TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከየካቲት 6-9/2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ የድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉ የመፈታኛ የይለፍ-ቃል (Password) ከስር በተገለፁት አማራጮች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። 1. በምዝገባ ወቅት በሞላችሁት email በኩል፣ 2. https://exam.ethernet.edu.et ላይ በመግባት የከፈላችሁበትን Transaction…
የመውጫ ፈተና ከየካቲት 6 እስከ የካቲት 11 ቀን 2016 ድረስ ይሰጣል።

የ2016 ዓ/ም የአመቱ አጋማሽ የሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከነገ ረቡዕ የካቲት 6 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ተልኮልናል ብለው ያጋሩትን የተሻሻለ የፈተና መርሃ ግብር የተመለከተ ሲሆን በዚህ መርሀ ግብር ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና እስካ የካቲት 11 /2016 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።

በፈተናው የመጀመሪያ ቀን በሺዎች የሚቆጠሩ የጤና ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ተላከልን ብለው አጋርተውት በተመለከትነው ዳታ ከ6 ሺህ በላይ የነርሲንግ፣ ከ1 ሺህ 900 በላይ የፋርማሲ፣ ከ1 ሺህ 700 በላይ የዶክተር ኦፍ ሜዲስን ተማሪዎች በመጀመሪያው ቀን ፈተናቸውን ከሚወስዱት ውስጥና ከፍተኛውን ቁጥር ከሚይዙት የጤና ትምህርት ዘርፍ ውስጥ ይገኙበታል።

ከዚህ ባለፈ በዘንድሮው የመውጫ ፈተና ከፍተኛ ተፈታኝ ከሚጠበቅባቸው የትምህርት ክፍሎች መካከል አካውንቲንግ ከ8 ሺህ በላይ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ ከ3 ሺህ በላይ ፣ ማርኬቲንግ ማኔጅመንት ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።

በአመቱ አጋማሽ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በአጠቃላይ በሺዎች የማቆጠሩ የመጀመሪያ ዙር እንዲሁም ባለፈው ፈተና ውጤት ሳያመጡ የቀሩ የድጋሜ ተፈታኞች የሚወስዱ ይሆናል።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ በአጠቃላይ ፈተናው 47 የመንግስት ተቋማት በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149,145  ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች ይፈተናሉ።

በሌላ ለኩል ከጥቂት ቀናት በፊት ፤ " በኦንላይን ለሚሰጥ የአንድ ቀን ፈተና በመቶዎች ኪሎ ሜትር ተጉዘን እንድንፈተን ተነገረን " በሚል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን ያሰሙ ተመራቂዎች አሁን ላይ ፈተናውን ባሉበት ከተማ በተቋማቸው እንዲወስዱ ማስተካከያ መደረጉንና ስም ዝርዝራቸውም መውጣቱን ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በሚል ከባለፈው አመት ጀምሮ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ተግባራዊ እያደረገ ሲሆን ፈተናው በዓመት ሁለት ጊዜ (በአመቱ መጨረሻና አጋማሽ) ላይ ይሰጣል።

(ከላይ ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ሚኒስቴር እንደተላከላቸው የገለፁትን የ2016 የአመቱ አጋማሽ ተሻሻለ የፈተና መርሀ ግብርን አይዘናል)

ከተፈታኞች እና ከፈታኞች ምን ይጠበቃል ? አምና በነበረው ፈተና ከትምህርት ሚኒስቴር የተላለፈው ትዕዛዝ በዚህ መመልከት ይቻላል ፦ https://t.iss.one/TikvahUniversity/10053

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመላው ተፈታኝ እጩ ምሩቃን ቤተሰቦቹ በሙሉ መልካም ፈተናን ይመኛል።

@tikvahethiopia
Ethiopian women with visionary ideas, it's your time to shine!

Jasiri is on the lookout for female entrepreneurs with groundbreaking business concepts. If you have the vision to lead and the determination to succeed, we're ready to help you make that leap.

