TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሳፋሪኮም ያልተገደበ ኢንተርኔት የምንወ​ደውን ሙዚቃ ያለምንም መቆራረጥ እናጣጥም! በ60 ብር ብቻ ያልተገደበ ዕለታዊ የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም የቻት ግሩፕ https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC https://t.iss.one/SafaricomETForum እንዲሁም @SafaricomETCare 24/7 መጠየቅ ይቻላል!

#SafaricomET
#FurtherAheadTogether
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether
በጋምቤላ_ክልል_የተለያዩ_አካባቢዎች_ከግንቦት_ወር_2015_ለያዩ_ያ_የደረሱ_የሰብአዊ_መብቶች_ጥሰቶችን.pdf
928.6 KB
#ጋምቤላ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፦

" ግንቦት 13/2015 ዓ.ም. በኢታንግ ልዩ ወረዳ ሥር በሚገኝ ፒኝዋ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩ አንድ ግለሰብ መጥፋታቸውን ተከትሎ፣ በፒኝዋ ቀበሌ እና አጎራባች በሆነው በሌር ቀበሌ ነዋሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት በወቅቱ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የግለሰቦች እና የተቋማት ንብረት ላይ ጉዳት እና ዘረፋ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚሁ ግጭት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በጎግ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ እና ጋምቤላ ከተማ ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ጥር ወር 2016 ዓ.ም. በተለያዩ ወቅቶች በሰዎች ሕይወት እና በንብረት ላይ ተጨማሪ ጉዳት ደርሷል።

ኢሰመኮ ማረጋገጥ በቻለው መረጃዎች እና ማስረጃዎች መሠረት ቢያንስ የ138 ሰዎች ሕይወት አልፏል ፣ 113 ሰዎች ላይ አካል ጉዳት ደርሷል ፤ በግለሰቦች እና ተቋማት ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። "

(ኢሰመኮ በጋምቤላ ክልል የተከሰቱ ግጭቶችና የፀጥታ መደፍረስ ሁኔታዎች ያስከተሉትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ የላከልን ባለ 15 ገፅ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በጋምቤላ_ክልል_የተለያዩ_አካባቢዎች_ከግንቦት_ወር_2015_ለያዩ_ያ_የደረሱ_የሰብአዊ_መብቶች_ጥሰቶችን.pdf
#ጋምቤላ

በጋምቤላ ብቻ እንዲህ ሆኖ ነበር ....

ከኢሰመኮ ሪፖርት ፦

ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ገደማ በጋምቤላ ከተማ፣ 04 ቀበሌ ብሔር ብሔረሰብ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አንድ ሰው እና ሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ትክክለኛ ቀኑ ባልታወቀበት ነገር ግን ሰዓቱ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት አካባቢ ዶምቦስኮ ትምህርት ቤት አካባቢ አንድ ሰው ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሰዎች ተገድለዋል።

ግንቦት 14/2015 ዓ/ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት አካባቢ 01 ቀበሌ ጀጀቤ ወንዝ አካባቢ 2 ሰዎች ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች በጥይት ተመትተው ሞተዋል።

01 ቀበሌ ጀጀቤ ተራራ አካባቢ ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ገደማ 7 ሰዎች በጥይት ተገድለዋል።

ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ አንድ በአካባቢው ማኅበረሰብ #የአእምሮ_ሕመም እንዳለበት የተገለጸ ሰው 04 ቀበሌ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አካባቢ #በቡድን በተሰባሰቡ ወጣቶች ጥቃት #በስለት_ተወግቶ ተገድሏል።

ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ገደማ 04 ቀበሌ ብሔር ብሔረሰብ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቁጥራቸው ከ200 በላይ የሚሆኑ ፦
* የቀድሞውን የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል፤
* የጋምቤላ ክልል መደበኛ ፖሊስ
* የጋምቤላ ክልል ሚሊሻ መለዮ ልብሶችን የለበሱ እና ሌሎች የታጠቁ ሰዎች በ3 የተለያየ አቅጣጫ በመግባት በቦታው የነበሩ 9 ሰዎችን በጥይት ገድለዋል፤ ሌሎች 4 ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት አካባቢ 04 ቀበሌ፣ ቄራ ሰፈር አጉኛ አካባቢ የታጠቁ ሰዎች ወደ አንድ መኖሪያ ቤት በመግባት ተኩስ ከፍተው፤ አንድ ሰው ሲገድሉ በሌላ አንድ ሰው ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፡፡

