#HawassaUniversity
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መውጫና የሙያ ፈቃድ ፈተና ከወሰዱት የህክምናና ጤና ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎቹ 99% ተፈታኞች ፈተናውን አልፈው ለመመረቅ ብቁ መሆናቸውን አሳውቋል።
ተቋሙ ይፋ ባደረገው ዳታ ፤ በ ' ዶክተር ኦፍ ሜዲስን ' ካስፈተናቸው 190 ተመራቂዎች 189 ተመራቂዎች የተሰጣቸውን ፈተና አልፈዋል።
More 👉 @tikvahuniversity

TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለሽያጭ አቅርቧል። ኮርፖሬሽኑ ፤ " ያለብኝን የፋይናንስ እጥረት በመፍታት ተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቼ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንድችል ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው #የተጠናቀቁ ፦ ➡️ 3,146 የመኖሪያ ቤቶችን ➡️ 306 የንግድ…
#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለሽያጭ ማቅረቡ ይታወቃል።
ኮርፖሬሽኑ ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው የተጠናቀቁ ፦
➡️ 3,146 የመኖሪያ ቤቶችን
➡️ 306 የንግድ ቤቶችን በድምሩ 3,452 ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ ነው በጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ የፈለገው።
የዚሁ የመኖሪያ እና ንግድ ቤቶች ጨረታ ሰነድ እየተሸጠ ሲሆን #ቀነገደቡ በቀን 20/06/2016 ዓ/ም ያበቃል።
ማንኛውም ለጨረታ የቀረቡ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን ለመግዛት የሚፈልግ ሰው ሁሉ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል።
ኮርፖሬሽኑ ፤ የመኖሪያና የንግድ ቤቶቹን በጨረታ ለሽያጭ ያቀረብኩት ያለብኝን የፋይናንስ እጥረት በመፍታት ተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቼ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንድችል ነው ብሏል።
የጨረታ ሰነድ መሸጫ ቦታዎችን በዚህ ሊንክ መመልከት ይቻላል👇
https://t.iss.one/tikvahethiopia/84877
ከመኖሪያ እና ንግድ ቤቶች ጨረታ መውጣት ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉና ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪዎች ምንም እንኳን ለሽያጭ የቀረቡት ቤቶች በካፒታል በጀት የተሰሩ ቢሆንም እኛ ለዓመታት ከምንበላው ቀንሰን ስንቆጥብ የቆየን እና ቤት ለማግኘት ተመዝግበን በስንት ተስፋ እየጠበቅን የምንገኝ ነዋሪዎችን ያላማከለ ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጣይ ቀናት በመንግሥት አማካኝነት የቤቶች ጨረታ ማውጣት ላይ ቅሬታ አለን የሚሉ ወገኖችን እንዲሁም ለቅሬታው በሚመለከተው አካል የሚሰጥ ምላሽ ካለ የሚያቀርብ ይሆናል።
@tikvahethiopia

#አቢሲንያ_ባንክ
ከአፖሎ መበደር ከእናት ኪስ እንደመበደር ነው።
አፖሎን በመጠቀም አነስተኛ ብድር ያለምንም ማስያዣ በአነስተኛ የአገልግሎት ክፍያ ይውሰዱ። መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628 #Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

