TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መተግበሪያዎን ሲቢኢ ብር ላይ ያስቀምጡ
በቀላሉ በርካታ ደንበኞች ዘንድ ይድረሱ!

#CBE #cbebirr #apps #digitalbanking
*************
የሲቢኢ ብር መተግበሪያ ማስፈንጠሪያ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
" ኑ ቸርነትን እናድርግ "

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን  እናድርግ " በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር መጋቢት 15 ቀን ከቀኑ 7:00 ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

ማህበሩ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን አመልክቷል።

ገቢ ማሰባሰቢያው በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶችን ለመደገፍ የሚውል እንደሆነ ገልጿል።

የማኅበሩ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም ፤ " በየጊዜው በሚከሰከቱ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት አስቸጋሪ ቢሆንም ወገን ለወገኑ መርዳት ስላለበት ሌሎች አገልግሎቶችን ለጊዜው በመግታት ኅብረተሰቡን በማስተባበር ትኩረት ተደርጎ እንዲሠራ ተወስኗል " ብለዋል።

በተለይም ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች ላይ በስፋት ድጋፍና እርዳታ እንደሚደረግ በዚህ የጾም ወቅት ደግሞ ምጽዋት ማድረግ አግባብም እንደሆነ ተናግረዋል።

አያይዘውም ፤ ሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች በዚህ ወቅት ፤ በአንድ ልብ እና ሀሳብ በመሆን ለተቸገሩት መድረስ እንደሚገባ ፤ ብፁዓን አባቶች በማስተማር ፤ ማኅበራት ፣ ሰንበት ት/ቤቶች ፣ አጠቃላይ የቤተክርስቲያን ልጅ የሆነ ሁሉ በገንዘብ በዓይነት ሊበላሹ የማይችሉ የታሸጉ ምግቦችን ጨምሮ ድጋፍ እንዲያደርጉ በማኅበሩ ስም ጥሪ አቅርበዋል።

በዕለቱ፦
- ብፁዓን አባቶች ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ይሰጣሉ ፤
- በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መምህራን ትምህርተ ወንጌል ፤
- የመዝሙር አገልግሎት፤
- ዶክመንተሪ ቪዲዮ የሚቀርብ ሲሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የገዳማትና አድባራት አባቶችን ጨምሮ የሚደረግ መርሐ ግብር ይሆናል ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከማህበሩ ባገኘው መረጃ ፤ የመግቢያ ትኬት መቶ ብር እየተሸጠ ሲሆን በዕለቱ እዛው በር ላይም ይሸጣል።

አሁን በተዘጋጀው የማኅበራዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ላይ መሳተፍ ለማይችሉ በተለያዩ በሚዘጋጁ የድጋፍ ማድረጊያዎች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

የመርሐ ግብሩን የመግቢያ ትኬት :-
1.  በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም)
2.  በወረዳ ማዕከላት ጽ/ቤቶች  
3.  በማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆች
4.  በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያዎች
5.  በአሐዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
6.  በሰ/ት/ቤት ጽ/ቤቶች ይገኛል ተብሏል።

ተጨማሪ መረጃ ለሚፈልጉ በ09 44 71 82 82 እና 09 42 40 76 60 መደወል ይችላሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC ወደ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ለሥራ ሲያመሩ በአማራ ክልል ጎጃም ውስጥ ስለታገቱ ዜጎች ሰምቶ እንደሆነና መረጃው ይኖረው እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ን ጠይቋል። የተጀመረ ምርመራ ካለም ማብራሪያ ጠይቀናል። አንድ የኮሚሽኑ አካል በሰጡት ምላሽ፣ “ መረጃው አለን። በሥራ ላይ ነን። ምናልባት እንግዲህ ፋይንዲንጎች ሲኖሩ እናሳውቃለን ” ሲሉ አረጋግጠዋል።…
#Update

• " በአማራ ክልል ውስጥ የተያዙት ልጆቻችን እንጀራ ፍለጋ የወጡ እንጅ ሌላ ተለእኮ እንደሌላቸዉ እኛ ምስክሮች ነን " - የጋርዱላ ዞን የሀይማኖት አባቶች

