TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Axum

በጭንቅላት የተጣበቁ መንትዮች ተወለዱ።

ሴት መንትዮቹ  (Conjoined twins) እንዲሁም እናቲቱ በመልካም የጤና ሁኔታ ይገኛሉ ተብሏል።

መጋቢት 22 /2016 ሌሊት በሪፈር የተላከች እናት በቆዶ ጥገና 5 ኪሎ የሚመዘኑ በጭንቅላት የተጣበቁ ሴት መንትዮች እንደተገላገለች የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ገልጿል። 

ወላጅ እናት ለአዋላጅ ሃኪም የሰጠችው መረጃ በመጥቀስ ባለሙያዎች እንዳሉት ፥ እናቲቱ የፅንስ ክትትል በአቅራቢያዋ በሚገኝ የጤና ማእከል ውስጥ ስታደርግ የቆየች ብትሆንም የአልትራሳውንድ ምርመራ ባለማድረግዋ በማህፀንዋ የነበሩት መንትዮች ሁኔታ ቀድማ ማወቅ አልቻለችም። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ  ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የመጨረሻ ተጨማሪ 3 ቀን ሰጥተናል " - ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 222 ግለሰቦች እስካሁን የወሰዱትን ገንዘብ መመልስ እንዳለጀመሩና እነዚህ ግለሰቦች ጋር ያለው ገንዘብ 4,034,979 ብር ከ75 ሳንቲም መሆኑን ገልጿል። ባንኩ አሁንም ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ የመጨረሻ የ3 ቀናት ስለመስጡትን አሳውቋል። ባንኩ ከዚህ ቀደም ሙሉ በሙሉና በከፊል ገንዘብ ያለመለሱ እንዲመልሱ 2 ጊዜ የመጨረሻ…
#ፎቶ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ108 ሺህ እስከ 305 ሺህ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ " እስካሁን አልመለሱልኝም " ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶግራፍ ይፋ አደረገ።

ወደዚህ እርምጃ ከመግባቱ በፊት በተደጋጋሚ ማስጠንቀቁን አስታውሷል።

በዚሁ መሠረት እስካሁን ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን የመጀመሪያ ዙር ፎቶግራፍ ይፋ ማድረጉን ገልጿል።

አሁንም ለመጨረሻ ጊዜ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም የተራዘመውን የገንዘብ መመላሽ ዕድል ተጠቅመው ገንዘብ ያልመለሱ እንዲመልሱ አስጠንቅቋል።

በተሰጠው የጊዜ ገደብ የማይመልሱትን ወደ ህግ እንደሚያቀርብም ገልጿል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ቴሌብርን ጨምሮ ከተለያዩ ባንኮች ገንዘብ ወደ አፖሎ ማስተላለፍና ማስቀመጥ ይችላሉ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628

#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#SOLElGarment

ልክ እንደ ክት ልብስ .....
የድርጅቶን ስምና የብራንድ ደረጃ የጠበቁ የሥራ ልብሶችን በተመጣጣኝ ዋጋና ጥራት በሶልኤል ጋርመንት ያገኛሉ።
▪️ለሆስፒታል እና ለተማሪዎች የሚሆኑ ዩኒፎርሞችን፤
▪️የፋብሪካ ቱታዎች እና የጥበቃ የደንብ ልብሶችን፤
▪️ለሆቴሎች እና ለመስተንግዶ የሚሆኑ ደረጃውን የጠበቁ የሥራ ልብሶችን ከእኛ ዘንድ ያገኛሉን።

በዘመናዊ ማሽኖቻችን የተለያዩ የኢምብሮይደሪ ወይም የክር ጥልፍ አግልግሎት እንሰጣለን። ከ200 በላይ ባለሙያዎቻችን ዝግጁ ናቸው።

👉 የተለያዩ የ ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞችን ለሚያሰሩ ኤጀንሲዎች የዱቤ አገልግሎት ማመቻቸታችንን ስንገልጽ በደስታ ነው።    

ይደውሉልን +251911236545  / +251992303030

በቴሌግራም ገጻችን ስራዎቻችንን ይመልከቱ ፦ https://t.iss.one/solelgarment

ይምጡ እና ይጎብኙን።
#ጊምቦ

" እንዲህ ያለዉን አረመኔ ህግ የሚለቀዉ ከሆነ መተማመኛችን ምንድን ነዉ ? " - የአካባቢዉ ነዋሪዎች

" ማስረጃ አሰባስቤ ለፍርድ ቤት ባቀርብም የቀረበዉ ማስረጃ በቂ ሆኖ  አለመገኘቱን ተከትሎ ከ3 ወራት እስር በኋላ ሊለቀቅ ችሏል " -  ፖሊስ

