TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም

ተናፋቂው የትንሳኤ በዓል ፋሲካ
እንደ ሁልጊዜው ደምቆ እንዲፈካ
በፍጥነት ግንኙነት የበዓል ድባቡን ለማቅለም
ልዩ የትንሳኤ ጥቅል ከ ኢትዮ ቴሌኮም

እስከ 25% ቅናሽ የተደረገባቸውን የትንሳኤ ጥቅል በተለያየ የጊዜ ገደብ አማራጮች ማቅረባችንን በደስታ እንገልጻለን!
ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል፣ አርዲ ቻትቦት ወይም በ*999# ይግዙ፤ ለሚወዷቸውም በስጦታ እያበረከቱ መልካም ምኞትዎን ይግለጹ!

መልካም የትንሳኤ በዓል !

ተጨማሪ መረጃ ፦
https://t.iss.one/telebirr
https://t.iss.one/ethio_telecom

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#Urgent

ዶ/ር ቤቴል ገርማሞ ትባላለች።

ገና የመመረቋን ደስታ ሳታጣጥም እንደቀልድ ለ " ቶንሲል ህመም " በሚል ምርመራ ስትደረግ ያልጠበቀችውን መጥፎ ዜና ተረድታለች።

ዶክተሯ የደም ካንሰር በአይነቱ ደግሞ " acute lymphoblaatic leukemia " የሚባል እንዳለባት በፓቶሎጂ ምርመራ ተረጋገጠባት።

የጥቁር አንበሳ ሜዲካል ቦርድም አፋጣኝ የሆነ የመቅኒ ንቅለ ተከላ እንዲደረግላት መወሰኑን ከቤተሰቦቿ መረዳት ተችሏል።

የደም ካንሰር ምንም እንኳን እጅግ አጣዳፊ እና አስደንጋጭ ቢሆንም በጊዜ ከታከመ እና የመቅኒ ንቅለ ተከላ በማድረግ የመዳን እድል ያለው በሽታ ነው።

መላው ኢትዮጲያዊያ የዚህችን ምስኪን እና ወደፊት ህዝቧን በሞያዋ የምታገለግል ሀኪም ህይወት እንዲታደግ ጥሪ ቀርቧል።

ዶ/ር ቤቴል በወላይታ ዞን በዴሳ በምትባል ከተማ ተወልዳ ያደገች እና በቤተሰቦቿ እና በአከባቢው ማህበረሰብ እንደምሳሌ ምትጠቀስ ብርቱ ሴት ናት።

እንደአብዛኛው ኢትዮጲያዊ ቤተሰብ አቅማቸው እሷን ለማሳከም የሚበቃ አይደለም። ስለሆነም አቅም ያላችሁ ሁሉ ድጋፋችሁ ታደርጉ ዘንድ ቤተሰቦቿ ተማፅነዋል።

በስልክ ደውሎ ለማነጋገር በ0913922441 ላይ መደወል ይቻለል።

Dr Bethel Germamo Ganebo
➡️ የባንክ አካውንት CBE 1000105102384

@tikvahethiopia
#ስቅለት

በክርስትና አስተምሮ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለ በደል ያለ ጥፋት ንጹሕ እና ጻድቅ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰቀሉበት ዕለት ነው።

ዕለቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዂሉ መድኀኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የሚታሰብበት ታላቅ ቀን ነው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን #በስግደት እና #በጾም የሚታሰብ ሲሆን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትም በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ታስቦ ይውላል፡፡

በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከንጋታው ጀምሮ እስከ ማምሻው በዕለቱ የተፈጸሙትን ክስተቶች በሰዓት ከፍላ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓትና በስግደት ታከብረዋለች ፦

ዓርብ ጠዋት

ዓርብ ጠዋት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በፍርድ አደባባይ መቆሙ ይታሰባል። የካህናት አለቆችና ሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ ፤ አስረውም ወሰዱት ፥ ለገዢው ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።

በ3 ሰዓት

ጲላጦስ በወቅቱ በነበረው ሕዝብ ግፊት መሠረት ወንጀለኛውን በርባንን ከእስር አስፈትቶ በምትኩ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠበት ፤ አካሉ እስኪያልቅም 6,666 የገረፉት ከሊቶስጥራ - ቀራኒዮ እርጥብ መስቀል አሸክመው የወሰዱበት ነው።