• " ወጣቶቹን መልምሎ የወሰደዉ የግል ድርጅት መሆኑ የወጣቶችን ለስራ መሰማራት ያሳያል " - የጋረዱላ ዞን አስተዳደር

ከሰሞኑ ለስራ ጉዳይ ወደታላቁ የህዳሴ ግድብ በመሄድ ላይ ሳሉ በፋኖ ተያዙ ስለተባሉ ወጣቶችን በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ያደረጉት የጋርዱላ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሀኑ ኩናሎ ፤ ከዞናቸዉ ለስራ ሄደዉ የተያዙ ወጣቶች እጅግ አሳሳቢ እንደሆነባቸዉና ከሀገር ሽማግሌ እስከ ሀይማኖት አባትና የመንግስት አካላት ወጣቶቹን ለማስለቀቅ ከፍተኛ እርብርብ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ብርሀኑ ፤ ወጣቶቹ ከደራሼ አሌና አካባቢዉ በባለሀብት በኩል ተመዝግበዉ እንጀራ ፍለጋ መሄዳቸውን በመግለጽ " ይህ ደግሞ ንጽህናቸዉን ይገልጻል " ብለዋል።

አሁን ላይ ጉዳዩን ውጤታማ ለማድረግ  ከቀይ መስቀል ጋርም ስራ እየተሰራ ሲሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፣ የአማራ ክልልና የፌደራል መንግስቱም እየጣሩ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ፤ የጋርዱላ ዞን ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ ቀሲስ መምሬ ተክሌ ደስይበለዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ " እነዚህ ወጣቶች ምስኪን እነጀራ ፈላጊ እንጅ የፖለቲካ ተልእኮ የላቸዉም " ብለዋል።

" አሁን ላይ የታጋቾቹ ቤተሰቦች ከአማራ ክልል ጋር ተነጋግራችሁ ልጆቻችን አስመልሱ " በማለት እየጠየቁን ነው የሚሉት ቀሲስ መምሬ ተክሌ ፤ " የልጆቹን ንጽህና ተረድተዉ  የያዟቸዉ አካላት ይለቁልን ዘንድ  እንጠይቃለን " ብለዋል።

ወደ ህዳሴው ግድብ ለስራ ሲሄዱ ተያዙ ከተባሉ ወጣቶች ጋር በተያያዘ ከቀናት በፊት ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት የሰጡት ' የአማራ ፋኖ የጎጃም ቃል አቀባይ ነኝ ' ያሉት ፋኖ ማርሸት ፀሀዩ ፦ " ልጆቹ አውቀውም ይሁን ተጭበርብረው ጎጃም ውስጥ ወደሚገኘው የብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲወሰዱ እንዳገኟቸው፤ ሲመሯቸው የነበሩትም ወታደሮች እንደነበሩ ከራሳቸው ከተገኘው መታወቂያቸው ማረጋገጣቸውን ነገር ግን በቀጣይ ከ72 እስከ 100 ሰዓታት ውስጥ ለቀይ መስቀል ለማስረከብ እየተዘጋጁ እንደሆነ " አሳውቀው ነበር።

ምንም እንኳን ይህ ከተባለ ቀናት ቢያልፉም የወጣቶቹ ጉዳይ ከምን እንደደረሰ የሚታወቅ ነገር የለም።

መረጃው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

➡️ " የቀብር ስርዓቱ ተፈጽሟል " - የዶክተር በሀይሉ ቤተሰብ 

➡️ " ይቅርታ መረጃው የለኝም " - የአዲስ አበባ ፓሊስ

እውቁና እጅግ የተዋጣላቸው የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶ/ር በኃይሉ ኃይሉ መገደላቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ዶ/ር በኃይሉ ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ለጥዋት ሩጫ በሚል በወጡበት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ነው የተገለጸው።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ አንድ የሟች ቅርብ ቤተሰብ፣ " ቤተሰብ ጠቅላላ ' ወጥቶ ሞተ ' ነው የምናውቀው። ሚዲያ ላይ ካለው ውጪ አዲስ የሰማነው ነገር የለም " ብለዋል።

ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል ? ቤታቸው የት አካባቢ ነው ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " ቀብሩ ተፈጽሟል፣ ከትላንት ወዲያ ሰዓሊተ ምህረት " ብለው፣ ቤታቸውን በተመለከተም፣ " ቦሌ ሚካኤል ነው። ሞተ ያሉት ደግሞ ወደ ሳሪስ በሚወስደው ድልድይ ጠዋት ወክ ሲያደርግ ነው። ዞሮ ዞሮ አስከሬኑን ፓሊስ ነው ያነሳው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስን ለመጠየቅ ጥረት አድርጓል።

የኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በሰጡት አጭር የፅሑፍ  ምላሽ፤  " ይቅርታ መረጃው የለኝም " ሲሉ ለጊዜው አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

በቀጣይም የአዲስ አበባ ፖሊስን ስለ ጉዳዩ የምጠይቅ ይሆናል።

በተጨማሪም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፣ የቀድ ጥገና ሀኪሙን ግድያ በተመለከተ የደረሰው መረጃ እንዳለ ለኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ አንድ የማኀበሩ ባለስልጣን በሰጡት ቃል፣ " እኔም በማኀበራዊ ድረገፅ ነው የሰማሁት በጣም ያሳዝናል " ብለዋል።

