TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
" የሟች ቤተሰብ ተገኝቷል " - ፖሊስ
በሟች ኪስ ማንነቱ የሚጠቅስ መረጃ በማጣቱ ምክንያት የሟችን ፎቶ በመለጠፍ ቤተሰቦቹን አፋልጉኝ ያለው የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ የሟች ቤተሰብ መገኘቱ አስታውቋል።
የማህበራዊ የትስስር ገፆችና ሚድያዎች በሟች ቤተሰብ ፍለጋ ያደረጉት የነቃ ወገናዊ ተሳትፎና ጥረት አመስግኗል።
ለሟቹ ቤተሰብ ክብር ሲባል ፎቶውን ከገፃቸው በማጥፋት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል።
በዚህም መሰረት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለሟች ቤተሰብ ክብር የሟችን ፎቶ #ማጥፋቱን ለመላ አባላቱ መግለጽ ይወዳል።
ምናልባት በውስጥ የተቀባበላችሁም የሟችን ፎቶ ከስልካችሁ እንድታጠፉ እንጠይቃለን።
ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት በዓዲግራት ከተማ አንድ ወጣት ተገድሎ ተጥሎ መገኘቱንና በግድያው የተጠረጠሩ 3 ግለሰቦች ሟቹ ከወደቀበት አቅራቢያ በሚገኝ አንድ መጠጥ ቤት በቁጥጥር ስር መዋላቸው መረጃ እንደላክልንላችሁ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

#BankofAbyssinia
በተለያዩ ቦታዎች በአፖሎ ሲከፍሉ ቅናሽ ያገኛሉ!
አሁኑኑ መተግበሪያውን በማውረድ ይጠቀሙ።
ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

የፋሲካ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የመግቢያ ትኬትዎን በቴሌብር *127# ወይም https://onelink.to/fpgu4m በመግዛት ጎራ ይበሉ፤ እስከ ብር 2500 ለሚደርሰው ግብይትዎ የአየር ሰዓት እና ጥቅል የሚገዙበት 10% ተመላሽ ያግኙ፡፡
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

" ልጄን አድኑልኝ " - መምህርቷ እናት
መምህርት አልሻምጌጥ ንጉስ ፤ ልጇ የአብቃል በተወለደ በሀያ አንድ ቀኑ ነው የልብ ህመም እንዳለበት ያወቀችው።
ላለፉት 5 አመታት የህጻናት የልብ ቀዶ ጥገና መዕከል አስመዝባ ብጠብቅም ወረፋ ሊደርሳት አልቻለም።
" አሁን ልጄ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደረሰ " ስትል ገልጻለች።
ከሀያ አንድ ቀኑ ጀምሮ ከሀዋሳ አዲስ አበባ እየተመላለሰች ሰርጀሪውን ስትጠብቅና ማስታገሻ መድሀኒት ስትጠቀም ብትቆይም እንደልጅነቱ መቦረቅ ያልቻለው የአብቃል " አሁን ላይ የልቡ ክፍተት አራት ሚሊ በመድረሱ እብጠት ፈጥሮበታል " ስትል አስረድታችለ።
ይህ እብጠት ምግብ እንዳይረጋለት ከማድረጉ በላይ በአፍና በአፍንጫዉ ደም መውጣት መጀመሩ እና ድንገት በየሰአቱ እራሱን ከመሳቱ በተጨማሪ ፍጹም የድካም ስሜት ውስጥ እንዲገባ በማድረጉ ለቤተሰቡ ታላቅ ድንጋጤ ፈጥሯል።
ይህን ተከትሎ ጤና ባለሙያዎች በቶሎ ሰርጀሪዉ መሰራት እንዳለበት ቢናገሩም የመምህር ደሞዙን ከእለት ጉርስ አበቃቅቶ ለመድሀኒት ሲጠቀም ለቆዉ የመምህር አልሻምጌጥ ቤተሰብ ዱብ እዳ ሆኖበታል።
ቤተሰብም አሁን ላይ የሚያደርገዉ ጠፍቶበታል።
በጉዳዩ ላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ በቲኪቫህ ኢትዮጵያ በኩል መልእክት አስተላልፉልኝ የምትለው እናት አሁን ላይ በግል ሆስፒታል ለሰርጀሪዉ ብቻ 650 ሽህ ብር እንደተጠየቀ በአጠቃላይ ከ800 እስከ 900 ሽህ ብር እንደሚያስፈልግ ገልጸለች።