ከዛሬ 3 ወራት በፊት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ በተፈጠረ የእርሻ መሬትን የተመለከተ አለመግባባት አቶ ታሪኩ ኃይሌ የተባለ ግለሰብ የገዛ አባቱን በመጀመሪያ በዱላ በመምታት በኋላም ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በገጀራ ቆራርጦ በመግደል መጠርጠሩን ተከትሎ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ይውላል።

የጊምቦ ወረዳ ፓሊስ ምርመራ ሲደረግ ከቆየ በኃላ ግለሰቡ ከወራት እስር በኋላ ተለቋል። ይህ ጉዳይም በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ግርምትን እና ድንጋጤን የፈጠረ ሆኗል።

የግለሰቡን ከእስር መለቀቅ ያዩ የአካባቢዉ ነዋሪዎች በተለይም የምስክርነት ቃላቸዉን የሰጡ ግለሰቦች በሁኔታው መደናገጣቸውንና ከመግለጽ ባለፈ " ፖሊስ ምን እየሰራ ነው ? " ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።

" እንዲህ ያለዉ ነብሰገዳይ በዚህ ሁኔታ ከተለቀቀ በፖሊስና በህግ አካላት ያለን መተማመን ይቀንሳል " የሚሉት የአካባቢዉ  ነዋሪዎች ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርተዋል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ ጉዳዩን ሲከታተሉት መቆየታቸውን በማንሳት ግለሰቡ በማስረጃ እጥረት ፍ/ቤት #ሊለቀዉ መቻሉን አንስተዋል።

የማህበረሰቡ ጥያቄ ልክ ቢሆንም የፖሊስ ስራ ከቅድመ መከላከል ባለፈ ወንጀል ሲፈጸም ማስረጃ አጠናቅሮ ፍርድ ቤቱ ማቅረብ ላይ እንደሚገታ የሚገልጹት ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ " አሁን ላይ የሁኔታውን ውስብስብና አሳሳቢ መሆን ተከትሎ የክልሉ ፍትህ ቢሮ በጉዳዩ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ ፕሮሰስ ላይ መሆኑን ከክልል ቢሮ መረጃ ደርሶኛል። ለዚህም ስራ ፖሊስ አስፈላጊዉን ድጋፍ ያደርጋል " ሲሉ ጠቁመዋል።

የማህበረሰቡን ቅሬታ በተመለከተም ፥ " ህግ ማስረጃ ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚንቀሳቀስ መሆኑ የግድ በመሆኑ የህግ ሂደቱን በትእግስት መጠበቅ ይገባል " ብለዋል።

ፖሊስ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ጥረት ላይ መሆኑንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

መረጃው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አዲስአበባ #ነዳጅ የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ፥ በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ዕጥረት መከሰቱንና ምክንያቱ ደግሞ ጅቡቲ ላይ የዘነበ ከባድ ዝናብን ተከትሎ የመንገድ መቆራረጥ በመፈጠሩ መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪም አስቀድሞም ከቦታዉ በበቂ ሁኔታ ነዳጅ እየተጫነ ባለመሆኑ መሆኑን አመልክቷል። የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ደሳለኝ አበባየሁ ፥ እነዚህ ምክንያቶች ከነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች የተነገራቸዉ…
#ነዳጅ

" እስከ ነገ ጠዋት ድረስ ችግሩ ይቀረፋል " - የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ፥ በአዲስ አበባ የነዳጅ እጥረት የተፈጠረው ጅቡቲ ላይ የዘነበውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ድልድይ በመሰበሩ ነው ብሏል።

በተጨማሪም ነዳጅ የጫነ አንድ የነዳጅ ቦቴ ተገልብጦ መንገድ መዘጋጋት በማስከተሉ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ገልጿል።

ችግሩን ለመቅረፍ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በድሬደዋ በኩል እንዲገቡ መደረጉን የገለጸው ድርጅቱ ይሄንኑ ተከትሎ ትናንት ከሰአት ጀምሮ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች መግባት መጀመራቸውን አሳውቋል።

#ዛሬ እና #ነገ ነዳጅ የጫኑ ተጨማሪ ቦቴዎች እንደሚገቡና ችግሩ እስከ ነገ ጠዋት ድረስ እንደሚቀረፍ ለብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጠው ቃል ገልጿል።

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ነዳጅ ማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል። አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማግኘት እጅግ ረጅም ሰልፍ ለመጠበቅ እየተገደዱ ሲሆን በዚህ ምክንያት ስራቸውም እየተስተጓጎለ ነው።

@tikvahethiopia
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና ብልፅግና ፓርቲ በፕሪቶሪያ ውል መሰረት ፓለቲካዊ ውይይት ለመጀመር መስማማታቸው ተገለጸ።

ህወሓት በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፁ ባሰራጨው መረጃ ፥ በብልፅግና ምክትል ፕረዚደንት አቶ አደም ፋራህ የሚመራ ቡድን ዛሬ መጋቢት 24/2017 ዓ.ም በመቐለ ከህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር ተወያይቷል።

የሁለቱም ፓለቲካዊ ፓርቲዎች የፓለቲካ ውይይት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ቀደም ብሎ መጀመር እንደነበረበት በመተማመን በአጭር ጊዜ ውስጥ ውይይት እንዲጀምሩ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ህወሓት ገልጿል።

@tikvahethiopia
በቢዝነስ ኤክሴል ንግድዎን ያዘምኑ!