አክለውም፣ " ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው ተመሳሳይ ነገር የተፈጸመው። ዶክተር እስራኤል ጥላሁን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገሏል። እየሆነ ያለዉ ነገር ልብ ይሰብራል። ሁኔታውን አጣርተን መግለጫ እናወጣለን። ለአሁኑ ግን በቂ መረጃ የለንም በጉዳዩ ዙርያ " ሲሉ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር በበኩሉ በዶክተር በሀይሉ ሀይሉ ሞት የተሰማውን ሀዘን በመግለጽ መግለጫ አውጥቷል።

ለዶክተሩ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች፣ የስራ ባልደረቦች መፅናናትን ተመኝቷል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
“ሹፌሩን፣ ጋቢና የነበሩ 2 ሰዎችን ጭንቅላታቸውን በሰደፍ መቷቸው። በገመድ አስረው፣ አፋቸውን በፕላስተር አስይዘው መኪናውን ይዘው ሄዱ ” - የተሽከርካሪው ባለቤት

“ እንዲህ አይነት ወንጀሎች ከዕለት ዕለት እየጨመሩ ነው ” - የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር

#ከአዲስ_አበባ ተነስቶ ወደ #ወላይታ_ሶዶ 70 ኩንታል ዱቄት ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ በሻሸመኔ እና ሀዋሳ መካከል ከቶጋ ካምፕ አለፍ ብሎ ቢሻን ጉራቻ (ጥቁር ውሃ) መግቢያ ላይ በሚገኝ ቦታ ማክሰኞ መጋቢት 3 ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ ላይ በታጠቁ ኃይሎች እንደተወሰደና እንዳልተመለሰላቸው የተሽከርካሪው ባለቤት፣ ሌላ እማኝና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የተሽከርካሪው ባለቤት በሰጡት ቃል፣ “ ሹፌሩን፣ ጋቢና የነበሩ 2 ሰዎችን ጭንቅላታቸውን በሰደፍ መቷቸው። በገመድ አስረው፣ አፋቸውን በፕላስተር አስይዘው መኪናውን ይዘው ሄዱ ” ሲሉ ገልጸዋል።

እንዲህ ያደረጉ አካላት ማን እንደሆኑ ሲያስረዱ ፣ “ ደብል ጋቢና በሆነ መኪና (አሮጌ ነገር ነው) እርሱ ላይ ሰዎች ነበሩ፣ 3 ክላሽ 1 ሽጉጥ የያዙ። ‘ኬላ ጥሳችሁ ነው የመጣችሁት አሉ’። ኬላ አልጣስንም ያው ደረሰኙ ቢላቸውም ‘አይ ውረድ ውረድ’ ብለው ሹፌሩን በሰደፍ መቱት ጭንቅላቱ ላይ፣ ጋቢና ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎችንም አስወረዱ እነርሱንም ጭንቅላታቸውን በሰደፍ መቷቸው ” ነው ያሉት።

በገመድ አስረው ፣ አፋቸውንም በፕላስተር አስይዘው እንደነበር በኃላም አላሙዲን እርሻ ፊት ለፊት ባለው አቅጣጫ መኪናውን ይዘው እንደሄዱ ተናግረዋል።

የተሽከርካሪው ባለቤት ፤ በሰደፍ ተመቱ የተባሉት ሰዎች ቢለቀቁም ቁስሉ እንዳልተሻላቸው ገልጸዋል።

“ ዱቄቱ 70 ኩንታል ነው። 210 ሺሕ ብር ይገመታል። መኪናው  አዲስ ነው 2022 ሞዴል ቢ 24 ነው። መኪናውን ይመልሱልኝ ” ሲሉ የመኪናው ባለቤት ተማጽነዋል።

ሌላኛው ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አካል በበኩላቸው፣ “ ሹፌሩንና ረዳቱን ደበደቡ። የኤሌክትሪክ ፓል ጋ ሹፌሩን አሰሩ። ከዚያ መኪናውን ይዘው ሄዱ። እስከዛሬ ፋይዳ የለም ” ሲሉ አረጋግጠዋል።

ተፈፀመ የተባለውን ድርጊት አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጥ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ቡኩሉ ፣  70 ኩንታል ዱቄት ጭኖ የነበረው ተሽከርካሪ በሻሸመኔ ቢሻን ጉራቻ (ጥቁር ውሃ) መግቢያ ላይ እንዲቆም ተደርጎ እንደተወሰደ፣ ሰዎቹ ተደብደብዋል መባሉም እውነት ነው እንደሆነ ገልጿል።

