#ከጠቀማችሁ
ከላይ በፎቶው የምትመለከቷቸው ተሽከርካሪዎች የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በጨረታ ለመሸጥ ያቀረባቸው ናቸው።
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የተለያዩ ፦
- ያገለገሉ ቀላል ተሽከርካሪዎች
- ያገለገሉ ከባድ ተሽክርካሪዎች ፤
- ቁርጥራጭ የመኪና አካላት (ስክራፕ) እና የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች (ስክራፕ) ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ እስከ የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ከጠዋቱ 03:00 እስክ 10:00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ በሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ከበብ በመገኘት የተሽከርካሪ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረት (ስክራፕ) ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች እስከ የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ/ም ባሉት ቀናቶች የሚሸጡትን ተሽከርካሪዎች ለማየት ኮፈን ተከፍቶ ስለሚቆይ ዘውትር በስራ ሰዓት ከጥዋቱ 3:09 እስከ 10:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ቢሾፍቱ በሚገኘው አውቶሞቲቭ ካምፕ ጀርባ በመሄድ ሞያተኛ ይዞ መመልከት ይችላሉ።
ጨረታው የካቲት 18/2016 ከጥዋቱ 4:00 ሰዓት የሚዘጋ ሲሆን በዚያው ቀን 4:30 ይከፈታል። የሁሉም ተሽከርካሪዎች ጨረታ የሚከፈተው በመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ክበብ ነው።
አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው ከከፈሉ በኃላ ተሽከርካሪዎቹን በ30 የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት ግዴታ አለባቸው።
ለስም ማዞሪያ ወጪ እና ብረታ ብረቶችን ከቦታው ለማንሳት የሚያስፈልግ ወጪ ሙሉ በሙሉ በገዢዎቹ ነው የሚሸፈነው።
ቁርጥራጭ ብረቶችን ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራች ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ብረታ ብርት የማቅለጥ ፍቃድ የተሰጠው ብቻ ነው ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምናልባት ለስራም ሆነ ለግል ጉዳያችሁ ከጠቀመ በሚል ነው ይህን መረጃ ያጋራው።
@tikvahethiopia

Embrace the power of collaboration and ignite the flames of innovation! Become part of Jasiri's talent investor community, where visionary co-founders await to align with your ambition, together forging ventures from inception to triumph. Let's unite under #Jasiri4Africa to pioneer change, inspire entrepreneurship, and foster a culture of collaboration that shapes the future of Africa's business landscape.
#CBE
CashGo (ካሽ ጎ) - ከውጭ ሀገራት ገንዘብ መላኪያ የሞባይል መተግበሪያ
===========================
በሞባይል ስልክዎ አማካኝነት ቪዛና ማስተር ካርድዎን በመጠቀም
• ከውጭ ሀገር በቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ወይም ወደ ሲቢኢ ብር ሂሳብ መላክ ይችላሉ፣ አሊያም
• ተቀባዩ ከ1900 በላይ በሚሆኑት የባንካችን ቅርንጫፎች መቀበል ይችላሉ!
