TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገር ውስጥ በረራ በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረ ገልጿል።

እየተጠናቀቀ ባለው በዚህ በጀት አመት የአገር ውስጥ ተጓጓዦች ቁጥር 3.5 ሚሊየን ይደርሳል፡፡

ይህ መጠን ከ2015 ዓ.ም በጀት አመት አንጻር የ34.6 በመቶ ጭማሪ ይኖረዋል።

በቀደመው አመት በአገር ውስጥ በረራ የተስተናገዱት ተሳፋሪዎች 2.6 ሚሊየን እንደነበሩ " ካፒታል ጋዜጣ " አየር መንገዱን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገር ውስጥ በረራ በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረ ገልጿል። እየተጠናቀቀ ባለው በዚህ በጀት አመት የአገር ውስጥ ተጓጓዦች ቁጥር 3.5 ሚሊየን ይደርሳል፡፡ ይህ መጠን ከ2015 ዓ.ም በጀት አመት አንጻር የ34.6 በመቶ ጭማሪ ይኖረዋል። በቀደመው አመት በአገር ውስጥ በረራ የተስተናገዱት ተሳፋሪዎች 2.6 ሚሊየን እንደነበሩ " ካፒታል ጋዜጣ " አየር መንገዱን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።…
' በረራው እንዴት ጨመረ ? '

" ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ በረራ መጨመር የሚገልጸውን መረጃ በእጅ ስልኬ ላይ ደረሶኝ አየሁት።

እንዲያው ዝም ብሎ የሀገረ ውስጥ በረራ ጨመረ ብሎ የሚታለፍ መስሎ አልተሰማኝም።

በእርግጥ አየር መንገዳችን ገቢ ማግኘቱ እጅግ የሚያስደስት ቢሆንም ሰዎችን በዚህን ያህል ልክ የአየር ትራንስፖርት እንዲጠቀሙ ያደረጋቸው ምንድ ነው ?  ብሎ ጥናት ማድረግ ይገባል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገራችን የየብስ ትራንስፖርት ማድረግ እኔን ጨምሮ ብዙ ሰዎችን የሚያሰጋ ሆኗል።

በተለያየ ጊዜ የሚሰማው የእገታ ወንጀል ፣ ጥቃት ሰዎች ቅርብ ከተሞች ሳይቀር በአየር እንዲጓዙ እያደረጋቸው ነው።

ለአብነት እኔ ከዚህ ቀደም ለስራ የግል መኪናዬን ይዤ ከከተማ ውጭ እስከ ድሬዳዋ ድረስ እየነዳው ሄጄ እመለስ ነበር ዛሬ ላይ ያን ለማድረግ አልችልም። የሆነ ነገር ብሆንስ ብዬ እፈራለሁ ስለዚህም በየጊዜው የአየር ትኬት መቁረጥ ግድ ብሎኛል።

እኔ ስላለኝ ነው ይህ ያደረኩት አቅሙ የማይፈቅድ ደግሞ የግዴታ ሆኖበት የየብስ ይጠቀማል።

እኔ እንኳን የማውቀው ብዙ ሰው ተቸግሮም ቢሆን በአየር ትራንስፖርት ለመጠቀም ሲገደድ ብዙ ጊዜ አይቻለሁ።

ወደ ሰሜኑ ክፍልም ብንመለከተ ካለው ጸጥታ ጋር በተያየዘ ሰዎች ከየብስ ትራንስፖርት ይልቅ አቅማቸው ባይፈቅድ እንኳን ተቸግረው የአየር ትራንስፖርት ይጠቀማሉ።

ስለዚህ የሀገር ውስጥ በረራ ቁጥሩ የመጨመሩ ብቻ ሳይሆን በዚህ ልክ እንዴት ሊጨምር እንደቻለ ምክንያቱ ቢታወቅ ጥሩ ነው ባይ ነኝ። "

(Ato Solomon K. Tikvah Family Addis Ababa)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION🔔 በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ወላይታ ዞን ባሉ ወረዳዎች ያሉ መምህራን ከደመወዝ ጋር በተያያዘ ስራ እንዳቆሙ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አማኑኤል ጳውሎስ ፦ " ... ጉዳዩ ስር የሰደደና የቆየ ነው። አሁን ላይ ' በተራበ አንጀታችን መስራት አልችልም ' በሚል መምህራኑ ስራ አቁመዋል። በፐርሰንት…
#Wolaita

