TIKVAH-ETHIOPIA
#ቲክቶክ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት " ቲክቶክ " የተሰኘውን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ሊያግድ የሚችል አዋጅ አጸደቀ። አዋጁ የቻይናው #ባይትዳንስ_ኩባንያ ንብረት የሆነው " ቲክቶክ " በስድስት (6) ወራት ውስጥ አክሲዮኖችን #ለአሜሪካውያን ካልሸጠ በመላው አሜሪካ ይታገዳል ብሏል። ይህ አዋጅ በሴኔቱ ጸድቆ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ካልተፈረመበት ህግ ሆኖ ተፈጻሚ አይሆንም ተብሏል። ፕሬዝዳንት…
#ቲክቶክ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዓለም ላይ ትልቅ ተፅእኖ የፈጠረው በቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ የሚተዳደረው " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ በአሉታዊም ይሁን አውንታዊ መንገድ ስሙ ይነሳል።
በቻይና ያለው የቲክቶክ ይዘት እና በተቀረው ዓለም ያለው ልዩነት አለው የሚሉም ብዙ ናቸው።
አንዳንድ ሀገራት ልጆች እና ወጣቶችን ከአጉል ባህል ለመጠበቅ በሚል በሙሉ ሲያግዱት ፣ አንዳንዶች ደግሞ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ከመንግሥት ቁሳቁሶች ፣ ከመ/ቤቶች አግደዋል።
ለመሆኑ ቲክቶክ በቻይና እና በተቀረው ዓለም ይለያያል ?
ትሪስታን ሃሪስ ፤ የቀድሞው የጉግል ሰራተኛ እና ለማህበራዊ ሚዲያ ስነምግባር ተሟጋች ሲሆኑ ፤ በቻይና ያለው የቲክቶክ ይዘት እና በተቀረው ዓለም ያለው ይዘት ልዩነት አለው ባይ ናቸው።
ዶዪን የቻይናው ቲክቶክ ልጆችን / ትውልድ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።
" የመተግበሪያው ባለቤቶች ቴክኖሎጅ በልጆች እድገት ላይ ያለው ተጽዕኖ በደንብ አድርገው የተገነዘቡ ናቸው " የሚሉት እኚሁ የማህበራዊ ሚዲያ ስነምግባር ተሟጋች ፤ " በቲክቶክ የሀገር ውስጥ (ቻይና) ስሪታቸው ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ፦
* በቤት ውስጥ ሊያደርጓቸው የሚችሏቸው የሳይንስ ሙከራዎችን፣
* የሳይንስ እና ሌሉች ሙዚየም ኤግዚቢቶችን
* የሀገር ፍቅር ቪዲዮዎችን፣
* ትምህርታዊ የሆኑ ቪዲዮዎችን ያሳያሉ " ብለዋል።
እንዲህም ሆኖ እራሱ በሀገሪቱ ያሉት ታዳጊዎች / ልጆች በቀን ውስጥ በቲክቶክ ላይ የሚያጠፉት ሰዓታቸው የተገደበ መሆኑንም አንስተዋል።
