TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ➡️ " የቀብር ስርዓቱ ተፈጽሟል " - የዶክተር በሀይሉ ቤተሰብ  ➡️ " ይቅርታ መረጃው የለኝም " - የአዲስ አበባ ፓሊስ እውቁና እጅግ የተዋጣላቸው የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶ/ር በኃይሉ ኃይሉ መገደላቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ዶ/ር በኃይሉ ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ለጥዋት ሩጫ በሚል በወጡበት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ነው የተገለጸው። ለቲክቫህ…
#AddisAbaba

በኢትዮጵያ እውቁ እና የተዋጣላቸው የቀዶ ጥገና ሃኪም ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ ባለፈው ሳምንት እሁድ መጋቢት 8 ሊነጋጋ ሲል ስፖርት ለመስራት ከቤት ወጥተው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጉዳዩን በተመለከተ ዛሬ ባሰራጨው መረጃው የሟች ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ አስከሬን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከቦሌ ሚካኤል ወደ ሳሪስ አቦ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኝ ቀጠና 3 በተለምዶ " ማሞ ድልድይ " ስር ወድቆ መገኘቱን ገልጿል።

በወቅቱ አስከሬኑ ተነስቶ የአሟሟታቸውን ምክንያት ለማወቅ ለአስክሬን ምርመራ  ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል እዲሄድ ተደርጓልም ብሏል።

ፖሊስ ፤ ከሆስፒታሉ የተገኘው የአስክሬን ምርመራ ውጤት ከከፍታ ቦታ በመውደቅ በአካላቸው ላይ በተከሰተ ጉዳት ህይወታቸው ማለፉን ይገልጻል ብሏል።

" ሟች ዶ/ር በይሉ ሐይሉ ከከፍታው ላይ ቁልቁል ወደ ገደሉ በመውረድ አካላቸው ድንጋይ ላይ ስላረፈ በጭንቅላታቸው፤ በእግራቸው በጀርባ አጥንታቸውና በውስጥ የሰውነታቸው አካላት ላይ በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ከሆስፒታሉ የተገኘው የአስክሬን የምርመራ ውጤቱ ያብራራል " ሲል ገልጿል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ስራ መቀጠሉን ከከፍታው የወደቁበትን ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ የምርመራ ውጤቶች ሲጠቃለሉ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አመልክቷል።

ከቀናት በፊት ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የዶክተር በሀይሉ ሀይሉ ቤተሰቦች ፤ ጥዋት ለሩጫ በወጡበት በአሰቃቂ ሁኔታ ሞተው መገኘታቸውን ተናግረው እንደነበር ይታወሳል።

አንድ የሟች ቅርብ ቤተሰብ፣ " ቤተሰብ ጠቅላላ ' ወጥቶ ሞተ ' ነው የምናውቀው። ሚዲያ ላይ ካለው ውጪ አዲስ የሰማነው ነገር የለም " ብለው ነበር።

ዶክተር በሀይሉ ቤታቸው ቦሌ ሚካኤል እንደነበር የገለጹት እኚሁ የቅርብ ቤተሰብ " ሞተ ያሉት ወደ ሳሪስ በሚወስደው ድልድይ ጠዋት ወክ ሲያደርግ ነው። ዞሮ ዞሮ አስከሬኑን ፓሊስ ነው ያነሳው " የሚል ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተው ነበር።

@tikvahethiopia
" ከእገታ ለማስለቀቅ 300 ሺህ ብር ክፈሉ ተብለን ብንከፍልም ልጃችን አልተለቀቀም፣ ያለበትንም ሁኔታ አናውቅም ፤ የድርጊቱ አቀናባሪ ሀገር ለቆ ሊወጣ እንደሆነ ሰምተናል " - አባት