#Hawassa
ከሰሞኑ በሀዋሳ ከተማ የሚከሰተዉን የዋይፋይ (WiFi) አገልግሎት መቋረጥ ተከትሎ በርካቶች ስራችን ላይ እንቅፋት እየተፈጠረ ነው ሲሉ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
እየተፈጠረ ላለው ችግር ኢትዮ ቴሌኮም አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ሲያስተካክለዉ ቢታይም አገልግሎቱ 24 ሰአት እንኳን ሳይቆይ መልሶ ሲቋረጥ ይስተዋላል።
በዚህም ተገልጋዮች ላልተገባ ወጭ እና እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም የደረሱትን ቅሬታዎች ይዞ የሚመለከተውን አካል አነጋግሯል።
በጉዳዩ ላይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው በኢትዮ ቴሎኮም ፤ የደቡብ ሪጅን ዳይሬክተሩ አቶ ጁነዲን አብዱልቃድር " ችግሩ መኖሩ ግልጽ ነው " በማለት አሁን ላይ እንዲህ ያለው የስርቆት ሁኔታ በሁሉም አካባቢ አሳሳቢ መሆኑን ያነሳሉ።
አቶ ጁነዲን አክለዉም ፤ ኬብሉ ከውጭ በውድ ገንዘብ ተገዝቶ ለማህበረሰቡ አገልግሎት የሚውል በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ ማህበረሰቡ ከፖሊስ ጋር ተጣምሮ ሊጠብቀው ይገባል ብለዋል።
በዚህ በኩል በሀዋሳም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ትልቅ እንቅስቃሴ መኖሩን የገለፁት ደግሞ በሪጅኑ የህግ ጉዳይ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ተድላመድህን ቀለመወርቅ ፤ " እስካሁን በተደረጉ እንቅስቃሴዎችም በርካታ ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ስርቆቱ #በሀዋሳ እና #ሻሸመኔ ከፍ ያለ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ተድላመድህን ካለፈዉ ሀምሌ 1 እስከ ታህሳስ 30 እንኳን በሀዋሳ ከተማ ብቻ 4 መዝገብ ላይ ውሳኔ ተሰጥቶ ከስድስት እስከ ሁለት አመት እስራት መፈረዱን አንስተዋል።
በሀገር ደረጃ የመሰረተልማት እንቅስቃሴዎችን ለመጠበቅ ታስቦ የወጣዉን 464/67 የተባለ አዋጅ መሰረት አድርጎ ያለመክሰስ ያለመመርመርና ውሳኔ አለመስጠት ችግር ፈተና እንደሆነባቸው ገልጸዋል።
የሚሰጡ ውሳኔዎች እስከ 20 አመት የሚዘልቁ ቢሆኑም ያ እየሆነ አለመሆኑን የሚገልጹት ስራ አስኪያጁ " በዚህ ቻሌንጅ ውስጥ ሆነንም ቢሆን አስተማሪ የሆኑ ውሳኔዎች እንዲሰጡ እየሰራን ነው " ብለዋል።
መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በሀዋሳዉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

" የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት አገልግሎቶች ተቋርጠዋል " - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ በባንኩ መረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም ፦
➡ በቅርንጫፎች፥
➡ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥
➡ በሞባይል ባንኪንግ፥
➡ በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመ አሳውቋል።
ባንኩ በምን ምክንያት ጉዳት እንደደረሰ ፣ የት ቦታ እንደሆነ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።
" አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት በከፍተኛ እርብርብ እየተሰራ ነው " ያለው ንግድ ባንክ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል።
ለተፈጠረው መጉላላትም ይቅርታ ጠይቋል።

" የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት አገልግሎቶች ተቋርጠዋል " - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ በባንኩ መረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም ፦ ➡ በቅርንጫፎች፥ ➡ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ ➡ በሞባይል ባንኪንግ፥ ➡ በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመ አሳውቋል። ባንኩ በምን ምክንያት ጉዳት…
" ችግሩ ተስተካክሏል " - ንግድ ባንክ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ በባንኩ መረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ ተፈጥሮ የነበረው ችግር መስተካከሉን ገልጿል።
በዚህም ፦
➡ በቅርንጫፎች፥
➡ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥
➡ በሞባይል ባንኪንግ፥
➡ በሲቢኢ ብር ላይ ተቋርጦ የነበረው አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መጀመሩን አመልክቷል።
ባንኩ ተፈጥሮ ለነበረው የአገልግሎት መስተጓጎልም ይቅርታ ጠይቋል።

ወዳጆችዎ ቴሌብር ሱፐርአፕ እንዲጠቀሙ ይጋብዙ፤ ሥጦታ ያግኙ!
ቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/fpgu4m ግርጌ ‘መለያ’ የሚለው አማራጭ ውስጥ ‘ይጋብዙ ይሸለሙ’ የሚለውን በመምረጥ በአጭር መልዕክት ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ቴሌብር ሱፐርአፕን ያጋሩ፤ ወዳጆችዎ በመተግበሪያው ግብይት ሲጀምሩ ለእርስዎ የአየር ሰዓት እና ጥቅል የሚገዙበት የ10 ብር ስጦታ እንሸልማለን!
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

