TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከእንግዲህ በሽፍትነት / rebel በመሆን መንግሥትን መጣል አይደለም ፤ መነቅነቅ አይቻልም " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ከእንግዲህ በኃላ በሽፍትነት / rebels በሚመስል ነገር መንግስትን መጣል አይደለም መነቅነቅ እንኳን አይቻልም " አሉ። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ይህን ያሉት በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ እና ታማኝ ግብር ከፋይ ባለሀብቶችን ሰብሰበው በመከሩበት ወቅት ነው።…
" በቅርቡ 5 ሚሊዮን ዶላር ከውጭ በአንድ ባንክ ተልኮ ይዘናል " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሁለት ቦታ (ከመንግስት ጋር እና ጫካ መንግስትን ለመጣል ከሚታገሉ ጋር) የሚጫወቱ አንዳንድ ባለሃብቶች አሉ ሲሉ ተናገሩ።

ይህን የተናገሩት ከታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር ምክክር ባደረጉበት ወቅት ነው።

ባለሃብቶቹ በምክክር መድረኩ ስለ #ሰላም ጉዳይ ያነሱ ሲሆን ጠ/ሚስትሩም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ፤ " ሰላም ተብሏል እውነት ነው አስፈላጊ ነው " ብለዋል።

" ድሮ ሀብታሞች አዝማሪ ቀጥረው ያጫውቱ ፣ ይገጠምላቸው ነበር ድሃው እራት እየበላ በግጥም ይተባበራል ፤ አሁን ድገሞ ሀብታሞች #ዩትዩበር ይቀጥራሉ ድሃው በላይክ እና ሼር ይተባበራቸዋል እነዚህ ሰዎች እንደፈለጉ ሲያተረማምሱ ይውላሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

" ዩትዩበሮቹን ባንቀልብ ወደ ስራ ወደ ኢንድስትሪ ይገቡ ነበር ፤ ለዚህ አስተዋጽኦአችን ምንድነው ብሎ ስራ ፈጣሪው ባለሃብቱ ግብር ከፋዩ ቢያስብ ጥሩ ነው " ብለዋል።

" እኛ እና እናተ ከተባበርን ሙስና ይቀንሳል፣ አገልግሎት ሊሻሻል ይችላል " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ " ጫካ ላሉ ሰዎች ብር ባለመላክ ብትተባበሩም እንዲሁ ይቀንሳል " ሲሉ ተናግረዋል።

" አንዳንድ በተለያየ ቦታ ሚታገሉን ሰዎች እስከ 10 ቤት በአባቱ፣ በወንድሙ  ያለው ሰው አለ፤ በረሃ ታጋይ አታጋይ የሚባል ሰው። በጣም ሃብታሞች ናቸው እዛ ተቀምጠው መነገድ የሚቻል ከሆነ ሰላም ጋር ምን አመጣቸው ሰላም ከመጣ ንግድ የለም ማለት ነው " ብለዋል።

" ቤት አላቸው፣ በተለያየ አካውንት ባንክ ውስጥ ገንዘብ አላቸው በቅርቡ እንኳን 5 ሚሊዮን ዶላር ከውጭ መጥቶ ይዘናል በአንድ #ባንክ ፣ ከፍተኛ ብር ይንቀሳቀሳል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሃብታሞች ማወቅ ፣ መብለጥ ፣ መላቅ ስለሚመስላቸው እዚህም ይጫወታሉ እዚያም ይጫወታሉ፤ እዚህ እኛን ' የተከበራችሁ ' ይላሉ እዛ ሄደው ' እንደናተ ጀግና የለም ' ይላሉ በዚህ ሰዎቹ እየተታለሉ እንደ ስራ መስክ ይዘውት ሀገር ያምሳሉ ወጣቶች ያልቃሉ ... ችግር አለ " ብለዋል።

" እናተም ልክ የድሃ ቤት እንደምትገነቡት ሁሉ በዚህም በኩል ችግሮች እንዲፈቱ ከልባችሁ ብታግዙ ያለው ነገር ይቀንሳል " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ምንም እንኳን ስም ባይጠቅሱም ከሀገር የወጡ ባለሃብቶች እንዳሉ ገልጸዋል።

" የሆኑ የሆኑ ሰዎች ጠፍተው ይሄዳሉ ከዚህ። ከቆየ በኃላ ስንሰማ ለምንድነው የጠፋው ሚስተር X ጥሩት ወደሀገሩ ይመለስ ሲባል ሚስተር X አይፈልግም ያደረጋቸው ትራዛክሽኖች ሁሉ ይታወቃሉ ብሎ ስለሚያስብ አይፈልግም " ብለዋል።