ከወራት በፊት ማለትም ነሀሴ 27 ቀን 2015 ዓ/ም በታጣቂዎች የታገተ ልጃቸዉን ለማስለቀቅ 300 ሺህ ብር በሰው በሰዉ የከፈሉት ቤተሰቦች ትእዛዙን ቢፈጹሙም ታጋቹ ግን ዛሬም ሊለቀቅ አልቻለም ብለዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪነታቸው በሀዋሳ የሆነው አቶ ፍቅሬ አበራ የተባሉ አባት ፤ በወቅቱ በመተሀራ ከተማ የሆቴል ማናጀር የነበረዉ ልጃቸዉ አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ በሆቴሉ ይሰራ የነበረዉን ልጅ ስህተት መስራቱን ተከትሎ የገንዘብ  ቅጣት መቅጣቱን ተከትሎ ልጃቸው መተሀራ ከሚገኘዉ የስራ ቦታዉ ውስጥ ካለ ማረፊያ እንዲታፈን መድረጉን አመልክተዋል።

ከዛም 300 ሺህ ብር ለማስለቀቂያ እንዲከፍል መደረጉን ገልጸዋል።

አባት ፤ " በግል የስራ ጸብ ምክኒያት ባልደረባውን ለኦነግ ሸኔ አሳልፎ የሰጠዉ ግለሰብ ብሩን ብንልክም ልጃችን እንዳይወጣ አድርጎ ' ሰራሁለት ' ሲል መደመጡን " የሚገልጹት አባት ለዚህ ደግሞ ተጨባጭ ማስረጃ በእጄ ላይ አለ ብለዋል።

ነገር ግን አቤቱታቸውን ሰምቶ መረጃቸውንም መርምሮ ወንጀለኛዉን አካል የሚይዝላቸው የህግ አካል እንዳጡ ተናግረዋል።

" አሁን ላይ ልጄን ለታጣቂዎች አሳልፎ የሰጠው ግለሰብ ከሀገር ለመዉጣት ፕሮሰስ ላይ እንደሆነ ሰምተናል " ያሉት አባት " የሚመለከተዉ አካል እጄ ላይ ያለዉን መረጃ ተጠቅሞ ፍትህ ያወርድልኝ ዘንድ እጠይቃለሁ " ሲሉ ተማጽነዋል።

አሁን ላይ ጉዳዩን ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋናው ቢሮ ለማሳወቅ እንደተዘጋጁ ገልጸው የልጃቸውን አሁናዊ ሁኔታ ካለማወቃችን በላይ " ለዚህ ሁሉ ሀዘን የዳረገን አካል አለመያዙም አሳምሞናል  " ብለዋል።

መረጃው የተዘጋጀው በሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

ትላንት ታጣቂዎች በሩስያ ፣ #ሞስኮ በሚገኘው የክሮከስ አዳራሽ የሙዚቃ ዝግጅት ለመታደም በተሰበሰቡ በርካታ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ የተገደሉ ሰዎች 115 የደረሱ ሲሆን 100 ሰዎች መቁሰላቸውን የሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል።

ከተገደሉት ውስጥ ህፃናትም እንደሚገኙበት ተነግሯል።

4 ታጣቂዎችን ጨምሮ 11 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሩስያ ባለስልጣናት አሳውቀዋል።

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተፈፀመውን ድርጊት " #የሽብር_ጥቃት_ነው " ሲል ጠርቶ አውግዟል።

ለጥቃቱ #IS ኃላፊነቱን መውሰዱን በበይነ መረብ የወጣ አንድ ያልተረጋገጠ መግለጫ አመልክቷል።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት ፤ IS ሩሲያን ለማጥቃት እንደሚፈልግ የሚያሳይ መረጃ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

አሜሪካ በሞስኮ ከተማ " ሕዝብ በሚበዛባቸው ስፍራዎች " ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ሩሲያን አስጠንቅቃ ነበር።

ከ2 ሳምንታት በፊት በሩሲያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ በርካታ ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ሕዝባዊ ስፍራዎች እንዳይሄዱ ማስጠንቀቂያ አስተላልፎ ነበር።

በማስጠንቀቂያው ላይ " ጽንፈኞች በሞስኮ ሕዝብ በሚሰባሰቡባቸው ስፍራዎችን (የሙዚቃ ኮንሰርትን ጨምሮ) የጥቃት ዒላማ ለማድረግ ዕቅድ አላቸው " የሚል ሪፖርትን እየተከታተልኩ ነው ሲል ገልጾ ነበር።

