TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ የመሬት አገልግሎቶች ታገዱ። በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት ተከናውኖ በአዳስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ጸድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ የተወሰነውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ የሠራተኞች የባህሪ እና የቴክኒክ ፈተና ተሰጥቶ ውጤቱ ይፋ መደረጉ ይታወቃል። በዚህም አዲስ በተጠናው መዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት መሰረት የሰራተኞች ድልድል ተሰርቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከዛሬ…
" ዓርብ መጋቢት 6 ምሽት ወደ ትግበራ እንዲገባ ይታወጃል " - ዶ/ር ጣሰው ገብሬ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞችና አመራሮች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ወስደው የወደቁ ከ7,500 በላይ ሠራተኞች ከደረጃ ዝቅ ተደርገው የተመደቡበት የሥራ ዕርከን ድልድል መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጣሰው ገብሬ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፤  " ፈተና ያላለፉት ከደረጃ ዝቅ ብለው ነው የሚሠሩት። ድልድሉ ስለተጠናቀቀ ደብዳቤው በየተቋሙ ይሰጣል " ብለዋል።

" ከሰኞ የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለ5 ቀናት የሚቆይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየሰጠናቸው ነው " ያሉት ኃላፊው " 2ኛው ዙር ሥልጠና ከመጪው ሳምንት ሰኞ መጋቢት 2 እስከ ዓርብ መጋቢት 6/ 2016 ዓ.ም. ይሰጣል። ዓርብ መጋቢት 6/ 2016 ዓ.ም. ምሽት ወደ ትግበራ እንዲገባ ይታወጃል፣ ሥልጠናው እንዳለቀ ወደ ትግበራ ነው የሚገባው " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የሠራተኞች ድልድል እንደ አዲስ ተካሂዶ እስኪጠናቀቅ ድረስ በከተማው ሁሉም ክ/ከተሞች " ማናቸውም የመሬት አገልግሎቶች " ለአጭር ጊዜያት መታገዳቸው ይታወሳል።

ታዲያ በመጪው ሳምንት ድልድሉ ይፋ ሲሆን የመሬት አገልግሎቶች መሰጠት ይቀጥላሉ ወይ ? ተብለው ከጋዜጣው የተጠየቁት ዶ/ር ጣሰው ፤ በጉዳዩ ላይ ምንም ዓይነት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። 

ጋዜጣው ግን ከመጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. አዲስ የሥራ ዕርከን ድልድል በኋላ የመሬት ሥራ አገልግሎት በቅርብ እንደሚጀመር በዘርፉ ከተሰማሩ ምንጮች መስማቱን አመላክቷል። #ሪፖርተር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PurposeBlack የፐርፐርዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አፈፃሚ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ በአሁን ሰዓት #አሜሪካ ሀገር እንደሚገኙ ተነግሯል። " አሜሪካ የሚገኙት ለስራ ነው " ያለው ድርጅቱ የፊታችን ሀሙስ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱና መግለጫም እንደሚሰጡ አመልክቷል። ዛሬ መግለጫ ሰጥተው የነበረው የድርጅቱ የቦርድ አባል እና የህግ አማካሪ ዶ/ር ኤርሚያስ ብርሃኑ ናቸው። ፐርፐዝ ብላክ ከቤቶቹ ግንባታ…
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ መግለጫ ሰጠ።

በቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መካከል ሲካሄድ የቆየው አ/አ #ሜክሲኮ የሚገኘው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ድርድር ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ መቋረጡን ተከትሎ ከሁለቱም ወገን መግለጫዎች መውጣታቸው ይታወሳል።

ቢጂአይ ኢትዮጵያ ውሉ ስለመቋረጡ ከገለጸ በኋላ ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በሰጠው መግለጫ ላይ በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ህግ ክፍሉ ዳይሬክተር አቶ ነጋ ምህረቴ እንዲሁም የህግ አማካሪ የሆነው "ምህረታብ እና ጌቱ አድቮኬትስ ኤል ኤል ፒ" መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ላይ የተነሱ ጉዳዮች ምንድናቸው ?