**************
የCashGo ሞባይል መተግበሪያን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ ይጠቀሙ።
• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo&hl=en&gl=US
• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/cashgo/id1559346306

#ሀዋሳ
" ... በነዳጅ እጥረት ስራችንን መስራት አልቻልንም። ተሰልፈን ነው የምንውለው " - አሽከርካሪዎች
" ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከጅቡቲ የሚመጣው ነዳጅ መዘግየቱን ተከትሎ ነው ችግር የተፈጠረው " - የከተማው ገበያ ልማት
በሀዋሳ ከተማ የነበረዉ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረትና ሰልፍ ተስተካከለ ተብሎ ጥቂት ጊዜያት ሳይቆይ ድንገት ችግሩ ማገርሸቱን ተከትሎ መጨረሻ የሌላቸው የሚመስሉ ሰልፎች በየማደያዉ እየታዩ ነዉ።
በከተማው ኑሯቸዉን ከህዝብ ትራንስፖርት ጋር ያደረጉ አሽከርካሪዎች ፤ " አሁን አሁን በረዣዥም ሰልፍችና በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ስራችን በአግባቡ መስራት አልቻልንም " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
አሽከርካሪዎች እንደሚሉት ሁሉም ማደያዎች በአግባቡ አለመስራትና ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ መኪኖች ለነዳጅ ሰልፍ ተገፍተዉ ከመግባት ባለፈ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ሳልቫቲዮ ገጥመዉ መምጣታቸው ቀኑን ሙሉ ተሰልፈዉ እንኳን መቅዳት እንዳይችሉ ምክኒያት እንደሆነባቸው ይገልጻሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸዉ የሀዋሳ ከተማ ገበያ ልማት ቢሮ የስነልኬት ባለሙያው አቶ ሀብታሙ መኮንን ፤ ችግሩ መኖሩን አምነው ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከጅቡቲ የሚመጣው ነዳጅ መዘግየቱን ተከትሎ የተፈጠረው ክፍተት ለችግሩ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።
ችግሩ ወደፊት ይቀረፋል የሚል ተስፋ እንዳላቸዉ ገልጸዋል።
ለህዝብ አገልግሎት የማይሰጡ ታክሲዎች ሰልፍ ዉስጥ እየገቡ ስለመሆኑ መረጃዉ እንዳላቸውና እነዚህን ተሽከርካሪዎች ለመቆጣጠር ከከተማዉ መንገድ ትራንስፖርት ጋር በመነጋገር እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቁመዋል።
ሀዋሳ ከተማ እጅግ በርካታ የነዳጅ ማደያዎች ያሉባት ሲሆን ነዳጅ የሚቀዳው ግን በተለያየ የአሰራር ዘዴ ነው። ለአብነት ዛሬ አንዱ ማደያ ከቀዳ ፣ ነገ እዛ ላይቀዳ ይችላል። ተገልጋዮች ከተማው ያወጣውን መርሀ ግብር በቴሌግራም በማየት ነው ነዳጅ መቅዳት የሚችሉት።
ከዚህ ባለፈ እሁድ እሁድ እለት ነዳጅ ማግኘት የማይታሰብ ነው።
በሌላ በኩል ፤ በከተማው ነዳጅ በጥቁር ገበያ በታሸገ የውሃ ፕላስቲክ እየተደረገ በየሱቁ የሚቸበቸብ ሲሆን ይህም ከመቶ ብር በላይ (110 ብር) ነው የሚሸጠው።
መረጃው አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

#AddisAbaba #ጋብቻ #ፍቺ #ልደት #ሞት
በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት አፈፃፀም ከባለፉት ዓመታት በከፍተኛ ቁጥር የላቀ የኩነት እና የዲጂታል ምዘገባ መመዝገቡን የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
ኤጀንሲው ፤ ከ393 ሺህ በላይ የዲጂታል ምዝገባ እና ከ210 ሺህ በላይ የኩነት ምዘገባ መደረጉን ነው የገለጸው።
ከተመዘገበው ጠቅላላ ኩነት ፦
➡ 181 ሺ 983 ልደት፣
➡ 16,933 ጋብቻ፣
➡ 2,813 ፍቺ
➡ 8,761 ሞት ሲሆን ከዚህም ውስጥ በአንድ ዓመት ገደብ ውስጥ የተመዘገበው ፦
