TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዓድዋ128 #ዓድዋ ፕሬዝዳንት ሥህለወርቅ ዘውዴ በታሪካዊቷ ከተማ ዓድዋ ለሚከበረው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ላይ ለመገኘት ትግራይ ክልል ገብተዋል። ፕሬዝዳንቷ መቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ከመቐለ በሄልኮፕተር ወደ ዓድዋ በመጓዝ ላይ መሆናቸው በስፋት እየተነገረ ነው። የዓድዋ በዓል የፌደራል መንግስት ባካተተ መልኩ መከበር የቆመው ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ነበር።…
#ዓድዋ

128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ ፕረዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳይ ፣ የሕወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለልስጣናት ተገኝተዋል።

በበዓሉ ላይ የአፍሪካ ሕብረት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችም በዓሉን ለማታደም በስፍራው ተገኝተዋል። መኮንኖቹ በበዓሉ ስፍራ ሲደርሱ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በዓድዋ የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል በበዓሉ ላይ ከፍተኛ የሰው ቁጥር የታደመበት መሆኑን አመልክቷል።

ፎቶ፦ በቲክቫህ ቤተሰብ አባል እና ትግራይ ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በታሪካዊቷ ዓድዋ እየተካሄደ ባለው የዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ባንዴራ የመስቀል ስነ-ሰርዓት ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ፣ የትግራይ ክልል ፣ የአፍሪካ ህብረት ባንዴራ በፕረዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ እንዲሁም የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ተወካይ በሆኑት ሜጀር ጀነራል ስቴፈን ራድያ ተሰቅሏል።

የባንዲራ መስቀል ስነስርዓቱ በኢትዮጵያ 🇪🇹 ህዝብ ብሄራዊ መዝሙር ታጅቦ መከናወኑን በስፍራው የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ዓድዋ ሲደርሱ የተደረገላቸው አቀባበል።

#ኢትዮጵያ #ዓድዋ128

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በታሪካዊቷ ዓድዋ እየተካሄደ ባለው የዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ባንዴራ የመስቀል ስነ-ሰርዓት ተካሂዷል። የኢትዮጵያ፣ የትግራይ ክልል ፣ የአፍሪካ ህብረት ባንዴራ በፕረዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ እንዲሁም የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ተወካይ በሆኑት ሜጀር ጀነራል ስቴፈን ራድያ ተሰቅሏል። የባንዲራ መስቀል ስነስርዓቱ በኢትዮጵያ 🇪🇹 ህዝብ ብሄራዊ መዝሙር ታጅቦ…
#ዓድዋ128

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በታሪካዊቷ ዓድዋ እየተካሄደ ባለው ስነስርዓት ላይ ንግግር አድርገዋል።

" ድሉ በድምቀት እንድናከብር ያበቁን አባት አያቶቻችን ስንዘክር የአሁኑ ትውልድ አገርና ህዝብ የሚያሳድግ አንድነት ልማት ስር እንዲሰድ የሚያስችል እንቅስቃሴ በማድረግ መሆን ይገባዋል " ብለዋል።

ድሉ የመላው ኢትዮጵያውን ድል መሆኑን ያስታወሱት ጄነራል ታደሰ ፤ " የአሁኑ ትውልድ የአባት አያቶቹ ክብር በማስቀጠል ለአገርና ህዝብ አንድነት መስራት ይጠበቅበታል " ብለዋል።

ምክትል ፕሬዜዳንቱ ፤ " የ128ኛው የዓድዋ ድል መታሰብያ ስናከብር ደም አፋሳሹ የትግራይ ጦርነት ለማስቆም የተደረገው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተከትሎ ፦
የትግራይ ወሰን አለመከበሩ
ከቄያቸው የተፈናቀሉ እንዲመለሱ አለመደረጉ መዘንጋት አይገባም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የፌደራል መንግስት የገባውን ውል እንዲፈፅም አሁንም ጥሪያችን እናቀርባለን " ሲሉ ሌ/ ጀነራል ታደሰ ወረደ መናገራቸውም በዓድዋ የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል መረጃውን አድርሶናል።

#AdwaTikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዓድዋ128 የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በታሪካዊቷ ዓድዋ እየተካሄደ ባለው ስነስርዓት ላይ ንግግር አድርገዋል። " ድሉ በድምቀት እንድናከብር ያበቁን አባት አያቶቻችን ስንዘክር የአሁኑ ትውልድ አገርና ህዝብ የሚያሳድግ አንድነት ልማት ስር እንዲሰድ የሚያስችል እንቅስቃሴ በማድረግ መሆን ይገባዋል " ብለዋል። ድሉ የመላው ኢትዮጵያውን ድል መሆኑን ያስታወሱት…
" ደማቁ የዓድዋ የድል መታሰብያ በዓልን በእርስ በርስ ግጭት ማቆሸሽ አይገባም " - ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መልእክት አስተለልፈዋል።

ከ3 ዓመት ተኩል በኃላ በትግራይ ታሪካዊትዋ የዓድዋ ከተማ በመገኘት በዓሉን ለማክበር በመቻላቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

ፕረዚደንትዋ #እንባ_እየተናነቃቸው ያለፈውን አስከፊ ጦርነት በማስታወስ ፣ ተፈናቃዮች ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ በማንሳት ተናገረዋል።

" አሁን ከገባንበት እንድንወጣ ፈጣሪ ይርዳን ፤ በሃይማኖትና በዘር መከፋፈል ይብቃን " ብለዋል።

የበዓሉ ታዳሚ ህዝብ በፕረዚደንትዋ ስሜታዊ ንግግር እጅግ ስሜቱ መነካቱ ከፊቱ ማንበብ እንደቻለ በስፍራው የነበረው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነግሮናል።

" የችግሮቻችን ምንጭ እውቀን ከስሩ ለማድረቅ መስራት አለብን " ያሉት ፕሬዜዳንቷ ፤ " ከእርስ በርስ ጦርነት ጊዚያዊ አሸናፊ እንጂ ዘላቂ አሸናፊ የለም ፤ ስለሆነም ከዚሁ በመቆጠብ በአንድነት ቆመን አገራችን ከውጭ ወራሪ መታደግ ይገባናል " ብለዋል።

" ኢትዮጵያውያን የዓድዋ የድል ዘላቂ እንዲሆን ከተፈለገ ወንድም ወንድሙ ላይ ጦር ከማንሳት መቆጠብ አለብን " ሲሉ አሳስበዋል።

" የሃሳብ ልዩነታችን ከጠብመንጃ በመለስ በጠረጴዛ ውይይት የመፍታት ልማድ ሳይሆን ባህል መፍጠር አለብን። ያለፈው ይብቃ ከስህቶቻችን እንማር " ብለዋል።

በሌሎች ክልሎች የሚታየው ገጭትም በሰላም እንዲፈታ መስራትና መተባበር አለበን ሲሉ ተናግረዋል።

ደማቁን የዓድዋ የድል መታሰብያ በዓል በአርስ በርስ ግጭት ማቆሸሽ አይገባም ማለታቸውንም በስፍራው የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ገልጾልናል።

#TikvahFamilyAdawa

@tikvahethiopia