TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
“ ... ለኩራዝ የሚጠቀሙበት ነዳጅ በግልጽ ሁኔታ በችርቻሮ፣ የአረቄ በርሜል በከፍተኛ መጠን የሚሸጥበት ቦታ ነው ” - አቶ ንጋቱ ማሞ

በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አቃቂ ገበያ ማዕከል ትላንት ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ የእሳት አደጋ አጋጥሞ ነበር።

በሰዎች ላይ ጉዳት ያልደረሰ ሲሆን 6 ሙሉ ለሙሉ፣ 10 በከፊል፣ በድምሩ 16 ሱቆች እንደተቃጠሉ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የአደጋው መንስኤ ታውቋል? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ “ ፓሊስ ምርመራ እያደረገ ነው። በንብረት ላይ የደረሰን ጉዳትም ባለንብረቶቹን ፓሊስ አጣርቶ ምርመራ እያደረገ ነው ” ብለዋል።

ገበያ ማዕከሉ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብሎ የተለዬ እንደሆነ ፣ ለአደጋ የተጋለጠባቸውን ጉዳዮች ለሚመለከታቸው አካላት ቢያቀርብም የማስተካከያ እንዳልተደረገ ኮሚሽኑ ያስታወቀ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ተሰጥቶ የነበረው ማስጠንቀቂያ ምን እንደነበር ኮሚሽኑን ጠይቋል።

አቶ ንጋቱ በሰጡት ምላሽ፣ “ ለገበያ ማዕከሉ አክሲዮን ማኅበራት አደጋ ውስጥ ናችሁ። ገበያ ማዕከሉ በዘመናዊ መልክ ይገንባ ንብረታችሁ ለአደጋ ሰለባ እንዳይሆን የሚል ምክረ ሀሳብ አቅርበናል። በግልባጭ ደግሞ ለወረዳውም ” ብለዋል።

“ ቤቶቹ በቀላሉ ሊቀጣጠሉ ከሚችሉ ግብዓቶች (ቆርቆሮ በቆርቆሮ) የተገነቡ ናቸው። መፍትሄ ብለን ያቀረብነው ገበያ ማዕከሉ ዘመናዊ ሆኖ እንዲገነባ ነው። ዘመናዊ ስንል እሳትን ሊቋቋም ከሚችል እንደ ድንጋይ ከመሳሰሉ ግብዓቶች እንዲሰራ ነው ” ሲሉ አስረድተዋል።

አቶ ንጋቱ፣ “ ከገጠር የሚመጡ ሰዎች ለኩራዝ የሚጠቀሙበት ነዳጅ በግልጽ በችርቻሮ፣ የአረቄ በርሜል በከፍተኛ መጠን የሚሸጥበት ቦታ ነው” ብለዋል።

“ ንግዱ ዘርፍ፤ ዘርፍ ያስፈልገዋል። በጎን ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እየተሸጡ፣ በጎን ደግሞ የካቲካላ ንግድ በፍጹም ምንም አይነት ህብረት የላቸውም ” ነው ያሉት።

የገበያ ማዕከሉ በተደጋጋሚ አደጋ እንደደረሰበት አስታውሰው፣ አደጋ ቢያጋጥም እንኳ የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ለማስገባት ምቹ ባለመሆኑ፣ በውስጡ የሚከናወኑ የንግድ ዘርፎች የተደበላለቁ በመሆናቸው የሚመለከታቸው አካላት አሁንም ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በበዓሉ ወቅት ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች ምንድናቸው ?

-  በምግብ ማብሰያ ወይም በማዕድቤት አካባቢ የኤሌክትሪክ ፣ የቡታጋዝ ፣ የከሰል ምድጃዎችን በአግባቡ እና በጥንቃቄ ይጠቀሙ።

- በገበያ ማዕከላት የገበያተኛውን ቀልብ ለመሳብ የሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክስ ዲኮሬሸኖች ቃጠሎ እንዳያስነሱ ይጠንቀቁ።

