TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፓስፖርት ፓስፖርት ፈልገው/ በሥራ ምክንያት ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጎራ ካሉ ረዥም ሰልፍ እና መጨናነቅ ማየት የተለመደ ነው። የሰልፍ አሰላፊዎች ዱላም ሊያጋጥም ይችላል። ወጣት፣ሴት፣ወንድ፣ልጅ ያዘሉ እናቶች እንዲሁም " ፓስፖርት ፈልገው ነው ? " እያሉ እግር በእግር የሚከተሉ ሕገወጥ ደላሎችም በአካባቢው ውር ውር ይላሉ። አገልግሎቱ 24 ሰዓት የፓስፖርት ህትመትና በበይነ መረብ ምዝገባ…
#ፓስፖርት

አዳማ ላይም ፖስፖርት ለመውሰድ አስቸጋሪ መሆኑን ተገልጋዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት ቅሬታ አመላክተዋል።

" ሰው ከመብዛቱ የተነሳ ሰው በየቀኑ ፓስፖርቱን ሳይወስድ ሳምንት ተመለሱ ይባላል። " ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎች " ፓስፖርት ለመስጠት የሚጠሩት በአልፋቤት ብሆንም Order የጠበቃ አይደለም። " ብለዋል።

" አንዱ የጠረውን በድጋሚ ሌላም አንስቶ የመጥራት ክስተት እንዳለ " አመላክተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አንድ ተገልጋይ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ይህንን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርቷል።

N ከአዳማ ፦

" አዲስ ፓስፖርትን ለመውሰድ ያለው እንግልት አለ።

አዲስ ፓስፖርት ካመለከትኩ አሁን ላይ 11 ወራት ሆኖኛል፡፡

በየካቲት ወር 7ኛው (February 15) ቀን በቴሌግራም አካውንት ላይ አዲስ ፓስፖርት የመጣላቸው ስም ዝርዝር ውስጥ ስሜን ስላገኘሁት ልቀበል አውራ ጎዳና በሚገኘው አዳማ ቢሯቸው ሄድኩኝ፡፡

ሆኖም ግን እዛ ስድርስ የመ/ቤቱ ጥበቃዎች በዱላ ጥያቄ ለመጠየቅ ግራ ገብቶት ያለውን ሰው መምታቱትን ተያይዘውታል፡፡

ከዛም ብቸኛ የመረጃ ምንጭ የሆኑት እነርሱ (ጥበቃዎቹ) ስለሆኑ ዱላው ሳያገኘኝ ጥያቄዬን ለመጠየቅ ተጋፍቼ ሳበቃ የአንተ ዛሬ አይደለም የሚቀጥለው ሳምንተ ከሰኞ በኃላ ና አሉኝ የሄድኩት ማክሰኞ እለት ነበር (February 19)፡፡

ወደ መስሪያ ቤቱ የሚያስገባው በር ሁለት ሰው እንኩዋን የማያስገባ ነው እናም መረጃ ለማግኘት ወደ ውስጥ መግባት የማይታሰብ ነው፡፡

ቀጥሎም አርብ እለት (February 23) ሄድኩ እንደምንም ተጋፍቼ ስጠይቅ አንድ ጊዜ ረቡህ አንዴ ሃሙስ አለኝ ጥበቃው፡፡

በቀጣይ ስለተጠራጠርኩ ቀደም ብዬ ማክሰኞ (February 26) ሄድኩ ከዛም በዛ ቀን የነበረው ጥበቃ አርብ እለት ነው አለኝ፡፡አርብ ስሄድ(March 01) ስሄድ ሰልፍ ያዝ ተባልኩ፡፡

ሰልፍ ከያዝኩ በኃላ ተሰላፊዎቹን ስጠይቅ የአንተ እኮ ሀሙስ ነበር አሉኝ(February 29)፡፡

መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ላይ ያለ ማስታወቂያ አሳኙኝ ማስታወቂያውን አነበብኩት የተለጠፈው February 23 ነው፡፡ እናም ጥበቃዎች ቢያንስ ተገልጋይ ማስታወቂያ እንዲያይ ቢያደርጉ የሰውን እንግልት ይቀንሳሉ፡፡

እኔ ቤተሰብ አዳማ ስለሆነ መመላለስ እችላለሁ ነገር ግን ከሩቅ ቦታ ለሚመጡ ምን ያህል ከባድ ነው በዚ ላይ የጥበቃዎቹ ዱላ ተጨምሮበት ?