Apply now at jasiri.org/application and join a community where your ideas have the power to create change.
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#እንድታውቁት

ከአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ጋር በተያያዘ ለኮንስትራክሽን እና ለጭነት ተሽከርካሪዎች የተከለከሉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

የተከለከሉ መንገዶች ፦

ቦሌ ድልድይ አካባቢ
ከቦሌ ድልድይ እሰከ ሩዋንዳ ድልድይ
ከቦሌ ድልድይ በወሎ ሰፈር  ደንበል አደባባይ እስከ መስቀል አደባባይ
ከመስቀል አደባባይ እስከ አራት ኪሎ
ከኡራኤል አደባባይ እስከ አትላስ ሆቴል
ከኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል እስከ ልማት ባንከ
ከአራት ኪሎ እስከ አምባሳደር መናፈሻ
ከብሄራዊ ቴአትር እስከ ሜክሲኮ አደባባይ
ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ አፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት እና
ከአፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት እስከ ቡልጋሪያ ማዞሪያ  ባሉት መንገዶች ላይ ተለዋጭ መረጃ እስከሚተላለፍ ድረስ የኮንስትራክሽን ከባድ እና የጭነት ተሽከርካሪንዎችን ማሽከርከርም ሆነ ማቆም የተከለከለ ነው።

አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተብሏል።

ይህን ትዕዛዝ ተላልፈው በተገኙት ላይ እርምጃ እንደሚወሰው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ የኮንስትራክሽን ተሽከርካሪዎች እና በኦፕሬተር የሚንቀሳቀሱ ማሽኖች ፦
* ጎማዎቻቸውን ሳያፀዱ መንገዶቹን እያበላሹ መሆኑን
* ለረጅም ጊዜ በመንገዶቹ ላይ በመቆም
* የሚጭኑትን አሽዋ ፣የቦካ  ሲሚንቶ እንዲሁም የግንባታ ግብአቶችን በአግባቡ ሳያስሩ እና ሳይሸፍኑ  እያፈሰሱ በመጓዝ በሚፈፅሙት የደንብ መተላለፍ ጥሰት የመንገዶቹ ውበት እየተበላሸ እና የአገልግሎት ዕድሜያቸው እያጠረ መምጣቱን ገልጿል።

በመሆኑም የትራፊክ ህግና ደንብን በማስከበር የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ከመከላከል ባሻገር ጤናማ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር እንዲሁም  በከተማዋ በቀጣይ ቀናት  ለሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የፀጥታ አካላት ለሚያከናውኑት የፀጥታ ስራ አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር ሲባል ከላይ የተዘረዘሩት መንገዶች ለእነዚህ ተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የሞተር እንቅስቃሴ ላይ ክልከላ ተጣለ።

በአዲስ አበባ የሚገኙ የሞተር ብስክሌተኞች በሙሉ ከአርብ የካቲት 08/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ሰኞ የካቲት 11/2016 ዓ.ም እስከ ጠዋት 2:00 ሰአት ድረስ በከተማዋ ውስጥ ሞተር ብስክሌት በፍጹም ማሽከርከር እንደማይችሉ የትራንስፖርት ቢሮ ክልከላ ጥሏል።

ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን አይመለከትም ተብሏል።

" የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ " ያለው ቢሮው " ይህንን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል " ሲል አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
8118 ይደውሉ!

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከክፍያ ነፃ የጥሪ ማዕከል ባንኩን የሚመለከቱ ማንኛውንም ጥያቄዎች በተለያዩ አማራጮች ለመመለስ ዝግጁ ሆነው ይጠብቅዎታል፡፡

በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን፡ https://bit.ly/3TkrrXD

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #GBE
ቆይ አንዴ.....

አዲሱን እለታዊ ኮምቦ ጥቅላችንን ሞክራቹታል?

ለመግዛት *777*3# እንደውል::

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ቀጥሎ በሚገኙት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

👉Facebook: https://www.facebook.com/SafaricomET
👉Telegram: https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
👉LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia
👉Twitter:
https://x.com/SafaricomET?t=y2XAHAhPNvFeZqXa2YE6aQ&s=08
👉 Instagram: https://www.instagram.com/safaricomet?igsh=MWJtcjJrMzNhMzVsNg==
YouTube: https://youtube.com/@safaricomethiopia2751?si=w2o8uz61oHeZM9gm
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ውጤት አልተገኘም " ደቡብ ወሎ ዞን ፣ ደላንታ ወረዳ የኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ ሳሉ ዋሻ የተደረመሰባቸውን በርካታ ሰዎች ለማውጣት የሚደረገው ጥረት 4 ቀኑን እንደያዘ ተነግሯል። የአካባቢው ባለሥልጣናት እና የከበረ ማዕድን አውጪዎች ማኅበር በሰጡት ቃል  ፤ በቁጥር ከ8 እስከ 30 የሚገመቱትን ሰዎች ለማውጣት የአካባቢው ማኅበረሰብ ጥረት እያደረገ ቢሆንም እስካሁን…
“ በተጨማሪ ማሽነሪ/ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ ለማከናወን አልተቻለም ” - የደቡብ ወሎ ዞን ኮሚዩኒኬሽን