#AddisAbaba #የተማሪዎችምገባ
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ፤ የውሃና የመሰረተ ልማት አቅርቦቶች በትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚከናወነው የምገባ ሥርዓት ፈተና መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።
ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገው የነበረው በአ/አ ት/ት ቢሮ የተማሪዎች ምገባ ባለሙያ አቶ አለሙ ሀይሉ ፥ የምገባ ሥርዓቱ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ትልቁ አጋዥ ነገር እንደሆነ አስረድተዋል።
የሥርዓቱ በት/ቤቶች መኖር ዘርፈ ብዙ ውጤቶች እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል።
ነገር ግን በዚህ ሂደት አንዳንድ ተግዳሮቶች እንዳሉ አንስተዋል።
ምንም እንኳን ካሁን በፊት ከነበረው አንፃር ሲታይ በርካታ ለውጦች ቢኖሩም #የውሃ_አቅርቦት ችግር ተግዳሮት መሆኑን አመልክተዋል።
በተለይ ምገባ ላይ ብዙ ውሃ እንደሚያስፈልግ የገለፁት አቶ አለሙ ፤ " 5 የምገባ ቀናቶች አሉ (ከሰኞ እስከ ዓርብ) በእነዚህ ቀናት መካከል የውሃ አቅርቦቱ እንደተፈለገ የማይሆንበት ጊዜ አለ " ብለዋል።
ችግሩን ለመቅረፍም አማራጮች እየተወሰዱ መሆኑና ተጨማሪ የውሃ ታንከር ጥቅም ላይ እንደሚውል አስረድተዋል።
አንዳንድ ት/ቤቶችን በተባለው ቀንም አድሬስ ከማድረግ አኳያ ችግሮች እንዳሉ ገልጸው " ከዚያ አኳያ ውሃ ነው መታገዝ ያለበት " ሲሉ አሳስበዋል።
ሌላው በመንግሥት እንዲሁም በዓለም ባንክ የተሰሩ የምገባ አዳራሾች የመብራት አቅርቦት እንዲኖራቸው ከማድረግ ጋር ተያይዞ በተወሰነ ደረጃ ተግዳሮት እንዳለ አመልክተዋል።
ምንም እንኳን የምገባ አዳራሾች ቢኖሩም ምግብ ለማብሰያ የሚሆን #የመብራት_ኃይል አቅርቦት ላይ የተወሰኑ ተግዳሮቶች እንዳሉ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በት/ቤቶች ምገባ ሥራ ተሰማርተው ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ ሰዎች በተለይ #ከኑሮ_ውድነቱ አኳያ ሲታይ የሚከፈላቸው ክፍያ " በጣም አነስተኛ ነው " በማለት ሲያማርሩ ይደመጣሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህንኑ ምሬታቸውን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።
አቶ አለሙ ፤ " ከምገባ ክፍያ ጋር ተያይዞ እየቀረበ ያለው በየጊዜው እንደዬ ኑሮ ሁኔታው እየታዬ ይሻሻላል። " ብለዋል።
" ለምሳሌ ያለውን የኑሮ ሁኔታ ማዕከል ያደረገ ጥናት በማድረግ ወደ #23 ብር በተማሪ (በነፍስ ወከፍ) እንዲያድግ ተደርጓል " ሲሉ ገልጸዋል።
" በዚህ ዓመት ለምገባ ፕሮግራሙ መጠቀም ያለባቸው ተብሎ የተመደበው ወደ 3.2 ቢሊዮን ብር ነው " ሲሉ አክለዋል።
" በዚያ ደረጃ የተወሰኑ ማሻሻያዎች እየተደረጉ ይኬዳል ማለት ነው። ሲጀመር (የምገባው ፕሮግራሙ) በ14 ብር ነበር አሁን #23 ብር የደረሰበት ሁኔታ አለ። ለቀጣይ ደግሞ ወቅቱን ባገናዘበ ሁኔታ እየተጠና የሚሻሻልበት አሰራሮች አሉ " ሲሉ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መረጃ ያገኘው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከሳምንት በፊት ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን የምግብና ሥርዓተ ምግባ ቅንጅታዊ አሰራርን አስመልክቶ የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ሲያደርግ በነበረበት ወቅት ጥያቄ አቅርቦ ነው።
መረጃው የተዘጋጀው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