" እኛ እንደ መንግስት አንድም ባለሃብት ከሆነ ክልል ጋር ግጭት ስላለ ከሀገር ውጣ ያልነው የለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ከመጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ/ም በፊት የባንክ ፈቃድ የተሰጠባቸው ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቀደ። ተሽከርካሪዎቹ እና እቃዎች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ የተፈቀደው በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል የሚቀርቡ ሠነዶች አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎባቸው ነው ተብሏል። ይህም የሚሆነው ለመጨረሻ ጊዜ  መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሸን ከፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል። የውጪ ምንዛሬ…
#Update

በጂቡቲ ወደብ ላይ የቆይታ ጊዜያቸው ያለፈ ተሸከርካሪዎች በባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ተጓጉዘው ወደ አገር ከገቡ በኋላ ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ እንዲቆዩ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ሚኒስቴሩ ፦
➡️ ለባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት
➡️ ለጉምሩክ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ፣ የተሽከርካሪዎቹ አስመጪዎች በሚያቀርቡት መረጃ መሠረት፣ በየወቅቱ በጂቡቲ ወደብ የተከማቹ ተሽከርካሪዎችን መጠንና የቆይታ ጊዜ ከጂቡቲ ወደብ ባለሥልጣንና ከጉሙሩክ ኮሚሽን እንዲሰበሰብ አዟል፡፡

የባህር ትራንስፖርት የሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የወደብ ፎርማሊቲ አሟልቶ ተገቢ ክፍያ በመፈጸምና በድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ማከማቻ ሥፍራ በማዘጋጀት ተለዋጭ ውሳኔ እስኪሰጥ በራሱ ኃላፊነት እና በራሱ ወጪ ተሽከርካሪዎቹን እንዲያቆይ ተወስኗል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በበኩሉ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በሚሰጠው የደብዳቤ ዋስትና፣ ተሽከርካሪዎቹ ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልባቸው እንዲጓጓዙ የትራንዚት ፈቃድ እንዲሰጥ የገንዘብ ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡ 

የገቢዎች ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ፣ በጂቡቲ ወደብ ተከማችተው የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ እንዲጓጓዙ መወሰኑን አስታውቆ፣ በውሳኔው መሠረትም አስመጪዎች ንብረቶቻቸውን ወደ ደረቅ ወደብ እንዲያስገቡ አሳስቧል፡፡

ነዳጅ ለማስመጣት የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ ጫና ለመቀነስ በሚል በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር እንዳይገቡ ውሳኔ መተላለፉን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር በስፋት እንዲገቡ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መደረጉን መግለጹ አይዘነጋም፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ከባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ምንጭ አገኘሁት ባለው መረጃ፣ አሁን ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ የተባሉት የነዳጅ ተሽከርካሪዎች ከዕግዱ በፊት የተገዙ ናቸው።

በውጭ ምንዛሪና በፍራንኮ ቫሉታ ምክንያት በጂቡቲ ወደብ እንዲቆዩ የተደረጉ መሆናቸውን፣ ውሳኔው የተላለፈው ለተሽከርካሪዎቹ የሚከፈለው የወደብ ኪራይ እየጨመረ በመምጣቱ መሆኑ ተመላክቷል።

ተሸከርካሪዎቹ ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ እንዲገቡ ከተደረገ በኋላ፣ ሰነድ ያላቸው የተሽከርካሪ አስመጭዎች ድርጅቱ ያወጣውን የታክስና የመጓጓዣ ወጪ በመክፈል መረከብ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

ስማቸውን እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የተሽከርካሪ አስመጪ " የአንድ ዓመት የወደብ ኪራይና የመጓጓዣ ወጪዎችን በመክፈል ተሽከርካሪዎቹን ቢረከቡ ገበያ ውስጥ ዋጋቸው ስለሚንር ሥጋት ገብቶናል " ብለዋል፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ምዕመናን #ክርስቲያናዊ_አለባበስ ለብሳችሁ እንድትገኙ እና የአቅማችሁን ያህል እድትለግሱ ጥሪ እናቀርባለን " - ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን  እናድርግ " በሚል መሪ ቃል ነገ እሁድ ከቀኑ 7:00 ላይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል። ገቢ ማሰባሰቢያው…
#Update

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን  እናድርግ " በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

ገቢ ማሰባሰቢያው በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን ፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶችን ለመደገፍ የሚውል እንደሆነ ተገልጿል።

በመርሃግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት  የማኅበሩ ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም ፤ " የመርሃ ግብሩ ዋነኛ ዓላማ ባለን አቅም ሁሉ ለወገን መድረስ ነው " ብለዋል።

" ረሃብ ጊዜ አይሰጥም " ያሉት የማህበሩ ሰብሳቢ " በውጭ ድርጅቶች ፣ በመንግስትና በሌሎችም የተለያዩ አካላት ብዙ እርዳታዎች ይደረጋሉ (የምግብም የአይነትም) በተለይ ግን ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ብዙ ጊዜ ትኩረት አያገኙም " ብለዋል።