የኢሰመኮ ባለ15 ገፅ ሪፖርት ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/85541

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Kenya ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኬንያ እያደረጉት በሚገኘው ይፋዊ ጉብኝት በፕሬዝዳነት ዊልያም ሩቶ በስቴት ሀውስ ኬንያ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፤ " የአቀባበል ስነስርዓቱ ሁለቱ መሪዎች እና ልዑካን ቡድኖቻቸው በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ እያደርጓቸው ያሉ ጉልህ ግንኙነቶች እና ውይይቶች ጅማሮ ነው። " ብሏል። ሁለቱ መሪዎች በድይይታቸው…
#Update

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የጋራ መግለጫ ምን ይላል ?

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኬንያ ያስራ ጉብኝትን እና ከፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ያደረጉትን ምክክር ተከትሎ የኬንያ " ስቴት ሀውስ " የጋራ ነው ያለውን መግለጫ ዛሬ ምሽት አውጥቷል።

በዚህም መግለጫ ፤ ፕሬዚዳንት ሩቶ እና ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ ከአፍሪቃ ቀንድ ደህንነት ጋር በተያያዘ ፤ በአህጉሪቱ ውስጥ ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋትን ማስጠበቅ ለኢኮኖሚ እድገትና ልማት አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን አጽንኦት መስጠታቸው ተገልጿል።

በዚህም መሠረት ፤ ለሀገራት ግዛቶች ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እውቅና መስጠት ሉዓላዊነታቸውን ማክበርና ማስከበር እንደሚገባ አረጋግጠዋል።

ሕገ መንግሥታዊ ያልሆኑ የመንግሥት ለውጦችን እንዲሁም በአፍሪካ አገሮች የውስጥ ፖለቲካ የውጭ ጣልቃ መግባት እንደማይቀበሉት አስረግጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪ መሪዎቹ ፤ ሁለቱ ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በግብርና፣ አሳ ሀብት፣ ትራንስፖርት፣ አይሲቲ፣ ቱሪዝም፣ ጤና፣ ባህል እና ደን ልማት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።

(ከስቴት ሀውስ የወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ፒያሳ

በአዲስ አበባ ፤ ፒያሳ አካባቢ በተለምዶ " ዶሮ ማነቂያ " ተብሎ በሚጠራው ቦታ የሚገኙ ነዋሪዎች፤ በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ ከስፍራው እንዲነሱ ቀነ ገደብ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ምትክ የመኖሪያ እና የንግድ ቦታ ሳያዘጋጅላቸው፤ ከስፍራው " በአጭር ጊዜ ውስጥ " ተነሱ ማለቱ በነዋሪዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ አስነስቷል።

የፒያሳና 4 ኪሎ አካባቢ መልሶ የማልማት ፕሮጀክትን በተመለከተ ትላንት በወረዳ ደረጃ የተደረጉ ውይይቶች " በአለመግባባት " እና " በረብሻ " መበተናቸውን ተከትሎ ዛሬ ከአዲስ አበባ አስተዳደር እና ከአራዳ ክ/ከተማ የስራ ኃላፊዎች ጋር ነዋሪዎች ውይይት አድርገው ነበር።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

° በፒያሳ አካባቢ በአክሲዮን የተደራጁ ነዋሪዎች ማህበርን በሰብሳቢነት የሚመሩ ግለሰብ ፦

" ቤት ለመቀባት እንኳ 3 ቀናት ይበቃል ወይ? ትላንት በነበሩ ውይይቶች ይህንን ውሳኔ የሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ለሊቱን ሙሉ ሳይተኙ አድረዋል።አሁንም በስጋት ላይ ናቸው። "

° 5 አባላት ያሉት ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን የገለጹ እናት ፦

" አብዛኞቹ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደ እኔ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ናቸው። በስፍራው የታቀደው የመልሶ ማልማት ነዋሪዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ እና ምትክ የመኖሪያ ስፍራ ያዘጋጀ ሊሆን ይገባዋል። "