ኤምባሲው ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ ወደደረሰበት ስፍራ ዜጎቹ ዝር እንዳይሉ ምክር ማስተላለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኑ ቸርነትን እናድርግ " በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን  እናድርግ " በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር መጋቢት 15 ቀን ከቀኑ 7:00 ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ማዘጋጀቱን ገልጿል። ማህበሩ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን አመልክቷል። ገቢ…
#Update

" ምዕመናን #ክርስቲያናዊ_አለባበስ ለብሳችሁ እንድትገኙ እና የአቅማችሁን ያህል እድትለግሱ ጥሪ እናቀርባለን " - ማህበረ ቅዱሳን

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን  እናድርግ " በሚል መሪ ቃል ነገ እሁድ ከቀኑ 7:00 ላይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል።

ገቢ ማሰባሰቢያው በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶችን ለመደገፍ የሚውል እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የመግቢያ ትኬቶች በ100 ብር እየተሸጡ ሲሆን ትኬቶቹን ፦
1. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም)
2. በወረዳ ማዕከላት ጽ/ቤቶች  
3. በማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆች
4. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያዎች
5. በአሐዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
6. በሰ/ት/ቤት ጽ/ቤቶች ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

ነገ በመግቢያ በር ላይም ትኬት ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች / ምዕመናን ነገ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ሲሄዱ ክርስቲያናዊ አለባበስ እንዲለብሱ እና የአቅማቸውን ያህል እንዲለግሱ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
# M-PESA

መክፈል፣ መገበያየት መቼም እንዲህ ቀሎ አያውቅም!
በፍሬሽ ኮርነር ያሻችንን ገዝተን በM-PESA ክፍያ በመፈፀም ወደ ሌላው የቀኑ ጉዳያችን መሄድ ነዉ!

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
" ስለ ትውልዱ ግድ ይለናል የምትሉ ኃላፊዎች መፍትሄ ስጡን " - ተማሪዎቹ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፤ " መፍትሄ የሚሰጠን አጥተን ያለ ትምህርት ቤታችን ቁጭ ብለናል ፤ ጊዜያችንም እየተቃጠለ ነው " ሲሉ አማረዋል። የባህር ዳር ዩንቨርሲቲ የ2016 ዓ/ም የ1ኛ ዓመት እና የሬሚድያል ተማሪዎች ወደ ግቢ እንዲገቡ ጥሪ ተደርጎላቸው በኃላም መራዘሙ ይታወሳል። ነገር ግን እስካሁን ምንም አይነት ጥሪ…
#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ለተከታተሉ ተማሪዎች ጥሪ አደረገ።

በዚህም በ2016 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ Freshman ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስትከታትለው ቆይተው የማለፊያ ውጤት በማምጣት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደበ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ከመጋቢት 26 እስከ 28/2016 ዓ.ም መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታውም ፦
➤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሰላም ግቢ
➤ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በግሽ አባይ ግቢ ነው ተብሏል።

በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን አቋርጠው ለአንደኛ ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላቸውና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞሉ ተማሪዎች ምዝገባ መጋቢት 30/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ያወጣው ጥሪ በማካካሻ መርሐ ግብር (Remedial Program) በ2016 ዓ/ም አዲስ የተመደቤ ተማሪዎችን #አይመለከትም ተብሏል።

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
" የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ለቅቄያለሁ " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በስሩ የነበሩ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን በምህረት መልቃቁ አስታወቀ። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ዛሬ አመሻሽ ባሰራጨው መግለጫ ፤ " በያዝነው ወር የአፍሪካ ህብረት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የደረሰበት ደረጃ ለመገምገም በአዲስ አበባ መቀመጡ ተከትሎ በተደረሰው ስምምነትና በተቀመጠው የትኩረት…
#Update

በትግራይ በእስር ላይ የነበሩ ተጨማሪ 100 የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እንደተለቀቁ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ዛሬ መጋቢት 14/2016 ዓ.ም በኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት በኩል ፥ " በምርኮ የቆዩት 100 ተጨማሪ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት በምህረት ተለቀዋል " ብሏል።