በዩኤስ እና ቻይና በታዳጊዎች ላይ አንድ የተደረገ ጥናት እንደነበር የሚያነሱት ተሟጋቹ ይኸውም " ወደፊት የምትፈልጉት የምኞት ስራ ምንድን ነው ? " የሚል እንደሆነ በዚህም ውጤቱ ፦
- በዩኤስ ውስጥ ቁጥር 1 የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ፤
- በቻይና ደግሞ ቁጥር 1 #የጠፈር_ተመራማሪ የሚል እንደነበር ገልጸዋል።
ከዚህ ወራት በፊት የቲክቶክ ዋናው ስራ አፈፃሚ በአሜሪካ ኮንግረስ ቀርበ ጠንካራ ጥያቄ በቀረበባቸው ወቅት አንዱ የተነሳው ፤ በቻይና ያለው ቲክቶክ ለልጆች የሚያስተዋውቀው ፦
° ሳይንስ
° የሒሳብ / ሌሎች የትምህርት ቪድዮዎችን ነው ፤ የሚያዩበት / የሚቆዩበት ሰዓትም ገደብ አለው ዩኤስ ውስጥ ግን የሚገፉት ቪድዮዎች ልጆች ራሳቸውን እንዲጎዱ የሚያደርግ ነው ይህ ለምን ? የሚል ነበር።
ቲክቶክ ሱስ የማስያዝ አሰራር እንዳለው የሚያነሱ ሌሎች ባለሞያዎች የሰዎችን ስሜት በማንበበ ረጅም ጊዜ እዛ ላይ እንዲያሳልፉ ያደርጋል ባይ ናቸው።
ለታዳጊዎ/ልጆች ተብሎ የተለየ ስሪት ስለሌለው ይተቹታል።
በቲክቶክ ላይ የመቆያ ጊዜ እንደ #ፍላጎት እና ያልተገደበ መሆኑም በተለይ ለወላጆች ፈተና እንደሆነ ያነሳሉ።
ምንም እንኳን በተለይ #አሜሪካውያኑ እያደረሰ ነው የሚሉት የማህበራዊ ተፅዕኖው እንዳለ ሆኖ ከደህንነትና ከቻይና ጋር ባላቸው ሁኔታ እንዲታገድ ወይም ድርሻ #እንዲሸጥላቸው በይበልጥ ቢፈልጉም በርካቶች በትውልድ ላይ ቀውስ እየፈጠረ ነው ፣ ቁጥጥርም የለው በሚል እንዲታገድ / የይዘት ቁጥጥር እንዲደረግበት ይፈልጋሉ።
ከዚህ በተቃራኒው ቲክቶክ በዩኤስ ሆነ በሌላው ዓለም የበርካታ ወጣቶችን ህይወት በገንዘብ ቀይሯል።
በርካቶችን ለብዙሃን አስተዋውቋል። ብዙ ገንዘብ እንዲሰሩም አድርጓል። አልጎሪዝሙ በትንሽ ድካምና ስራ ሚሊዮኖች ጋር ማድረስ መቻሉ ሰዎች በአንድ ሌሊት ብቻ የዝና ማማ ላይ ቁጭ እንዲሉ አድርጓል።
ከደህንነት ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ሰፊ ጉዳዮች አስተዳዳሪዎቹ የተጠቃሚዎችን ምንም መረጃ ለቻይና መንግሥት አሳልፈው እንደማይሰጡ ደጋግመው ተናግረዋል። ሌሎች ወቀሳዎችንም አጥብቀው ይሞግታሉ።
@tikvahethiopia

#DStvEthiopia
ደማቁ የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎች ቀጥለዋል💥
🔥 ወደ ግማሽ ፍፃሜ ሚደርሱትን ቡድኖች ይገምቱ!
🔥 የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች ይከታተሉ!
👉ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22 ደንበኝነትዎን ሲያሳድጉ... እኛም ቀጣዩን ለአንድ ወር እንጋብዝዎታለን!