" እነዚህን ክፍተቶች እና ጉድለቶች መሙላት አለብን " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" አሁን ላይ በየቦታው ያሉት መፈናቀሎች ፣ በየቦታው ያሉ የረሃብ ችግሮችን በማሰብ ማህበረ ቅዱሳን ሌሎች አገልግሎቶችን ገቶ መጀመሪያ ነፍስን የማዳን፤ ህይወትን የመታደግ ስራ ይቀድማል ብሎ እየሰራ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሁሉን ማድረግ የምንችለው ስንኖር ነው " ያሉት ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ " እኛ በልተን እያደርን ሌሎች ወገኖቻችን በረሃብ እና ጥማት መሞት ስለሌለባቸው ' ኑ ቸርነትን እናድርግ ! ' በሚል በዚህ በታላቁ ዐብይ ጾም ወቅት ዝግጅቱ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

ዛሬ ሚሊኒየም አዳራሽ መገኘት ያልቻሉ ምዕመናን በየቤታቸው ሆነው በማህበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም የሂሳብ ቁጥሮች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000309803648 ፣ አሃዱ ባንክ 0025393810901 ፣ ወጋገን ባንክ 0837331610101 ፣ አቢሲንያ ባንክ 37235458 ፣ አዋሽ ባንክ 01329817420400 ድጋፍ ማድረግ ይቻላሉ ተብሏል።

ፎቶ ፦ ከማኅበረ ቅዱሳ ቴሌቪዥን

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የተለያዩ ምርጥ የልጆች ቻናሎችን እና ሌሎች መዝናኛዎችን ከ290 ብር ጀምሮ በዲኤሲቲቪ

የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,199 ብር ከ1 ወር ነፃ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የዲኤስቲቪ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በቅርቡ 5 ሚሊዮን ዶላር ከውጭ በአንድ ባንክ ተልኮ ይዘናል " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሁለት ቦታ (ከመንግስት ጋር እና ጫካ መንግስትን ለመጣል ከሚታገሉ ጋር) የሚጫወቱ አንዳንድ ባለሃብቶች አሉ ሲሉ ተናገሩ። ይህን የተናገሩት ከታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር ምክክር ባደረጉበት ወቅት ነው። ባለሃብቶቹ በምክክር መድረኩ ስለ #ሰላም ጉዳይ ያነሱ ሲሆን ጠ/ሚስትሩም…
" እኛ አንቆይም በ5 እና 6 ወር እንጨርሳለን " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከታማኝ ከፍተኛ  የግብር ከፋዮች / ባለሃብቶች ጋር በነበራቸው ምክክር ወቅት ከሰሞኑን በአዲስ አበባ እየታየ ስላለው ፈረሳ አንስተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

" ብዙ ቦታ እየፈረሰ ነው " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ " ለምንድነው? የምትሉ ከሆነ የወደፊት የኢትዮጵያም፣ የአፍሪካም፣ የዓለምም የኢኮኖሚ አቅጣጫ 70 እና 80 ፐርሰንት አይቲ እና ቱሪዝም ነው። ሃብት ያለውም እዛ ነው ቱሪዝም እና አይቲ ደግሞ ኤርጎኖሚክስ በጣም ትልቅ ተፅእኖ ያደርግባቸዋል። የተስተካከለ አካባቢ ካልሆነ ይረበሻሉ " ብለዋል።

አዲስ አበባን መቀየር ካልተቻለ የሚታሰበውን ያህል የውጭ ሀብት ማምጣት አይቻልም ሲሉ ተናግረዋል።

" ዱባይ እንዴት ገንዘብ እንደሄደ ታውቃላችሁ፤ መሰረተ ልማቶች የሚታዩ ነገሮች በጣም በከፍተኛ ደረጃ ሃብት ይስባሉ " ብለዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ" አሁን የሚፈርሰው እንደሚባለው አይደለም። እኛ ብዙ አንቆይም ቢገፋ 5 እና 6 ወር ነው እንጨርሳለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" የቦሌው መንገድ እኛ የምናስበው ብዙ ሀገር ሲኬድ እንዳሉት ዎክ ማድረጊያ ያለው መንገድ እንዲሆን ነው " ያሉ ሲሆን የመንገዱ መስፋት አብዛኛው ሰው እግረኛ ስለሆነ እንደሚጠቅም ገልጸዋል። መንገዱ የባይክ ሩትም እንዲጨመርበትና #ሰፊ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ከቦሌው መንገድ በተጨማሪ የሚክሲኮ መንገድ፣ የመገናኛ ጫካ ሲኤምሲ መንገድ ዋና ዋናዎቹ  እንደሆኑም ጠቁመዋል።

