍሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ትክክለኛው ስንት ነው ? 478 ሺህ ብር ወይስ 470 ሺህ ብር ? ሲል ጠይቋል።

ቢሮውም ትክክለኛው 470 ሺህ (በዝርዝሩ ላይ ያለው) እንደሆነ ገልጿል።

478 ሺህ የሚለው ስህተት እንደሆነ አመልክቷል።

#AddisLisan
#AddisAbabaLandDevelopmentandAdministrationBureau

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
የተለያዩ ተቋሟት የአገልግሎት ክፍያዎችን እንደዚሁም የአዲስ አበባ ትራፊክ ቅጣትዎን በባንካችን መክፈል እንደሚችሉ ያውቃሉ?
በአቅራቢያዎ የሚገኙ ቅርንጫፎቻችንን እና የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻችንን ይጎብኙ እንዲሁም እጅዎ ላይ በሚገኙ የተለያዩ የዲጂታል መክፈያ ዘዴዎች በመጠቀም ይክፈሉ።
የተለያዪ ጠቃሚ ምክሮችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ።
https://t.iss.one/BoAEth

#banksinethiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
 #Tigray

በአንድ ቀን ብቻ የ 7 ሰዎች ህይወት በትራፊክ አደጋ ሲቀጠፍ ከ20 በላይ ሰዎች የአከል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ከሟቾቹ ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባል ናቸው።

የትራፊክ አደጋው ያጋጠመው ግንቦት 28/2016 ዓ.ም በአንድ ቀን በሁለት የትግራይ አከባቢዎች ነው።

ከዓድዋ ከተማ ወደ ጥንታዊትዋ የይሓ የቱሪስት ማእከል በየዓመቱ የሚከበረውን የቤተክርስትያን ዝክር ለማክበር በግል መኪና ሲጓዙ የነበሩት የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ በተከሰተው የትራፊክ አደጋ አራቱ ለህልፈት ሲዳረጉ ፤ ከ10 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል።

በዚያው በተመሳሳይ ቀን በሓውዜን ወረዳ ሙሽሮች የጫነ መኪና ከሞተር ሳይክል ጋር በመጋጨቱ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ10 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል።

የአደጋዎቹ መነሻ በማይመች ቦታ ከሚፈቀደው በላይ መፈጥንና መጫን መሆኑ የትራፊክ ባለሙያዎች ገልጸዋል።

አሽከርካሪዎች ለራሳቸውና ለሰው ደህንነት ትኩረት ሰጥተው እንዲያሽከርክሩ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሬሜዲያል " በበዓል ቀናት ሆነ ማግስት የሚወጣ የፈተና ሰሌዳ አግባብነት የለውም " - የፌዴራል መጅሊስ የሬሜዲያል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ቅሬታ አስነስቷል። የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የሪሚዲያል ተማሪዎች የፈተና መርግብር፤ ፈተናው ከሰኔ 3-10/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ያሳያል። የማኅበራዊ ሳይንስ…
" ፈተናው ወደ ሰኔ 11 ተዘዋውሯል " - ትምህርት ሚኒስቴር

በኢድ አል አድሃ አረፋ ቀን ሊሰጥ የነበረው ሀገር አቀፉ የሬሚዲያል ፈተና ወደ ሰኔ 11 ቀን ተዛወረ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ/ም ሊሰጥ የነበረው የሬሚዲያል ፈተና ወደ ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም መዛወሩን ዛሬ አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፥ የሬሚዲያል ትምህርት የማጠቃለያ ፈተናን ከሰኔ 3 እስከ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለመስጠት የፈተና ፕሮግራም ተዘጋጅቶ እንደነበር አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም የዒድ አል-አድሃ አረፋ በዓል በመሆኑ በዕለቱ ይሰጥ የነበረው ፈተና ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን  አስታውቋል፡፡

የዘንድሮ የሬሜዲያል ፈተና ቀንን በተመለከተ ትላንትና የፌዴራል መጅሊስ ፤ " በበዓል ቀናት ሆነ ማግስት የሚወጣ የፈተና ሰሌዳ አግባብነት የለውም " ሲል መቃወሙ ይታወሳል።

የፌዴራል መጅሊሱ " የትኛውም የተማሪዎች የመፈተኛ የጊዜ ሰሌዳ የሙስሊሙን በዓላት ታሳቢ አድርገው መውጣት አለባቸው " ሲል ማሳሰቡ አይዘነጋም።

ከዚህም ቀደም ከበዓል ጋር በተያያዘ መሰል ሁኔታዎች ማጋጠማቸው ይታወቃል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ለ2017 በጀት አመት 1 ትሪሊዮን የሚጠጋ በጀት ቀረበ።

ዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ስብሰባ ተቀምጦ ነበር።

በዚህም ስብሰባው ላይ የተለያዩ ውሳኔዎች አሳልፏል።

ከውሳኔዎቹ አንዱ ደግሞ የ2017 በጀት አመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ የበጀት አዋጅ ነው።

በዚህም ፦
➡️ ለፌዴራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች ፣
➡️ ለካፒታል ወጪዎች ፣
➡️ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ፣
➡️ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ
➡️ ተጠባባቂ ወጪን ጨምሮ ወደ #አንድ_ትሪሊየን የሚጠጋ በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

(ተጨማሪ መረጃ እና ሌሎች ውሳኔዎች ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#Amhara

በአማራ ክልል ፤ በሰሜን ጎንደር ዞን በአድርቃይ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት 15 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን እና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች እና የአካባቢው አስተዳደር አሳውቀዋል።