- ሻማ እና ጧፍ ሲጠቀሙ ከተቀጣጣይ ነገር ያርቁት።

- ካምፋዬር ሚያዘጋጁ ከሆነ ከአካባቢው ከመራቅዎ በፊት በደንብ መጥፋቱን ያረጋግጡ።

- በፍጹም ጠጥተው አያሸከርክሩ።

ለማናቸውም የእሳት እና የድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም የአምቡላንስ አገልግሎት የሚከተሉትን የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስልክ ቁጥሮች መዝግበው ይያዙ።

24 ሰዓት መደወል ይችላሉ።

1. ማዕከል - 0111555300/ 0111568601
2. አራዳ - 0111567004/ 0111560249
3. ቂርቆስ - 0114663420/21
4. አዲስ ከተማ - 0112769145/46
5. ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 0114425563/64
6. አቃቂ ቃሊቲ - 0114340096 / 0114343063
7. ቦሌ - 0116630373/74
8. ኮልፌ ቀራንዮ- 0113696085/ 0113696104
9. ጉለሌ - 0112730731/ 0112730653
10. ቦሌ ሰሚት - 0116680846/ 0116680760
11. ልደታ - 0115589043/ 0115589533

(በእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የቀረበ)

እንኳን አደረሳችሁ !

@tikvahethiopia
" በየቤቱ የቁም እንስሳት ማረድ / በየአካባቢው ቅርጫ አድርጎ መከፋፈል አልተከለከለም " - የአዲስ አበባ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ፥ ከትንሳዔ በዓል ጋር በተያያዘ " ህብረተሰቡ በየቤቱ የቁም እንስሳት እርድ በማካሄድ ወይም በየአካባቢው ቅርጫ በማድረግ የሚከፋፈልበት አሰራር ተከልክሏል " በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ #ሐሰተኛ ነው ሲል አሳወቀ።

ከዚህም ጋር በተያያዘ #ምንም_ዓይነት_ክልከላ ያልተደረገ መሆኑን አረጋግጧል።

ነገር ግን በየአካባቢው #በሕገወጥ_መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ድርጊቱ በከተማው ነዋሪዎች ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ብሏል።

የከተማዋ ነዋሪዎችም ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#DV2025

የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2025 አሸናፊዎች ነገ ይፋ ይደረጋሉ።

ለዲቪ (Diversity Visa) 2025 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov/ESC/ ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።

NB. የማረጋገጫ ቁጥር ማመልከቻው ሲሞላ የተሰጠ ነው። ይህ ቁጥር የጠፋበት Forgot Confirmation Number በማለት አስፈለጊ መረጃ በመሙላት በኢሜል አዲስ ቁጥር ማግኘት ይቻላል።

ውጤቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽት 1 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይሆናል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል ፣ ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው ምንደውለው / ይህን ኢሜል / ቴክስት የምንልከው " በማለት #የሚያጭበረብሩ_አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁ አሳስቧል።

አንድ አመልካች ዲቪ 2025 ደርሶት እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማወቅ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ከላይ የተጠቀሰው ድረገጽ መሆኑን አስገንዝቧል።

አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ (ኢትዮጵያ ጨምሮ) ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 55 ሺህ ሰዎችን በዲቪ (DV) ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።

@tikvahethiopia
#LionInternationalBank

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኙ የጥያቄና መልስ ውድድር ይዞላችሁ መጥቷል፡፡
እርስዎም የሽልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያሉትን የባንኩን ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች በመቀላቀል እና ጥያቄውን ቀድመው በመመለስ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉl
ጥያቄው የሚካሄዳው እሁድ ሚያዚያ 27 ከቀኑ 5:00 ሰዓት ሲሆን ጥያቄውን ቀድመው ለመለሱ 3 ሰዎች ሊሸልም ዝግጅቱን ጨርሷል።

1ኛ ለሚወጣ ተሸላሚ የበግ ሽልማት
2ኛ ለሚወጣ  የ5000 ብር ሽልማት 
3ኛ ለሚወጣ የ3000 ብር ሽልማት      ያበረክትላችኋል።

እርስዎም ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የውድድሩ ተሳታፊ ይሁኑ!!

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ     
    የስኬትዎ አጋር!   