- የድርድር ሂደቱ 8 ወራት ፈጅቷል። ቀድመን የተፈራረምነው የቀብድ ውል ነው። የቀብድ ውሉ የጊዜ ገደቡ ሦስት ወር ቢሆንም በእኛ በኩል በቅንነት 8 ወራት ጠብቀናል።

- ቀብድ ውሉን ከተፈራረምን በኋላ በእኛ በድርጅታችን ኃላፊ ጭምር እንዲሁም የመክፈል አቅም እንዳላቸው በተደጋጋሚ ማስረጃ እንዲሰጡን ብንጠይቅም እንከፍላለን ከሚል ደብዳቤ በስተቀር የሚጠበቅባቸውን ብር ለመክፈል አቅም እንዳላቸው ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም።

- ግብር ለመክፈል ወደኋላ የምንል አይደለንም። የሚሸጠውም ህንጻ እዳ ያለበት አይደለም ቢጂአይ እዳ ያለበት ንብረት ለሽያጭ አያቀርብም።

- ካፒታል ጌን ኪሊራንስ ለማውጣት በቅድሚያ የሽያጭ ውል መሟላት አለበት። ይህ በሌለበት ሁኔታ ክሊራንስ ማውጣት አንችልም። ይህ በህጉ የተቀመጠ የታወቀ አሰራር ነው። ቢጂአይ ክሊራንስ ለማምጣት ዝግጁ ቢሆንም ነን በቀብድ ውሉ በተጠቀሰው መሰረት በቅደም ተከተል በተቀመጠው መሰረት የሽያጭ ውሉ ላይ መስማማት ያስፈልጋል። የተለያዩ ውይይቶች ቢደረግም እሱን መፈረም አልቻሉም።

- በቀብድ ውሉ መሰረት የተከፈለው 1 ቢሊዮን ብር +15 VAT ሲሆን ቀጣዩን ክፍያ ለመክፈል የሽያጭ ውሉን መፈረም እንዲሁም በውልና ማስረጃ ሌሎች የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች ቀርቦ እንዲጸድቅ ይጠበቃል። ይህንን ለማድረግ ከሚያስፈልገው አንዱ የሽያጭ ውል ሲሆን ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ይህንን መፈረም ባለመቻሉ ውሉን ለማቋረጥ ተገደናል።

- ከፐርፐዝ ብላክ ጋር ያለን ውል ተቋርጧል። ዳግም ተመልሰን የምንደራደርበት ነገር የለም። ይህ ውል ከተጠናቀቀ በኋላ ህንጻውን የመሸጥ አሁንም ፍላጎት አለን።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ መግለጫ ሰጠ። በቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መካከል ሲካሄድ የቆየው አ/አ #ሜክሲኮ የሚገኘው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ድርድር ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ መቋረጡን ተከትሎ ከሁለቱም ወገን መግለጫዎች መውጣታቸው ይታወሳል። ቢጂአይ ኢትዮጵያ ውሉ ስለመቋረጡ ከገለጸ በኋላ ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በሰጠው መግለጫ ላይ በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ የቢጂአይ…
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ፤ " ውሉ የተቋረጠው ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው " ሲል ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

" የመክፈል አቅም እንዳላቸው በተደጋጋሚ ማስረጃ እንዲሰጡን ብንጠይቅም ' እንከፍላለን ' ከሚል ደብዳቤ በስተቀር የሚጠበቅባቸውን ብር ለመክፈል አቅም እንዳላቸው ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም " ሲልም ገልጿል።

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ግብር ለመክፈል ወደኋላ የሚል እንዳልሆነና የሚሸጠውም ሜክሲኮ የሚገኘው የዋናው መስሪያ ቤት ህንጻ እዳ እንደሌለበት አስገንዝቧል።

እዳ ያለበት ንብረት ለሽያጭ እንደማያቀርብም ገልጿል።

" ከፐርፐዝ ብላክ ጋር ያለን ውል ተቋርጧል። " ያለው ቢጂአይ-ኢትዮጵያ " ዳግም ተመልሰን የምንደራደርበት ነገር የለም። ይህ ውል ከተጠናቀቀ በኋላ ህንጻውን የመሸጥ አሁንም ፍላጎት አለን " ብሏል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DStv

ቀላል እና ፈጣን መላ ለዲኤስቲቪ ደንበኞች በሙሉ!

ወደ ዲኤስቲቪ የጥሪ ማዕከል ሳይደውሉ በማንኛውም ሰዓት በሞባይልዎ *9299# በመደወል እና My DStv App ስምዎንና የስማርት ካርድ ቁጥርዎን አስገብተው የዲኤስቲቪ ክፍያ መጠንዎንና ቀኑን በቀላሉ ለማወቅ ፓኬጅ ለመቀየር ብሎም በቴሌብር ፣ በሲቢኢ ብር እና በአዋሽ ብር መክፈል ይችላሉ።

የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/2WDuBLk

የፕሌይ ስቶር ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/3qJ95Us 

የአፕ ስቶር ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/45hIwEU

በተጨማሪም ስለ አገልግሎታችን ጥራት በሚደርስዎት የፅሁፍ መልዕክት ላይ ሊንኩን በመጫን መጠይቁን እንዲሞሉ በትህትና እንጠይቃለን።

ይሞክሩትና የማይጠገብ የመዝናኛ አማራጭ ያለማቋረጥ ያጣጥሙ ፤ የእርስዎንም አስተያየት ያጋሩ!

