TIKVAH-ETHIOPIA
#ለጥንቃቄ " በፎሬክስ ትሬዲንግ የኦንላይን ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን " የሚል የፌስቡክና የቴሌግራም ማስታወቂያ በሚያስነግሩ የተደራጁ ቡድኖች መጭበርበራቸውን ተበዳዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። እነዚህ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገጾች ስያሜአቸው ከፎሬክስ ትሬዲንግ ጋር የተያያዘ ሲሆን " ትሬድ እናደርጋለን ትርፋማ ትሆናላችሁ " የሚል ቃል በመግባት ከሰዎች ገንዘብ እያስላኩ የማጭበርበር ስራ…
#በድጋሜ⚠️
ውድ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ አድርጉ።
በሀገራችን ያለውን ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ጫናን ለመቋቋምና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ብዙ ሳይደክሙ በርካታ ገንዘብ ለማግኘት በሚደረግ ጥረት በርካታ የሀገራችን ልጆች ደክመው በላባቸው ያገኙትን ፤ ከቤተሰብም ለስራ በሚል የተቀበሉትን ብር በኦንላይን አጭበርባሪ ዘራፊዎች በየዕለቱ እየተበሉ ይገኛል።
ከዚህ ቀደም መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በኦንላይን ከሚደረጉ የማጭበርበር ስራዎች እራሳችሁን እንድትጠብቁ የአደራ ማሳሰቢያ መላክችን ይታወሳል።
አሁንም ሰዎች በመቶ ሺህ የሚቆጠር ብራቸውን እየተበሉ ይገኛል።
እባካችሁን በ " ዋትአፕም " ይሁን በ " ቴሌግራም " አድራሻችሁን አግኝተው የሚያናግሯችሁን የማታውቋቸውን ሰዎች መልዕክት አትመልሱ።
" በተለያየ ኦንላይን ስራ ፣ በፎሬክስ ትሬዲንግ እና በሌሎችም በትንሽ እና በማያደክም ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን ፤ ይሄን ይሄን ስራ ስሩ በዚህ አካውንት ገንዘብ አስገቡና እኛም መልሰን ትርፉን እናስገባለን " የሚሉ አጭበርባሪዎች ተንሰራፍተዋልና ተጠንቀቁ።
በነገው ዕለት ከዚህ ጋር በተያያዘ ስላጋጠመ ክስተት እናጋራችኃል። ለአሁኑ ግን ምናልባት " ይሄን ስራ ስሩና ትርፋማ ትሆናላችሁ ፤ ገንዘብ ላኩና ትርፉን እንልካለን " በሚል እያባበሉ ገንዘብ እድትልኩ የሚጠይቋችሁን ሰዎች ከማናገር ተቆጠቡ፤ ምንም ገንዘብም አትላኩላቸው።
@tikvahethiopia

ግሎባል ባንክ
መልዕክቱን ያጋሩ፣ ከ1ሺህ ብር ጀምሮ ተሸላሚ ይሁኑ!
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል
1. በመጀመሪያ ቀጣዩን የቦት ሊንክ ይጫኑ፡- https://t.iss.one/global_bank_referral_bot?start=476862805
2. START የሚለውን ይጫኑ፣
3. JOIN CHANNEL የሚለውን ይጫኑ፣
4. ወደ መጀመሪያው ቦት ይመለሱ፣
5. CONTINUE የሚለውን ሲጫኑ የመጋበዣ ሊንክዎን ያገኛሉ፣
6. መልዕክቱን ቢያንስ ለ50 እና ከዚያ በላይ ወዳጅ ዘመድዎ ሼር ሲያደርጉ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በየሳምንቱ ከአንድ ሺ ብር ጀምሮ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ያበረክታል፡፡
ሽልማቱ በየሳምንቱ ለተሸላሚዎች ይደርሳል፡፡
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ናቸው፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን

" ጥሪ መቀበያው ከእውቅናችን ውጭ ለ7 ወር ተቋርጦ ነበር " - የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም
የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ህዝቡ የሚደርስንበትን አስተዳደራዊ በደል የሚያሳውቅበት ነጻ የስልክ ጥሪ መቀበያ 7502 ከእውቅና ውጪ ለባለፉት 7 ወራት ተቋርጦ እንደነበር ገለጸ።
ተቋሙ አገልግሎቱ በመቋረጡ ለተፈጠረው እንግልት ይቅርታ ቢጠይቅም እንዴት ? በምን ? ለምን ? ከእውቅና ውጭ አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ተደርጎ እንደነበር ያለው ነገር የለም።
በአሁን ሰአት 7502ን ጠግኖ በድጋሚ ማሰራት ባለመቻሉ የነጻ ስልክ ጥሪ መስመሩን ለመቀየር መገደዱን አሳውቋል።
በዚህ መሰረት ማንኛውም ዜጋ በመንግስት አስፈጻሚ አካላት እና በግል ተቋማት በተለይ በሽርክና በተቋቋሙ የግል ተቋማት የሚደርሱ #የአስተዳደር_በደል እንዲሁም ከመልካም አስተዳደር ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን በነጻ የስልክ ጥሪ 9503 ማቅረብ ይችላል ብሏል።

#በድጋሜ⚠️ ውድ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ አድርጉ። በሀገራችን ያለውን ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ጫናን ለመቋቋምና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ብዙ ሳይደክሙ በርካታ ገንዘብ ለማግኘት በሚደረግ ጥረት በርካታ የሀገራችን ልጆች ደክመው በላባቸው ያገኙትን ፤ ከቤተሰብም ለስራ በሚል የተቀበሉትን ብር በኦንላይን አጭበርባሪ ዘራፊዎች በየዕለቱ እየተበሉ ይገኛል። ከዚህ ቀደም መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ…
ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ ትላንትና ምሽት ከላክንላችሁ የድጋሜ የጥንቃቄ መልዕክት በኃላ በርካታ ሰዎች በኦንላይን የማጭበርበር ስራ ገንዘባቸው ተዘርፎ የውሃ ሽታ መሆኑን አመልክተዋል።
ለአብነት ከ150 ሺህ ብር እስከ 300 ሺህ ብር ከዚህም ከፍ ሲል እስከ 470 ሺህ ብር በቀናት ውስጥ የተጭበረበሩ ሰዎችን መልዕክት ተቀብለናል።
አጭበርባሪዎቹ ፦
* " የኦንላይን ስራ እናሰራችኋለን፣ "
* " የፎሬክስ ትሬዲንግ ስራ እናሰራለን "
* " በትንሽ ብር ኢንቨስት በማድረግ ያለ ብዙ ድካም ትርፋማ ትሆናላችሁ "
* " ይሄን ያህል ገንዘብ ላኩና ስራ ሰርታችሁ የከፈላችሁትን በእጥፍ አግኙ " በማለት በተደራጀ መልኩ በዋትሳፕና በቴሌግራም የማጭበርበር ስራ የሚሰሩና የበርካቶችን ገዘንብ እየዘረፉ በመሆኑ በድጋሜ ከየትኛውም የማታውቁት ሰው " ስራ እናሰራችሁ " በሚል የሚመጣላችሁን የዋትስአፕና ቴሌግራም መልዕክት አትመልሱ።
ሰዎች እንዴት እየተጭበረቡ እንደሆነ በቀጣይ ይናቀርባለን።