አንድ የማኀበሩ ኃላፊ ፤ ሌላም እዚህም ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ ከድሬዳዋ ዘይት ጭኖ የቆመ መኪና ሰሞኑን ጠፍቶ እንደነበር፣ መጨረሻም ጭነቱ ተራግፎ ቆሞ እንደተገኘ አስታውሰው፣ " ትክክል ነው የሻሸመኔውም። እንዲህ አይነት ወንጀሎች ከዕለት ዕለት እየጨመሩ ነው " ብለዋል።

" ምክያቱም በአሽከርካሪዎችና በተሽከርካሪዎች ላይ የሚደርስን ወንጀል በወንጀልነት ቆጥሮ በጸጥታ አካል አድኖ የመያዝ ሂደት አናሳ ሆኗል። አይደለም እቃውን የሰውን ሕይወት መጥፋትም በተለይ በመንግሥት ሚዲያዎች ሲዘገብ አናይም " ሲሉ አክለዋል።

" እገታና ዝርፊያ በጣም ተበራክቷል። " ያሉት እኚህ ኃላፊ " ሜዳ ላይ አስቁመው ደብድበው የሚፈልጉትን ይዘው ነው የሚሄዱት " ሲሉ የሁኔታውን አስከፊነት አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ምላሽ ለማግኘት ወደ ሻሸመኔ ከተማ ፓሊስ ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም። #TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
" ... ምንም አይነት ሽያጭ ሳያካሄድ ደረሰኞችን ብቻ በመሸጥ መጠኑ 2,951,053,749.86 ብር የሚሆን ሽያጭ አከናውኗል " - ፖሊስ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ፤ በመንግስት ላይ ከ2 ቢሊዮን 951 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አደረሰ ያለውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለጸ።

እንደ ፖሊስ መረጃ ...

ተጠርጣሪው ግለሰብ ቴዎድሮስ ንጉሴ ሀያርያ እና  ቴዎድሮስ ንጉሴ ወልድሀዋሪያ በተባሉ ሀሰተኛ ስሞችን በመጠቀም ከ2 ቢሊዮን 951 ሚሊዮን 053 ሺህ 7 መቶ 49 ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሷል።

ከሌሎች ግብረ-አባሮቹ ጋር በመሆን ቴዎድሮስ ንጉሴ ሀያርያ በሚለው ሀሰተኛ ስም ንግድ ፍቃድ በማውጣት፣ የወንጀል ድርጊቱ እንዳይደረስበት ለማድረግ እና ከታክስ ሰብሳቢው መ/ቤት ክትትል ለመሰወር በቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በመቀየር ህጋዊ በመምሰል ሲንቀሳቀስ ነበር።

የዕቃ እና አገልግሎት ግብይት ሳይኖርም የተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች የመለያ ቁጥር ርLB 0019300 ከሆነው የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ በ1 ሺህ 2 መቶ 70 ደረሰኞች አማካኝነት ምንም ሽያጭ ሳያካሄድ ደረሰኞችን ብቻ በመሸጥ መጠኑ 2,951,053,749.86 ብር የሚሆን ሽያጭ አከናውኗል።

ከዚህ በተጨማሪ " ግዥ ፈጽመናል " በማለት ሀሰተኛ ደረሰኞቹን ከተጠርጣሪው ላይ የገዙ ግብር ከፋዮች ደግሞ በሀሰተኛ ሰነዶች አማካኝነት ወጪያቸውን በማነር ለመንግሥት የሚከፈለውን ግብርና ታክስ እንዲቀንስና ያልተገባ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመላሽ ከመንግሥት ካዝና አንዲወስዱ ማድረጉም ተገልጿል።

የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኢንተለጀንስ ሥራ ሂደት ባሰላው መሠረት ተጠርጣሪው ምንም ግብይትና አገልግሎት ሳይሰጥ ደረሰኞችን ብቻ በመሸጥ በመንግስት ላይ ያደረሰው ጉዳት መጠን ፦

1ኛ. የንግድ ትርፍ ግብር:- 769 ሚሊየን 890 ሺህ 1 መቶ ከ08 ሣንቲም፤

2ኛ. የተጨማሪ እሴት ታክስ( VAT) መጠን፦ 384 ሚሊየን 920 ሺህ 054 ብር ከ04 ሣንቲም ሲሆን፤

በአጠቃላይ በድምሩ 1 ቢሊዮን 154 ሚሊዮን 760 ሺህ 1 መቶ 62 ብር ከ12 ሣንቲም በመንግስት ላይ ጉዳት ማድረሱም ተረጋግጧል።

