TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢንተርን

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንተር ሀኪሞች ከስራ ሰዓትና ክፍያ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ኢንተርን ሀኪሞቹ ምን አሉ ?

“ ከጥቂት ዓመታት በፊት የሆስፒታሉ የኢንተርን ሀኪሞች የሥራ ሰዓት ወደ 24 ሰዓታት ዝቅ እንዲል ተደርጎ ነበር።

ነገር ግን የኮሌጁ ግለሰብ / #ዳይሬክተር ሲቀየር በራሱ ውሳኔ የራሱን መላምት በመፍጠር መልሶ ወደ 36 ሰዓታት ከፍ አድርጎታል።

ይህን ውሳኔ ተከትሎ የሥራ ሰዓት ከዚህ በፊት ሴኔቱ በወሰነው መሠረት ይሁንልን ብለን ጠየቅን። ይህንንም በመጠየቃችን የተበሳጨው የዲፓርትመንት አስተባባሪ ፦
• ከቀዶ ጥገና፣
• ከህፃናት፣
• ከማህፀንና የፅንስ ዲፓርትመንት ጋር መከረ። እነዚህ ዲፓርትመንቶች አስገድደውን ሥራ ጀመርን።

የሥራ ሰዓታችን እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ጠየቅን።

በዲፓርትመንት ደረጃ እየተሰበሰቡ ' ከዚህ በኋላ ይህን ጥያቄ የሚያየሳ ሀኪም እስከ ዲሲሚሳል ድረስ እንቀጣቸዋለን ' አሉ። ከዚህ በተጨማሪ የቀን ሥራ ሰዓታትን በአንድ ሰዓት ከፍ እንዲል ከነበረው ሕግ ውጪ ሆነብን።

ያንን ሁሉ ችለን ደመወዝ ይከፈለናል ብለን ብንጠብቅም ሳይከፈለን መጋቢት 14/2016 ዓ/ም 10ኛ ሳምንታት ጨርሰናል። ” የሚል ቅሬታ አቅርበዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቺፍ ኤክሴኩይቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር አይንሸት አዳነን ጠይቀናል።

ምን አሉ ?

ዶ/ር አይንሸት ፥ “ የሰዓት ጭማሪ ለሚለው እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት የተጨመረ ነገር የለም። ከድሮው የተቀየረ አሰራር የለም። እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት እነርሱን #ያስፈራራቸው_ሰው_የለም ” ብለዋል።

Q. ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢንተርን ሀኪሞች የሥራ ሰዓት ስንት ተብሎ ነው የተወሰነው ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

ዶ/ር አይንሸት አዳነ ፦

“ በክሬዲት ደረጃ ይህን ያህል የትርፍ  ፤ ይህን ያህል የመደበኛ ተብሎ የተቀመጠ ነገር የለም።

ለበርካታ አመታት ሲሰራበት ከነበረው መንገድ የተለየ እነርሱ ጋ የተጨመረ ነገር የለም። ”

Q. ዩኒቨርሲቲው 36 ሰዓታት የነበረውን የሥራ ሰዓት ወደ 24 ሰዓታት ዝቅ እንዳደረገ መረጃዎች ያሳያሉ ፣ ሀኪሞቹም ወደ 24 ሰዓት ዝቅ ተደርጎ የነበረ ወደ 36 ሰዓት ከፍ እንዳለባቸው ገልጸዋል ፣ እርስዎ ደግሞ የተወሰነ ሰዓት እንደሌለ እየገለጹ ነው ለዚህስ ያለዎት ማብራሪያ ምንድን ነው ? ስንል ጠይቀናል።

ዶ/ር አይንሸት አዳነ ፦

“ የሆነ ጊዜ ጫናው ስለበዛ በኢንተርን ሀኪሞች ጥያቄ ተነሳና ዲፓርትመንቶች ራሳቸው ከኢንተርን ሀኪሞች ጋር ውይይት አድርገው (የተወሰኑ ዲፓርትመንቶች እንዲያውም ሙሉ አይደለም) አምነውበት ወደ ተግባር ተገባ። አሳማኝ ስለሆነ የሥራ ጫናው።

ይሁን እንጂ ለተወሰነ ወራት ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ አድረው በሚወጡትና ተተኪ ሆነው በሚገቡት ኢንተርን ሀኪሞች መካከል የርክክብ ክፍተት መፈጠሩ የጤና አገልግሎት ላይ ተፅዕኖ ስላመጣ፣ የኢንተርን ሀኪሞች ተመርቀው ሲወጡ የተሟላ እውቀት እንዳይቀስሙ ያደርጋል በሚል ወደ ነበረበት ይመለስ ተብሎ ተመልሷል። ”