አመሰግናለሁ፡፡ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፓስፖርት ፓስፖርት ፈልገው/ በሥራ ምክንያት ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጎራ ካሉ ረዥም ሰልፍ እና መጨናነቅ ማየት የተለመደ ነው። የሰልፍ አሰላፊዎች ዱላም ሊያጋጥም ይችላል። ወጣት፣ሴት፣ወንድ፣ልጅ ያዘሉ እናቶች እንዲሁም " ፓስፖርት ፈልገው ነው ? " እያሉ እግር በእግር የሚከተሉ ሕገወጥ ደላሎችም በአካባቢው ውር ውር ይላሉ። አገልግሎቱ 24 ሰዓት የፓስፖርት ህትመትና በበይነ መረብ ምዝገባ…
#AddisAbaba

4 ኪሎ አካባቢ የሚገኙ ሁለት የእግረኛ መሸጋገሪያ የብረት ድልድዮች የማንሳት ስራ እየተከናወነ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ዓለም አቀፍ የስማርት ሲቲ ስታንደሰርድን የሚያሟሉ አዳዲስ አራት የመንገድ ኮሪደሮች ግንባታ እንዲከናወን ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ 4 ኪሎ አካባቢ የሚገኙትን ሁለት የእግኛ መሸጋገሪያ የብረት ድልድዮች የማንሳት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አሳውቋል።

" 4 ኪሎ ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ የሚገኘው የእግረኞች መሸጋገሪያ ድልድይ ጉዳት ደርሶበታል " በሚል የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የተላለፈው ዘገባ የተሳሳተ መሆኑ ተገልጿል።

የብረት ድልድዮችን የማንሳት ስራ በሁለት ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን፣  የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#JASIRI: ታለንት ኢንቨስተር

- ለፈጣን ዕድገት አቅም ካላችሁ እና አዲስ ቢዝነስ ለመፍጠር ከቆረጣችሁ፤

- በማንኛናውም ዘርፍ ውስጥ ክፍተቶችን መለየት እና እድሎችን ማወቅ ከቻሉ፤

- ትኩረት ባደረጋቹበት ቦታ ሁሉ የስኬት፣ የችግር አፈታት እና ዋጋ የመፍጠር ልምድ ካላቹ፤

- በሙያዊ መስካችሁ ከፍተኛ መረጃ እና እውቀት ያላቹ ከሆነ፤

- በቡድናቹ ውስጥ ካሉ ተመሳሳይ ትልቅ ፍላጎት ካላቸው መስራቾች ጋር ለመገናኘት እና ከመሰረቱ ቬንቸር ለመገንባት እና በቡድን ለመስራት ዝግጁ ከሆናችሁ፤

- ስራዎን በሙሉ ጊዜ ለመገንባት ቃል ገብታቹ እና በሁሉም ታለንት ኢንቬስተር ደረጃዎች ለ14ወራት እንዲሁም በሩዋንዳ ባለው ፕሮግራም ለ3 ወር ተገኝታቹ በንቃት ለመሳተፍ ዝግጁ ከሆናቹ፤

አሁኑኑ በ jasiri.org/application ላይ ይመዝገቡ

ሴት ስራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ በጣም እናበረታታለን!
ከባንክ ሂሳብዎ ወደ M-PESA 1,000 ብር እና ከዚያ በላይ በማስተላለፍ ከ0.5% እስከ 50 ብር ድረስ ስጦታ ያግኙ።

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም የቻት ግሩፕ
https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC https://t.iss.one/SafaricomETForum እንዲሁም @SafaricomETCare
24/7 መጠየቅ ይቻላል!