ይህን ማድረግ ባለመቻሏ እና ገንዘብም ስለሌላት ልጇን አይኗ እያዬ ልታጣዉ መሆኑን በእንባ ተናግራለች።
በመሆኑም ፥ " ደጉ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚቻለዉን አድርጎ ልጄን ያድንልኝ " በማለት ተማጸናለች።
መምህር አልሻምጌጥ ንጉስን በስልክ ማነጋገር የሚፈልግ የግል ስልክ ቁጥሯ 0916155490 ነው። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000243926053 የሂሳብ ቁጥሯ ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

#ትግራይ #መምህራን " ጥያቄያችን ፍትሃዊ ምላሽ ካላገኘ ወደ ቀጣይ እርምጃ እንገባለን " - የትግራይ መምህራን ማህበር የትግራይ መምህራን ማህበር ፤ ጥያቄያችን ፍትሃዊ መልስ ካላገኘ በምክር ቤት አስወስነን ለቀጣይ ትግል እንዘጋጃለን " አለ። የትግራይ መምህራን ማህበር ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የ5 ወራት ውዙፍ ደመወዝ ለመክፈል የገባው ቃል እስከ አሁን አልተገበረም ብለዋል። መምህራን ውዙፍ ደመወዝ…
" የመምህራን የስነ-ልቦና ቁስል ሳይሽር ስለ የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ማሰብ ይከብዳል " - ማህበሩ
የትግራይ መምህራን ማህበር በድጋሚ የመምህራን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛቸው እንዲከፈል ጠየቀ።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርንም ዳግም አስጠነቅቋል።
ማህበሩ ሚያዚያ 8 በኣክሱም ከተማ 33ኛው ጉባኤውን አካሂዶ ነበር። በጉባኤው ማጠቃለያ ባወጣው የአቋም መግለጫ " የትግራይ መምህራን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛቸው እንዲከፈል " ሲል ጠይቋል።
የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ እስከ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባለው ጊዜ ከሚመለከታቸው የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር በመገናኘት ስለ ውዙፍ ደመወዝ መከፈል የመጨረሻ አቋሙ እንደሚያሳውቅ አመልክቷል።
ለጥያቄው በጊዜ ገድብ የተወሰነ አሳማኝ መልስ ካላገኘ ጠበቃ አቁሞ ክስ እንደሚመሰርት አሳውቋል።
" ተቃውሟችን እና ጥያቄያችን ትምህርት ቤቶች በመዝጋትና ተተኪ ዜጋ በመጉዳት የማሳካት ፍላጎት የለንም " ያለው ማህበሩ " ግዴታችን እየፈፀምን መብታችን እስከ ጫፍ እንጠይቃለን " ብሏል።
" የመምህራን የስነ-ልቦና ቁስል ሳይሽር በትምህርት ስለሚገነባው ትውልድና የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ማሰብ ይከብዳል " ሲልም አክሏል።
ማህበሩ የመምህራን ጥያቄ እስኪመለስ ህጋዊ ተቋውሞ ማሰማቱን እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
መረጃውን የመቐለው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ፥ ድምጺ ወያነ ቴሌቪዥንን ዋቢ አድርጎ ነው የላከው።
ፎቶ ፦ ፋይል

የከባድ መኪና ሆነ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሹፌሮች በተለያዩ ወቅቶችና ቦታዎች በታጣቂዎች የሚደርስባቸውን ፦
- ግድያ ፣
- እገታ ፣
እምዲሁም የተሽከርካሪዎች ቃጠሎ በተመለከተ በተደጋጋሚ መረጃዎችን መለዋወጣችን ይታወሳል።
ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን መቂ አካባቢ “ የታጠቁ ኃይሎች ” በአሽከርካሪና ረዳት ላይ ጉዳት እንዳደደረሱ ፣ ከወራት በፊትም በርካታ ተሽከርከርካሪዎች ታቃጥለው እንደነበር ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ቃላቸውን የሰጡ የመቂ ነዋሪ ፥ አንድ የአይሱዚ ሹፌር ሲገደል ፣ ረዳቱ አካላዊ ጉደት እንደረሰበትና ሌሎች ተሽከርካሪዎች በጥይት እንደተበሳሱ አስረድተዋል።
" የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው ሹፌሩ ተገደለ። ሚያዚያ 9 ቀን 2016 ዓ/ም ነው የተቀበረው ፤ ረዳቱም ቆሰለ " ሲሉ ነው የተናገሩት።
የተኩስ እሩምታ የተከፈተባቸው ከ7 በላይ ተሽከርካሪዎች መሆናቸውን ጠቁመው " ተዘግቦ እንኳን አየዋለሁ ብዬ ነበር የዘገበው ሚዲያ የለም " ብለዋል።
ሟቹ ሹፌር መነሻውን አዲስ አበባ በማድረግ እየተጓዘ በነበረበት ወቅት መቂ አካባቢ ማታ ላይ በታጣቂዎች ተኩስ እንደተከፈተበት አስረድተዋል።
" ሌሎቹ ሹፌሮች ፈጣሪ አትርፏቸው አልተጎዱም። ተሽከርካሪዎቻቸው ግን በጥይት ተበሳስተዋል። ጎማው እስከ 15 ጥይት ያረፈበት አለ " ብለዋል።
እኚሁ ነዋሪ ታጣቂዎች " ወደ ኦሮሚያ ተሽከርካሪ እንዳይሄድ ሰሞኑን እቀባ ጥለዋል " ያሉ ሲሆን ጥቃቱን በከፈቱ በማግስቱ " ከመከላከያ ጋ ተታኩሰዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
ሌላኛው ነዋሪ ፤ የዛሬ ወር ገደማ በተመሳሳይ እዛው ቦታ/መቂ ብዙ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል ሲሉ አስታውሰዋል።
" ጥቃቱ አለ አሁንም አልቆመም። የተወሰነ ጊዜ መከላከያ ሲመጣ ጋብ ይላል እንጂ። ሹፌሮች ስቃይ ላይ ናቸው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ እጅግ ትኩረት ይሻል የተባለውን የሹፌሮችን ጥቃት በተመለከተ ከክልሉም ሆነ ከዞኑ ኃላፊዎች ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን፣ ምላሽ የሚሰጡ ከሆነ የሚያስተናግዳቸው መሆኑን ያሳውቃል።
NB. መቂ ከሰሞኑን ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር ግድያን ያስተናገደች ከተማ ናት።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

" ቲክቶክ " ኪርጊስታን ውስጥ እንዲታገድ ተወሰነ። ኪርጊስታን " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ ለልጆች አእምሯዊ እድገት እና አጠቃላይ ደህንነት ጠንቅ እየሆነ ነው በሚል ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ ወስናለች። ውሳኔውን ያሳለፈው የሀገሪቱ የባህል ፣ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ነው። ሚኒስቴሩ ባደረገው ግምገማ መሰረት " ቲክቶክ " ህጻናት እጅግ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ይዘቶችን እንዳያገኙ ለመከላከል በቂ መቆጣጠሪያ…
#Update
የ " ቲክቶክ " እገዳ በኪርጊስታን ተግባራዊ ሆነ።
ኪርጊስታን " ቲክቶክ " በመላ ሀገሪቱ እንዲታገድ ውሳኔ ማስለፏ ይታወሳል በዚሁ ውሳኔ መሰረት የቴሌኮም አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ትዕዛዙን ወደ መፈጸም #እርምጃ ገብተዋል።
በሀገሪቱ " ቲክቶክ " መስራት እንዳቆመም ተነግሯል።
ሰዎች መተግበሪያውን ሲከፍቱን የሚያገኙት መልዕክት " Unable to load, please try again." የሚል ነው።