" መምህራኑ በተራበ አንጀት አንሰራም በማለት ስራ አቁመዋል " -  የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማህበር

" መምህራኑ ወደስራ ያለተመለሱት የሙያ ማረጋገጫ ፈተና ላይ በመሆናቸዉ ነው " - የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ

ከሰሞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች መምህራን ከደሞዝ ጋር በተያያዘ ስራ ማቆማቸው ተነግሯል።

መምህራኑ በተለያየ ጊዜ ደሞዝ ሲዘገይና ሲቆራረጥ መቆየቱ ለስራቸው እንቅፋት ለህይወታቸውም አደጋ መሆኑን በመግለጽ ለሚመለከታቸዉ አካላት በተለያየ መልኩ ለመግለጽ ሲሞክሩ መቆየታቸውን ይገልፃሉ።

ከነዚህ መምህራን ውስጥ አንዱ የሆኑት መምህር አሸብር ፤ እርሳቸዉና በዳሞት ገሌ ወረዳ ያሉ መምህራን በደሞዝ መቆራረጥና የእርከን ጭማሪ እጦት ምክኒያት ምሬት ውስጥ እንደገቡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በተደጋጋሚ የግማሽ ወር ደሞዝ ሲወስዱ መቆየታቸዉን የሚገልጹት መምህር አሸብር አሁን ላይ ጉዳዩ ለመምህራን በህይወት የመኖርና ያለመኖር መሆኑን ገልጸዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመምህራን ማህበር ፕሬዚዳንቱ አቶ አማኑኤል ጳውሎስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በተደጋጋሚ " ችግሩ ይቀረፍ " በማለት በደብዳቤም ሆነ በውይይት ባለስልጣናትን ስናናግር ቆይተናል ብለዋል።

ጉዳዩ ስር የሰደደና የቆየ መሆኑን ገልጸው አሁን ላይ መምህራኑ " በተራበ አንጀታችን መስራት አልችልም " በሚል ስራ ማቆማቸዉን ገልጸዋል።

መምህራን በፐርሰንት እየተቆራረጠ የሚከፈላቸዉ ደሞዝ በዚህ ወር ለ16 ቀን መዘግየቱን ተከትሎ ስራ እንዳቆሙ አስረድተዋል።

" ችግሩ ከደሞዝም በላይ የሌሎች ጥቅማጥቅሞች ማለትም የወዝፍ ደሞዝ ፣ ከደረጃ እድገት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደሞዝ ጭማሪና የእርከን እድገት መቅረት ፈተና ሆኖባቸዋል " ብለዋል።

በሌላ በኩል አሁን ላይ እንደ ሶዶ ባሉ ከተሞች ብቻ ደሞዝ መከፈሉ ወረዳ ላይ ካሉ መምህራን በላይ የገጠር ተማሪ ወላጆችን ልጆቻችን በዚህ ምክኒያት ከትምህርት ራቁ በሚል እያናደደ መሆኑን በመግለጽ ይህን አሳሳቢ ችግር የዞኑም ሆነ የክልሉ መንግስት በአፋጣኝ ሊቀርፈዉ እንደሚገባ አቶ አማኑኤል ጳውሎስ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመምህራኑን ቅሬታ ተከትሎ ምላሽ እንዲሰጡ የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊዉ አቶ ታደሰ ኩማን አነጋግሯል።

እሳቸውም ፤ " ነገሩ እንደሚባለዉ ሳይሆን ክፍያዉ የዘገየዉ በ8 መዋቅሮች ብቻ ነው " ብለዋል።

" አሁን ላይ ደሞዙ በመከፈሉ ችግሩ ተቀርፏል " ሲሉ ገልጸዋል።

ለቀናት የዘገየዉ ደሞዝ ከተከፈለ በኋላ መምህራን በአመጽ ሳይሆን በነበረባቸዉ የሙያ ማረጋገጫ ፈተና ምክኒያት ወደስራ አለመግባታቸውን አስረድተዋል።