° ሌላኛዋ የአካባቢው ነዋሪ ፦

" ለልማት ተነሺዎች የሚያዘጋጀው አማራጭ የስፍራውን ማህበራዊ ትስስር በማይበጥስ መልኩ ሊደርግ ይገባል። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያለን የአካባቢው ነዋሪዎች እርስ በእርስ ተደጋግፈን የምንኖር በመሆናችን ምትክ የኮንዶሚኒየም ቤት የሚሰጠን ከሆነ በአንድ ቦታ ላይ የምንሰፍርበት ሁኔታ ይመቻች ። "

ከባለስልጣናት ምን ምላሽ ተሰጠ ?

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽህፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጥላሁን ፤ ነዋሪዎቹን ከቦታው ለማንሳት ያቀደው በዘጠና ቀናት ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል።

አስተዳደሩ ለነዋሪዎች  ምትክ የኮንዶሚኒየም፣ የቀበሌ እና የኪራይ ቤቶች እንደሚያዘጋጅ ቃል ገብተዋል። 

የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አበበ ተቀባ ፤ አስተዳደሩ " ቅደመ ሁኔታ ሳያሟላ አንድም ሰው አይነቃነቅም " ብለዋል።

የከተማው አስተዳደር " ቅደመ ሁኔታውን ካሟላ " ነዋሪዎች በ3 ቀን ቢነሱ ችግር እንደማይፈጥርም ጠቁመዋል።

" ይህ ፕሮጀክት እንዳያልቅ የሚያንጓትት ካለ ኃላፊነቱን ራሱ ነው የሚወስደው " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በዛሬው ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ በመልሶ ማልማቱ የልማት ተነሺዎቹን ሂደት የሚከታተል ኮሚቴ አባላት ምርጫ ተከናውኗል።

በመልሶ ማልማት እቅዱ የተካተተውን የፒያሳ አካባቢን በ6 በመክፈል፤ ከእያንዳንዱ ስፍራ 6 ሰዎች በህዝብ ተመርጠዋል። 

(ከላይ በፒያሳ ስለሚካሄደው መልሶ ማልማት ስራ ማብራሪያ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ የ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
#Tecno_Mobile

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ብራንድ የሆነው TECNO ሞባይል ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የዋጀ ምርቶቹን በMWC Barcelona አስተዋወቀ !

በኤግዚቢሽኑ ላይ ከቀረቡት የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል Dynamic 1 ፣ የመጀመሪያው የሆነው AI- ሮቦት ውሻ እና Pocket Go ይገኙበታል ። Pocket Go የተሰኝው የፈጠራ ውጤት የኢንዱስትሪው የመጀመሪያ የሆነው  የኤአር መነፅር እና የዊንዶውስ ጌሚንግን ያጣመረ የቴክኖሎጂ  ውጤት ነው ። በተጨማሪም አዲሱን የPolarAce የተሰኘ AIን የሚጠቀም ኢሜጂንግ ሲስተም በዝግጅቱ ላይ አስተዋውቋል ።

#TecnoMobile #Tecno
#መቐለ
 
" ባለ ውለታ ይከበራል እንጂ ፤  በረሃብና በሽታ አይቀጣም " - የትግራይ ጡረተኞች

የትግራይ ጡረተኞች ዛሬ የካቲት 21/2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።

ሰልፎኞቹ በመቐለ ከተማ ባካሂዱት ሰልፍ :- 
- የትግራይ ጡረተኞች ድምፅ ይሰማ !!
- የ18 ወራት ውዙፍ አበል በአስቸኳይ ይከፈለን !
- የፕሪቶሪያ ውል በአስቸኳይ ይተግበር !
- የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የጡረተኞች መብት ያክብር ያስከብር !!
- መንግስት የጡረተኞች አዋጅና ደንብ ያክብር ! 
- ባለ ውለታ ይከበራል እንጂ ፤ በረሃብና በሽታ አይቀጣም !!
- የዓለም አቀፍ ተቋማት የት ናችሁ ? !