በ6 ሰዓት

ኢየሱስ ክርስቶስን እጆቹን እና እግሮቹን ቸንክረው በቀራንዮ ጎልጎታ ተራራ በ2 ወንበዴዎች መካከል የተሰቀለበት ነው።

በ9 ሰዓት

በእምነቱ አስተምሮ ይህ ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ የለየበት ወደ ሲዖል ወርዶም የታሠሩትን ሁሉ ያስፈታበት ነው።

11 ሰዓት

ዮሴፍ እና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብር እና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር የቀበሩበት ነው።

(Tikvah Ethiopia Family)

@tikvahethiopia
" የመኪና እቃ የተሰረቀባችሁ በአካል ቀርባችሁ ንብረታችሁን ምረጡ " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በከተማይቱ የመኪና እቃ ስርቆት ወንጀል ስጋትን ለመቀነስ ሕግን መሰረት ያደረገ ኦፕሬሽን በልደታ ፤በአራዳ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዋሳኝ ወረዳዎች ላይ መስራቱን አሳውቋል።

ፖሊስ በተለምዶ ሱማሌ ተራ በሚባለው አካባቢ ባካሄደው ኦፕሬሽን ፦
528 ልዩ ልዩ ፍሬቻዎችን ፣
187 ስፖኪዮችን ፣
113 የመኪና መብራቶች ፣
172 የዝናብ መጥረጊያ በአጠቃላይ 33 ልዩ ልዩ በድምሩ 1 ሺ 269 አይነት የመኪና እቃዎችን መያዙን አስታውቋል፡፡

የተሰረቁ የመኪና እቃዎችን ሚገዙና የሚያሻሽጡ 89 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉን ገልጿል።

በተለያየ ጊዜ የመኪና እቃ የተሰረቀባቸው ግለሰቦች ፦
° በልደታ ፣
° በአራዳ
° በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች በመቅረብ  ንብረታቸውን መምረጥ እንደሚችሉም ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፥ በከተማው ለመኪና እቃ ስርቆት መስፋፋት ልዩ ልዩ ምክንያቶች ቢኖሩም በተለይ ወንጀለኞችን በማደራጀትና በማሰማራት የመኪና እቃ የሚያሰርቁ እና የተሰረቁ እቃዎችን የሚገዙ ህገ-ወጦች ለወንጀሉ መስፋፋት ዋና ምክንያት ናቸው ብሏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማኅብረቅዱሳን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል። የሁለቱም አገልጋዮች የመኖሪያ ቤት መፈተሹም ተገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌዴራል…
#Update

የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉኅን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ ትላንት በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚገኙ ተገልጾ ነበር።

ዛሬ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ማኅበረ ቅዱሳን አሳውቋል።

ምንም እንኳን አመራሮቹ በምን ምክንያት ተይዘው እነደነበር  ያብራራው ነገር ባይኖርም ፥ " በሂደቱ ጉዳዩን በመረዳት #አፋጣኝ_ምላሽ የሰጡንን የመንግሥት የጸጥታ አካላት እናመሰግናለን " ብሏል።

@tikvahethiopia
ከዘመናዊ የATM ማሽኖቻችን ብር ለማውጣት ካርድዎን ወደ ማሽኑ በማስጠጋት እና የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት መገልገል ይችላሉ።

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#BoAATM #ATM #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #contactless #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
“ ... ለኩራዝ የሚጠቀሙበት ነዳጅ በግልጽ ሁኔታ በችርቻሮ፣ የአረቄ በርሜል በከፍተኛ መጠን የሚሸጥበት ቦታ ነው ” - አቶ ንጋቱ ማሞ

በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አቃቂ ገበያ ማዕከል ትላንት ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ የእሳት አደጋ አጋጥሞ ነበር።

በሰዎች ላይ ጉዳት ያልደረሰ ሲሆን 6 ሙሉ ለሙሉ፣ 10 በከፊል፣ በድምሩ 16 ሱቆች እንደተቃጠሉ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የአደጋው መንስኤ ታውቋል? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ “ ፓሊስ ምርመራ እያደረገ ነው። በንብረት ላይ የደረሰን ጉዳትም ባለንብረቶቹን ፓሊስ አጣርቶ ምርመራ እያደረገ ነው ” ብለዋል።