[Telegram]  [Facebook]

https://t.iss.one/LionBankSC

#LIB #lioninternationalbank #anbesabank #keytosuccess
#ለጥንቃቄ

በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ በተለያየ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የመኪና ስፖኪዮ በመስረቅ ወንጀል የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች (ታዳጊ ልጆች) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ሚያዚያ 23 እና 24/ 2016 ዓ.ም ወረዳ 2 ጋዜቦ አደባባይ እና ወረዳ 9 አካባቢ ነው የተያዙት ተብሏል።

ተጠርጣሪዎቹ #ከመስቀል፣አደባባይ ወደ #ቦሌ በሚወስደው መንገድ ላይ የትራፊክ መብራቶችና ተሽከርካሪ በሚቆምባቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ በመንቀሳቀስ ስፖኪዮ ሲሰርቁ እንደነበር ፖሊስ አመልክቷል።

በዚህ የወንጀል ድርጊት ለይ ተሳትፈው የተገኙት ህፃናቶች መሆናቸውን ገልጿል።

በዚህ መነሻ በተደረገ ምርመራ ለህፃናቱ ስምሪት የሚሰጡ የተደራጁ ወንጀለኞች መኖራቸውን ፖሊስ ማረጋገጡን አሳውቋል።

" አንዳንድ ህፃናት መኪና የሚጠብቁ እንዲሁም ደግሞ እርዳታ የሚፈልጉ መስለው በመቅረብ የወንጀል ተግባራት እንደሚፈፅሙ አሽከርካሪዎች ተገንዝበው በትራፊክ መብራቶችም ሆነ የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ ሲቆሙ እና በዝግታ ሲያሽከረክሩ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል " ሲል ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት…
" የኦንላይን ፈተናው በተመረጡ 25 ከተሞች ይሰጣል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ 25 ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ገልጿል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በኦንላይን ለሚሰጠው ፈተና እንዲዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከሁሉም ክልሎች በተመረጡ 25 ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በወረቀት ከሚሰጠው ፈተና ጎን ለጎን የሚሰጠው የኦንላይን ፈተና ተማሪዎች ከቦታ ቦታ ሳይጓጓዙ በየአካባቢያቸው #ቤተሰቦቻቸው_ጋር_እያደሩ ፈተናውን ይወስዳሉ ሲሉ አሳውቀዋል።

ወ/ሮ አየለች ፤ ተማሪዎች ለፈተናው እንዲዘጋጁ፣ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ፣ ወላጆችንም ልጆቻቸውን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ፈተናው በኦንላይን የሚሰጥባቸውን 25 ከተሞች በዝርዝር ይፋ አላደረገም።

የኦንላይን ተፈታኞች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአብን አባሉ አቶ ጣሂር መሐመድ " በግል ምክንያት " ከአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊነት መልቀቃቸውን ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ተናግረዋል። " ከባለፉት ሶስት፣ አራት ወራት ወዲህ አንስቶ ከኃላፊነት የመልቀቅ ጉዳይ ላይ ከክልሉ አመራሮች ጋር በዝርዝር ንግግር አድርጌያለሁ " ያለቱ አቶ ጣሂር " የክልሉ መንግሥት ጥያቄውን ተቀብሏል " ብለዋል። " ትንሽ የቤተሰብ ጉዳይ ስለነበረብኝ…
“ ...  ተገምግመው ተነሱ እንጅ አመልክተው አልተነሱም ” - አየለ አናውጤ (ዶ/ር)

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባሉ አቶ ጣሂር መሐመድ " በግል ምክንያት" ከአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊነት መልቀቃቸውን፤ በእሳቸው ምትክ ሌላኛው የፓርቲው አባል አቶ መልካሙ ፀጋዬ መሾማቸውን መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

አቶ ጣሂር ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጡት ቃል፣ " ከባለፉት ሶስት፣ አራት ወራት ወዲህ አንስቶ ከኃላፊነት የመልቀቅ ጉዳይ ላይ ከክልሉ አመራሮች ጋር በዝርዝር ንግግር አድርጌያለሁ። የክልሉ መንግሥት ጥያቄውን ተቀብሏል " ነበር ያሉት።

