TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢንተርኔት እንደልብ በሽ በሽ ነው!
ባልተገደበ ኢንተርኔት እንደፈለግነው ፈታ ነው!

በ999 ብር ብቻ ያልተገደበ ወርሃዊ የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ! በእንደልብ ኢንተርኔት ወደፊት!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም የቻት ግሩፕ @SafaricomETForum እንዲሁም @SafaricomETCare
24/7 መጠየቅ ይቻላል!

#SafaricomET
#FurtherAheadTogether
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether
#ሴጅ_ማሰልጠኛ

የካፒታል ማርኬት ገበያ በኢትዮጵያ ሊጀመር ነው:: እርስዎም ኢንስቲትዩታችን ውስጥ የሚሰጠውን የፋይናንስና ካፒታል ማርኬት ስልጠና በመውሰድ ራስዎን ለትግበራው ያዘጋጁ። ብቁ በሆኑ መምህራን የሚሰጠው ስልጠናው ከመሰረታዊ የካፒታል ገበያ ምንነት አንስቶ እንዴት አንድ ግለሰብ ወይም ተቋም ከስጋት ነፃ በሆነ መንገድ በገበያው ላይ መሳተፍ እንደሚችል ግልፅ ያደርጋል::

ስልጠናውን ይውሰዱና ትግበራውን ይጠባበቁ!

ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ

Telegram: https://t.iss.one/sagetraininginstitute
Facebook: https://www.facebook.com/sagetraininginstitute
Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute

የበለጠ ይጠብቁ ...
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ የምክር ቤቱ አባል የሆኑት የዶ/ር ካሣ ተሻገርን ያለመከሰስ መብት  አንስቷል።

ምክር ቤቱ በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔው ዶ/ር ካሣ ተሻገር ላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ክስ መመስረት እንዲቻል የፍትህ ሚኒስቴር ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ያለመከሰስ መብታቸውን መነሳቱ ተነግሯል።

ዶ/ር ካሣ ተሻገር ከወራት በፊት መታሰራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Axum

ትላንት ምሽት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ፅዮን ቅጥር ግቢ የእሳት ቃጠሎ  አደጋ አጋጥሞ ነበር።

የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ታማኝ ምንጮች እንዳሉት ፡ የካቲት 15/2016 ዓ.ም ከ 2:30 ምሽት ጀምሮ " እንዳ ፍሕሚ " ተብሎ በሚጠራውና ፅላቱ በሚቀመጥበት አከባቢ ነው የእሳት ቃጠሎ የተነሳው።

ባጋጠመው የእሳት አደጋ ቃጠሎ በሰው ህይወት ያጋጠመ አደጋ እንደሌለ የገለፁት የቲክቫህ ምንጮች ፤ ቃጠሎድ በከተማው ነዋሪዎችና በፀጥታ አካላት ከፍተኛ ተሳትፎ በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።   

የትግራይ ማእከላይ ዞን ፓሊስ የካቲት 15/2016 አመሻሽ በማህበራዊ የትስስር ገፁ  " የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ስር ውሏል " ከማለት ውጪ ያለው የለም። 

በርካታ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ፀሃፊዎች የእሳት አደጋ ቃጠሎው ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንዲሆንና ፣ ቅዱስ ቦታ ከተመሳሳይ አደጋ ለመታደግ የሚመጠነው ጥበቃ ያሻዋል የሚሉ አስተያየቶች በብዛት በማንሸራሸር ላይ እንደሚገኙ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
                             
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
የግብፁ መሪ የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብፅን እንዲጎበኙ ግብዣ አደረጉ። ከቀናት በፊት ለሶማሊያው ፕሬዜዳንት ተመሳሳይ መልዕክት መላካቸው ይታወሳል። የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአስመራ ቆይታቸው ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝተው ነበር። በዚህም ወቅት ከፕሬዜዳንት አልሲሲ የተላከ መልዕክት አድርሰዋል…
የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ ግብፅ ካይሮ ገብተዋል።

ካይሮ ሲደርሱ የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሁለቱ አካላት በሁለትዮሽ እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል።

ከወራት በፊት የግብፁ መሪ የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብፅን እንዲጎበኙ ግብዣ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ግብፅ ግብዣውን አቅርባ የነበረው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሳሜህ ሽኩሪ በኤርትራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው።