ተጠርጣሪው ግለሰብ ቴዎድሮስ ንጉሴ ሀያርያ እና ቴዎድሮስ ንጉሴ ወልድሀዋርያ የተባሉ ሀሰተኛ ስሞችን በመጠቀም ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ከተለያዩ አራት ወረዳዎች የነዋሪነት መታወቂያ እንዳወጣ በማስመሰል እና አራት ሀሰተኛ የውክልና ሠነዶችን በማዘጋጀትና በመጠቀም፤ በገቢዎች ሚኒስቴር የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ አቅራቢ ድርጅት፣ በተለያዩ ባንኮች፣ በንግድ ፅህፈት ቤቶች እና በሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የግል ድርጅቶችና ግለሰብ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ በመምሰል ወንጀል ሲፈጽም መቆየቱን ፖሊስ እንደደረሰበት አመልክቷል።

ፖሊስ ከፍርድ ቤት የብርበራ ፈፍቃድ በማውጣት አያት ሆሴ ሪልስቴት በሚገኘው የተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት ውስጥ ባደረገው ብርበራ፤ ስምንት  ፍላሾችን፣ በተጠርጣሪው ሀሰተኛ ስሞችና በራሱ በተጠርጣሪው ትክከለኛ ፎቶግራፍ የወጡ እና የተዘጋጁ ሌሎች የሰነድ ማስረጃዎችንም መያዙን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ  ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጾ ኅብረተሰቡም ወደ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ በአካል ቀርቦ በተጠርጣሪው ላይ ተጨማሪ መረጃ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ትላንት በተጠናቀቀው የካቲት ወር በተፈፀሙ ጥቃቶች በርካቶች ተገድለዋል። ጉዳትም ደርሷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወሩ ስለነበሩት ሁኔታዎች ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት እጅግ በርካታ ቀናትን የወሰደ ሙከራ ቢያደርግም ምንም ምላሽ የሚሰጠ አካል አላገኘም። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ግን ስለነበሩት ሁኔታዎች…
#AmharaRegion

° " ህዝቡ በታጠቁ ቡድኖች ነው ለጥቃት የተዳረገው በገዛ ከተማው ነው መአት ያወረደበት ... ጥቃት ፈፃሚዎቹ ከአጎራባች ' ሸኔ ' ናቸው " - የአጣዬ ከተማ ከንቲባ

° " #ሀሰት_ነው የኦሮሞ አርሶ አደሮች እንጂ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት አይደሉም " " - አባገዳ አህመድ ማህመድ

በአማራ ክልል ፤ የሰሜን ሸዋን እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደርን በሚያጎራብቱ አካባቢዎች ላይ ግጭት ከጀመረ ከሳምንት በላይ ሆኖታል።

በተደጋጋሚ ፦
- የሰዎች ደም በሚፈስበት፣
- ንብረት በሚወድምበት ፣
- ሰዎች ቄያቸውን ለቀው በሚፈናቀሉበት በዚህ ቀጠና ባለፈው የካቲት ወር ውስጥም በርካቶች መገደላቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ #ከ8_ቀናት በፊት የተቀሰቀሰው ግጭት እጅግ መባባሱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በመነሻው ላይ በሁለቱም በኩል እርስ በእርስ መወነጃጀል ያለ ሲሆን በኤፍራታ ግድምና ቀወት ውስጥ ግጭቱ ከፍቶ መዋሉ ነው የተሰማው።

በሁለቱም በኩል ያሉት ነዋሪዎች ፣ የአጣዬ ከንቲባ ፣ የአካባቢው አባገዳ ምን አሉ ?

በኤፍራታ ግድም ወረዳ የአላላ ከተማ ነዋሪ ፤ ጦርነት ከተጀመረ 8 ቀን መያዙን ፣  ብዙ ቤቶች መቃጠላቸውን ገልጸዋል።

ነዋሪው " የአርሶ አደሮች ዱቄት ሳይቀር ፣ በግ ፣ ፍየል ፣ ግመል ፣ አህያ፣ ከብት በሙሉ ሙልጭ አድርገው ወስደውብናል። ኃላሸት የሚባል ሰውም ገድለውብናል እኛው ክልል ላይ ገብተው " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ካደረጉ በኃላ ህዝቡ ተሬ እና ዘንቦ ወደሚባለው አካባቢ በለበሰው ልብስ ሸሽቶ ተጠልሎ እንደሚገኝ ገልጸዋል። " በተከታታይ 18 ሰዎችን ገድለውብናል "ም ብለዋል።

በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰንበቴ ነዋሪ ፤ " እስከ ጅሌ ጥሙጋ ባርሲሳ ፣ ካራ ሌንጫ ፣ መከና ወይም አጣዬ ከተማ ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች ከትላንትና ጀምሮ ተኩስ ነበር። ትላንት አንዲት ሴት እንዲሁም ግመልና ከብቶችም ተመተው ነበር ግጭቱ የቀጠለው በዚህ ነው፤ አንድ ሰው ሲሞት ሁለት ሰው ቆስለዋል፤ አንዱ ወደ አዳማ ተልኳል። ዛሬ ደግሞ 4 ሰው ሲሞት 3 ሰው ቆስሏል " ብለዋል።

ዋነኛው እቅዳቸው የጅሌ ጥሙጋ ከተማ #ሰንበቴን " እንይዛለን ፣ እናጠፋለን " የሚል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አንድ የአጣዬ ነዋሪ ደግሞ ፤ ሰሞኑን ግጭት ተባብሶ ዛሬ አጣዬን በተኩስ ልውውጥ ሲያናውጥ መዋሉን ፣ 5 ሰው መገደሉም. ጥቃት ፈፃሚዎቹ የታጠቁ አካላት " ሸኔ " ናቸው ብለዋል።

ሌላው የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ፣ የሰንበቴ ነዋሪ " ግጭቱ የጀመረው #መጋቢት_አንድ ላይ ነው። ይህም በጅሌጥሙጋ ኮላሽ የሚባል ስፍራ 1 ሰው ገድለው 2 ሰው አቁስለው ከብቶችንም ነድተው ከሄዱ በኃላ ነው ግጭቱን የተስፋፋው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ከባልች ቀበሌ እስከ ሰንበቴ እና መከና አጣዬ ድረስ ጦርነት ነው። የዛሬውን ለየት ያደረገው ታጣቂዎቹ #ከሰሜን_ሸዋ ተሰባስበው ፤ እራሳቸውን አደራጀትው ሌሊቱን በተሽከርካሪዎች ተጉዘው መጥተው ውጊያ መክፈታቸው ነው " ሲሉ አክለዋል።

ባለፉት 10 ቀናት 29 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረው የተወሰዱት ከብቶችና የወደመው ንብረትም ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ አስተያየት #አልቀበልም ያሉት የአላላ ነዋሪው ፤ " አማራው ሲያጠፋ በአማራው አጥፊውን መዞ ለህግ ማቅረብ፤ ከኦሮሞውም ሲያጠፋ አጥፊውን መዞ ለህግ ማቅረብ ሰላም የሚያሰፍነው ይሄ ብቻ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" በህግ እና በሽምግልና  ነገሩ መክሰም አለበት እነሱ የሚሉት ከጨፋ ጀምሮ እስከ ሸዋሮቢት ድረስ የኦሮሞ ቦታ ነው። አጣዬም #የኛ_ነች ፤ አላላም ፣ ሞላሌም ፣ ማጀቴም ... ሁሉም የኛ ነው የሚሉት። መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ችግሩን ሊፈታው ይገባል " ብለዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን #አባገዳ አህመድ ማህመድ " መንገድ የለም። ከጅሌ ጥሙጋ እና አርጡማ ፋርሲ ወረዳዎች እንዲሁም ከዞን መገናኘት አልቻልንም " ብለዋል።

" በዚህ ምክንያት የሃይማኖት አባቶች እና አባ ገዳዎች ተሰባስበው መፍትሄው ምንድነው ? ለማለት መንገዱ ተከፍቶ ለህዝቡ ምግብ ለማድረስ ፣ የቆሰሉትንም ወደ ህክምና ቦታ ለመውሰድ ጥረት ላይ ነን። መንገድ ከተዘጋ 1 ወር ሊሆነው ነው። እኛም ሆነ መንግሥታዊ አመራሩ ሄደን ማየት አልቻልንም። የአማራ ክልልም #ታጣቂዎቹን_ስለሚፈሯቸው ቀርበው ለማነጋገር አልተቻለም። እኛ ጋር ያሉትን #ወሰናችሁን አልፋችሁ አትሂዱ እያልን እየመከርናቸው ነው ። " ገልጸዋል።

ነዋሪዎችና የአካባቢው አስተዳደሮች ጥቃቱን የከፈቱት " ሸኔ (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) " ናቸው ቢሉም አባገዳ አህመድ " ሀሰት ነው " ብለዋል።

" ሀሰት ነው የኦሮሞ አርሶ አደሮች እንጂ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት አይደሉም። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እዚህ አልገባም። እየተዋጋ ያለው እራሱ ነዋሪው ነው " ብለዋል።