ከዚህ ዉጭ አንዴ ብቻ በተፈጠረ የደሞዝ እጥረት ለአንድ ወረዳ ብቻ ስልሳ ፐርሰንት እንደተከፈለ በመግለጽ ከዛ ውጭ ምንም አይነት የደሞዝም ሆነ የጥቅማጥቅም ችግር እንደሌለ ምላሽ ሰጥተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

(ለተማሪዎች እና ለወላጆች)

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለ2 ወር የሚቆይ የAI ሰመር ካምፕ የስልጠና መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

በስልጠናው መርሃ ግብር ላይ መሳተፍ የሚችሉት የመጀመሪያ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑ ናቸው።

ተማሪዎቹ ስልጠናውን በሳምንት ለ4 ቀናት መከታተል የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ለተከታታይ 2 ወራት ለሚሰጠው ስልጠና ፍላጎት ያላቸው ታዳጊዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 07/2016 ባሉት ተከታታይ ቀናት መመዝገብ ይችላሉ።

ስልጠናው የሚያተኩርባቸው ፦
➡️ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣
➡️ ሮቦቲክስ፣
➡️ ፕሮግራሚንግ፣
➡️ ማሽን ለርኒንግ
➡️ ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ (IoT) እንደሆኑ ተገልጿል።

በስልጠናው መሳተፍ የሚፈልጉ አመልካቾች ፦

👉 forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8

👉 https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/ ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

በተጨማሪ እውቀትና ክህሎታቸውን ለተማሪዎች በማካፈል በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ትውልዱን ለመገንባት ዕድሉን የሚፈልጉ አሰልጣኞች ፦

👉 www.aii.et/ethiopian-ai-summer-camp-2024-application-form-trainer-for-summer-camp/

👉 forms.gle/P2vAoZuWT7JgYQtT6 ላይ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

#AI #ETHIOPIA

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ከዘመናዊ የATM ማሽኖቻችን ብር ለማውጣት ካርድዎን ወደ ማሽኑ በማስጠጋት እና የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት መገልገል ይችላሉ።

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#BoAATM #ATM #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #contactless #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ኢትዮ_ቴሌኮም

የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ማዕከላት መጀመሩን በይፋ ማብሰራችን ይታወቃል።

በማስከተል ምዝገባ በተጀመረባቸው ማዕከላት የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ተገኝተው አተገባበሩን ተመልክተዋል።

በዚህም ወቅት ለምዝገባው አስፈላጊ ግብአቶች መሟላታቸው እና የምዝገባ አገልግሎቱ በላቀ ፍጥነት መስጠት መቻሉን በተግባር መመልከት ችለዋል፡፡

አገልግሎቱ በሌሎች ተጨማሪ ማዕከላት የሚስፋፋ መሆኑም የተገለጸ ሲሆን ተገልጋዮች ስለዲጂታል መታወቂያ ጠቀሜታ እንዲረዱ የማድረግ ሥራ በስፋት እንደሚከናወን ተነግሯል።

ዜጎች በአቅራቢያቸው የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ የሚከናወንበትን የኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት ማዕከል ለማወቅ ቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/fpgu4m ውስጥ የተካተተውን አዲስ የአቅጣጫ ጠቋሚ መተግበሪያ ዳታ በማብራት ብቻ በነጻ መጠቀም ይችላሉ።

ተጨማሪ መረጃ ፦
https://t.iss.one/telebirr
https://t.iss.one/ethio_telecom

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #NIDP
" የፀጥታ አካላት ነን ፤ #በወንጀል_ትፈለጋለህ " በማለት አስፈራርተው ከኖክ ነዳጅ ማደያ ስራ አስኪያጅ ገንዘብ የተቀበሉ ግለሰቦች በእስራትና ገንዘብ መቀጣታቸው ተነገረ።

የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾች ፦
1ኛ. ጫላ መገርሳ፣
2ኛ. ለሊሳ በቀለ፣
3ኛ  ዳዊት ጉደታ፣
4ኛ. ዮሃንስ ደረጄ
5ኛ  ብርቱካን ለታ ናቸው።

ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች በመጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በሸገር ከተማ ገፈርሳ ክ/ ከተማ አካባቢ በሚገኝ የኖክ ነዳጅ ማደያ ስራ አስኪያጅ የሆነን የግል ተበዳይን " የፀጥታ አካላት ነን ፣ በወንጀል ትፈለጋለህ " በማለት መንገድ ላይ ያስቆሟቸዋል።

በኃላም ከውጭ ወደ ውስጥ እንዳይታይ አድርገው በስቲከር ሸፍነው ወደአዘጋጁት የቤት መኪና ውስጥ በማስገባት ወደ መልካ ናኖ ክ/ከ አንፎ ወደ ተባለ አካባቢ ይወስዷቸዋል።

ከዚህም በኋላ የሞተ ሰው ፎቶ ለግል ተበዳዩ በማሳየትና በመሳሪያ በማስፈራራት ግማሽ ሚሊየን ብር እንዲያመጣና እንደሚለቁት ይገልጻሉ።

ገንዘቡን ካልከፈለ ደግሞ " ወደ ጦር ኃይሎች እንወስድኃለን " በማለት ገንዘብ እንዲከፍል ያስፈራሩታል።

ይህን ተከትሎ የግል ተበዳዩ በባንክ ሂሳቡ ውስጥ 100 ሺህ እንዳለው ይገልጽላቸዋል።

በዚህም ጊዜ 1ኛ ተከሳሽ ባለቤቱ በሆነችው በ5ኛ ተከሳሽ የባንክ ሂሳብ በሞባይል ባንኪንግ የግል ተበዳዩ 100 ሺህ ብር እንዲያዘዋውር ያደረገና ቀሪውን 400 ሺህ ብር እንዲያመጣ በማስጠንቀቅ ይለቁታል።

በህገወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ደግሞ 5ኛ ተከሳሽ ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ምንጩን ለመደበቅ በማሰብ በተለያዩ መጠኖች ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅም እንዳዋሉት የክስ መዝገቡ ያስረዳል።

ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ድርጊቱን ክደው የተከራከሩ ሲሆን ዐቃቤ ሕግ ያሉትን የሰው ምስክሮች ፣ አስረጂና ገላጭ የሰነድ ማስረጃዎች አቅርቧል።

ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ስላልቻሉ ፍ/ቤቱ  የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል።

በዚህም ፦
1ኛ ተከሳሽ በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ፤

ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾችን ደግሞ እያንዳንዳቸውን በ7 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ

5ኛ ተከሳሽ በ1 ዓመት እስራትና በ1 ሺህ ብር ገንዘብ እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ወስኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኤፍ ቢ ሲ (ታሪክ አዱኛ) መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
“ ልጅ ያለው የልጅን ነገር ያውቀዋል። ቶሎ ካልታከመች ክፍተቱ እየጨመረ ነገሮች ሁሉ ይከብዳሉ ” - የ9 ዓመቷ ታዳጊ እናት

ልጃቸው ለየልብ ህመም የታመመችባቸው እናት ደጋግ ኢትዮጵያውያን እንዲያግዟቸው ተማጽኑ።

ወ/ሮ መባ አላምረው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ሊያ የ3ኛ ክፍል ተማሪ 2ኛ ልጄ ናት። #ልቧ 15 ሚሊ ሜትር #ክፍተት አለው ” ብለዋል።

የልብ ስፔሻሊቲ ዶክተርም፣ “ ‘ችግሩ ክፍተት መፍጠሩ ብቻ ሳይሆን የቀኝ ልቧ አቅጣጫውን በመሳት ወደ ሳምባዋ ክፍል ደም እየረጨ ነው። ሳምባዋም ወደ ማበስበስ ደረጃ እየደረሰ ነው። በአስቸኳይ ቀዶ ጥገና መደረግ አለበት’ ” እንዳሏቸው አስረድተዋል።

“ በፊት ላይ ‘#የሳንባ #ምች ነው’ እየተባለ ነበር። አሁን ‘የልብ ክፍተት ነው’ ተባለች። #እጇንም #እግሯንም #መሸምቀቅ ጀመራት። ትምህርቷን አቋርጣ ቤት ከተቀመጠች 1 ወር ሆናት ” ብለዋል።