ገበያ ማዕከሉ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብሎ የተለዬ እንደሆነ ፣ ለአደጋ የተጋለጠባቸውን ጉዳዮች ለሚመለከታቸው አካላት ቢያቀርብም የማስተካከያ እንዳልተደረገ ኮሚሽኑ ያስታወቀ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ተሰጥቶ የነበረው ማስጠንቀቂያ ምን እንደነበር ኮሚሽኑን ጠይቋል።

አቶ ንጋቱ በሰጡት ምላሽ፣ “ ለገበያ ማዕከሉ አክሲዮን ማኅበራት አደጋ ውስጥ ናችሁ። ገበያ ማዕከሉ በዘመናዊ መልክ ይገንባ ንብረታችሁ ለአደጋ ሰለባ እንዳይሆን የሚል ምክረ ሀሳብ አቅርበናል። በግልባጭ ደግሞ ለወረዳውም ” ብለዋል።

“ ቤቶቹ በቀላሉ ሊቀጣጠሉ ከሚችሉ ግብዓቶች (ቆርቆሮ በቆርቆሮ) የተገነቡ ናቸው። መፍትሄ ብለን ያቀረብነው ገበያ ማዕከሉ ዘመናዊ ሆኖ እንዲገነባ ነው። ዘመናዊ ስንል እሳትን ሊቋቋም ከሚችል እንደ ድንጋይ ከመሳሰሉ ግብዓቶች እንዲሰራ ነው ” ሲሉ አስረድተዋል።

አቶ ንጋቱ፣ “ ከገጠር የሚመጡ ሰዎች ለኩራዝ የሚጠቀሙበት ነዳጅ በግልጽ በችርቻሮ፣ የአረቄ በርሜል በከፍተኛ መጠን የሚሸጥበት ቦታ ነው” ብለዋል።

“ ንግዱ ዘርፍ፤ ዘርፍ ያስፈልገዋል። በጎን ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እየተሸጡ፣ በጎን ደግሞ የካቲካላ ንግድ በፍጹም ምንም አይነት ህብረት የላቸውም ” ነው ያሉት።

የገበያ ማዕከሉ በተደጋጋሚ አደጋ እንደደረሰበት አስታውሰው፣ አደጋ ቢያጋጥም እንኳ የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ለማስገባት ምቹ ባለመሆኑ፣ በውስጡ የሚከናወኑ የንግድ ዘርፎች የተደበላለቁ በመሆናቸው የሚመለከታቸው አካላት አሁንም ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በበዓሉ ወቅት ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች ምንድናቸው ?

-  በምግብ ማብሰያ ወይም በማዕድቤት አካባቢ የኤሌክትሪክ ፣ የቡታጋዝ ፣ የከሰል ምድጃዎችን በአግባቡ እና በጥንቃቄ ይጠቀሙ።

- በገበያ ማዕከላት የገበያተኛውን ቀልብ ለመሳብ የሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክስ ዲኮሬሸኖች ቃጠሎ እንዳያስነሱ ይጠንቀቁ።

- ሻማ እና ጧፍ ሲጠቀሙ ከተቀጣጣይ ነገር ያርቁት።

- ካምፋዬር ሚያዘጋጁ ከሆነ ከአካባቢው ከመራቅዎ በፊት በደንብ መጥፋቱን ያረጋግጡ።

- በፍጹም ጠጥተው አያሸከርክሩ።

ለማናቸውም የእሳት እና የድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም የአምቡላንስ አገልግሎት የሚከተሉትን የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስልክ ቁጥሮች መዝግበው ይያዙ።

24 ሰዓት መደወል ይችላሉ።

1. ማዕከል - 0111555300/ 0111568601
2. አራዳ - 0111567004/ 0111560249
3. ቂርቆስ - 0114663420/21
4. አዲስ ከተማ - 0112769145/46
5. ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 0114425563/64
6. አቃቂ ቃሊቲ - 0114340096 / 0114343063
7. ቦሌ - 0116630373/74
8. ኮልፌ ቀራንዮ- 0113696085/ 0113696104
9. ጉለሌ - 0112730731/ 0112730653
10. ቦሌ ሰሚት - 0116680846/ 0116680760
11. ልደታ - 0115589043/ 0115589533

(በእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የቀረበ)

እንኳን አደረሳችሁ !

@tikvahethiopia