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ "018 አለኋት" ቀበሌ በተለምዶ ቆቅ ውኃ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ/ም ሌሊት የኦፓል ማዕድን በቁፋሮ ለማውጣት ሲሞክሩ የነበሩ ከ20 በላይ ወጣቶች የቆፈሩት አለት በመናዱ ያሉበትን አልታወቀም ስለተባሉት ወጣቶች ሁኔታ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዞኑን ኮሚዩኒኬሽን ዛሬ (ጥር 6 ቀን 2016 ዓ/ም) ጠይቋል።

የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ኢያሱ ዮሐንስ በሰጡት ቃል፣ “በተጨማሪ ማሽነሪ/ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ ለማከናወን አልተቻለም። ቁፋሮው ግን አሁንም እንደቀጠለ ነው” ብለዋል።

ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተሁኖ በትብብር ቁፋሮ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፣ እካሁን (ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ) “ከ50 ሜትር በላይ ቁፋሮ ተከናውኗል” ሲሉ ተናግረዋል።

ቁጥሩ በማኀበራዊ ሚዲያዎች ከፍና ዝቅ እያለ ነው፣ በትክክል ስንት ወጣቶች ናቸው የጠፉት? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ “ቁጥራቸው ከ20 ያላነሰ እንደሆነ ነው ያሉን መረጃዎች የሚያመላክቱት። አካባቢው ላይ ወጣቶቹ ስለሚታወቁ እንደዛ የሚል ነው የተሰጠን መረጃ” ብለዋል።

እስካሁን ምን የተገኘ ፍንጭ አለ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ኢያሱ፣ “የተገኘ ነገር የለም። በመግቢያነት የሚጠቀሙበትን የዋሻውን ክፍል መሠረት አድርገው ነው የአካባቢው አስተዳደሮች ቁፋሮ ለማድረግ እየሞከሩ ያሉት” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አክለውም፣ “ተስፋ ተደርጎም እየተሰራ ያለው ከሁለትና ከሦስት ዓመታት በፊት ተመሳሳይ ችግር አጋጥሞ ከ11 ቀናት ቆይታ በኋላ አራት ወጣቶች በሕይወት ተገኝተዋል። አሁንም እንደዚህ አይነት ዕድል ቢገኝ ተብሎ ነው እየተሰራ ያለው። ጥረቱ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል” ነው ያሉት።

ከሦስት ዓመታት በፊት በነቀረው ክስተት ጠፍተው የነበሩ ወጣቶች በሕይወት ሊገኙ የቻሉት በምን ሁኔታ እንነበር ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽም፣ “ተመሳሳይ ነው፣ ሲቆፍሩ ዋሻው ተንዶ ነው እነዛም አደጋው አጋጥሟቸው የነበረው” ብለው፣ “ሁኔታው ከተሰማ በኋላ የአካባቢው ማኀበረሰብ እንዳሁኑ የቁፋሮ ስራ በማከናወን ነው ሕይወታቸውን ለማትረፍ የሞከረው” ሲሉ አውስተዋል።

አክለውም፣ “ሕይወታቸውንም ያጡ ወጣቶች ነበሩ። ነገር ግን በጊዜው ወደ አራት የሚደርሱ ወጣቶች ሕይወት ማግኘት ተችሎ ነበር” ሲሉ በአሁኑ ክስተት የጠፉ ወጣቶች ይገኛሉ የሚል ተስፋ ሰጪ ያሉትን የቀድሞ ክስተት አስታውሰዋል።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ሲሆን፣ ሁኔታውን በመከታተል የምናሳውቅ ይሆናል።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በአዲስ አበባ ከተማ ፤ አጎና (የጎተራ ኮንዶሚኒየም መግቢያ) በሚገኝ ህንፃ ላይ ምሽቱን የእሳት አደጋ መነሳቱን የአካባቢው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