“ ‘ሳንባዋ ለንቅለ ተከላ የሚደርስ ነው’ አሉኝ ” ያሉት እኝሁ እናት፣ ለሰርጀሪው ብቻ 595 ሺሕ ብር፣ የሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ 700 ሺሕ ብር ለቀዶ ጥገና እንደተጠየቁ አስረድተዋል።

የታዳጊዋ እናት፣ “ ልጅ ያለው የልጅን ነገር ያውቀዋል። ቶሎ ካልታከመች ክፍተቱ እየጨመረ ነገሮች ሁሉ ይከብዳሉ። ሁሉም ያቅሙን በገንዘብም በጸሎትም እንዲተባበረኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲረዳኝ እለምናለሁ ” ሲሉ ተማጽነዋል። 

እናት መባ አላምረውን በስልክ ለማግኘት በ +251939665539 መደወል ይቻላል። የባንክ የሒሳብ ቁጥራቸው 1000470071536 ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
“... ኮንትራክተሮችና ባለንብረቶች አደጋ አጋጥሞ ስንደርስ እንኳ #ቦታው_ላይ_አይገኙም ” - አቶ ንጋቱ ማሞ

የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን፥ በከተማው በአደጋ የሚከሰት ሞት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አንጻር ዘንድሮ መጨመሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

በብዛት የሞት አደጋ እየደረሰባቸው ያሉት ደግሞ የቀን ሠራተኞች መሆናቸውን ጠቁሟል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነተ ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ምን አሉ ?

- “ ከተማው ውስጥ ብዙ የግንባታ ሥራዎች ይከናወናሉ። በተለይ አሁን ሕይወታቸውን እያጡ ያሉት በኮንክትራክሽን / በግንባታ ዘርፉ ያሉ የቀን ሠራተኞች ናቸው። ”

- “ የቀን ሠራተኞች በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ ብዙ ጊዜ ጉልበታቸውን ነው ይዘው የሚገቡት፤ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል የሚል ቴክኒካል እውቀት ላይ የተመሰረተ መረጃ የላቸውም።  እንዴት የሥራ ላይ አደጋን መከላከል እንደሚችሉ ስለጠና እንኳ አይሰጥም። ”

- “ ' #የቀን_ሠራተኞች_እንፈልጋለን ' የሚሉ ማስታወቂያዎችን የኮንስትራክሽን ሳይቶች ላይ እናያለን። በዚያው ሥራ ያጣ መንገደኛ ይገባል ግን ሥራውን ለመከናውን ምን ሊያጋጥም ይችላል ? ብሎ አስቀድሞ የመገመት እውቀት አይኖርም። ”

- “ ኮንትራክተሮችና ባለንብረቶች ላይ ትልቁ ኃላፊነት ይወድቃል። እነርሱ ደግሞ በሚፈለገው ደረጃ ለዘርፉ ትኩረት እየሰጡ አይደለም። አደጋ አጋጥሞ ስንደርስ እንኳ #ቦታው_ላይ_አይገኙም። ”

- “ ፈቃድ ከወሰዱ በኋላ ግንባታው እስኪጠናቀቅ የደህንነት መርሆዎችን ያለመከተል ሁኔታ አለ። ”

Q. መፍትሄውን ምንድነው ?

- “ መፍትሄውማ ፈቃድ ሰጪው አካልም ፈቃድ ከሰጠ በኋላ በየጊዜው ጠብቅ ቁጥጥር በማድረግ ለአደጋ የተጋለጡ አሰራሮችን እየለዩ በህንጻ አዋጁ መሠረት እርምጃዎችን ቶሎ ቶሎ መውሰድ ያስፈልጋል። ”

ሰሞኑን የ7 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የድንጋይ እና አፈር ናዳ አደጋ በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ ባሉ ሠራተኞች ላይ ባለመድረሱ ለየት ያለ ቢሆንም ይህንኑ አደጋ ጨምሮ በ2016 ዓ/ም እስካሁን 12 ሰዎች በተለያዩ ጊዜዎችና አደጋዎች ሞተዋል።

የሟቾች ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ጨምሯል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@thikvahethiopia