* አዲስ ጋብቻ 5,171
* በፍርድ ቤት በተከናወነ በአንድ ዓመት ግዜ ውስጥ የተመዘገበ ፍቺ 1,296
* ሞት 2,312 መሆኑ ታውቋል።
ከ2015 ዓመት በንፅፅር ሲታይ ፦ አዲስ ልደት በ65%፣ ፍቺ በ106.7% እንዲሁም ሞት በ25.29% ጭማሪ ብልጫ ያሳየ ሲሆን ጋብቻ በ5% የቀነሰ መሆኑ ተገምግሟል።
በነዋሪነት አገልግሎት ዘርፍ ለ393,303 ነዋሪዎች በአዲስ፣ በምትክ፣ በእርማት እና በእድሳት የመታወቂያ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን 311 ሺ 446 (93%) የዲጂታል መታወቂያ መሆኑ በአፈፃፀሙ የተሻለ አድርጓታል።
በተጨማሪም በዚሁ ዘርፍ 76,299 የያላገባ ማስረጃ እንዲሁም 15,369 የመሸኛ (Clearance ) አገልግሎት በከተማዋ ተሰጥቷል።
ከተመዘገበው ኩነት ትንተና በዕድሜ ሲታይ ፦
☑ ልደት
6% ከ1 ዓመት በታች፣
28% ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት፣
26% ከ6 ዓመት እስከ 17 ዓመት እንዲሁም
40% ከ17 ዓመት በላይ መሆናቸው ትንተናው ያመላክታል፡፡
☑ ጋብቻ
72.8% የሚሆነው ተገቢ ከ18 - 40 ዓመት
27.2% የሚሆነው ከ41 በላይ መሆኑ ትንተናው አሳይቷል።
☑ ሞት
0.01% ከተወለደ ከ28 ቀን እስከ 1 ዓመት የተከሰተ ሞት፣
0.6% ከተወለደ ከ2 ዓመት እስከ 17 ዓመት የሞተ፣
22.9% ከተወለደ ከ18 ዓመት እስከ 40 ዓመት የሞተ፣
28.5% ከተወለደ ከ41 ዓመት እስከ 60 ዓመት የሞተ፣
35% ከተወለደ 61 ዓመት እስከ 80 ዓመት የሞተ፣
12% ከተወለደ 81 ዓመት እስከ 100 ዓመት የሞተ፣
0.9% ከተወለደ ከ100 ዓመት በላይ የሞተ መሆናቸው ያመላክታል፡፡
በስድስት ወራት አፈፃፀም በከተማው የዲጂታል ምዝገባ እና ልደት ምዝገባ የተሻለ አፈፃፀም የታየባቸው መሆኑ ተነግሯል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ምንም እንኳን የተሻለ አፈፃፀም ቢኖርም ፤ አገልግሎቱን በጥራት ከመስጠት አንፃር የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን ከአፈፃፀሙ እኩል ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የቀሪ ወራት አቅጣጫ ነው ብለዋል።

#Grade12NationalExam
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና (12ኛ ክፍል) የተፈታኞ ምዝገባ በሚመለከት ለሚዲያ አካላት ማብራሪያ ሰጥቷል።
የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ምን አሉ ?
- የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ለፈተና ከመቀመጣቸው በፊት የመመዝገቢያ መስፈርቱን ማሟላት አለባቸው። በተቀመጠው የጊዜ ገድብ ውስጥም መምዝገብ አለባቸው።
- ምዝገባዉ የሚከናወነዉ በበይነመርብ /Online Registration / አማካኝነት ሲሆን ከየካቲት 3 -30/2016 ዓ.ም
ይሆናል።
- በየደርጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ትኩርት ማድርግ ያለባቸውን ጉዳዮችም የሚከተሉት ናቸው ብለዋል ፦
1ኛ. ተፈታኞች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መምዘገብ አለባቸው። ከየካቲት 3 -30 /2016 ዓ.ም ብቻ።
2ኛ. ምንም አይነት ስህትት ማለትም የፆታ ߹የስም ስህተት߹የፎቶ ߹የትምህርት መስክ እና የመሳስሉት ችግሮች እንዳይፈጠሩ በትኩርት መስራት መቻል አለባቸው።
3ኛ. ከየካቲት 30 /2016 ዓ.ም በኃላ የሚመጣ ምዝገባ ተቀባይነት እንደሌለዉ ማወቅ አለባቸው።
4ኛ. የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወንው በተማሩበት ት/ቤት ይሆናል።
5ኛ. የግል ߹ የርቀት /የበይነ መርብ /ተፈታኞ ምዝገባ በክፍለ ከተማ ߹በወርዳና ትምህርት ፅ/ቤቶች ይሆናል።
መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ ስፍራ ምን ተፈጠረ ?