ይህ አካባቢ የትግራይ እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ ነው።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

- ባለፈው ማክሰኞ ግንቦት 27 ከንጋቱ በ11፡00 ሰዓት አሊጣራ ቀበሌ አንካቶ በተባለ ጎጥ የቡድን መሳሪያ #ከትግራይ_በኩል በመጡ የታጠቁ ኃይሎች ከባድ ጥቃት ተከፍቶ ነበር።

- ጥቃቱ ከንጋቱ 11፡00 ጀምሮ እስከ ጠዋት 2፡30 ገደማ ነበር የዘለቀው።

- አንድ የአካባቢው ነዋሪ ፥ " #በአንድ_ቤት 5 ነበርን፣ ከአምስታችን እኔ ነኝ በአጋጣሚ የተረፍኩት፤ ሌሎቹ ሞቱ። አሰልፈው ነው የተኮሱብን።...እኔንም ሞቷል ብለው ነው ትተውኝ የሄዱት። በፈጣሪ ፈቃድ ነው የተረፍኩት ፤ ጀርባዬን በጥይት ተመትቼ ሆስፒታል ነው ያለሁት " ብለዋል።

- ሌላ ነዋሪ ፤ " በጥቃቱ 15 ሠዎች መገደላቸውን በዐይኔ ተመልክቻለሁ። ሁለት የ16 እና የ19 ዓመት የእህት ልጆቼም ተገድለዋል። " ሲሉ ተናግረዋል።

- ሌላኛው ነዋሪ ፥ " በእሳት እና በጥይት 3 ታዳጊዎችን ጨምሮ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አልፏል። ህጻናትን ጨምሮ 15 ሠዎች መገደላቸውን አይቻለሁ " ብለዋል።

- የአካባቢው #የሚሊሻ አባል ፤ " ከጥቃት ፈጻሚዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ነበር። አብሮኝ የነበረው ታናሽ ወንድሜ በጥቃቱ ተገድሏል። ቦምብ ጉዳት አድርሷል፤ ጥይቱ፤ መሳሪያውም ብዙ ስለሆነ፤ ድሽቃ፣ ስናይፐር፣ ብሬን አላቸው። በእርቀት እየተኮሱ ነው ጉዳት ያደረሱት " ብለዋል።

-  ታጣቂዎቹ አካባቢውን ለቀው ሲወጡ 3 ሰዎችን ወስደዋል። 500 ከብቶችን ዘርፈወል። ቤቶችም ተቃጥለዋል።

ወረዳው ምን አለ ?

ዋና አስታዳዳሪ አቶ ሚሊዮን ታደሰ ጥቃቱን የፈጸሙት በዋልድባ ገዳም በኩል አድርገው የገቡ የትግራይ ኃይሎች ናቸው ብለዋል።

ቀብራቸው መፈጸሙን #ማረጋገጥ የቻሉት የስምንት ሰዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከ8ቱ ሟቾች መካከል 6ቱ #ንጹሃን_ነዋሪዎች እንደሆኑ 2ቱ የአካባቢው ሚሊሻ አባላት እንደነበሩ ገልጸዋል።

ጥቃተ የፈጸሙት የትግራይ ኃይሎች ስለመሆናቸው በምን እንዳወቁ ተጠይቀው ፥ ነዋሪዎች በሚናገሩት ቋንቋ እንደለይዋቸውና በተለያዩ ጊዜያትም ትንኮሳዎችን ይፈጽሙ እንደነበር ገልጸዋል።

" የትግራይ ታጣቂዎች ናቸው። ከእነሱ ውጪ የሚመጣብን ሌላ እንደሌለ ነው የተረዳነው " ብለዋል።

" ቡድኑን የሚመራውን ግለሰብ ጭምር እናውቃለን ፤ የህወሓት ታጣቂዎች ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

ቦታው ይገባኛል የሚነሳባቸውን አካባቢዎችን ለመያዝ " ስልታዊ " መሆኑን ተንተርሶ ጥቃቱ ሳይፈጸም አልቀረም ብለዋል።

" የማንነት ጉዳይ ሚነሳባቸውን አካባቢዎች በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ የግድ የእኛን አካባቢ ማጥቃት አለባቸው። በ2013ም የተመለከትነው ይህን ነው። ስለዚህ ይህን አካባቢ የመቁረጥ፤ ቆርጦ መሀል ላይ ያለን የመንግሥትን መዋቅር የማጥቃት ፍላጎት አለ " ሲሉ ተናግረዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምን ምላሽ ሰጠ ?

የትግራይ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ባልደረባ አቶ አማረ ኃይሌ ፤ የትግራይ ኃይሎች ጥቃት አልፈጸሙም ብለዋል።

" እስካሁን ድረስ ወደዚያ አካባቢ ያደረግነው ምንም እንቅስቃሴ የለም " ብለዋል።

" እኛ ያለንበት ቦታና አሁን እየተባለ ባለው ቦታ በጣም ሰፊ ርቀት ነው ያለው። በቀጥታ የሚዋሰን ቦታም አይደለም " በማለት ጥቃቱን እንዳላደረሱ ገልጸዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር " ያሉ ችግሮችን ግጭት አልባ በሆነ መንገድ ለመፍታት ነው የሚያስበው ወደ ግጭት የመግባት ሁኔታ የለንም " ብለዋል።

Credit - BBC AMHARIC

@tikvahethiopia