TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.3K photos
1.55K videos
215 files
4.25K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በነገው ዕለት የዐቢይ ጾም እንዲሁም የረመዷን ወር ጾም ይጀምራል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መልካም የዐቢይ ጾም እንዲሁም መልካም የረመዷን ጾም እንዲሆን ከልብ ይመኛል።

በነገው ዕለት የሚጀምሩት አጽዋማት የፈጣሪን በረከት ፣ ዕርቅ ፣ ምህረት ፤ ለመላው ሀገራችን ፍጹም ሰላም እና መረጋጋትን የሚያመጡ እንዲሆኑ እንመኛለን።

#ኢትዮጵያ #Ethiopia #ክርስትና #እስልምና

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Empowering Africa, One Venture at a Time. Jasiri Talent Investor strives to remove barriers that hinder the success of new businesses. The program guides the Fellows from ideation to venture creation, by providing funding, coaching, strategic advisory, and guidance in the complex innovation space.

Application for Cohort 6 is ongoing, submit your application via https://jasiri.org/application

#Jasiri4Africa
#MertEka

እነዚህ የቤት ዕቃዎች በሱቃችን በቅናሽ ዋጋ እየተሸጡ ነው። የሁሉንም ዕቃዎች ዋጋ  ይሄንን👉  t.iss.one/MerttEka 👈 ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
አድራሻችን፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ ሱቅ 376
PHOTO ፦ የመጀመሪያው ምሽት ተራዊህ ሶላት በሳዑዲ አረቢያ - #RAMADAN #ረመዷን ☪️

Photo Credit : Haramain

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ዛሬ በአዲስ አበባ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ ስትራቴጂካዊ ግምገማ ተጀምሯል።

እነማን ተገኙ ?

- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት
- የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዛዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ
- የቀድሞው የኬንያ ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ
- የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ይገኙበታል።

የፌደራል መንግስትን ከወከሉት መካከል ፦

* የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎትን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣
* የፍትህ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣
* የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተሾመ ቶጋ ይገኙበታል።

ህወሓትን ከወከሉት መካከል ፦

° ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ሊቀመንበር)
° አቶ ጌታቸው ረዳ (ም/ሊቀመንበር እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት)
° ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ (የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት)
° ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ (በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ) ይገኙበታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ "...መግለጫው የኤርትራ ጦር የተለያዩ አካባቢዎችን በኃይል ይዞ እንደሚገኝ ያመላከተ ነው " - አቶ ረዳኢ ኃለፎም የትግራይ ጦርነት መቀስቀስን ተከትሎ የኤርትራ ጦር  የኢትዮጵያን መሬት በኃይል ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላም ቢሆን መሬቱን ለቆ እንዳልወጣ የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደርን ጨምሮ ሀገራትና ተቋም በተደጋጋሚ መግለፃቸው ይታወሳል። በቅርቡ እንግሊዝ የሚገኘው…
#Tigray

" የኤርትራ ሰራዊት በራሱ ግዛት ነው ያለው የሚለው የኤርትራ መንግስት መግለጫ ራስን ከማሞኘት ያለፈ ትርጉም የለውም " - አኒና የኢሮብ  ማህበረሰብ መብት ጠባቂ ማህበር

አኒና የተባለው የኢሮብ ሲቪክ ማህበረሰብ  ማህበር መጋቢት 1/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ኢትዮጵያ በሚገኙ 3 ዞኖች የሚገኙ በርካታ አከባቢዎች ተቆጣጥሮ ነዋሪዎች እያንገላታና ግፍ እየፈፀመ ይገኛል ብሏል።

ስቪክ ተቋሙ የኤርትራ መንግስት የካቲት 28/2024 ያወጣው መግለጫን በተመለከተ " የኤርትራ መንግስት የትግራይ ኢትዮጵያ መሬቶች መያዙ በዚህ በሰለጠነ የመረጃ ዘመን ፈፅሞ መካድ አይቻልም " ብሎታል።

የኤርትራ መንግስት የሰጠው መግለጫ ከእውነት የራቀና በፍፁም መወገዝ ያለበትን ነውም ብሏል።

የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ፦
- የዛላኣንበሳ ከተማ
- በጉሎመኸዳ ወረዳ ማርታ ፣ አዲስ ተስፋ ፣ አዲስ ዓለም ፣ ሸዊት ለምለምና ሰበያ
- በኢሮብ ወረዳ እንዳልጌዳ ፣ ወርዓትለ ዓገረ ሎኽማና ዓሊቴና የተባሉ የኢትዮጵያ አከባቢዎች ተቆጣጥሮ ይገኛል ሲል ገልጿል።

በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በታሕታይ ኣድያቦ የኩናማ ማህበረሰብና ሌሎች የሚኖሩባቸው ገማህሎ ፣ አደመይቲ ፣ የባድመ ከተማና አከባቢው ፣ ዓዲ ፀፀር ፣ ለምለም ሸዊት ፣ ሸምበሊና ፣ መንጠብጠብ ፣ ዓዲ ኣሰር ፣ ሰየምቲ አድያቦ በኤርትራ ስራዊት ስር እንደሚገኙ ፀሃይ የሞቀው ሃቅ ነው ሲልም አክሏል።

የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ማእከላዊ ዞን የእገላና ራማ አከባቢዎች ሙሉ በሙሉና በከፊል ተቆጣጥሮ የአከባቢው ህዝብ የመንግስት አገልግሎት እንዳያገኝ በማድረግ ለበርካታ ችግሮች እንዳጋለጠው  ያመለከተው አኒና የኢሮብ ስቪክ ማህበረሰብ መግለጫ ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ህዝቡ ከእንግልትና መከራ እንዲታደገው ጥሪ አቅርቧል።

አኒና የኢሮብ ሲቪክ ማሕበረሰብ ያወጣውን መግለጫ የተከታተሉ የመቐለ ነዋሪዎች ለመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በሰጡት አስተያየት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈራሚዎች የፌደራል መንግስትና ህወሓት ፣ የአሜሪካ ፣ የአውሮፓ ፣ ኢጋድና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተዛቢዎች በተገኙበት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ዛሬ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚካሄደው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውል አተገባበርና አፈፃፀም አስመልክቶ በሚካሄደው ግምገማ በኤርትራ ሰራዊት ስር ስላሉ የትግራይ ኢትዮጵያ ግዛቶች ጉዳይ የውይይቱ አካል ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                           
@tikvahethiopia