ትናንት የተለቀቁት 112 ጨምሮ በሁለት ቀን የተለቀቁት የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ቁጥር 212 ደርሷል።

አሁንም ትግራይ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙ ተጨማሪ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እንዳሉ ይነገራል።
                                             
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከባንኩ ገንዘብ ያለአግባብ የወሰዱ ግለሰቦች በዲጂታል የክፍያ አማራጭ መመመለስ ይችላሉ አለ። ባንኩ ፤ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ እና ያዘዋወሩ ሰዎች እስክ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ ም ድረስ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመገኘት እንዲመልሱ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። ዛሬ ምሽት ባወጣው መልዕክት ደግሞ ፤ " ያለ አግባብ ገንዘብ የወሰዱ ግለሰቦች…
#Update

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ወይም ወደተለያየ ሂሳቦች ያስተላለፉ ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ በፍቃዳቸው እንዲመልሱ ያስመቀጠው የመጨረሻ ቀን ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 14 ያበቃል።

ባንኩ ሰጥቶ የነበረው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው።

ገንዘቡን በአቅራቢያ ባለው ቅርንጫፍ ወይም በዲጂታል መንገድ ቀድሞ ገንዘቡ ወጪ ወደተደረገበት የባንኩ ሂሳብ ማስገባት ይቻል ነው የተባለው።

ዛሬ በሚጠናቀቀው የመጨረሻ ቀን የወሰዱትን ገንዘብ ተመላሽ የማያደርጉ ግለሰቦች ላይ ደረጃ በደረጃና ጠንከር ያሉ እርምጃዎች ለመውሰድ ዝግጅት መደረጉን ባንኩ አሳውቋል።

ገንዘቡን የወሰዱ እንዲሁም ያዘዋወሩትን ሰዎች ስምና ፎቶግራፋቸውን በሚዲያ ለህዝብ እንደሚያሰራጭም አስጠንቅቋል።

አርብ ለሊት ከባንኩ ሲወጣና ሲዘዋወር ያደረው ገንዘብ በትክክል ምን ያህል እንደሆነ በይፋ ባይገለጽም ባንኩ ግን የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ የወሰዱ ሁሉ ገንዘቡን እንዲመልሱ እያስጠነቀቀ ነው።

" አሶሼትድ ፕሬስ " ባንኩ የሲስተም ችግር በገጠመው ወቅት የተወሰደበት ገንዘብ 2.4 ቢሊዮን ብር (40 ሚሊዮን ዶላር) መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ግን ፤ " የኦዲት ምርመራው ባለመጠናቀቁ የተወሰደውን ገንዘብ መጠን አሁን ላይ አይታወቀም " ብለዋል።

አጠቃላይ ኦዲት ተደርጎ ስላላቀም እስካሁን ምን ያህል እንደተመለሰ የሚታወቅ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " 4 ሚሊዮን ብር ለማስለቀቂያ ከፍለናል ሰነዱ በእጄ አለ፤ ከለቀቋቸው በኃላ ድጋሜ በመያዝ 6 ሚሊዮን ብር ጠይቀዋል " - ቀጣሪ ድርጅቱ ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለደን ምንጣሮ ስራ በግል ድርጅት ተመልምለው ወደ ስፍራው በአማራ ክልል፣ በምስቅው ጎጃም ፣ ጎዛመን በኩል አቋርጠው ሲጓዙ የካቲት 18/2016 ዓ/ም " በፋኖ ታጣቂዎች " ታገቱ የተባሉ ሠራተኞች እስካሁን ከእገታ አልተለቀቁም ሲል…
#Update

" ታጋቾቹ ተለቀው በሰላም #አዲስ_አበባ ገብተዋል " - የጋርዱላ ዞን አስተዳደር

" ለማስለቀቂያ መጀመሪያ ከከፈልነው 4 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ በእያንዳንዱ መኪና (4 መኪናዎች) 500 ሺህ ብር ከፍለናል " - ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን

" አንድም ገንዘብ አልተቀበልንም " - ፋኖ ማርሸት ፀሀይ

በአማራ ክልል ፣ ምስራቅ ጎጃም ታግተዋል የተባሉ የቀን ሰራተኞች ከእገታው ተለቀው በሰላም አዲስ አበባ መግባታቸው ተነግሯል።

የጋርዱላ ዞን አስተዳደር ፤ " በኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሐይቅ የሚያርፍበት ስፍራን ለመመንጠር ከዞኑ 246 ተመልምለው ሲጓዙ የነበሩና በአማራ ክልል የታገቱ ሠላማዊ ዜግች ተለቀዋል " ብሏል።

ታጋቾቹ ትላትን ምሽት መለቀቃቸውን ያሳወቀው የዞኑ አስተዳደር ዛሬ በሠላም ተጉዘው አዲስ አበባ መድረሳቸውን አሳውቋል።

ወደ ህዳሴው ግድብ ለደን ምንጣሮ ስራ ሲሄዱ የታገቱት 272 ሰራተኞች እንደሆኑ ገልጾ የነበረው ቀጣሪ ድርጅቱ ኒኮቲካ ኮንስትራሽን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል ታጋቾች መለቀቃቸውን አረጋግጧል።

የተለቀቁት ግን 271 ሰራተኞች እንደሆኑና 1 ሰው ሾልኮ መጥፋቱን ነገር ግን ከቤተሰብ ጋር መደዋወሉን አመልክቷል።

ድርጅቱ በመጀመሪያ #ለማስለቀቂያ 4 ሚሊዮን ብር ከፍሎ እንደነበር ተለቀው ሲሄዱ አማኑኤል አካባቢ ድጋሚ በሌላ የቡድኑ ክንፍ ተይዘው ለማስለቀቂያ 6 ሚሊዮን ብር መጠየቁን በኃልም በእያንዳንዱ መኪና 500 ሺህ ብር ተከፍሎ ሰራተኞቹ መለቃቃቸውን አሳውቋል።

' የአማራ ፋኖ ምስራቅ ጎጃም ቃል አቀባይ ' ፋኖ ማርሸት ፀሀይ " ' ሰራተኞች ' የተባሉት ወደ ብርሸለቆ ሲያመሩ የነበሩ ምልምል ወታደሮች ናቸው ፤ ይመሯቸው የነበሩትም ማዕረግ ያላቸው ወታደሮች ነበሩ ፤ ምርኮኞች እንጂ ታጋቾች አይደሉም፤ ቁጥራቸውም 246 ነው " ብለው ነበር።

ትላንትና በሰጡት ቃል ፤ የግለሰቦቹን መለቀቀ አረጋግጠው ፤ " የተለቀቁት 240 ናቸው። አንድም ብር አልተቀበልንም " ብለዋል።

"ልጆቹን እንዲረከበን የቀይ መስቀል ማህበረን ጠይቀን ቀርቷል ፤ ሊቀበለንም አልቻለም። እኛ ከልጆቹ ጋር ባደረግነው ስምምነት የትራንስፖርት ወጪያቸውን ብንሸፍን በቀጥታ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሚሄዱ ስለተነጋገርን እነሱም ስላመኑበት ወደ ቤተሰቦቻቸው ሸኝተናቸዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ፤ " ፋኖ ገንዘብ አይቀበልም። ገንዘብ መቀበል ብንፈልግ ኖሮ እኮ ከሁሉም እንቀበል ነበር። ከአንዱ ተቀብለን ከአንዱ የማንቀበልበት ምክንያት የለም። በስነስርዓት ለመከላከያ ስልጠና የሚመጡ ቤተሰብ ያላቸው ሰዎች ገንዘብ ተጠይቀናል ወደ ሚል ስም ማጥፋት ገብተዋል ምክንያቱም አላማቸው ስለተስተጓጎለ " ብለዋል።

" ገንዘብ ከማንም አልጠየቅንም " የሚሉት ማርሸት " እንደውም ለተሽከርካሪ ነዳጅ ሞልተናል፣ የሹፌሮች አበል ሰጥተናል እውነቱ ይሄ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን ግን ታግተው የነበሩ ሰራተኞች ለማስቅለቅ በቅድሚያ 4 ሚሊያን ብር በሶስት ሰዎች ስም የገባበት ማስረጃ በእጁ እንዳለና በቀመጠልም በእያንዳንዱ መኪና 500 ሺህ ብር በድምሩ 6 ሚሊዮን ብር መክፈሉን አሳውቋል።