የአጣዬ ከተማ ከንቲባው ተመስገን ተስፋ ፤ ከተማዋና ህዝቡ በታጠቁ ቡድኖች ነው ለጥቃት የተዳረጉት ብለዋል።

አጣዬ ላይ ' #ወረራ ' መፈፀሙን ገልጸው " ሰውም አልቋል፤ ሚሊሻውም የሚችለውን ያህል ሞከረ አለቀ " ብለዋል።

ይህን የሚፈፅሙት ከአጎራባች  " #ሸኔ በሏቸው " ሲሉ የጠሯቸውን የታጠቁ ኃይሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

" ዋናው መፍትሄ መንግሥት ጠንከር ብሎ #እርምጃ መውሰድ ያለበት ላይ እርምጃ መውሰድ ፤ ይሄ ነበረ መፍትሄው  አሁን ባለው መንገድ ፣ #በእሹሩሩ ሰውም አለቀ " ብለዋል።

#የአጣዬ_ህዝብ የገዛ ከተማው ላይ እንዳለ መአት እንደወረደበት የገለጹት ከንቲባው " እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው፤ መንግስት ቢደርስልን ጥሩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ከኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በኩል ለጥፋቱ ለችገሩ " የፋኖ ታጣቂዎችን " ተጠያቂ ሲያደርጉ ከሰሜን ሸዋ ዞን በኩል ደግሞ " ሸኔን (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) " ተጠያቂ ያደርጋሉ።

NB. ባለፉት አምስት ዓመታት አጣዬ ከ10 ጊዜ በላይ የመቃጠል አደጋ አስተናግዳለች።

እስካሁን የአማራ ክልል መንግሥት ስለ ጉዳዩ ያለው ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ #ባለቤትነቱ የቪ.ኦ.ኤ. ራድዮ (ጋዜጠኛ መስፍን አራጌ) መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አንዲት እናት ሁለት ራስ ቅል ያለው ልጅ በሰላም ተገላግላለች።

የአምስት ልጆች እናት የሆነችው ወላዷ ከአንገቱ በታች በኩል የተያያዘ ሁለት ራስ ያለው ሆኖ የተወለደው ሕፃን ስድስተኛ ልጇ መሆኑ ተነግሯል።

እናት እንዲህ ዓይነት ክስተት መኖሩን ሳታውቅ ቆይታ ለህክምና ከመጣች በኋላ ያወቀች ሲሆን፤ በሆስፒታሉ ሃኪሞች እርዳታ በመለስተኛ ቀዶ ሕክምና ነው የተገላገለችው።

በትክክለኛ የእርግዝና ወራት ቆይታ የተወለደው ባለ ሁለት ራስ ሕጻን አራት ነጥብ ሁለት ኪሎ ግራም ይመዝናል።

የሆስፒታሉ የህፃናት ህክምና ክፍል ፤ የተወለደው ህጻን አሁን ላይ ጤንነት ችግር ባይኖርበትም ወደፊት አፈጣጠሩ እክል ሊፈጥርበት እንደሚችል አመላካች ነገሮች መኖራቸውን ገልጿል።

ተጨማሪ ምርመራዎች በማስፈለጋቸው የሐኪሞች ቡድን ምርመራና ክትትል እያደረገ ነው ተብሏል።

ክስተቱ በሆስፒታሉ ታሪክ የመጀመሪያ ሲሆን እንደ ህክምና መረጃዎች ደግሞ ከሚወለዱ ከአንድ መቶ ሺህ ህፃናት መካከል አንድ መሰል ክስተት ሊገጥም እንደሚችል ኢዜአ ዘግቧል።

Via https://t.iss.one/thiqahEth

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ገንዘቡን ካልመለሱ ማንነታቸውን ለፖሊስ እናሳውቃለን - ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ከ " ቢቢሲ ኒውስ ዴይ " ጋር በነበራቸው ቆይታ ባንኩ የሲስተም ብልሽት ባጋጠመው ወቅት የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ደንበኞች እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ድረስ ገንዘቡን ካልመለሱ ማንነታቸውን ለፖሊስ እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል። " በዲጂታል ነው ዝውውር የፈጸሙት። ደንበኞቻችን…
#Update

" ቅዳሜ የመጨረሻው ገንዘቡን የመመለሻ ቀን ነው " - ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ወይም ወደተለያየ ሂሳቦች ያስተላለፉ ግለሰቦች እስከ መጪው ቅዳሜ መጋቢት 14 ድረስ በፈቃዳቸው እንዲመልሱ አሳስቧል።

ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነውም ብሏል።

በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተጠቅመው አላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ተመላሽ የማያደርጉ ግለሰቦች ላይ ደረጃ በደረጃና ጠንከር ያሉ እርምጃዎች ለመውሰድ ዝግጅት መደረጉን ገልጿል።