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET'
 #PretoriaPeaceAgreement

በኢትዮጵያ ሆነ በትግራይ ክልል ውስጥ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ከተፈለገ የፕሪቶሪያ የሰላም ውል በሙሉነት መተግበር አጅግ አስፈላጊ መሆኑ የክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ገለፁ።  

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ዛሬ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምነት የአተገባበር  ሂደት ያተኮረ ተፈራራሚ አካላትና የአፍሪካ ህብረት ያሳተፈ ግምገማ በአዲስ አበባ መካሄድ መጀመሩን አመልክተዋል።

በኢትዮጵያም ሆነ በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የፕሪቶሪያ የሰላም ውል በሙሉነት መተግበር የግድ ነው ያሉት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ፡ ስምምነቱ ሕግና ሕገ-መንግስታዊ የትግራይ ህዝብ ጥያቄዎች ባከተተ መልኩ መገምገም ያስፈልጋል ብለዋል። 

ስምምነቱ የጠብመንጃ ላንቃ ህልም በኢትዮጵያና በመላ ትግራይ ክልል በሚያጠፋ  መልኩ ሙሉ በሙሉ መፈፀምና መተግበር ይገባዋል ሲሉ አክለዋል።

የአፍሪካ ህብረት የፕሪቶሪያው የሰላም የስምምነት መሬት ላይ እንዴት እየተፈፀመና እየተተገበረ  አንደሆነ አስመልክቶ  በጀመረው ስትራቴጂክ ግምገማ ከስምምነቱ ፈራሚዎች በተጨማሪ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፣ የአውሮፓ ህብረት ፣ ኢጋድ እና አሜሪካ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
                        
@tikvahethiopia            
የግጭት ዳፋ በትምህርት ተቋማት !

(በጋዜጠኛ ኢዮብ ትኩዬ የተዘጋጀ)

ተማሪ ፀሐይ አፈወርቅ (ለዚህ ዘገባ ስሟ ተቀይሯል) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ታጣቂዎች ሲሰነዝሩት በነበረው ጥቃት በወደመ ትምህርት ቤት በመማር ትምህርቷን ላለማቋረጥ የምትፍገመገም ተማሪ ነች። 

ታዳጊዋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠችው ቃል ምን አለች ?

" ትምህርት ቤቴ ስለፈረሰ የተሟላ አይደለም፣ ግን መማር እፈልጋለሁ።

የምማርበት ትምህርት ቤት በግጭት ምክንያት ከመውደሙ በፊት በተሟላ መቀመጫ ወንበር፣ ላይብረሪ፣ ኮምፒዩተሮች እንማር ነበር።

የምንማርበት ትምህርት ቤት መፈራረሱ ለትምህርት ያለኝን ልዩ ፍላጎት ስላልገደበው ብፍጨረጨርም ፣ ባልተሟላ ትምህርት ቤት መማር ከትምህርት አቀባበል ጀምሮ አንዳች አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል።

ውድድሩ በቴክኖሎጂ በሆነበት ዓለም ከቴክኖሎጅ ርቆ መማር ለአሁኑ ካለመማር ቢሻልም፣ ለችግሩ መፍትሄ ካልተሰጠው ደግሞ ለወደፊት ግን በዚህ መልኩ ከመማር አለመማር ሊሻል የሚችልበት ደረጃ እንዳይደረስ እሰጋለሁ።

በምንማርበት ትምህርት ቤት እንደቀድሞው የመማር ማስተማር ቁሳቁሶች እንዳልነበሩ ሆነዋል። ይህም አንዱ የግጭት አስከፊ ገጽታ የሚያስገነዝብ ነው።

ትምህርቷን ላለማቋረጥ የቻልኩትን እያደረኩ ነው። ቢሆንም ቁሳቁስ ባልተሟላበት ትምህርት ቤት መማራችንን ተከትሎ በርካታ ተማሪዎች የትምህርት አቀባበላቸው እየተሸረሸረ ይገኛል። "

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/TikvahEthiopia-03-07

@tikvahethiopia
#Wolkite

ለአመታት በውሃ ችግር የሚፈተነው የወልቂጤ ከተማ ህዝብ ዛሬም " የመንግስት ያለህ " እያለ ነዉ።

ችግሩን ለመፍታት ጥረት ላይ እየተደረገ ነዉ የሚለው የከተማው አስተዳደር በበኩሉ " ሩጫ ላይ ነኝ " ይላል።

የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች የውሀ ጀሪካኖች በጫኑ ባጃጆችና ጋሪዎች ተሞልተዉ ይታያሉ። ሆቴሎች የሻወር አገልግሎትን ከረሱ የቆዩ ይመስላሉ።

በአጠቃላይ ውሀ ቅንጦት መሆኑ ግለጽ ነዉ ይህን ጉዳይ ተመልክቶ የአካባቢዉን ማህበረሰብ ስለጉዳዩ የጠየቀዉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ችግሩ ለአመታት የቀጠለ መሆኑን ተረድቷል።