ውሳኔው በሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት መ/ቤት የተላለፈ ነው።
የኪርጊስታን ዲጂታል ሚኒስቴር ቲክቶክን የሚያስተዳድረው ' ባይት ዳንስ ' ኩባንያ ፥ " #የልጆችን ፦
- አእምሯዊ፣
- አካላዊ፣
- መንፈሳዊ እና #ሥነምግባራዊ እድገትን ለመጠበቅ በህግ የተዘረዘሩ ህጋዊ መስፈርቶችን ማክበር አልቻለም " ብሏል።
በዚህም ምክንያት " ቲክቶክ " በሀገሪቱ እንዳይሰራ ተደርጓል።
ውሳኔው የተቃወሙ አካላት ይህ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ገደቡ እንዲነሳ ጠይቀዋል። ከገደብ ይልቅ ቁጥጥር ይደረግበት ብለዋል።
ከዚህ ቀደም የኪርጊስታን የባህል፣ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ፥ " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ ለልጆች አእምሯዊ እድገት እና አጠቃላይ ደህንነት ጠንቅ እየሆነ ነው " ማለቱ ይታወሳል።
መተግበሪያው #ህጻናት እጅግ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ይዘቶችን እንዳያገኙ ለመከላከል በቂ #መቆጣጠሪያ እንደሌለው ነበር የገለጸው።
በተጨማሪም ለተጠቃሚዎቹ ትክክለኛ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎች እንደለለው እና ተጠቃሚዎችን በአጫጭር የቪዲዮ ክሊፖች ወደ ምናባዊ ግዛት በመሳብ #ሱስ የሚያስይዝ ይዘት እንዳለው አስረድቶ ነበር።
ሚኒስቴሩ " ቲክቶክ " በወጣቱ ትውልድ ደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው በአጠቃላይም ለትውልዱ ጠንቅ እየሆነ እንደመጣ አሳውቆ ነበር።
በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ውስጥ ከመረጃ ደህንነት ጋር በተያያዘ መተግበሪያው እንዲታገድ ከፍተኛ ግፊት እየተደረገ ሲሆን " ቲክቶክ " ከቻይናው ኩባንያ ካልተፋታ / አሜሪካ የምትቆጣጠረው አይነት ካልሆነ በመላ ሀገሪቱ መታገድ ዕጣ ፋንታ ሊገጥመው ይችላል ተብሏል።

ከባንክ ወደ M-PESA ብራችንን በማስተላለፍ እስከ 50ብር ሽልማት እንፈስ!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!
🔗የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether

#Update በአዲስ አበባ ከተሞ ቦሌ ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከቀናት በፊት መገደላቸው የተነገረው የፋኖ አባላት ወላጆች የልጆቻቸው አስከሬን እንዲሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን ተናግረዋል። ይህ የተናገሩት ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ክፍል በሰጡት ቃል ነው። ባለፈው ሳምንት አርብ ዕለት የተገደሉት ናሁሰናይ አንዳርጌ እና አቤኔዘር ጋሻው ከሞቱ አራተኛ…
#AddisAbaba
ከአንድ ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ሚሊኒያም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ኃይል ጋር በነበረው የተኩስ ልውውጥ ወቅት ሁለት " የፋኖ አባላት (አንድ አመራር እና አንድ አባል) " ፦
- ናሁሰናይ አንዳርጌ
- አቤነዘር ጋሻው መገደላቸው መነገሩ ይታወሳል።