#SafaricomET
#MPESASafaricom
#FurtherAheadTogether
የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መሥሪያቤት ህንፃ ሽያጭ ተቋረጠ።

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ መካከል ሲካሄድ የቆየው ድርድር የሽያጭ ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ መቋረጡን ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ለቲክቫህ ገልጿል።

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የሽያጭ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንዲኖር እና የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጩ እውን እንዲሆን ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀ ሲሆን " በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ምክንያት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ሂደቱን ለማቋረጥ ተገደናል። " ሲል አሳውቋል።

" ስለዚህም በተዋዋይ ወገኖቹ ቀድም ሲል በተፈረመው የቀብድ ውል ውስጥ በተገለጹት ድንጋጌዎች መሠረት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጩ በይፋ ተቋርጧል " ብሏል።

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ከዋና መስርያ ቤቱ ሽያጭ ድርድር ጋር በተገናኘ በዚህ ወቅት ምንም አይነት ተጨማሪ አስተያየት እንደማይሰጥ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው የኢሜል መልዕክት አሳውቋል።

ቀደም ብሎ ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በሜክሲኮ የሚገኘውንና የቢጂአይ ኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ ዋና መሥሪያ ቤት አድርጎ ሲጠቀምበት የነበረውን ሥፍራ ለመግዛት መስማማታቸውን ከሁለቱም ወገን መገለጹ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል። ሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ? - ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም - ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም - ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም …
#እንድታውቁት

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል።

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በየካቲት ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ?

- ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
- ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ16 ሳንቲም ነው።

@tikvahethiopia
#ትግራይ

"...መግለጫው የኤርትራ ጦር የተለያዩ አካባቢዎችን በኃይል ይዞ እንደሚገኝ ያመላከተ ነው " - አቶ ረዳኢ ኃለፎም

የትግራይ ጦርነት መቀስቀስን ተከትሎ የኤርትራ ጦር  የኢትዮጵያን መሬት በኃይል ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላም ቢሆን መሬቱን ለቆ እንዳልወጣ የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደርን ጨምሮ ሀገራትና ተቋም በተደጋጋሚ መግለፃቸው ይታወሳል።

በቅርቡ እንግሊዝ የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ አውጥቶት በነበረ አንድ መግለጫ የኤርትራ ጦር በትግራይ ግዛት ውስጥ እንደሌለ፣ ባድመም ጨምሮ ሌሎችም አከባቢዎች ህወሓት በህገወጥ መንገድ ለሁለት አስርት ዓመታት ይዟቸው የቆዩ የኤርትራ ሉዓላዊ ግዛቶች ናቸው ብሏል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የኤርትራ ጦር በምስራቃዊና ሰሜን ምዕራብ የትግራይ አካባቢዎች ጨምሮ በተለያየ አካባቢ እንዳለ በተደጋጋሚ በመግለፅ በኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ያሉ የውጭ ኃይሎችን የማስወጣትና ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው የመመለስ ኃላፊነት የፌዴራል መንግሥት መሆኑን ገልጿል።

የትግራይ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ረዳዒ ኃለፎም በኤርትራ መግለጫ ዙሪያ ምን አሉ ?

- የኤርትራው ኤምባሲ መግለጫ የኤርትራ ጦር የተለያዩ አካባቢዎችን በኃይል ይዞ እንደሚገኝ አመላካች ነው።

- ከአልጀርስ ስምምነት አፈፃፀምናና ሌሎች የድሮ በ90ዎቹ የሚነሱ ጥያቄዎች ጉዳዮች ካሉ በህጋዊ መንገድ በዓለም አቀፍ ስርዓት እንዲፈፀም ማድረግ እንጂ ጉልበት አለኝ ብሎ በጉልበት የያዛቸውን አካባቢዎች " የኔ ናቸው " የሚል መግለጫ መስጠቱ ተቀባይነት የለውም።