Q. ‘ደመወዝ አልተከፈለንም’ ሚለው የሀኪሞቹን ቅሬታስ?

ዶ/ር አይንሸት አዳነ ፦

“ ሀኪሞቹ አጠያየቃቸው ልክ አልነበረም።

ኦረንቴሽን እንዲሰጣቸው በደብዳቤ ጭምር ቢጠሩም መገኘት አልቻሉ።

‘ይህ ካልተደረገልን (ቅሬታው ምላሽ ካላገኘ) ሥራ አንገባም’ በማለታቸውና ሳምንቱን ሙሉ ከሥራና ት/ት ገበታ ባለመገኘታቸው የሕክምና ትምህርት ቤቱ ባሳለፈው ውሳኔ፣ የ3 ወራት ደመወዝ ነው የተቀጡት። ያለ ደመወዝ እንዲሰሩ ነው የህክምና ት/ቤቱ የወሰነው። ”

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IOM " እ.ኤ.አ ከ2014 እስከ 2023 ቢያንስ 63,285 ሰዎች ሞተዋል / የገቡበት አይታወቅም " - IOM እ.ኤ.አ. ከ2014 እስከ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 63,285 ሰዎች በዓለም ላይ ባሉ ስደተኞች በሚጓዙበት መስመር ህይወታቸውን አጥተዋል ወይም ጠፍተዋል። አብዛኞቹ ህይወታቸውን ያጡት ደግሞ በውሃ መስጠም ምክንያት ነው። እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ሪፖርት…
" 480 ስደተኞች #በሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ ተይዘዋል " - IOM

ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 480 ስደተኞች በሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ መያዛቸው ተነግሯል።

የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት/IOM ሰኞ'ለት ባወጣው መግለጫ 480 ስደተኞች በባህር ላይ ጠባቂዎች መያዛቸውን አስታውቋል።

ድርጅቱ "ከመጋቢት 24 እስከ 30,2024 ውስጥ 480 ስደተኞች ተይዘው ወደ ሊቢያ ተመልሰዋል " ነው ያለው።

ከተያዙት ስደተኞች ውስጥ 26 ሴቶች እንዲሁም 5 ህፃናት እንደሚገኙበትም ተነግሯል።

የስደተኞች 2 #አስክሬንም ተገኝቷል።

በዚህ ዓመት በጠቅላላ 3,791 ስደተኞች የተያዙ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 120ዎቹ #ሲሞቱ ፣ ሌሎች 250 የሚሆኑት #ጠፍተዋል መባሉን MDN ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

Via t.iss.one/+LM-bJ8NzZMcxMjA8

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Puntland #Somalia ፑንትላንድ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ይፋ አድርጋለች። ከፊል ራስ ገዝ የሆነችው #ፑንትላንድ በሞቃዲሾ ለሚገኘው ለሶማሊያ የፌደራል መንግሥት ከዚህ ቀደም ሰጥታው የነበረውም ዕውቅና አንስታለች። የፑንትላንድ መንግሥት ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዶ ፑንትላንድ የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ተቋማት ላይ የነበራትን መተማመን በማጣቷ ትሰጥ የነበረውን ዕውቅና…
#Somalia

° " ስለዚህ ጉዳይ መረጃው የለኝም " - አቶ ነብዩ ተድላ

ሶማሊያ ፥ በሶማሊያ #የኢትዮጵያን_አምባሳደር የሆኑትን ሙክታር ሞሃመድ ዋሬን ወደ ሀገራቸው #እንዲመለሱ ማድረጓን ሁለት ከፍተኛ የሶማሊያ ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ #ሮይተርስ ዘግቧል።

ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ያደረገችበት ምክንያት ከሶማሊላንድ ጋር የገባቸው የወደብ መግባቢያ ስምምነት እንደሆነ ተነግሯል።

ከዚህ ባለፈ ሶማሊያ በፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ያሉ የኢትዮጵያን ቆንስላ ጽህፈት ቤቶችን ዘግቻለሁ ብላለች።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በጉዳዩ ዙሪያ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው እንደነገሩት ሮይተርስ አስነብቧል።

የፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ነገር ?