ከዛ በኃላ እናቶቻቸው በሀዘን ውስጥ ሆነው አስክሬን ለመውሰድ እንዳልቻሉና እላይ ታች እያሉ እንደሆነ ግን ምንም መፍትሄ እንዳላሀኙ ተነግሮ ነበር።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ትላንት ምሽት ለቪኦኤ ቃላቸውን የሰጡ አንድ የቤተሰቡ አባል ፥ እስካሁን አስክሬን ለቤተሰብ እንዳልተጠ ተናግረዋል።
የናሁሰናይ አንዳርጌ እናት ወ/ሮ ሀረገወይን አዱኛ እና የአቤነዘር ጋሻው እናት ወ/ሮ ኤልሳ ሰለሞን የልጆቻቸውን አስክሬን ለመጠየቅ በየቦተው እየተንከራተቱ እንደሆነ ገልጸዋል።
" እንድህ ያለው ክስተት በዓለም ላይ ያልተከሰተ እስኪመስል ድረስ ነው ከሀዘን በላይ ስቃይ ሆኗል። በጥዋት ጉዳይ አስፈጻሚ መስለው ነው የሁለቱ እናቶች የሚሄዱት አዲስ አበባ ፖሊስ ይሄዳሉ ' እኛን አይመለከትም ፌዴራል ነው ' ይባላሉ ፌዴራል ይሄዳሉ ' እኛን አይመለከትም ' ይባላሉ ከዛ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ እዛ ጭራሽ የሚያናግራቸው የለም " ብለዋል።
" ማንም ሰብዓዊ ሰው ይሄን ይረዳል ብዬ አስባለሁ። ሰው ሞቶ አስክሬን የተከለከልን ብቸኛ ሰዎች እኛ ነን ብዬ ነው የማስበው አስክሬን ማየት እንኳን ተከልክለናል። " ሲሉ አክለዋል።
ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይሄ ጉዳይ የሚመለከተው የፀጥታ እና ደኅንነት ግብረ ኃይል ወይም የፌደራል ፖሊስን እንደሆነ መናገሩ ይታወሳል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ደግሞ ፥ " ይህ ጉዳይ የሚመለከተው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ነው " ማለቱ አይዘነጋም።
በሌላ በኩል ፥ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ አስክሬን ለመጠየቅ የሄዱ ሁለት የቤተሰብ አባላት (ዳዊት መንግሥቱ እና ዳዊት መኮንን የተባሉ) መታሰራቸውን እኚሁ የቤተሰብ አባል ገልጸዋል።
" መንግሥት ከሚለው አይነት ነገር ጋር ምንም ግንኝኑት የላቸውም በግል ስራ ነው የሚተዳደሩት አክሬን ለመጠየቅ ሲሄዱ ነው ቤታቸው እንዲፈተሽ ተደርጎ በቁጥጥር ስር የዋሉት " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው አስረድተዋል።

" 4 አባቶች ተገድለዋል " - ቤተክርስቲያኗ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም " እራሱን ' ኦነግ ሸኔ ' ብሎ የሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ 4 አባቶችን ገድሏል " ሲል አሳወቀ። ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ 3 አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ…
#ዝቋላ
በወራት በፊት የጥንታዊው እና በታሪካዊው ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አራት መነኮሳት በግፍ መገደላቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ግድያው በ " ሸኔ ታጣቂዎች " መፈፀሙን መግለጿም አይዘነጋም።
በወቅቱ አንድ የገዳሙ መነኩሴ ከሟቾቹ ጋር የነበሩ ዱካቸው መጥፋቱም ሲገለጽ እንደነበር ይታወሳል።
እኚሁ መነኩሴ ግድያውን ፈጽሟል ከተባለው ታጣቂ ቡድኑ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ተደርሶባቸው በእስር ቤት እንዳሉ ተሳምቷል።
ይህ የተሰማው ከቀናት በፊት በመንግስታዊ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በዝቋላ ገዳም በታጣቂዎች ስለሚደርሰው ግፍን በተመለከተ በተሰራጨ አንድ ፕሮግራም ላይ የገዳሙ አባቶች ሲናገሩ ነው።
በወቅቱ ምን ሆነ ?