ሚኒስትሩ ወደ ኤርትራ ለጉብኝት የሄዱት የኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመና ከማንም ቀድማ ስምምነቱን #በመቃወም አቋሟን ካሳወቀች በኃላ ነው።

ለኤርትራው መሪ ግብዣ ከመቅረቡ ቀደም ብሎ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ በነበረበት ወቅት የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ተመሳሳይ ግብፅን ይጎብኙ የሚል መልዕክት ማድረሳቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#Attention

የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ፤ ከዛሬ ጀምሮ የትኛውም አይነት የትራንስፖርት አገልግሎት ከደሴ - ሸዋሮቢት_ ደ/ብረሀን እንዲሁም ከደ/ብረሀን -ሸዋሮቢት - ደሴ እንዲቆም ውሳኔ መተላለፉን አሳውቋል።

የትራንስፖርት እንቅስቃሴው እንዲቆመ የተደረገው ኮማንድ ፖስቱ " ፅንፈኛ " ባላቸው ታጣቂዎች ላይ ኦፕሬሽን በመጀመሩና ቀጠናውን ነፃ ለማድረግ እርምጃ መውሰድ በመጀመሩ እንደሆነ ተገልጿል።

በመሆኑም በቀጠናው የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቆም የተወሰነው ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ መሆኑን ያሳወቀው ኮማንድ ፖስቱ ውሳኔው ለጊዜው ነው ብሏል።

ህብረተሰቡ ከዛሬ ጀምሮ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ #እንዲቆም የተወሰነ መሆኑ እንዲያውቅና አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ፤ የፀጥታ ሀይሉም ውሳኔው እንዲፈፀም ክትትል እንዲያደርግ ትዕዛዝ መሰጡቱ ታውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጥንታዊውና ታሪካዊው ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አራት መነኮሳት በ " ኦነግ ሸኔ " ታጣቂዎች መገደላቸው አንድ አባት ደግሞ አምልጠው ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ መነገሩ ይወሳል። ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ምክትል ኃላፊ መላከሰላም ቀሲስ ዳዊት ያሬድ በሰጡት ቃል ፤ " ከተገደሉት አባቶች መካከል ያልተገኙ አንደኛው…
#Update

በታጣቂዎች በግፍ የተገደሉት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች አስክሬን ተረሽነው ከተቀበሩበት ከጊዳ ተክለሃይማኖት አካባቢ ተነስቶ በገዳሙ በክብር ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ።

ሰኞ የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ/ም በ " ኦነግ ሸኔ " ታጣቂዎች እንደተገደሉ የተገለፀው ፦
-  የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራትን
- የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
- የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
- በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም አስክሬን ተረሽነው ከተቀበሩበት በረሀማው ከጊዳ ተክለሃይማኖት አካባቢ ተነስቶ በገዳሙ በክብር ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ተፈጽሟል።

ለጊዜው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለገዳሙ ጥበቃ እያደረገ ሲሆን ነገሮች እስኪረጋጉ ጥበቃው እንዲቀጥል ገዳሙ መጠየቁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
ለቴሌግራም ተከታዮቻችን፡ የሚያሸልም ጥያቄ

ነገ እሁድ በካራባኦ ዋንጫ ፍፃሜ ቼልሲ እና ሊቨርፑል የሚያደርጉትን ጨዋታ በትክክል ለሚገምቱ 4 የቴሌግራም ተከታዮቻችን ሽልማት አዘጋጅተናል፡፡

1. የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቴሌግራም https://t.iss.one/+BiR6VdrAieQ3NzRk ገፅን ይከተሉ፡፡
2. ምላሽ ማስተካከል ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
3. ትክክለኛ መላሾች ከ 4 በላይ ከሆኑ አሸናፊዎቹን የምንለየው በዕጣ ይሆናል፡፡

መልካም ዕድል!!

#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #Bank #GBE #CheLiv #chelsea #Liverpool #CarabaoCup
#Infinix_Hot40

የሚወዷቸውን ጌሞች በልዩ ጥራት እና ፍጥነት በአዲሱ ኢንፊኒክስ ‘Hot 40 pro’ ስልክ ይጫወቱ!