" የትግራይና የአማራ ሊህቃን ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው " - አቶ ከበደ አሰፋ
የትንሳኤ 70 እንደርታ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ከበደ አሰፋ፣ በመቐለ ዙሪያ ስለሚስተዋለው፦
* የመሬት ሊዝ ሁኔታ፣
* ስለወልቃይትና ራያ ተፈናቃዮች፣
* ስለፕሪቶሪያው ስምምነት የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
አቶ ከበደ በመቐለ ዙሪያ የመሬት ጉዳይ ምን አሉ?
➡ 70 እንደርታ ውስጥ፣ እንደ አጠቃላይ መቐለና ዙሪያው ያለውን የመሬት ወረራ በልዩ ሁኔታ እንቃወማለን። ይሄ የመሬት ፓሊሲ አርሶአደሩን የሚያደኸይ ነው። ይሄም በተጨባጭ እየታዩ ነው።
➡ የስርዓቱ ሰዎች ከአርሶ አደሩ መሬቱን በጉልበት ይቀማሉ። ለሚፈልጉት ባለሃብት ያቀርባሉ። ከባለሃብቱ የሚፈልጉትን ገንዘብ ይጠይቃሉ። በተለይ ትግራይ ውስጥ ያለው የመሬት ፓሊሲ የኪራይ ስብሳቢነት፣ የሙስና ምንጭ ነው።
➡ በሊዝ ስም መሬት በካሬ በ85,000 ብር ይገዛሉ። ይህን 20፣ 30 ፐርሰንት እየከፈሉ ይወስዳሉ። ይሄ ገንዘብ ከሕዝቡ በሕገ ወጥ መንገድ የተወሰደ ነው። የሕዝብ ሀብት ዘረፉ፣ መልሰው የድሃውን መሬት በመግዛት ሕጋዊ እያደረጉ ነው ያሉት። ምንጩ ግን ሕገ ወጥ ነው። ጭቆናው ድርብ ነው።
➡ ባለን መረጀ መሠረት 1867 አካባቢ መሬት የመጀመሪያው ሊዝ ተዘጋጅቷል፣ በመቐለ ዙሪያ ለምሳሌ ስራዋት፣ እግረወንበር…ብዙ ናቸው።
➡ ያካተቷቸው አንሷቸው ተጨማሪ 13 ቀበሌዎችን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ወደ መቐለ አካተው፣ የእንደርታ ህዝብን መሬት ሸጠው ለመበልጸግ ዝግጅት ላይ ናቸው።
ስለተፈናቃዮች ምን አሉ ?
☑ የትግራይና የአማራ ሊህቃን ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው። ከምንም ነገር በላይ ለወልቃይትም ሆነ ለራያ ሕዝብም መታሰብ አለበት። ማዶና ማዶ ባሉ ሊህቃን ምክነያት ይህን ሕዝብ የጦር ሜዳ እየሆነ ነው። እየተፈናቀለ፣ የገፈቱ ቀማሽ እየሆነ ያለው ይሄ ሕዝብ ነው።
ስለኘሪቶሪያው ስምምነት ምን አሉ?
- ትግራይ ውስጥ እስቲል #ታጣቂዎች ትጥቃቸውን #አልፈቱም። እኛ መፍታት አለባቸው የሚል አቋም ነው ያለን። ለምን ዓላማ ነው ከነመሳሪያቸው እስካሁን የሚቆዩት ? ሕዝባችን ከዚህ በላይ ጦርነት የመሸከም አቅም የለውም።
- ኢትዮጵያን የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት መከላከያ ሠራዊት ነው። ከዛ በመለስ ያሉ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ይፍቱ። የፕሪቶሪያው ስምምነት አንዱ ይህ ነው።
- ለምን እንደተቀመጡ አናውቅም ስጋት አለን።
መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።