- ከአልጀርስ ስምምነት አፈፃፀም ጋር በተያያዘ በኃይል የተወረረው መሬት ከተመለሰ በኃላ በህጋዊ መንገድ ሊፈፀም የሚችል ነው።

- መግለጫው አንድ ውለታ የዋለው በኃይል የያዧቸው አካባቢዎች እንዳሉ ገልጸ " በኃይል የያዝኩት የኔ ነው " የሚል መስፋፋት ነው። " የለሁም " አላለም መኖሩን አምኗል ይሄ የያዘው ቦታ ነው በጉልበት ስለያዝኩት " የኔ ነው " እያለ ያለው ይሄ በፍፁም ተቀባይነት የለውም።

- የፌዴራል መንግሥት ማስወጣት አለበት እነዚህን ኃይሎች ሁሌም እያልን ነው። ማለት ያለበትን ማለትም አለበት። ኃላፊነቱን መወጣት አለበት።

- በትግራይ ከኤርትራ ጦር በተጨማሪ የአማራ ክልል ታጣቂዎችም አሉ። ይህ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚፃረር በትግራይ ያለውን አሳሳቢ የተፈናቃዮች ችግር እንዳይፈታ ያደረገ ነው።

- እንዚህ ኃይሎች እያሉ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ማድረግና ማቋቋም አይቻልም። ከሞት አምልጠው የመጡ ገዳዮች ወዳሉበት እንዴት ነው የሚመለሱት ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው የዶቼቨለ ሬድዮ መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#BGI #PurposeBlack

" ነገ ጥዋት መግለጫ እንሰጣለን "- ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያን አ/ማ

በቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መካከል ሲካሄድ የቆየው አ/አ #ሜክሲኮ የሚገኘው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ድርድር ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ ተቋርጧል።

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ በባከልን ኢሜል የሽያጩ ውል የተቋረጠው ፤ በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎትና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ነው።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ምን አስተያየት አለው የሚለውንና የሚሰጠው ምላሽ ይኖር እንደሆነ ለድርጅቱ ኃላፊዎች ስልክ ደውለንላቸው የነበረ ሲሆን ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም ነገ ጥዋት 2 ሰዓት ይፋዊ መግለጫ / ምላሽ እንደሚሰጡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ድርጅቱ የሚሰጠውን መግለጫ ተከታትለን መረጃ እንልካለን።

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ የሚገኘው ጥንታዊ እና ግዙፉ መስጅድ " መስጅድ ጃሚዕ " በድጋሚ በሐጂ አሕመድ አብዲ (አጋዋይን) ተገንብቶ ዛሬ ሰኞ በይፋ ተመርቆ ለረመዷን ክፍት ሆኗል። በፕሮግራሙ ላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድን ጨምሮ ታላላቅ ዓሊምች የአካባቢው ሙስሊሞች  ታድመው እንደነበር " ሀሩን ሚዲያ " ዘግቧል።

@tikvahethiopia
ኤርፖርት ...

በፎቶው 👆 ላይ የምትመለከቷቸው አቶ ነቢዩ ሲራክ ይባላሉ ፤ በአንደኛው ፎቶ ላይ አብሯቸው የሚታየው ልጃቸው ነው።

ትላንት ምሽት ለስራ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄደውን ልጃቸውን ለመሸኘት ቦሌ ኤርፖርት በነበሩበት ወቅት አንድ የኢሚግሬሽን ሰራተኛ ልጃቸው ላይ ፍፁም ከስነምግባር ያፈነገጠ ተግባር መፈፀሙን ገልጸዋል።

ልጃቸው ምንም እንኳን በሱዑዲ አረቢያ ተወልዶ ቢያድግም አማርኛ አቀላጥፎ የሚናገርና ሀገሩን ኢትዮጵያን ወዶ ወደዚህ የተመለሰ ፣ እዚህም በስራ ላይ የተሰማራ ነው።