በትግራይ ክልል እና በአማራ ክልል የራያ ወረዳ አዋሳኝ አከባቢዎች በትጥቅ የተደገፈ ግጭት እንደነበረ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመስማት ችሏል።
የካቲት 6 / 2016 ዓ.ም የተቀሰቀሰው መጠነኛ ነው የተባለው ግጭት በሀገር መከላከያ ሰራዊት ጥረት ሊቆም እንደቻለ ነው የተነገረው።
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአላማጣ ከተማ ነዋሪ ለመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በሰጡት ቃል ፤ " በትግራዩ የራያ ጨርጨር አከባቢ ታጣቂ ምልሻና በአጎራባች የአማራ ክልል ራያ ቆቦ ምልሻ መካከል ለአጭር ጊዜ የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተከስቷል " ብለዋል።
የካቲት 6/2016 ዓ.ም በሁለቱ ክልል አጎራባች የተካሄደው ለአጭር ጊዜ የቆየ ግጭት ትክክለኛ መነሻው በግልፅ የማይታወቅ ቢሆንም በሁለቱም ወገን የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቷል።
በትግራይ በኩል ያሉ ፀሃፊዎች " የራያ ቆቦ ታጣቂዎች የትግራይ የራያ ጨርጨር ታጣቂ ምልሻዎች ትጥቅ ፍቱ " በማለታቸው የተነሳ ነው ብለዋል።
በአማራ በኩል ደግሞ የትግራይ ኃይሎች " መሬታችንን እናስመልሳለን " በማለት በከባድ መሳሪያ የታገዘ ተኩስ ከፍተው ነው ብለዋል።
የተፈጠረውና ለአጭር ጊዜ የቆየውን ግጭት በአከባቢው የሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዳረጋጋው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በትግራይና በአማራ ክልል አዋሳኝ ስፍራ አጭር ጊዜ የቆየውን ግጭት የሰሙ የተለያዩ ነዋሪዎች ተግባሩ ከማውገዝ አልፈው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሳንካ እንዳይሆን ስጋታቸው እየገፁ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን በተመለከተ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት በኩል ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።
ምላሽ ለማግኘት ቢሮ ድረስ የሄድን ሲሆን ስልክም ብንደውል አይነሳም።
በአሁን ሰዓት በአማራ ክልል ስር እየተዳደረ የሚገኘውን የአላማጣ ከተማን እየመሩ ያሉት ከንቲባ ግን በአማራ ክልል በኩል ያለውን ማብራሪያ ገልጸውልናል።
ተቀሰቀሰ የተባለው የጸጥታ ችግር እውነት ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የአለማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ በሰጡት ቃል፣ " በእርግጥ #እንቅስቃሴ ነበር ። ያው እንቅሰቃሴው ከሽፏል ። ወረራ ለማድረግ ሙከራ አድርገው ነበር " ብለዋል።
ከወደ ትግራይ ክልል በኩል ታጣቂዎች በባላ በኩል እንደመጡ የገለጹት ከንቲባው ፣ " ወደ ሁለት ቀበሌዎች ሰርገው ገብተው ነበር ተመትተው ተመልሰዋል " ብለዋል።
አሁን ላይ የሰላም መደፍረሱ እንደቆመ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ከንቲባው የሰጡትን ተጨማሪ ማብራሪያ ነገ የምናቀርብ ይሆናል።
ይህ መረጃ የተዘጋጀው በመቐለው እና በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ቅንጅት ነው።

#ማስታወሻ
ለአዲስ አበባ ከተማ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ፦
1ኛ. የሞተር ባለንብረቶች እንዲሁም በሞተር እየተንቀሳቀሳችሁ ስራችሁን ለምትሰሩ አባላቶች ከነገ አርብ የካቲት 8 /2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ሰኞ የካቲት 11/2016 ዓ.ም ጠዋት 2:00 ሰአት ድረስ ሞተር ማሽከርከር ፍፁም ተከልክሏል። የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ክልከላውን በሚተላለፉ ላይ " ጥብቅ እርምጃ እወስዳለሁ " ብሏል።
__
2ኛ. ለአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ #መሪዎች ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ይገኛሉ። በዚህ ምክንያት መሪዎች እስኪያልፉ ድረስ መንገዶች ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ሊዘጉ ይችላሉ።
ፖሊስ አማራጭ / ተለዋጭ መንገዶችን ተጠቀሙ ብሏል።
➡ ከፓርላማ መብራት-በውጭ ጉዳይ ሚ/ር - መስቀል አደባባይ ፍላሚንጎ - ኦምሎፒያ - ወሎ ሰፈር - ጃፓን ኤምባሲ - ፍሬንድ ሺፕ -ቦሌ ቀለበት መንገድ - ኤርፖርት