#InfinixEthiopia #InfinixMobile #Infinix_Hot40 #Infinix_HotSeries
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የመፍረስ አደጋ ተደቅኖብኛል " - የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ

" ቅሬታዎችን ተቀብለን እየመረመርን ነው " - የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

ከወራት በፊት የሲዳማ ክልል የጸጥታ ሀይሎች የቀድሞ አባል የነበረና ከፓርቲዉ ጋር በገባዉ ግጭት ምክኒያት በዲስፕሊን የተገለለን ግለሰብ ወደ ፓርቲዉ ቢሮ ይዘዉ በመምጣት ቢሯችን ተሰብሮ የተለያዩ ንብረቶች አዘርፈዉብናል ማለታቸዉና ጉዳዩንም ወደምርጫ ቦርድ በመዉሰድ ክስ መመስረታቸዉ ይታወሳል።

ይህ ክስ እልባት ባላገኘበት ሁኔታ ደግሞ ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ አካሄዶችን በተቃረነ መልኩ ጣልቃ በመግባት የፓርቲዉን ህልዉና አደጋ ላይ በሚጥሉ  አካላት ላይ የተወሰነዉን ዉሳኔ  በማያገባዉ ገብቶ ዉድቅ አድርጎብኛል በማለት ቅሬታዉን ለቲክቫህ ኢትዮጽያ አቅርቧል።

ፓርቲዉ ህጋዊ አካሄዶችን ተከትሎና በዉስጡ ሊያጠፉት የሚተጉ አባላቶችን ድርጊት መርምሮ የዲስፕሊን ግድፈት በሚል ከወራት በፊት የዉሳኔዉን  ቃለ ጉባኤ ለምርጫ ቦርድ ማስገባቱን የሚያነሱት የፓርቲዉ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ ሆሳና ከወራት መዘግየት በኋላ እንደገና ቃለጉባኤ ተጠይቀናል ይላሉ።

ይሁንና ቢሯችን በህገወጥ ሀይሎች ተሰብሮ ዶክሜንቶች በመወሰዳቸዉና አሁንም ወደቢሮ መግባት ባለመቻላችን በድጋሜ ቃለጉባኤ ማቅረብ አልቻልንም ብለዋል።

አቶ ገነነ አሁን ላይ አስራ ሁለቱ የፓርቲዉ ስራ አስፈጻሚ ከቢሮ ዉጭ በሆነበት ወቅት " ድጋሜ ቃለ ጉባኤ ካልመጣ " በሚል የምርጫ ቦርድ ዉሳኔያችን ዉድቅ ሊያደርግብን አይገባም በማለት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሀላፊን ለማነጋገር  የተወከሉ የፓርቲዉ አመራሮች ቢላኩም " ሀሳባችሁን ለሌላ ጊዜ በደብዳቤ ይዛችሁ ተመለሱ " መባሉ በጣም አሳዝኖናል በማለት ቅሬታቸዉን አቅርበዋል።

በጉዳዩ ላይ በኮምዩኒኬሽን ክፍሉ በኩል ምላሽ የሰጠን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንደገለፀው የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን በፓርቲውን ተቀዳሚ ሊቀ-መንበርና በሌሎች አራት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ላይ ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. የዕግድ ውሣኔ መስጠቱን አስታዉሷል።

ይኽ ውሣኔ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ለፓርቲው የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ ቀርቦ ያለመታየቱንና ውሣኔውም የተሰጠው ሥልጣን በሌለው አካል መሆኑን ቦርዱ እንዳረጋገጠ ገልጿል።

በዚህም በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 36 እና ተከታዮቹ ደንቦች መሠረት እንዲኽ ዓይነት ውሣኔ በፓርቲው የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ የሚታይ መሆኑን በመግለጽ ቀድሞ የተሰጠውን የዕግድ ውሣኔ ውድቅ መደረጉን መስከረም 2 ቀን 2016 ዓ.ም. እና መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም  በተጻፉ ሁለት ደብዳቤዎች ቦርዱ ለፓርቲው ማሳዎቁን ገልጿል።

ፓርቲው እነዚኽ ሁለት ደብዳቤዎች ሲደርሱት ጉዳዩን በሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ እንዲታይ አድርጊያለሁ በማለት ቀደም ሲል ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበሩን ጨምሮ በሦስቱ የማዕከላዊ ኮሚት አባላት ላይ የተሰጠው ከኃላፊነት አንስቻለሁ የሚል ውሣኔ በመቀየር ውሣኔ አስተላልፌያለሁ በማለት ኅዳር 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ለቦርዱ ገልጿል።