" አዲስ አበባ ላይ ትልቁ ድህነትና ችግር ያለው መሃከል ላይ ነው፤ መርካቶ፣ ፒያሳ፣ ሜክሲኮ የሚባለው ነው። ሲኤምሲ፣ ለቡ እንደዛ አይደለም ዋናው ችግር ያለው መሀከል ነው ዋናውን ችግር ደፍረን ካፈረስነው በ5 ዓመት ከተማው ምን እንደሚመስል ታዩታላችሁ " ብለዋል።

" በዚህ ሂደት፦
-በግለሰብ ደረጃ አጥሬ ተነካብኝ ብለው የሚያዝኑ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ
-ባለስልጣናትም ያስቸግሩናል አጥር ሲነካባቸው የሚፈርስባቸው ብዙ ስለሆነ፣ የመንግስት ቤቶች ስለሚፈርሱ
-የመንግስት ኪራይ ቤቶች የሚያከራየውም ይጮሃል
-የቀበሌ ቤት የሚያከራየውን ይጮሃል... ብዙ ነው ጩኸት ያለው። ጨክነን ካላፈረስን ግን ሀገር አይሰራም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የአዲስ አበባን ለውጥ በአንድ አመት እናየዋለን፤ ያኔ ቱሪስት በደንብ ይመጣል። ያኔ የባላሃብቶች ንብረት ትልቅ ዋጋ ይኖረዋል " ብለዋል።

እየተካሄደ ያለውን ስራ ባለሃብቶቹ እንኳን በትዕግስት እንዲጠብቁ የጠየቁት ዶ/ር ዐቢይ " ከማማት ውጡ፣ አፈረሱት ምናም የሚለውን ትታችሁ በትዕግስት ጠብቁን በአንድ ውስጥ ከተማውን ካለበት ደረጃ ከፍ እናደርገዋለን የዛኔ ልጆቻችሁን ዱባይ ከምትወስዱ ታቆያላችሁ እዚህ " ብለዋል።

በሌላ በኩል፤ ጠ/ሚኒስትሩ እየፈረሱ ባሉ ቦታዎች ፋይበር እንደሚቀበር እና ውጭ ላይ የሚታዩት ሽቦዎች እንደሚቀበሩ ተናግረዋል።

" ቦሌ ላይ ይሁን ፒያሳ መንገድ የምናፈርሰው አሮጌ ቤት ብቻ አይደለም። እዛው ላይ ፋበር እንዘረጋለን፣ እዛው ላይ በየቦታው ያለውን ሽቦ እንቀብራለን፣ የውሃ መስመር እንዘረጋለን ዩቲሊቲስ በቢሊዮን እያወጡ ነው ያሉት " ብለዋል።

" አዲስ አበባ ውስጥ ከ4 ኪሎ አንስቶ እስከ ሜክሲኮ ቢነዳ ብርሃን አለ ጨለማ አለ፤ ብርሃን አለ ጨለማ አለ መብራት ዘላቂ ሆኖ አይታይም፥ ይህ መሰረተ ልማቱን ካልቀየርነው በስተቀር ሽቦው የተቀጣጠለ ስለሆነ ኃይል እና ዳታ (ኢንተርኔት) አክሰስ ማድረግ አይቻልም " ሲሉ አስረድተዋል።

አሁን እየፈረሰና እየተሰራ ያለው ስራ የሚቋረጠውን ኃይል እንዲሁም የኢንተርኔት ዳታ ችግርን ለመፍታትም ጭምር እንደሆነ ተናግረዋል።

" ካልፈረሰ ሌላ አማራጭ የለም " ብለዋል።

@tikvahethiopia
ዛሬ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ጠንከር ያለ ዝናብ ዘንቦ ነበር።

በተለይ በዳውሮ ዞን በ " ቶጫ ወረዳ " በተለያዩ ቀበሌዎች ላይ ከቀኑ 7:30 እስከ 8:10 ድረስ በረዶና ንፋስ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰብልና በንብረት ላይ መጠነኛ ጉዳት ማድረሱ ተሰምያል።

ወቅቱን ካልጠበቀ ከፍተኛ ዝናብ ጋር ተያይዞ ሊከሰት ከሚችለው አደጋ የወረዳው ህዝብ እራሱንና ወገኑን እንዲከላከል ጥሪ ቀርቧል።

ዝናቡ ቀጣይነት ልኖረው ስለሚችል ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ ተብሏል።

በሌላ በኩል፤ ላለፉት ሳምንታት ከፍ ያለ ሙቀት ስታስተናግድ የነበረችው የሀገራችን መዲና አዲስ አበባ ዛሬ ጠንከር ያለ ዝናብ አግኝታለች።

@tikvahethiopia