እንደነዋሪዎቹ ገለጻ የቧንቧ ውሀ በወር አንዴ በጣም ፈጠነ ሲባል በሁለት ሳምንት አንዴ ያውም ለሰአታት ብትመጣም አንዳንዴ የምትመጣዉ ሌሊት ሲሆን እንደምታመልጣቸዉ ይገልጻሉ።

ለሽንኩርትና ቲማቲም ከሚያወጡት እኩል ለውሀ ግዥ እንደሚያወጡ የሚገልጹት ነዋሪዎቹ መንግስት ችግራቸዉን ይቀርፍላቸዉ ዘንድ በምሬት ይጠይቃሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንካራ ጥያቄ ከሰሞኑ በነበረ የምክር ቤት ጉባኤ የቀረበለት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በበኩሉ የውሀ ችግሮች ያለመፈታታቸዉ ምክኒያት በየዞንና ከተሞች የተጀመሩ የውሀ ጉድጓድ ፕሮጀክቶች እየተጀመሩ በመቆማቸዉ የተከሰተ መሆኑን ገልጾ የማህበረሰቡን ጥያቄ ለመመለስ በሙሉ ሀይሉ እንደሚሰራ ገልጾ ነበር።

ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ የህዝብ ጥያቄ  የቀረበላቸዉ የወልቂጤ ከተማ የውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ቢሮ ሀላፊዉ  አቶ ዳዊት ሀይሌ በበኩላቸዉ ችግሩ መኖሩን በመግለጽ አሁን ላይ የቅሀ አጥረቱ ከተማዉን እየፈተነ መሆኑና ችግሩን ለመቅረፍ የተጀመሩ ስራዎች እንዳሉና ከሚጠበቁ መፍትሄዎች አንዱ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ስራው ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ዳዊት አክለዉም ፤ በቅርቡ የጉራጌ ዞን የውሀና መአድን ቢሮ ጋር በመሆን ሁኔታዎች እንደሚገመገሙና ለህዝብ አስፈላጊዉ መረጃ እንደሚሰጥ በመግለጽ ሁኔታዉን ከከተማዉ ባለስልጣናት ባለፈ የዞኑም ሆነ የበላይ አካላት በትኩረት እየሰሩበት መሆኑን ጠቁመዋል።

መረጃው ወደ ወልቂጤ ተጉዞ የነበረው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው አዘጋጅቶ የላከው።

ፎቶ ፦ Tikvah Family

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የደብረ ብርሃን 2 - ሸዋ ሮቢት - ኮምቦልቻ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠግኖ ማምሻውን ሥራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።

በሸዋ ሮቢት አቅራቢያ ጉዳት ደርሶበት የነበረው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመጠገኑ ካለፈው እሁድ ጀምሮ ኃይል ተቋርጦባቸው የነበሩ የአፋር መዲና ሠመራን ጨምሮ በሰሜን ምሥራቅ የሚገኙ ከተሞች ዳግም ኃይል አግኝተዋል ብሏል።

በአሁኑ ሰዓት ኤሌክትሪክ ተቋርጦባቸው የቆዩት ሁሉም የሰሜን ምሥራቅ ከተሞች ኤሌክትሪክ ዳግም አግኝተዋል ተብሏል።

@tikvahethiopia
በዲጂታል እና ፋይናንሻል አካታችነት ሴቶችን ማብቃት!

ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ስርዓተ-ፆታ ልዩነትን ለማጥበብ እና የሴቶችን የዲጂታል ተካታችነት ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት “Connected Women” ኢኒሼቲቭ- ከ GSMA ጋር በባርሴሎና ስፔን ተፈራርሟል::

ስምምነቱ በሀገራችን የሴቶችን የሞባይል ኢንተርኔት እና የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት /ቴሌብር/ ተጠቃሚ ቁጥር እ.ኤ.አ እስከ 2026 በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያለመ ሲሆን ኩባንያው ለተግባራዊነቱ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ እና በመተግበር እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሴቶች የሚያጋጥሟቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍታት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት አካታች የሞባይል ኢንተርኔት እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ማቅረብን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

በስምምነቱ ወቅት የኩባንያው ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ “ሴቶች በሀገራችን ልማት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ኩባንያችን አሁን የሚታየውን የዲጂታል ስርዓተ-ፆታ ክፍተት ለማጥበብ የሞባይል ኢንተርኔትና የሞባይል ፋይናንሺያል አገልግሎቶችን ለሴቶች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ሴቶች በዲጂታል ኢኮኖሚው ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡” ብለዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #EthiopianCommunicationAuthority #GSMA #AU #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #SmartAfrica #HOPR #HOF