ለሚሰጡን አስተያየት በቅድሚያ እያመሰገንን፣ ስለ አገልግሎታችን ጥራት የሚደርስዎትን የፅሁፍ መልዕክት ሊንኩን በመጫን መጠይቁን እንዲሞሉ በትህትና እንጠይቃለን።
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2
#FACupAllOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET

“ ከ4,000 በላይ ሴቶች ተደፍረዋል ” - የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር የኢትዮጵያ ሴቶች ማኀበር ሴቶች ላይ እየደረሱ ናቸው የተባሉ ፈርጀ ብዙ ችግሮችን በተመለከተ በየክልሉ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን በመጋበዝ ትላንት ረቡዕ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። በዚህም ላይ ከተገኙት ባለድርሻ አካላት መካከል የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር አንዱ ነው። በአማራ ክልል በ “ፋኖ”…
#Amhara
“ ' 4 ሺህ ሴቶች ተደፍረዋል ' በሚል ያልተረጋገጠ ሀሳብ አንስተዋል ” - ወ/ሮ ሁሉአየሽ አወቀ
የኢትዮጵያ ሴቶች ማኀበር ፤ ሴቶች ላይ እየደረሱ ናቸው የተባሉ ፈርጀ ብዙ ችግሮችን በተመለከተ በየክልሉ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን በመጋበዝ ባለፈው የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ እንደነበርና ቲክቫህ ኢትዮጵያም መረጃ ማጋራቱ ይታወሳል።
በወቅቱ የአማራ ሴቶች ማኀበርን የወከሉት ወ/ሮ በላይነሽ ሽባባው ስለሴቶች በአማራ ክልል ያለውን ሁኔታ ለተሳታፊዎችና ኃላፊዎች ገለጻ ሲያደርጉ፣ “ አማራ ክልል ራሱ የበፊቱን እንኳን ትተነው አሁን በሚስተዋለው ግጭት ብቻ ከ4,000 በላይ ሴቶች #ተደፍረዋል ” ሲሉ ገልጻ አድርገው ነበር።
ይህንንም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዘግቦት እንደነበር ይታወሳል።
ሆኖም የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ሁሉአየሽ አወቀ፣ ዘገባው ከተሰራ በኋላ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ የወ/ሮ በላይነሽን ገለጻ መሠረት በማድረግ የተዘገበውን ዜና ጠቅሰው፣ “ የእናንተ ስህተት አይደለም በእርግጥ የልጆቷ ስህተት ነው ” ብለው ዘገባው #ማስተካከያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል።
ወ/ሮ በላይነሽ በስብሰባው ላይ ያደረጉት ገለጻ የድምጽ ቅጅ እንደገና ሲረጋገጥ፣ “ 4 ሺህ ሴቶች ተደፍረዋል ” የሚል ሆኖ እያለ፣ መረጃውን የት እንዳገኙት እንዲገልጹ የአማራ ሴቶች ማኀበር ሲጠይቃቸው፣ “ ‘4 ሺህ የተባለው እንደ ኢትዮጵያ የቀረበ እንጂ እኔ አላልኩም፣ 400 ነው ያልኩት " ሲሉ ለመካድ እንደሞከሩ ያስረዱት ም/ዳይሬክተሯ፣ “ 400 ከየት አመጣሽ ? ሲባል ‘ከሴቶች ሕጻናት ጉዳይ ቢሮ ሲባል ሰምቼ ነው’ የሚል ሀሳብ ነው ያመጣች ግን 400ም የእኛ መረጃ አይደለም ” ብለዋል።
አክለው “ የ6 ወራት ሪፓርታችንም ‘ፆታዊ ጥቃት ደረሰብን’ ብለው ተቋማችን ድረስ የመጡ 4 ሴቶች ናቸው። እነዚያን ሴቶችም ሁለቱን ሰጥተናል። ሁለቱን ከፓሊስ ጋ ሁነን ገና በሂደት ላይ ያለ ጉዳይ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ አንድ ሰው ከአንድ ተቋም ሲላክ ታምኖበት፣ ዘርፉን ያውቀዋል ተብሎ ነውና የሚላከው ባለሙያዋ የተናገረችው ስህተት መሆኑን እንዴት ነው የምታረጋግጡልኝ ? የሚል ጥያቄ ለም/ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሁሉአየሽ አቅርቧል።
“ እውነት የምነግርህ እኔ ምክትል ዳይሬክተር ነኝ ፤ ልጅቷ ፕላንድ የሚባል ፕሮጀክት አለ የእርሱ አስተባባሪ ነች ” ያሉት ም/ ዳይሬክተሯ፣ “ ዙሮ ዙሮ ግን እርግጠኛ ሆኘ የምነግርህ ክልሉ ያለበት ሁኔታ ይታወቃል። ቁጥሩ ከዚህ በላይ ሊሆንም ይችላል፣ ሊያንስም ይችላል፣ ስትሰበስበው ነው የምታገኘው ” ሲሉ አስረድተዋል።