የትላንት ጉዞውም የስራ ነበር።

ልጃቸው አስፈላጊውን ዶክመንት ሁሉ አሟልቶ የሚጠበቅበትን አድርጎ ኢሚግሬሽን ቢሮ ሲደርስ አንድ ሰራተኛ  " የት ነው የምትሄደው ? " ይለዋል። ልጅም ቦታውን ይናገራል። " ስራህ ምንድነው ? " ሲል ሌላ ጥያቄ ያስከትላል " ስራዬን ሴልስ ማን ነው " ሲል ይመልስለታል።

ከዚህ በኃላ የኢሚግሬሽን ሰራተኛው ፓስፖርቱን ንጥቆ ወርውሮ ፣ ከዚህ ሂድ በማለት ያንገላታዋል ፤ ልጅም " ፓስፖርቴን መልስልኝ " ሲለው " ፓስፖርትህን አልሰጥም ሂድ ውጣ " በማለት እስከ ድብደባ ሊደርስ እንደነበር አባት በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆነው ተናግረዋል።

በኃላም አባት ለኢሚግሬሽንና ደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊና ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ በተደረገው ማጣራት ከአንድ ሰዓት መጉላላት በኃላ ኢሚግሬሽን አልፎ ጉዞውን ማድረግ ችሏል።

" ህጋዊ ወረቀት ፓስፖርት ቪዛ ይዞ የሄደውን ሰው በዚህ ደረጃ ለምን ማንገላታት ያስፈልጋል ? ለምን ፓስፖርት መወርወር አስፈለገ ? ግልምጫ ማንጓጠጡስ ለምን አስፈለገ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በአንዳንድ የኢሚግሬሽን እና ደህንነት ሰራተኞች የሚፈፀም ህገወጥ አሰራር ፣ እጅግ በጣም የብዙ ሰዎችን ልብ እየሰበረ መሆኑን ፤ ለጥቅም ተብሎ በሚሰራ ስራ እጅግ ከፍተኛ ግፍ እና በደል እየተፈፀመ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ነብዩ ፤ እንዲህ ያለው አሳዛኝ እና ህገወጥ ተግባር በሁሉም ሰራተኞች ይፈፀማል ባይባልም በአንዳንድ ሰራተኞች የሚፈፀም ህገወጥ ተግባር የተቋሙን የቅን አገልጋዮችን ስም እንደሚያጎፍ እና ማረም እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተውበታል።

አቶ ነብዩ ሲራክ ፤ ለረጅም አመታት የህገ ወጥ ስደትን በመቃወምና በመከላከል ፣ በህገወጥ መንገድ ወጥተው ሌላ ሀገር እየተቸገሩ ስላሉ ዜጎች ጉዳይ ላይ ስራ እንዲሰራ ብዙ እየደከሙ ያሉ ሰው ናቸው።

ይህ የአንድ ሰው ገጠመኝና በማህበራዊ ሚዲያ የወጣ ይሁን እንጂ በተለይ በተለይ በቦሌ ኤርፖርት በአንዳንድ  ፦
- ስነምግባር በጎደላቸው
- የገዛ ዜጋቸውን በማያከብሩ
- ስራቸውን አክበረው በማይሰሩ፣
- ገንዘብ እና ጥቅም በሚያሳድዱ የኢሚግሬሽና ደህንነት ሰራተኞች ስንት ዜጎችን ተበድለው ፣ አንብተው ፣ የሚጮኹበት አጥተው ፣ መፍትሄ ተነፍገው ፣ መፍትሄ ፍለጋ የሚሄዱበትም ይሁን የሚደውሉበት አጥተው ይሁን ?

ተቋማት ፤ ሰራተኞቻቸው #ከህዝቡ በሚሰበሰብ ገንዘብ ደመወዝ እንደሚከፈላቸው በአግባቡ እንዲያወቁት በማድረግ ህዝብን #ጎንበስ ብለው ማስተናገድ እንዲለምዱ ፣ ሙስና እና ጥቅምን እንዲፀየፉ የማድረግ #ግዴታ አለባቸው።

@tikvahethiopia