#Hawassa በፀጋ በላቸው ላይ የጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰው ኮንስታብል የኋላመብራት ወልደማርያም በ16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል። የህግ አማካሪና ጠበቃ እንዲሁም በፆታዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩት አበባየሁ ጌታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ውሳኔው የከተማውን ገፅታ የሚያበላሽ እንደሆነ ስለታሰበ ነው መፍትሄ ያገኘው ብለዋል። አበባየሁ ጌታ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው…
" ፍርዱ ለሚዲያ 16 ዓመት ከተባለ በኃላ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ ሰምቻለሁ " - ጸጋ በላቸው
" ጉዳዩ ለቢሮዉም ሆነ ለኔ አዲስ ነው " - ወ/ሮ ወይንሸት ብርሀኑ
በሀዋሳ ከተማ የዳሽን ባንክ ሰራተኛ ከሆነችዉ ጸጋ በላቸዉ ጋር በተያያዘ በጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ የነበረው ኮንስታብል የኃላመብራት ወ/ማርያም " ለብዙዎች አስተማሪ ይሆናል " በተባለ መልኩ የ16 አመት ጽኑ እስራት እንደተፈረደበት ይታወሳል።
ይሁንና ይህ ለሚዲያ የተገለጸው ፍትህ ከተበዳዩዋ እውቅና ውጭ በሆነ መልኩ የእስራት ፍርዱ ከ16 አመት ወደ 10 መቀነሱን እንደሰማች በሶሻል ሚዲያ ባስተላለፈችዉ በዕንባ የታጀበ ቅሬታ ገልጻለች።
ወይዘሪት ጸጋ ፤ ጉዳዩን ለማወቅ ብዙ ድካም እንደነበረዉና በመጨረሻ የሰማችዉ ጉዳይ እጅግ እንዳሳዘናት በመግለጽ አቤቱታዋን አሰምታለች።
ጸጋ ፤ " የፍርድ ሂደቱ በጥሩ ሂደት ሄዶ ፍርድ ቤት 16 ዓመት ተፈርዶበታል በሚል ለኔ ውሳኔ ሰጥቶኝ ነበር ፤ አሁን ግን እኔ በማላውቅበት ሁኔታ የፍርዱ ውሳኔ ይግባኝ ብሎ #እንደተስተካከለ ሰምቻለሁ፤ ይህ ውሳኔ መቼ እንደተላለፈ አልተነገረኝም ለግል ጉዳዬ የውሳኔ ወረቀት እንዲሰጠኝ በተደጋጋሚ ወደ ፍርድ ቤት በምደውልበት ጊዜ ምላሽ እየተሰጠኝ አልነበረም ጉዳዩን አጥብቄ በተደጋጋሚ ስጠይቅ ውሳኔው በይግባኝ እንደተስተካከለ ተነገረኝ " ስትል አስረድታለች።
ውሳኔው አሁን ላይ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ የገለፀችው ጸጋ ፤ በድርጊቱ እጅግ እንዳዘነችና ካሳለፈችው የስቃይ ሁኔታ ጋር በፍፁም እየሚገባ እንዳልሆነ በእምባ ታጅባ ገልጻለች።
ከዚህ ባለፈ ህዝብ የማያውቀው ብዙ ነገር እንደተፈፀመ ፤ ከጠለፋው እገታ ከተለቀቀች በኃላ በማታውቀው ምክንያት ታስራ እንደነበር አመልክታለች።
ፍርዱ ለሚዲያ 16 ዓመት ከተባለ በኃላ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ ገልጻ ፤ " ይህ አይነት ተግባር ለቀጣይ ምን እንደሚያስተላልፍ አላውቅም " ብላለች።
ውሳኔው ተግቢና ትክክል እንዳልሆነ ፤ በድብቅ ሊሆን እንደማይገባው፣ እንዲከላከሉም ሊደረጉ እንደሚገባ አስገንዝባለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረበላቸዉና የጸጋን ጉዳይ ሲከታተለዉ በነበረዉ የሀዋሳ ከተማ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ውስጥ የሴቶችና ህጻናት መብትና ደህንነት ማስጠበቅ ቡድን መሪ የሆኑት ወይዘሮ ወይንሸት ብርሀኑ ጉዳዩ ለቢሮዉም ሆነ ለእርሳቸዉ አዲስ መሆኑን ገልጸዋል።
ወይዘሮ ወይንሸት ፤ ጉዳዩን እንደሚከታተሉትና የተፈጠረዉን ጉዳይ እንደሚያጣሩ በመግለፅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃል ገብተዋል።
መረጃዉን አጠናቅሮ የላከዉ የሀዋሳዉ ቲኪቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነዉ።