ተቋማቸው መልዕክቱን በሰነድ መልኩ እንዲልክ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጠይቀው ምክትል ዳይሬኮተሯ ፈርመው የላኩት ደብዳቤ ፦
- " ወ/ሮ በላይነሽ ሽባባው ' በክልሉ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት 4,000 ሴቶች ተደፍረዋል ' የሚል ያልተረጋገጠ ሀሳብ አንስተዋል " ይላል።
- ክልሉ በዚህ ወቅት በግጭት ላይ በመሆኑ በሴቶች ላይ የተለያዩ ጥቃቶች እንደሚፈጸሙ ቢገመትም ተቋሙ ግን ታች ድረስ ወርዶ መረጃ ለመሰብሰብ ባለው ግጭት ምክንያት ምቹ ሁኔታ ስለሌለና ኢንተርኔት በመዘጋቱ ምክንያት መረጃዎችን ሰብስቦ ማረጋገጥ እንዳልተቻለ ይገልጻል።
* የተባለው መረጃው በተቋሙ ውስጥ እንደሌለ፤ ምቹ ሁኔታን ሲገኝ ታች ወርዶ ያረጋገጥነውን መረጃ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደሚያሳውቅ ያመለክታል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያደረጉት ገለጻ ስህተት እንደሆነ የተነገረላቸው ወ/ሮ በላይነሽን በድጋሚ ማብራሪያ እንዲሰጡ ያደረገው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።
#AATikvahFamily

" ዳሽን ባንክ ላይ የሲስተም ችግር አጋጥሟል " የሚለው መረጃ ሐሰተኛ ነው ሲል ባንኩ ገለጸ።
ትላንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጋጥሞኛል ባለው ሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው አገልግሎቱ ዳግም መስተካከሉ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ዳሽን ባንክም ተመሳሳይ አይነት የሲስተም ችግር ማለትም ሰዎች፦
- ያለገደብ ገንዘብ ከኤቲኤም የማውጣት
- በሞባይል ባንኪንግ ገደብ የሌለው ገንዘብ የማስተላለፍ ችግሮች ገጥሞታል በሚል እየተሳራጨ ይገኛል።
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይም ሰዎች ወደ ዳሽን ኤቲኤሞች በመሄድ ያለ ገደብ ገንዘብ ማውጣት እንደሚችሉ የሚገልጹ መልዕክቶች እየተዘዋወሩ ነው።
ባንኩ ግን " ይህ ፍፁም #ሐሰተኛ መረጃ ነው " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።
የባንኩ ኤትኤሞች እና የዲጂታል አውታሮች ሁሉ ደህንነታቸው በአስተማማኝ ሁኔታ የተጠበቀ እንደሆነ ገልጾ ደንበኞቹ ምንም አይነት ስጋት ላይ እንዳይወድቁ አስገንዝቧል።

#እንድታውቁት ነገ በአዲስ አበባ ፤ መስቀል አደባባይ ከሰዓት በሗላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የፀሎት መርሐ-ግብር እንደሚያከናወን ተገልጿል፡፡ ይህን መርሐ-ግብር ተከትሎ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል። በዚህም ፡- ➡ ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች…
#Update
ዛሬ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመስቀል አደባባይ ያዘጋጀው ፦
- የንስሀ ፤
- የምልጃ
- የምስጋና በዓል መርሐ-ግብር መካሄድ ጀምሯል።
ለዚሁ መንፈሳዊ መርሐ-ግብር እጅግ ከፍተኛ ምዕመን በመስቀል አደባባይ መሰባሰቡን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከስፍራው ያገኘው መረጃ ያሳያል።
መርሐ-ግብሩ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (etv) ፣ በአዲስ ቴሌቪዥን ፣ በፋና ቴሌቪዥን ፣ በኤልሻዳይ ቴሌቪዥን ፣ በEvangelical Media የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በቀጥታ እየተላለፈ ይገኛል።
Video Credit - Generation Eng.