የእሳት ደጋው ከተነሳ ከአንድ ሰዓት በላይ እንዳለፈውና የእሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች እሳቱ ተጨማሪ ጥፋት እንዳያደርስ በቁጥጥር ስር ለማዋል ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።

እስካሁን በህንፃውን አንደኛው ጎን ውስጥ የነበሩ ንብረቶች እየወደሙ ይገኛሉ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ተከታትለን እናሳውቃለን።

#TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia
" በተለያየ ሶሻል ሚዲያ ' አስቸኳይ ፓስፖርት እናወጣለን ' ከሚሉ ህገወጦች ራሳችሁን ጠብቁ ፤ ... በኦንላይ ምንም አይነት አስቸኳይ ፓስፖርት አይሰጥም " - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስቸኳይ ፓስፖርት ለማውጣት ምን ያስፈልጋል / ለምን ምን ጉዳዮች ይሰጣል አለ ?

- የህክምና ማስረጃ
- የትምህርት ዕድል ማስረጃ
- ለመንግስት ስራ ጉዳይ ለስብሰባ፣ ለወርክሾኘ
- ጊዜው ያላለፈ የመኖሪያ ፈቃድ ያለው ለባል/ለሚስት/ለልጅ
- ለአስመጭና ላኪ /ከፍተኛ ግብር ከፋይ/
- ፓስፖርት ላይ ጊዜው ያላለፈ የተመታ ቪዛ ካለ /ለማሳደስ/

ከእነዚህ ሰነዶች በአንዱ ዋናው ቢሮ በአካል በመገኘት ብቻ የተሟላ ማስረጃ በመያዝ በአስቸኳይ መስተናገድ ይቻላል ሲል አሳውቋል።

ክፍያ የሚከፈለው በቢሮ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል።

ዜጎች በተለያየ ሶሻል ሚዲያ " አስቸኳይ ፓስፖርት እናወጣለን " ከሚሉ ህገወጦች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።

በኦን ላይን ምንም አይነት አስቸኳይ ፓስፖርት የማይሰጥ መሆኑንም ገልጾ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የመውጫ ፈተና ከየካቲት 6 እስከ የካቲት 11 ቀን 2016 ድረስ ይሰጣል። የ2016 ዓ/ም የአመቱ አጋማሽ የሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከነገ ረቡዕ የካቲት 6 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ተልኮልናል ብለው ያጋሩትን የተሻሻለ የፈተና መርሃ ግብር የተመለከተ ሲሆን በዚህ መርሀ ግብር ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና እስካ የካቲት 11 /2016 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።…
የመውጫ ፈተና ዛሬ በጤና ትምህርት ፕሮግራሞች  መሰጠት ጀምሯል።

ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከዛሬ ካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት እንደተጀመረ ገልጿል።

በዛሬው እለት በጤና ፕሮግራሞች በተጀመረው ፈተና ጠዋት 15,440 ተማሪዎች በ23 የጤና ፕሮግራሞች የተፈተኑ ሲሆን ከሰዓት 14,807 ተማሪዎች በ13 ፕሮግራሞች ተፈትነዋል።

ፈተናው በሁሉም የፈተና ማዕከላት ከተማ እየተሰጠ ሲሆን የመውጫ ፈተና አሰጣጡ ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የተመደቡ ታዛቢዎች በየተመደቡበት ተቋማት በመገኘት ስራ መጀመራቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

የሁለተኛ ዙር ፈተናው ፦
- በ47 የመንግስት ተቋማት
- በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149,145  ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች ይፈተናሉ።

ፈተናው የካቲት 11/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አመላክቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በአዱስ አበባ አጎና የተነሳው እሳት መጀመሪያ ላይ ከነበረበት የወደ መጥፋት ደረጃ ቢቀንስም እሳቱ ሙሉ በሙሉ አልጠፋም።

በስፍራው የአዲስ አበባ እሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች እና ተሽከርካሪዎች የሚገኙ ሲሆን የፌዴራል ፖሊስም አጋዥ ተሽከርካሪዎችን ወደ ስፍራው በመላክ እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

የእሳት አደጋ በተነሳበት ህንፃ ላይ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የሚገኙበት ነው።

የአደጋው መንስኤ እና ሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ይኖር እንደሆነ እስካሁን በውል አልታወቀም።

መረጃውን የላኩት በስፍራው የሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ናቸው።

@tikvahethiopia