Women aspiring entrepreneurs, this is your golden moment to realize your entrepreneurial dreams! Apply for the Jasiri Talent Investor Cohort 6 at https://jasiri.org/application to find your co-founder and build from scratch the business venture you've been dreaming of.
#Jasiri4Africa
#Jasiri4Africa
አስደሳች ዜና ከሳፋሪኮም!!!
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መልካም ዜና ይዞ ወደ እናንተ ቀርቧል! ሳምንታዊ ያልተገደበ ጥቅል በ350 ብር ብቻ በመግዛት ሳምንቱን በሙሉ ፈታ እንበል! በፈጣኑ የሳፋሪኮም ኢንተርኔት እንንበሽበሽ!
በM-PESA APP ተጠቅመው በ350 ብቻ በመግዛት ቀኑን እንደልብ ዘና ፈታ እያልን እናሳልፍ!
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ቀጥሎ በሚገኙት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።
Facebook: https://www.facebook.com/SafaricomET
Telegram: https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia
Twitter:
https://x.com/SafaricomET?t=y2XAHAhPNvFeZqXa2YE6aQ&s=08
Instagram: https://www.instagram.com/safaricomet?igsh=MWJtcjJrMzNhMzVsNg==
YouTube: https://youtube.com/@safaricomethiopia2751?si=w2o8uz61oHeZM9gm

#Update የቤቶች ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ተጠናቀቀ። የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ያስገነቧቸውና ለጨረታ ያቀረቧቸው 3,146 የመኖሪያና 306 የንግድ ባጠቃላይ 3,452 ቤቶች የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ በዛሬው ዕለት መጋቢት 02/2016 ዓም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት መጠናቀቁ ተገልጿል። ከጥር 27/2016 ዓ/ም ጀምሮ ሲከናወን የቆየው የሰነድ ሽያጭ…
ለጨረታ የቀረቡ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወርቁ ሰፈር ሳይት የሚገኙ ቤቶች ተሰረዙ።
የተሰረዙት ጠቅላላ በሳይቱ ለጨረታ የቀረቡ ቤቶች ናቸው።
የአ/አ/ዲ/ግንባታ ሥራዎች ቢሮ እና የአ/አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በመንግስት በጀት የተገነቡ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ በጨረታ አውጥቶ ነበር።
ይሁን እንጂ ለጨረታ ከወጡት ቤቶች ለልማት ተነሺዎች የተፈለጉ እንዳሉ ተመላክቷል።
በዚህም በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወርቁ ሰፈር ሳይት የሚገኙ ጠቅላላ ከጨረታ ተሰርዘዋል።
በዚህ ሳይት ብቻ የተወዳደሩም ከመጋቢት 9/7/2016 ጀምሮ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ ከፋይናንስ ክፍል сро መውስድ እንደሚችሉ ተነግሯል።