የጋርዱላ ዞን እንዳሳወቀው 246 ታጋቾች ተለቀው ዛሬ አዲስ አበባ ደርሰዋል። ታጋቾቹ እንዲለቀቁ የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶች፣ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ፣ የአማራ ክልል የመንግስት አካላት በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች የሃይማኖት ተቋማት ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር ትልቅ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መረጃ ከጋርዱላ ዞን ኮሚኒኬሽን እንዲሁም ከቪኦኤ ሬድዮ ማግኘቱን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ታጋቾቹ ተለቀው በሰላም #አዲስ_አበባ ገብተዋል " - የጋርዱላ ዞን አስተዳደር " ለማስለቀቂያ መጀመሪያ ከከፈልነው 4 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ በእያንዳንዱ መኪና (4 መኪናዎች) 500 ሺህ ብር ከፍለናል " - ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን " አንድም ገንዘብ አልተቀበልንም " - ፋኖ ማርሸት ፀሀይ በአማራ ክልል ፣ ምስራቅ ጎጃም ታግተዋል የተባሉ የቀን ሰራተኞች ከእገታው ተለቀው በሰላም…
" 271 ዜጎችን ከእገታ አስለቅቄያለሁ " - ኮማንድ ፖስት

ላለፉት 25 ቀናት በአማራ ክልል ፣ ምስራቅ ጎጃም ውስጥ በታጣቂዎች እገታ ላይ እንደነበሩ የተነገረላቸው የቀን ሰራተኞች ከእገታ ተለቀው ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

በሀገር መከላከያ ሠራዊት የጎጃም ኮማንድ ፖስት አንድ ኮር ፤ ታግተው የነበሩ 271 ዜጎችን ማስለቀቁን አሳውቋል።

ኮማንድ ፖስቱ በአራት አውቶብስ ተጭነው ሲጓዙ የነበሩት 273 ዜጎች እንደሆኑ እና " በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ማርቆስ እና በኤሊያስ ከተማ መካከል ሲደርሱ ነው በጽንፈኛኞች ታግተዋል " ብሏል።

ታጣቂ ቡድኑ ከ3 ሰዓት በላይ ወደማይታወቅ ቦታ አስገድዶ ከወሰዳቸው በኋላ ሁለቱን #በመረሸን ለቀናት ደብቆ ሲያሰቃያቸው መቆየቱን ገልጿል።

በኃላም " ኮሩ ወደ አካባቢው በመሠማራት ከበባ በማድረግ ምቹ ሁኔታ ሲጠባበቅ መከበቡን የተረዳው ፅንፈኛ ለቋቸው ሊሸሽ ችላል " ሲል አመልክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጋርዱላ ዞን ባገኘው መረጃ በእገታ ላይ የነበሩና ከዞኑ ተመልምለው ለደን ምንጣሮ ስራ ወደ ህዳሴው ግድብ ሲያቀኑ የነበሩ 246 ሰራተኞች ትላንት ምሽት ተለቀው በሰላም አዲስ አበባ ገብተዋል።

ዞኑ ለሰራተኞቹ ከእገታ መለቀቅ ላለፉት ቀናት የፌዴራል መንግሥት ፣ የአማራ ክልል በየደረጃው ያሉ የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ ቀይ መስቀል ትብብር ማድረጋቸውን እና የባለሃብቶች ጥረት እንዳለበትም ጠቁሟል።

የኧሌ ዞንም ፤ " ለጉልበት ስራ ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሲሄዱ በአማራ ክልል በታጣቂዎች የታገቱ ዜጎች ተለቀዋል " ብሏል።

ዞኑ ፤ መንግሥት እና ባለሃብቱ አድርገዋል ባለው ጥረት ነው ታጋቾች ነፃ የወጡት።

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል አማካኝነትም ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን ነው ያመለከተው።