ይሁን እንጂ አቶ ጣሂር ከኃላፊነት የተነሱት “ በግል ምክንያት ” እንደሆነ ቃላቸውን ከሰጡ በኋላ፣ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ም/ ኃላፊ ዶክተር  አየለ አናውጤ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰራጩት መልዕክት፣ “ ተገምግመው ተነሱ እንጂ አመልክተው አልተነሱም ” ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣ የተነሱት በምን ምክንያት እንደሆነ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ ለአየለ አናውጤ (ዶ/ር) ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ “ በፌስቡክ ገፄ በዝርዝር ፅፌዋለሁ። ለጊዜው ከዚህ የተለየ ነገር የለኝም ” ብለው ለዘገባ ያንኑ ፅሑፍ መጠቀም እንደሚቻል ገልጸዋል።

በፌስቡክ ገጻቸው ባሰራጩት ፅሑፍ “ ላለፈው አንድ አመት ተቋሙ በአንድ በኩል በአግባቡ እየተሰራ ባለመሆኑ፣ በሌላ በኩል ከፍተኛ የሀብት ብክነት አለ ብለን በማመናችን ተደጋጋሚ ግምገማዎች አድርገናል ” ብለዋል።

“ ለ2 ዓመት ከ8 ወራት አዲስ አበባ ተቀምጠው በ3 ወር አንዴ እየመጡ፣ ለዛውም ተደብቀው ገብተው ሕገ ወጥ ድርጊት ፈጽመው ይሄዳሉ ” ሲሉም ገልጸዋል።

“ በመሆኑም በቢሮው ማኔጅመንት ፣ በዘርፉ ማኔጅመንት ፣ በክልል ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ፣ በከተማ ክላስተር ደረጃ በርካታ ግምገማዎች አድርገናል ” ያሉት ዶ/ር አየለ “ በመጨረሻ ከኃላፊነት እንደተነሱ ከተገለጸልን ቆይቷል፤ ደብዳቤው በእርሳቸው ጥያቄ ቢዘገይም ” ብለዋል።

“ ይህ ብቻ ሳይሆን ከወር በፊት የክልሉ መንግስት ልዩ የኦዲት ምርመራ አድርጎ እርምጃ እንዲወስድ ለርዕሰ መስተዳደሩ በደብዳቤ አሳውቄአለሁ ” የሚለውንና ሌሎች ማብራሪያዎች ሰጥተው፣ “ ተገምግመው ተነሱ እንጂ በግል ምክንያት በእሳቸው ጠያቂነት አልተነሱም ” ነው ያሉት። (ሙሉ ፅሑፋቸው ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ🚨

" በከፍተኛ ሁኔታ የሚንቀሳቀስ #የጅብ_መንጋ ተከስቷል ማህበረሰቡ ሊጠነቀቅ ይገባል " - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሠላምና ጸጥታ ቢሮ

ከሰሞኑ በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል በምሽት አንዳንዴም በቀን ጅቦች በሰው ላይ በተለይ በህጻናት እና ሴቶች እንዲሁም በአቅመደካሞች ላይ ጥቃት እያደረሱ ተነግሯል።

በደረሰን መረጃ በስልጤ ዞን 2 ሰዎች ሲሞቱ በሀዲያ ዞን እንዲሁም በሀላባ አካባቢ ሌሎች 2 የአካል ጉድለት ያደረሱ ጉዳቶች ተመዝግበዋል።

ከሟቾች አንዷ የ3 ዓመት ህጻን ናት። በስልጤ ዞን ላንፉሮ ወረዳ ነዋሪ የሆነችው ይህች ህጻን በእናቷ ጀርባ ላይ ታዝላ (እናትየው ከወፍጮ ቤት እህል አስፈጭታ ስትመለስ) በነበረበት ወቅት አድፍጦ ይጠብቅ በነበረ የተራበ ጅብ ተወስዳ ጉዳት ከደረሰባት በኃላ ህይወቷ አልፏል።

በአጠቃላይ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ተመስገን ካሳን አነጋግሯቸዋል።

አቶ ተመስገን ፤ በዚህ አመት ከፍተኛ የጅብ መንጋ መፈጠሩን አመልከተዋል። መንጋው ሲበዛ ለረሀብ በመጋለጡ ወደ ሰዎች እንደሚሄድ ገልጸዋል።

እስካሁን በክልሉ የሁለት ሞትና በርካታ ለሞት ያላበቁ ጉዳቶች ሪፖርት እንደደረሳቸዉ ጠቅሰዉ ጉዳቱ በህጻናት ላይ የበረታ መሆኑን ተናግረዋል።