#UK
" ማንም ሰው ወደ #ሩዋንዳ ለመሄድ 3 ሺህ ፓውንድ ለማግኘት ብቻ ወደዚህ ለመምጣት የሚሞክር አይመስለኝም " - የገንዘብ ሚኒስትር ኬቨን ሆሊንራክ
ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በአገሯ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞችን እስከ 3 ሺህ ፓውንድ በመክፈል ወደ ሩዋንዳ ልትልክ መሆኑን እንዳስታወቀች ቢቢሲ ዘግቧል።
ይህ አዲስ የስደተኞች ዕቅድ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ያልተሳካላቸው ስደተኞች በበጎ ፈቃደኝነት ወደ አገራቸው እንዲመለሱና ለዚህም የሚሆን ገንዘብ ይሰጣቸዋል ተብሏል።
የጥገኝነት ጥያቄያቸው በዩናይትድ ኪንግደም ውድቅ ለተደረገባቸው ለማንኛውም ስደተኞች ክፍት ይሆናል ተብሏል።
ይህ ዕቅድ በተለይም ወደ አገራቸው መመለስ በማይችሉ ስደተኞች ላይ ያነጣጠረ ነው።
የዩናትድ ኪንግደም የገንዘብ ሚኒስትር ኬቨን ሆሊንራክ ምን አሉ ?
- ወደ ሩዋንዳ ለመሄድ ለተስማሙ ስደተኞች የሚከፈለው ክፍያ የህዝብን ገንዘብ በአግባቡ መጠቀም ይሆናል።
- እነዚህን ሰዎች ያለ ምንም ጥቅም እዚህ ማቆየት ከዚያ የበለጠ ገንዘብ ያስወጣናል።
- " እዚህ በህገወጥ መንገድ ከመጣችሁ በዚህች አገር መቆየት አትችሉም " የሚለውን መልዕክት ያስተላልፋል። መሰረታዊ ነጥብ ይህ ነው።
- ማንም ሰው ወደ ሩዋንዳ ለመሄድ 3 ሺህ ፓውንድ ለማግኘት ብቻ ወደዚህ ለመምጣት የሚሞክር አይመስለኝም።
የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት " በህገወጥ መንገድ ገብተዋል " የተባሉ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ተልከው ጥያቄያቸው ከዚያ የሚታይበትን የተለየ እቅድም ለመተግበር መንግሥት እየሞከረ ይገኛል ተብሏል።
ይህ እቅድ ከሩዋንዳ የደህንንት ስጋት ጋር በተገናኘ በፍርድ ቤቶች ታግዶ ነበር።
እነዚህን ሙግቶች ለማሸነፍ መንግሥት የምስራቅ አፍሪካዊቷን አገር አስተማማኝ አድርጎ የሚፈርጃት ‘የሩዋንዳ ሴፍቲ ቢል’ (የሩዋንዳ የደህንነት ረቂቅን) ለማጽደቅ እየሞከረ ይገኛል።
አዲሱ ዕቅድ ከዚህ ከነበረው የተለየ እንዲሁም በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ እና በፓርላማው በሚጸድቀው ረቂቅ ላይ የተመሰረተ አለመሆኑንም ቢቢሲ ዘግቧል።
መረጃው የቢቢሲ እና ታይምስ ሬድዮ ነው።

#HoPR
በእስር ላይ የሚገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብት ተነሳ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ ባለው ስብሳባ የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።
ዛሬ ያለ መከሰስ መብታቸው የተነሳው የተወካዮች ምክር ቤት አባል እና በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስቲያን ታደለ ከወራት በፊት ከቤታቸው ተወስደው መታሰራቸው የሚዘነጋ አይደለም።
እስሩ በአማራ ክልል በመንግሥት የፀጥታ ኃይል እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የትጥቅ ግጭት ከተጀመረ በኃላና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኃላ የተፈፀመ እንደነበር ይታወሳል።
አቶ ክርስቲያን ታደለ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ምርጫ ክልል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው በማሸነፍ ነበር።

Photo
#ተጠንቀቁ⚠️
በምስሉ የተያያዙት በኦንላይን " ቀላል በሆነ ስራ ብዙ ትርፍ ታገኛላችሁ " በሚል #የማጭበርበር ስራ ተታለው ገንዘባቸውን የላኩ ሰዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት ማስረጃ እና ያጨብረበሯቸውን አካላት የቴሌግራምና የዋትአፕ አድራሻ የሚያሳይ ነው።
" ቀላል ስራ፣ ብዙ ትርፍ የሚያስገኝ ስራ " በሚል ከ65 ሺህ ብር እስከ 600 ሺህ ብር የተበሉ አሉ።
ምንም እንኳን አጨብረባሪዎቹ በውጭ ሀገር ስልክ የሚያጭበረብሩትን ሰው ቢያናግሩም የገንዘብ ልውውጡ እንዲደረግ የሚያደርጉት እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለ አካውንት ነው።
ገንዘብ የሚያስልኩትም የሚልኩትም እጅግ በጣም በበዙ አካውንቶች ነው። (ይህም በኦንላንይ የክሪፕቶ ግብይት ሊሆን እንደሚችል አንድ ባለሞያ ለቲክቫህ ጠቁመዋል)
ማሳሰቢያ ፦ በተለያዩ የማጭበርበሪያ ግሩፕ ውስጥ ያሉት ሰዎች ለማጭበርበር የተሰማሩ አልያም በሆነ ቡድን የሚመሩ ሲሆን ፕሮፋይል ምስላቸው የታወቂ ሰዎች / ዝም ብሎ ከኢንተርኔት የተገኙ የሴቶች / የወንዶች ፎቶ ናቸው።