ሥራዎን የሚያቀሉ ቴምፕሌቶች እና ስለንግዱ ዓለም ወሳኝ መረጃዎችን ያገኛሉ።

በተጨማሪ ይህን መድረክ በመጠቀም በሳምንታዊ ጥያቄና መልስ ውድድር በመሳተፍ በየሳምንቱ 50,000 ብር ተሸላሚ መሆን ይችላሉ።

ለመመዝገብ ok ብለው ወደ 6424 ይላኩ

በቀን 2ብር ብቻ፤ ለ3 ቀናት በነፃ

ለተጨማሪ https://www.businessexcel.et ይጎብኙ

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
ወ/ሮ አያንቱ ሙስጠፋ ላይ የተፈፀመው ምንድነው ?

ወ/ሮ አያንቱ ሙስጠፋ ነዋሪነቷ በምስራቅ ሀረጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ ቀበሌ 02 ነው።

በ2008 ዓ/ም ነው ከባለቤቷ አቶ አሪፍ አልዬ ጋር በጋብቻ የተሳሰረችው።

ላለፉት 8 ዓመታት በትዳር ስትቆይ 2 ወንድ ልጆችን አፍርተዋል።

ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም ፍፁም ባልጠበቀችው ሁኔታ በገዛ ባለቤቷ እና የልጆቿ አባት ዘግናኝ በሆነ መንገድ በአሲድ ተቃጥላለች። አንድ አይኗንም አጥታለች።

ከባለቤቷ ጋር በተደጋጋሚ አለመግባባቶች ቢፈጠሩም ይህን ያደርግብኛል ብላ በፍፁም አልጠበቀችም።

ወ/ሮ አያንቱ ሙስጠፋ ፦

" በዕለቱ (ጥር 15  ቀን 2016) ቀን ስራ ውዬ ልጆቼን ከቤተሰቦቼ ጋር ይዤ ወደ ቤት ገባሁ።

ማታ ተሰብስበን እራታችንን በላን እጅግ ደክሞኝ ስለነበር ልጆቼን በግራ እና በቀኝ አስተኝቼ እኔም ተኛው።

በዛ ቀን ምን ክፉ ደግ አልተነገርንም። ከለሊቱ 9 ሰዓት ተኩል አካባቢ #አሲድ በማስታጠቢያ አድርጎ በተኛሁበት በጭንቅላቴ አፈሰሰብኝ።

ወይኔ ጭንቅላቴን ተቃጠልኩ ! ብዬ ከተኛሁበት ተነስቼ እጁን ልይዘው ስሞክር ' ገና መቼ ተቃጠልሽ ' ብሎ አሲዱን አይኔ ውስጥ ጨመረው።

ያኔ አንዱ አይኔን ለማትረፍ በእጄ ሸፍኜ በሩን ለመክፈት ስሞክር የተረፈውን አሲድ ጀርባዬ ላይ ረጨብኝ።

ለረጅም ጊዜ #በቅናት ምክንያት ያስቸግረኝ ነበር። ከዛሬ ነገ ይሻለዋል እያልኩኝ አብሬው ቆየሁ። በዚህ ውስጥ ነው 2 ልጆች የወለድነው።

በተደጋጋሚ ይዝትብኝ የነበረ ቢሆንም እንዲህ ይጨክናል ብዬ አላሰብኩም። "

እንደ ሀረማያ የሕይወት ፋና ሆስፒታል መረጃ ከሆነ በወ/ሮ አያንቱ ላይ የደረሰው ቃጠሎ 3ኛ ደረጃ የሚባለው ነው። የአሲድ ጥቃቱ በአይኗ፣ በጭንቅላቷ፣ ፊቷ ላይ ፣ ደረቷ ፊት ፣ እጇ ላይ ጉዳት ደርሷል።

የቀኝ አይኗ ላይ በአሲድ ቃጠሎው ምክንያት የብሌን ጉዳት ስላጋጠመ ማየት አትችልም። የግራውን ግን በህክምና ማትረፍ ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረጃው ባለቤት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ታደሰ) እውቅና ይሰጣል።

@tikvahethiopia