አሁን ላይ ባካሄዱት ግምገማ መንጋዉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው እንደሆነ ገልጸዋል። ይህን ለማጥፋት ከሚመለከተዉ አካል ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ማህበረሰቡ ግን የራሱን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DV2025 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2025 አሸናፊዎች ነገ ይፋ ይደረጋሉ። ለዲቪ (Diversity Visa) 2025 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov/ESC/ ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ። NB. የማረጋገጫ ቁጥር ማመልከቻው ሲሞላ የተሰጠ ነው። ይህ ቁጥር የጠፋበት Forgot Confirmation…
ዲቪ 2025 ዛሬ ምሽት ይፋ ሆኗል።

የአሜሪካ ዲቪ (Diversity Visa) ሎተሪ 2025 ዛሬ ምሽት ይፋ መደረጉን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት አሳውቋል።

መ/ቤቱ፥ አመልካቾች መመረጥ አለመመረጣቸውን / ደርሷቸው እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማየት የሚችሉት በ dvprogram.state.gov/ESC/ ላይ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት #ብቻ መሆኑን አሳስቧል።

ከዚህ ውጭ የዲቪ ውጤት የሚታይበት ምንም አይነት መንገድ የለም።

N.B. ዲቪ የሚደርሳቸው ሰዎች የሚስጥር ቁጥሩን እስከ ቀጣይ አመት መስከረም መጨረሻ ቀናት መያዝ አለባቸው።

ምናልባትም  " ዲቪ ደርሷችኃል ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው የምንደውለው፣ ኢሜል / ቴክስት መልዕክት የሚንልከው " የሚሉ አጭበርባሪ ስለሚኖሩ ጥንቃቄ አድርጉ ተብሏል።

እንደ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ፥ የዲቪ ተመራጭ መሆን ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና አይሆንም።

የዲቪ ሎተሪ ተመራጭ መሆን የቪዛ ጥያቄ ለማቅረብ የመጀመሪያው መስፈርት ሲሆን በቀጥታ ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና አይሰጥም።

@tikvahethiopia
#ትንሣኤሎተሪ

የ2016 የትንሳኤ ሎተሪ ዕጣ የወጣ ሲሆን 10 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የአንደኛ ዕጣ ቁጥር 1407747 ሆኖ ወጥቷል።

5 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የሁለተኛው የዕጣ ቁጥር ደግሞ 0179265 ሆኖ ወጥቷል።

የ2.5 ሚሊዮን ብሩ የሶስተኛው ዕጣ ቁጥር 2160591 እንዲሁም የ1.5 ሚሊዮን ብር የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 0165786 ሆኖ ወጥቷል።

(ተጨማሪ ዝርዝር የዕጣ ማውጫው ከላይ ተያይዟል)

#NationalLottery

@tikvahethiopia
#ትንሣኤ

ለመላው #የክርስትና_እምነት_ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ !

" በዚህ የለም ፤ እርሱ እንደተናገረው ተነሥቶአል "  


በማቴዎስ ወንጌል ፥ " እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶአልና ፤ ቀርቦም በመቃብሩ አፍ ላይ ድንጋይዋን አንከባሎ በላይዋ ተቀመጠ፡፡

መልኩም እንደ መብረቅ ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር፡፡

እርሱንም ከመፍራት የተነሣ መቃብሩን የሚጠብቁ ታወኩ ፤ እንደ በድንም ሆኑ፡፡

መልአኩ መልሶ ሴቶቹን እንዲህ አላቸው፥ ' እናንተስ #አትፍሩ ፤ የተሰቀለውን #ኢየሱስን_እንደምትሹ አውቃለሁና፡፡ በዚህ የለም ፤ እርሱ እንደ ተናገረው ተነሥቶአል ' " ተብሎ እንደተጻፈው #መድኃኒዓለም ብርሃንን ተጎናጽፎ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን በክብር #ተነሥቶአል፡፡

መልካም የትንሣኤ በዓል !
በዓሉ የሰላምና የፍቅር ይሆን ዘንድ እንመኛለን !


#TikvahEthiopiaFamily❤️

@tikvahethiopia