Photo Credit - Evangelical TV

#Update ዛሬ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመስቀል አደባባይ ያዘጋጀው ፦ - የንስሀ ፤ - የምልጃ - የምስጋና በዓል መርሐ-ግብር መካሄድ ጀምሯል። ለዚሁ መንፈሳዊ መርሐ-ግብር እጅግ ከፍተኛ ምዕመን በመስቀል አደባባይ መሰባሰቡን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከስፍራው ያገኘው መረጃ ያሳያል። መርሐ-ግብሩ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (etv) ፣ በአዲስ ቴሌቪዥን ፣ በፋና ቴሌቪዥን ፣ በኤልሻዳይ…
#Update
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው መርሃግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
በንግግራቸው ፤ " የወንጌል አማኞች በዚህ ምድር አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከ125 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ቢሆንም ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ጌታን በጋራ ለማምለክ ስለቻልን፤ የእግዚአብሔርን ፊት በንስሃ፣ በምልጃና በምስጋና እንድንፈልግ ስለረዳን ክብር ሁሉ ለእርሱ ይሁን " ብለዋል።
የካውንስሉ ፕሬዜዳንት ፤ " የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ፦
* ልዩነታችንን ፈተን፤
* አለመግባባታችንን አስተካክለን ፤
* ወደኃላ በማይመለስ መልኩ ሁሉን ነገር #በእርቅ ጨርሰን በአንድ ልብና መንፈስ በምድሪቱ ወንጌል እንዲሰራጭ ነፍሳት እንዲድኑ የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲሰፋ የመራንና የደገፈንን እንዲሁም ዛሬ የወንጌል አማኞች ይህን ፕሮግራም በሙሉነት እንድናዘጋጅ የፈቀደ የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም ከፍ ይበል " ሲሉ ተናግረዋል።
" ለዘመናት በገዛ ሀገራችን እውቅና ተነፍገን ፦
- ስንገደል
- ስንታሰር
- ሞተን እንዳንቀበር ተከልክለን የኖርነውንና እንደ ተራ ማህበር ስንቆጠር ከነበረበት አሰራር የላቀን የወንጌል አማኞችን በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአዋጅ እውቅና እንዲሰጥ ያደረገውን አምላካችንን እናመሰግናለን " ሲሉም ተደምጠዋል።
ካውንስሉ እንዲፀድቅ ለፈቀደው መንግሥትም በምእመኑ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
የካውንስሉ ፕሬዜዳንት ፤ " የዛሬው ፕሮግራም ዋና ዓላማ ፦
1ኛ. እግዚአብሔርን ባለመታዘዛችን ቃሉንም ባለማክበራችንና ባለመተግበራችን የተነሳ ጉስቁልናችን ከልክ በላይ መሆኑና ሁሉንም ዓይነት ሃጢያቶች እየተለማመድን በረከት ስለማይጠበቅ " እግዚአብሔር መልሰን እኛም እንመለሳለን ፤ ዘመናችንን እንደቀድሞው አድስ " በማለት ከልባችን ንስሃ ለመግባት ነው።
2ኛ. ለሀገራችን #ኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍንና እንዲዘልቅ የእግዚአብሔር መንግሥት ይበልጥ እንዲሰፋ ፣ ለሀገራችን ልማት የበኩላችንን አስተዋጽኦ እንድናደርግ ጌታ እንዲረዳን የምንማልድበት ነው።
3ኛ. ትንፋሻችንን እና መንገዳችንን የያዘውን አምላካችንን በሁሉም መልኩ ማመስገን ፤ ስለ ሀገራችን፣ ስለ ቤተክርስቲያናችን፣ ስለ እያንዳንዳችን ፣ ስለ ሁላችን እግዚአብሔርን ማመስገን ነው " ብለዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ዛሬ በመስቀል እየተካሄደ ባለው መርሐግብር ሁሉም ወገኖች ፦
° ለጸሎት
° ለምልጃ
° ለሰላም
° ለምክክር
° ለውይይት በቂ ጊዜና ቦታ እንዲሁም ቅድሚያ እንዲሰጡ በይፋ ጥሪ አቅርቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