1ኛ. ከሕግ አካላት ጋር በመተባበር የግለሰቦችን ሥም ዝርዝር በየቅርንጫፎች እና እንደሁኔታው ግለሰቦቹ ሊታወቁ በሚችሉበት ኣካባቢ ይፋ በማድረግ ቀጣይ ሕጋዊ እርምጃዎችን እንዲቀጥሉ፤

2ኛ. ከዚህ በላይ በተጠቀሰው እርምጃ መሰረት ኣሁንም ቀርበው የማይመልሱ ከሆነ በሕጋዊ ሂደቱ ተገቢው ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በድርጊቱ የተጠረጠሩትን ግለሰቦች #ፎቶግራፋቸውን እና ዝርዝር ማንነታቸውን የሚገልፁ መረጃዎች ባንኩ በመረጠው የብዙሀን መገናኛ መንገድ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ፤

3ኛ. ከፍትህ አካላት እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ተገቢውን የወንጀል፣ የፍትሐ ብሔርና አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ እንደሚያደግ አሳውቋል።

" አሶሼትድ ፕሬስ " ባንኩ አርብ መጋቢት 6 ለሊት የሲስተም ችግር በገጠመው ወቅት የተወሰደበት ገንዘብ 2.4 ቢሊዮን ብር (40 ሚሊዮን ዶላር) መሆኑን ዘግቧል።

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ግን ፤ " የኦዲት ምርመራው ባለመጠናቀቁ የተወሰደውን ገንዘብ መጠን አሁን ላይ አይታወቀም " ብለዋል።

አጠቃላይ ኦዲት ተደርጎ ስላላቀም እስካሁን ምን ያህል እንደተመለሰ የሚታወቅ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አጋፋሪ - ምዕራፍ 2 በዲኤስቲቪ አቦል ዱካ ቻናል 466

በጉማ የፊልም ሽልማት ፕሮግራም ላይ በምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ ዋና የወንድ ተዋናይ በመሆን አለማየሁ ታደሰ ያሽነፈበት በይዘቱ ለየት ያለ ተከታታይ ድራማ … አጋፋሪ ሁለተኛው ምዕራፍ … በዲኤስቲቪ!

አጋፋሪ ምዕራፍ አንድን በETV መዝናኛ ተከታትላችሁ ተደሰታችሁ አሁን ደግሞ ሁለተኛውን ምዕራፍ በዲኤስቲቪ አቦል ዱካ ቻናል 466 በ290 ብር ብቻ እየተከታተሉ ዘና ይበሉ!

ዘወትር ሐሙስ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በዲኤስቲቪ አቦል ዱካ ቻናል 466

ዲኤስቲቪ-ሁሉም ያለው እኛ ጋር ነው!

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #አቦልቲቪ #DStvSelfService #Agafari #StepUp
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ

እንኳን ደስ አላችሁ!

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “መልዕክቱን ያጋሩ፣ ከ1ሺህ ብር ጀምሮ ተሸላሚ ይሁኑ!” https://t.iss.one/global_bank_referral_bot?start=476862805 በሚል መሪ ቃል በቴሌግራም ቻናላችን ባካሄድነው የይጋብዙ ይሸለሙ መርሃ- ግብር ላይ ከ17 በላይ የቻናላችን ተከታዮች ባስቀመጥነው ሕግጋቶች መሠረት አሸናፊ ሆነዋል፡፡

የመጀመሪያውን ዙር ተሸላሚ ተከታዮቻችንን እያመሰገንን በቀጣይም በሁለተኛ ዙር ላይ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ከ1ሺ ብር ጀምሮ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ይቀበሉ፡፡

እናመሰግናለን!

#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #GBE #winnerslist
#እንድታውቁት

የጉምሩክ ኮሚሽን ተሽከርካሪ ሳይጨምር ከመጋቢት 22 /2015 ዓ/ም በፊት የባንክ ፈቃድ የተሰጣቸውንና ግዥ የተፈፀመባቸው እቃዎች እና በፍራንኮቫሉት ፈቃድ ያገኙ ድርጅቶችን መረጃ ሊሰበስብ ነው።

በዚህም ሁሉም አስመጪዎች እና የጉምሩክ አስተላላፊዎች ፦
-  የአስመጪውን ስም
- የባንክ ፈቃድ ቁጥር
- የእቃው አይነት እና ብዛት
- የማስጫኛ ሰነድ ቁጥር
- ግዥ የተፈፀመበት ኢንቮይስ ቁጥር
- ዲክላሬሽን ቁጥር እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በመያዝ እስከ መጋቢት 18/2016 ዓ/ም ድረስ በጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የታሪፍ ምደባና ስሪት ሀገር አወሳሰን ዳይሬክቶሪት ቀርበው እንዲሰጡ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

@tikvahethiopia