ቦርዱም ይኽ ደብዳቤ እንደደረሰው የፓርቲው የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ የተቋቋመው አግባብነት ያላቸውን ሕጎች ተከትሎ መሆኑን ለማረጋገጥ ይረዳው ዘንድ፤ ኮሚቴው የተፈራረመበት ቃለ-ጉባዔ እንዲቀርብለት የጠየቀ ሲሆን ይሁንና ቃለ-ጉባዔው ለቦርዱ እንዳልቀረበለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።

በመሆኑም ኮሚቴው ሰጠ የተባለው ውሣኔ ውድቅ እንዲሆን ተደርጓል።

በዚኽም የቦርዱ ውሣኔ ላይ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. የተጻፈ አቤቱታ ለቦርዱ ቀርቦ እየተመረመረ ይገኛል በማለት ምላሽ ሰጥቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ሰው በእሳት አይተዳደርም " - ጃርሶ ዱጎ

ከቀናት በፊት 75ኛው የጉጂ አባገዳ በመሆን ለቀጣይ 8 ዓመታት ኃላፊነቱን የተረከቡት ጃርሶ ዱጎ ስለ ሰላም ምን አሉ ?

አባገዳ ጃርሶ ዱጎ ፦

" የተሰጠኝ ኃላፊነት ቀላል አይደለም። ገዳ ደግሞ ሰላም ነው። ከችግር እና መከራ መውጫ መንገድም ጭምር።

ባለፈው የገዳ ሃርሙፋ የሥልጣን ዘመን ቀዳዳዎች ነበሩ። ሰው መግባባት ተሳነው። ሰው ተቀምጦ ማረስ ህይወቱን መምራት አለበት። ለዚህ ደግሞ ሰላም መሰረት ነው። ሰላም ማስፈን ከቻልን ጉጂ በሰላም ያድራል። ኦሮሞ ሁሉ ሰላም ይሆናል።

የተሰጠንን ኃላፊነት ይዘን ይህን ህዝብ ማስተዳደር እንዲቻለን በሰላም ላይ ነው በአጽንኦት መሥራት ያለብን።

ሰላም መውረድ አለበት። ተመካክረን ሰላም ማምጣት የግድ ነው። ጦርነት መልካም ነገር አይደለም። ሰው በእሳት አይተዳደርም። ተደማምጠን ይህን ገዳ ሮባሌን የጥጋብና የሰላም ማድረግ አለብን።

... በዚህ ገዳ አገዛዝ ውስጥ ምንም አይነት የጥይት ድምጽ እንዳይሰማ ገዳ ጦርነት ሳይሆን ሰላም ያውጃል። "

@tikvahethiopia
#JASIRI: ታለንት ኢንቨስተር

- ለፈጣን ዕድገት አቅም ካላችሁ እና አዲስ ቢዝነስ ለመፍጠር ከቆረጣችሁ፤

- በማንኛናውም ዘርፍ ውስጥ ክፍተቶችን መለየት እና እድሎችን ማወቅ ከቻሉ፤

- ትኩረት ባደረጋቹበት ቦታ ሁሉ የስኬት፣ የችግር አፈታት እና ዋጋ የመፍጠር ልምድ ካላቹ፤

- በሙያዊ መስካችሁ ከፍተኛ መረጃ እና እውቀት ያላቹ ከሆነ፤

- በቡድናቹ ውስጥ ካሉ ተመሳሳይ ትልቅ ፍላጎት ካላቸው መስራቾች ጋር ለመገናኘት እና ከመሰረቱ ቬንቸር ለመገንባት እና በቡድን ለመስራት ዝግጁ ከሆናችሁ፤

- ስራዎን በሙሉ ጊዜ ለመገንባት ቃል ገብታቹ እና በሁሉም ታለንት ኢንቬስተር ደረጃዎች ለ14ወራት እንዲሁም በሩዋንዳ ባለው ፕሮግራም ለ3 ወር ተገኝታቹ በንቃት ለመሳተፍ ዝግጁ ከሆናቹ፤

አሁኑኑ በ jasiri.org/application ላይ ይመዝገቡ

ሴት ስራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ በጣም እናበረታታለን!