የሚሉ መፈክሮች እያሰሙ በከተማዋ በዋና ዋና መንገዶች ተዘዋውረዋል። 

የጡረተኞቹን ሰላማዊ ጥያቄ ያዳመጠውና የተቀበለው በኢፌዲሪ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የሰሜን ሪጅን ቅርንጫፍ ፤ የታህሳስ 2015 ዓ.ም የውል አበል በተያዘው ሳምንት ለመከፈል መዘጋጀቱን ፤ ቀሪ የ18 ወራት የጡረታ አበል እንዲከፈል ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደርና ከፌደራል መንግስት በመነጋገር ላይ መሆኑ አስታውቋል።

መረጃው በመቐለው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia            
#ጋና

የጋና ፓርላማ ከተመሳሳይ ፆታ ግንኙነቶች እና በዚህ ዙሪያ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ በሚከሰሱ ሰዎች ላይ ጠንከር ባለ እስር የሚቀጣ ሕግ አጽድቋል።

አዲሱ ሕግ ምን ይላል ?

በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ውስጥ መሆናቸውን የሚገልጹ እንዲሁም ሆነው የተገኙ ሰዎችን እስከ 3 ዓመት የሚደርስ እስር ፤

ቡድኖችን የሚያቋቁሙ እና በገንዘብ የሚደግፉ እስከ 5 ዓመት እስር እንዲቀጡ ያደርጋል።

በአገሪቱ ሁለት ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተደገፈው እና ፓርላማው ያጸደቀው ይህ ሕግ ተግባራዊ የሚሆነው የጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ-አዶ በፊርማቸው ሲያጸድቁት ነው።

ፕሬዝዳንቱ ቀደም ሲል አብዛኛው የአገሪቱ ዜጎች የሚፈልጉት ከሆነ ሕጉን እንደሚያጸድቁት ተናግረው ነበር።

የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት በጋና ውስጥ ቀደም ብሎም ሕገወጥ ሆኖ በ3 ዓመት እስር የሚያስቀጣ ነው።

አዲሱ የጋና ሕግ በተለይ ህጻናት ላይ አተኩሮ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ለማስተዋወቅ በሚደረግ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የተሳተፈ ማንኛውም ሰው አስከ 10 ዓመት የሚደርስ እስር የሚቀጣ ነው።

ባለሥልጣናት “ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ” ለማስቻል ሕብረተሰቡ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ማኅበራት አባላትን እንዲጠቁሙ ሕጉ ያበረታታል።

ይህ ሕግ እንዲረቅ ምክንያት የሆነው ከ3 ዓመት በፊት በጋና ዋና ከተማ አክራ የመጀመሪያው የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የማኅበረሰብ ማዕከል መከፈቱን ተከትሎ እንደሆነ የፓርላማ አባላቱ ተናግረዋል።

ይህንንም ተከትሎ ብዙኃኑ ክርስቲያን በሆነባት ጋና የሃይማኖት እና ባህላዊ መሪዎች በፈጠሩት ግፊት ሕዝባዊ ተቃውሞ በመቀስቀሱ ፖሊስ ማዕከሉ እንዲዘጋ አድርጓል።

በወቅቱ የጋና የክርስትና እምነት ማኅበራት ባወጡት የጋራ መግለጫ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት “ ለአገሪቱ ባህል እና የቤተሰብ ዕሴት እንግዳ በመሆኑ የጋና ዜጎች ሊቀበሉት አይችሉም ” ሲሉ ተቀውመዋል።

የተለያዩ አገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የጋና ፓርላማ ያጸደቀውን ሕግ በመቃወም አስተያየት እየሰጡ ነው።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
📣 አዲስ ነገር ይዘን መጥተናል!

👉ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22  ፓኬጅ ሲያሳድጉ...እኛም ቀጣዩን ፓኬጅ ለአንድ ወር እንጋብዝዎታለን!

ይህ አገልግሎት ክፍያ ከፈፀሙ ከ48 ሰዓት በኋላ ተግባራዊ ይሆናል።

*ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።

ለሚሰጡን አስተያየት በቅድሚያ እያመሰገንን፣ ስለ አገልግሎታችን ጥራት የሚደርስዎትን የፅሁፍ መልዕክት ሊንኩን በመጫን መጠይቁን እንዲሞሉ በትህትና እንጠይቃለን።

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET #StepUp