ከዞኑ ተመልምለው የሄዱት 38 የቀን ሰራተኞች ናቸው።

ከላይ ያሉት የሰራተኞች ቁጥር ድምር 284 ሲሆን ቀጣሪው ድርጅቱ ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን ግን ይህን ቁጥር አይቀበለውም ታግተው የነበሩትም 272 ናቸው ነው የሚለው። ለዚህም በቂ የሰነድ ማስረጃ እንዳለው ይገልጻል።

ላለፉት ቀናት ወደ ስፍራው ከፍተኛ የድርጅቱን ኃላፊ በመላክ ሰራተኞቹ ደህንነታቸው ተጠብቆ ምንም ሳይሆኑ እንዲለቀቁ ጥረት ሲያደርግ የቆየው ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን ታጣቂዎቹ በድምሩ 6 ሚሊዮን ብር ወስደው ልጆቹን እንደለቀቋቸው ገልጿል።

መጀመሪያ 4 ሚሊዮን ብር ለማስለቀቂያ በሶስት ሰው ስም ከተከፈለ በኃላ ሰራተኞቹ ተለቀው በ4 መኪና ጉዞ ጀምረው ለዋናው አስፓልት ትንሽ ሲቀራቸው አማኑኤል አቅራቢያ ሌላ የቡድኑ ክንፍ ይዟቸው 6 ሚሊዮን ብር ሲጠይቅ እንደነበር ድርጅቱ ገልጿል።

በኃላ ግን ለእያንዳንዱ መኪና 500 ሺህ ብር በመክፈል በድምሩ አጠቃላይ በ6 ሚሊዮን ብር እንዲለቀቁ መደረጉን ተናግሯል።

እንደድርጅቱ መረጀ ከተለቀቁት 271 ሰዎች አንዱ ሾልኮ የጠፋ ሲሆን በኃላም በስልክ ከቤተሰቦቹ ጋር መነጋገሩ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ትላንት ታጣቂዎች በሩስያ ፣ #ሞስኮ በሚገኘው የክሮከስ አዳራሽ የሙዚቃ ዝግጅት ለመታደም በተሰበሰቡ በርካታ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ የተገደሉ ሰዎች 115 የደረሱ ሲሆን 100 ሰዎች መቁሰላቸውን የሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል። ከተገደሉት ውስጥ ህፃናትም እንደሚገኙበት ተነግሯል። 4 ታጣቂዎችን ጨምሮ 11 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሩስያ ባለስልጣናት አሳውቀዋል። የሩሲያ…
#ሩስያ

" ሽብርተኞችን የሚጠብቀው የበቀል እርምጃ ብቻ ነው " - ቭላድሚር ፑቲን

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከትላንትና የሽብር ጥቃት በኃላ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም ነገ መጋቢት 15 በመላው ሩሲያ የሀዘን ቀን እንደሚሆን ተናግረዋል። " የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ዜጎቻችን ይዘከሩበታል " ብለዋል።

አሁን ላይ በጥቃቱ ላይ ቀጥታ ተሳትፎ የነበራቸው ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጠር ስር መዋላቸውን ያስታወቁት ፕሬዝዳንቱ፤ ሌላ የጅምላ ግድያ እንዳይፈጸም የጸጥታ ኃሎች ሰፊ ስራ እየሰሩ ነው ብለዋል።

" በትናንትናው የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፈ እና ያገዛቸው የትኛውም አካል ለህግ ይቅርባል " ሲሉ ዝተዋል።

ፕሬዜዳንቱ በትናንትናው የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፉ 4 ወንጀለኞች ወደ ዩክሬን ሊያመልጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

" አሁን ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንደሚያመላክተው በዩክሬን በኩል ሽብርተኞች ለማስመለጥ የሚያስችል መንገድ በድንበር በኩል ተዘጋጅቶ እንደነበረ ነው "  ብለዋል።

" ሩሲያ በዚህ የሽብር ጥቃት ላይ የተሳተፉ ሁሉንም አካላት ለይታ ትቀጣለች " ያሉት ፑቲን፤ " ሽብርተኞችን የሚጠብቀው የበቀል እርምጃ ብቻ ነው፤ ከዚህ ውጪ ምንም አማራጭ እና ተስፋ የላቸውም " ሲሉ ዝተዋል። #አልአይን

@tikvahethiopia