ፑንትላንድ ከሕገ-መንግስት ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ከቀናት በፊት ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።

ከአሁን በኃላም ማንኛውም ፍላጎቷን ለማስጠበቅ ከማዕከላዊ የሶማሊያ መንግሥት እውቅና ውጪ በራሷ የውጭ ግንኙነትም እንደምታደርግ ገልጻለች።

ሶማሌላንድም ምንም እንኳን እስካሁን ሶማሊያ ' የራሴ ግዛት ነሽ ' ብትላትም ራሷን እንደ ነጻ ሀገር መቁጠር ከጀመረች አመታት አልፈዋል። የውጭ ግኝኑነቶችንም ታደርጋለች።

የሰሞኑን የፑንትላንድ ነገር ለሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት " በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ " ሆኖበታል።

ከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድ ሰሞኑን ፥ " ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ተቆራጠናል ፤ እውቅናም አልሰጥም " ካለች በኃላ ከፍተኛ ባለስልጣናቷ ኢትዮጵያ / አዲስ አበባ ለውይይት መግባታቸው መነጋገሪያ ሆኗል።

እዚህ አዲስ አበባ የመጣው በገንዘብ ሚኒስትሯ ሞሃመድ ፋራህ ሞሀመድ የተመራ ልዑክ ነው።

ልዑኩ ከኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ጋር መክሯል።

በዚህም ኢትዮጵያ ከፑንትላንድ ጋር ያላትን ዘርፍ ብዙ ትብብሮች ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗ ተገልጿል።

የፑንትላንድ ልዑክም ፥ ኢትዮጵያ በፑንትላንድ በጸጥታና በትምህርት ዘርፍ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን ገልጾ የፑንትላንድ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት የማሳደግ ፍላጎት እንዳለው አረጋግጧል።

በዚህ ወቅት የፑንትላንድ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ መምጣታቸው ግጥምጥሞች ወይስ ከወቅታዊ ሁኔታው ጋር የተያያዘ ነው ?

" ጉብኝቱ የቆየ ቀጠሮ ነው " - አቶ ነብዩ ተድላ

ዛሬ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፑንትላንድ በገንዘብ ሚንስትሯ መሀመድ ፋራህ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ አ/አ ጉብኝት ማድረጉን ገልጸዋል።

ይህ ጉብኝት ከሰሞነኛው የፑንትላንድ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር #የማይገናኝ እንደሆነ እና የጉብኝት ፕሮግራሙም የቆየ ቀጠሮ መሆኑን አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበት ጓደኛቸውን ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጪ የሆኑ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲያሰባስቡ የነበሩ 10 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው " አዲስ ሰፈር " አካባቢ መሆኑን አሳውቋል።

ግለሰቦቹ የሰሌዳ ቁጥር " ኮድ 3- B21705 አ.አ " የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪን በመጠቀም ገንዘቡን ሲሰበስቡ የቆዩት " የኩላሊት ታማሚ ነው " ያሉትን ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ በማስተኛት ነው።

በተያዙበት ወቅት ከ5 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እጃቸው ላይ መገኘቱን ፖሊስ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ የድጋፍ ጥያቄዎች ሲቀርቡ የሚስተዋል መሆኑን ገልጾ ነገር ግን ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት #የማታለል ተግባርም የሚፈፅሙ ሰዎች መኖራቸውን ተገንዝቦ ድጋፍ ሲያደርግ ከህክምናው ጋር የተያያዙ አግባብነት ያላቸውን #ሰነዶች በማየትና ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ሊሆን ይገባል ሲል አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somalia ° " ስለዚህ ጉዳይ መረጃው የለኝም " - አቶ ነብዩ ተድላ ሶማሊያ ፥ በሶማሊያ #የኢትዮጵያን_አምባሳደር የሆኑትን ሙክታር ሞሃመድ ዋሬን ወደ ሀገራቸው #እንዲመለሱ ማድረጓን ሁለት ከፍተኛ የሶማሊያ ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ #ሮይተርስ ዘግቧል። ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ያደረገችበት ምክንያት ከሶማሊላንድ ጋር የገባቸው የወደብ መግባቢያ ስምምነት እንደሆነ…
#Update

የሶማሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት #ለማቋረጥ በመወሰን በአገሪቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደር እና ዲፕሎማቶች ለቀው እንዲወጡ ማዘዟ ተሰምቷል።

አዲስ አበባ ያሉትን አምባሳደሯንም ጠርታለች።

የሶማሊያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስቴር ይፋ እዳደረገው በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሐመድ ዋሬ በ72 ሰዓታት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ አዛለች።

በተጨማሪም ከሶማሊያ ነጻ አገርነቷን ባወጀችው ሶማሊላንድ እና በከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድ ውስጥ የሚገኙት ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች በ7 ቀናት ውስጥ እንዲዘጉ መወሰኑን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

በተመሳሳይም ሶማሊያ በአዲስ አበባ የሚገኙትን አምባሳደሯን “ ለአጠቃላይ ምክክር ” ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸው ተገልጿል።