የካቲት 12 /2016 ዓ/ም ከገዳሙ ከተወሰዱት እና በኃላም ለምምክር ተብለው ከተጠሩት 5 መነኮሳት አንድ መነኩሴ ሳይገደሉ በህይወት ተርፈው ወደ ገዳሙ ተመልሰዋል።
አባ ገ/ኢየሱስ ፀጋዬ ፦
" መጀመሪያውኑ መረጃውን የሚሰጥ ከኛ ውስጥ አደራጅተዋል። እነሱ ናቸው የኛን እያንዳንዱን መረጃ የሚሰጧቸው።
ይሄን እኛ አናውቅም በወቅቱ ፤ አሁንም ቢሆን ሀገር መከላከያ መጥቶ መረጃው እንዲህ እንዲህ ነው ብሎ ስልካቸውን ጠልፎ ያለውን መረጃ ከእንቅስቃሴያቸው አኳያ ነው ያወጣልን እንጂ ውስጡን አናውቅም።
እንደኛው ቆብ ያደርጋሉ፤ መናኝ ናቸው።
እነሱ ተርፈው የመጡት አባት የምንጠራጠራቸው መከላከያው በትክክል መረጃ አግኝቶባቸዋል።
እሳቸው ወደ ማታ መጡ ተባሉ ግን የሸኛቸው ሸኔ ነው እስከ ግማሽ መንገድ ከመጡ በኃላ በራቸውን ዘግተው በውጭ አስቆልፈው ተቀምጠዋል።
ማታ 2 ሰዓት ላይ ሀገር መከላከያ ሰራዊት መጡ እኚያን በአስቸኳይ መያዝ ስለነበረባቸው የት ነው ያሉት አሉ ? ሄደው ከቤታቸው ሲፈለጉ ጠፉ በውጭ ተቆልፏል ከዛ በሩ ይሰበር ተብሎ በሩን መከላከያዎቹ ሰብረው አገኟቸው በቁጥጥር ስር አዋሏቸው።
ከዛ መከላከያው እኛን የማረጋጋት ስራ ነው የሰራው። እርግጠኛ ሆኜ ምናገረው በወቅቱ ሀገር መከላከያ ባይመጣ አናድርም ነበር።
አሁንም በየጫካው ተሰማርተው ጥበቃ እያደረጉ ነው። "
አባ ተ/መድህን ገ/መስቀል ፦
" ገንዘባችንን ፣ መሳሪያዎቻችንን በመውሰድ ባላቸው ሲስተም ከውስጣችንም ሳይቀር ከነሱ ጋር የተዋሃደ ኃይል ያለውን ንብረታችንን ሁሉ እስከማጣት ደርሰናል። መከላከያ ኃይል በመረጃ ነው ሊያወጣቸው የቻለው። "
ገረመው ይርጋ (የሉበን ጩቃላ ወረዳ ሚሊሻ) ፦
" ይሄን ሁሉ ሲያደርጉ ብቻቸውን አይደለም። የራሳቸውን ሰው ከቤተክርስቲያን ውስጥ አሰማርተው ይህ ስራ ሲሰራ ነበር። ከህዝቡም ከነዋሪው አደራጅተው ያንን ስራ ይሰራ ነበር።
መጨረሻ ላይ እነዛ አባቶች ታግተው ሄደው አባቶችም መስእዋትነት ከፈሉ።
እነዛም ተመሳጥረው የነበሩት በጣም አደገኛ የተባለው ተይዟል። በቁጥጥር ስር የዋሉም አሉ። "
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ፤ " ድሮም የሚጎዳው የውስጥ አዋቂ ነው " ብለዋል።
" የቀረቡ መስለው ፣ አብረው የመነኑ መስለው ፣ አብረው ከገዳሙ ሰዎች ጋር በደባልነት በአስመሳይነት የሚኖሩ እንደነበሩ ጭላንጭሎች ነበሩ ይሄን ሁላችንም እናውቃለን " ሲሉ ገልጸዋል።
በዚሁ በቀረበው ፕሮግራም ላይ የገዳሙ አባቶች ፥ ታጣቂዎቹ ከውስጥ ባላቸው ሰዎች አማካኝነት እያንዳድኑ ንብረት የት እንደሚቀመጥ በማወቅ በተደጋጋሚ ጊዜ ዝርፊያ ሲፈጽሙ እንደከረሙ ተናግረዋል።
ይህንን ለፀጥታ ኃይል ካሳወቁ ቤተክርስቲያኗን ጭምር በቦምብ እንደሚያወድሙ ሲዝቱ እንደነበር ገልጸዋል።
#ዝቋላገዳም2016