➡ ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - በብሔራዊ ቤተ - መንግስት - በፍልውሃ - በብሔራዊ ቴአትር- ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ
➡ ከፓርላማ መብራት -ብሔራዊ ቤተ-መንግስት - ወዳጅነት ፓርክ - ንግድ ማተሚያ ቤት - ሞናርክ ሆቴል-ቴዎድሮስ አደባባይ-ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል- ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን- ብሔራዊ ቴአትር - ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት መንገዶች እንግዶች የሚያልፉባቸው ናቸው።
ከዚህ ባለፈ ፦
☑ ከፓርላማ መብራት-በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን-ፍልውሃና አምባሳደር ቴአትር ዙሪያውን
☑ ከንግድ ምክር ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ - አፍሪካ ህብረት ዋናው በር - ሳርቤት ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች እንግዶች ተጠቃለው እስኪመለሱ ግራና ቀ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል።
__
3ኛ. 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል። የ2024 መሪ ቃል ፤ " ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት " የሚል ነው።
#TikvahFamilyAddisAbaba

#ጥቆማ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ #በግል_ከፍለው የአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለሚፈልጉ ጥሪ አቀረበ።
ዩኒቨርሲቲው ፤ ለአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የ10% ቅናሽ ማድረጉንም አሳውቋል።
" በግል ከፍለው የአውሮፕላን አብራሪ ለመሆን ለሚማሩ ስልጠናውን ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ " ያለው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው ብሏል።
1ኛ. የትምህርት ደረጃ ፦ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት የወሰዱ፣ እንዲሁም ፦
* በሂሳብ፣
* በእንግሊዘኛ
* በፊዚክስ ዉጤት አመርቂ አፈጻጸም ያስመዘገቡ
2ኛ. ዕድሜ ፦ 18 እና ከዚያ በላይ
3ኛ. እንግሊዘኛ ፦ ደረጃ 4
4ኛ. ቁመት፦ 1ሜ 62 ሴ.ሜ እና ከዚያ በላይ
5ኛ. የጤና ሁኔታ፦ ደረጃ 1 የጤና ሰርተፊኬት
የስልጠናው ርዝማኔ 1 አመት ከ 3 ወር ነው ተብሏል።
" የተደረገው ቅናሽ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነው " ያለው ዩኒቨርሲቲው ፤ " የምዝገባ ሂደቱን ለማወቅ እና ለበለጠ መረጃ በኢሜል አድራሻ ፦ [email protected] / [email protected] ያነጋግሩን " ብሏል።
ስልክ በመደወል መረጃ ለመቀበል የምትፈልጉም +251-115174600/8598 ነው ተብሏል።
ከዚህ ባለፈ የዩኒቨርሲቲውን ድረገፅ መመልከት ይቻላል ፦ ethiopianaviationuniversity.azurewebsites.net/admission/applyonline

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ
ፈጣን እና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ እንሆ ብለናል።
ሊንኩን በመጠቀም መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ!
ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765
ለሁዋዌ ስልኮች https://appgallery.huawei.com/app/C110106115

@samcomptech
⭐ አሁንም አዳዲስ ላፕቶፕች ገብተዋል!!!!
ብዛትም ጥራትም በአንድ ቦታ እኩል የተገናኙበት ሁሉንም አይነት ላፕቶፕ የያዘ የላፕቶፕ መደብር አለን።
🟥ለተማሪዎች፣ ለቢሮ ሰራተኞች, ለጌመሮች, ለቪዲዮ ኤዲተሮች ,ለግራፌክስ ዲዛይነሮች አዳዲስ ላፕቶፕች እና ስልኮች በቅናሽ ከአንድ አመት ዋስትና ጋር ይዘን ቀርበናል።
🔵 @samcomptech
👏የሚገርም ፍጥነት ያላቸው ፣ ቀላል እና ከ 10 ሰዓት በላይ የባትሪ ቆይታ ያላቸዉ ዘመናዊ ላፕቶፖች አሉን ፦
ቴሌግራም ላይ ሁሉም ዝርዝር አለ በመቀላቀል የሜፈልጉትን ይምረጡ ።
https://t.iss.one/samcomptech
@sww2844
☎️ 0928442662/ 0940141114