የሶማሊያ እርምጃ ኢትዮጵያ #ሶማሌለንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ማድረጓን ተከትሎ " በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገብታለች " በሚል ምክንያት ነው።

ሮይተርስ ከሰዓት በፊት የሶማሊያ ባለሥልጣናትን ዋቢ በማድረግ ባሰራጨው መረጃ የኢትዮጵያ አምባሳደር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል ብሎ የነበረ ሲሆን አሁን የሶማሊያ መንግሥት በይፋ አምባሳደሩ በ72 ሰዓታት ለቀው እንዲወጡ ማዘዙን አሳውቋል።

የሶማሊያን መንግሥትን ውሳኔን በተመለከተ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ በዚህ ጉዳይ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸው ነበር።

መረጃው የቢቢሲ እና ሮይተርስ ነው።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

መንግስት ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች/startups እንዲያብቡ በርካታ የፖሊሲ ለውጦችን ለማድረግ መወሰኑ ተሰማ።

ከነዚህም መካከል ፦
- ከስራ ፈቃድ፣
- ከግብር፣
- ከቢሮ ኪራይ፣
- ከፋይናንስ አቅርቦት፣
- ከጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ ወሳኝ ለውጥ የሚደረግባቸው ይሆናሉ ተብሏል።

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተገኙበት ዛሬ ይፋ የተደረጉ ለውጦች በተለይ ስራ ፈጣሪዎች ከውጭ ለሚኖራቸው ግዥ የቀጥታ ክፍያ መፈፀም እንዲችሉ እንዲሁም ያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ሙሉ ለሙሉ መጠቀም እንዲችሉ የሚፈቅድ መሆኑን " ካፒታል ጋዜጣ " አስነብቧል።

@tikvahethiopia
" በቦምብ ጥቃቱ 31 ተማሪዎች ተጎድተዋል " - ፖሊስ

ዛሬ በፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ዳሞት  መሰናዶ ቁጥር 1 ት/ቤት ላይ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት በ31 ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የፍኖተ ሰላም ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ገለጸ።

በት/ቤቱ በተፈፀመው የቦምብ ጥቃት 6 ተማሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ብሏል።

የቦምብ ጥቃቱ (ቦምቡ የተጣለው) ጥዋት 2፡30 ሰዓት ተማሪዎች በፈተና ላይ እንዳሉ መፈፀሙን የገለጸው ፖሊስ ፤ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው 6ቱ ተማሪዎች ለከፍተኛ ህክምና ሪፈር ተፅፎላቸዋል ህክምና ላይ ናቸው ብሏል።

15 ተማሪዎች ደግሞ በፍኖተ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል ህክምና እያገኙ ሲሆን 10 ተማሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው አመልክቷል።

አደጋውን ተከትሎ አንድ ተጠርጣሪ #ተማሪ መያዙን ፤ እጁና እግሩ ላይም መቁሰሉን ያሳወቀው ፖሊስ ሌሎች በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፎቶ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 6 ከባንኩ ገንዘብ " ያለአግባብ ወስደው አልመለሱልኝም " ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶ ማሰራጨት ቀጥሏል። ዛሬ ከ80 ሺ እስከ 70 ሺ ብር ወስደው ያልመለሱ ግለሰቦችን ፎቶግራፍ አሰራጭቷል። ባንኩ ባለፉት ቀናት ለ3 ዙር ያህል ፎቶግራፍ ማሰራጨቱ ይታወሳል። @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 6 / 2016 ዓ/ም ለሊት ችግር በገጠመው ጊዜ " የህዝብን ገንዘብ ያለአግባብ  ወስደው እስካሁን #አልመለሱልኝም " ያላቸው ግለሰቦች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ፎቷቸውን እያሰራጨ ይገኛል።

ከሚዲያዎች በተጨማሪ በየባንኩ ቅርንጫፎች እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋም በር ላይ ለህዝብ በሚታይ መልኩ " ገንዘቡን አልመለሱም " ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶግራፍ በትልልቅ ባነር በማሰራት ለጥፏል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ " ብር ተመላሽ አድርገን እስካሁን ፎቷችን በሚዲያዎች እንዲሰራጭ እየሆነ ነው " ያሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ባንኩ ገንዘብ የመለሱትንም በፎቶግራፍ ማውጣት እንዳለበት ገልጸዋል።

" የወሰድነውን ብር ተመላሽ አድርገን ሳለ ባንኩ ብር ካልመለሱት ጋር አደባልቆ ፎቶግራፋችንን ማሰራጨቱ ተገቢ አይደለም በመሆኑንም ህዝብ በሚያውቀው መንገድ መመለሳችንን ሊያሳውቅ ይገባል " ብለዋል።

@tikvahethiopia