TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#CBE

እጥፍ ወለድ....
********
ከባህር ማዶ ገንዘብ ሲላክልዎ፤
አዲሱን የውጭ ሐዋላ የቁጠባ ሂሳብ ይክፈቱ!

• ከመደበኛው ሂሳብ እጥፍ ወለድ ያስገኛል ፣
• ለውጭ ሀገር ጉዞዎ ቅድሚያ የውጪ ምንዛሬ አገልግሎት እና
• የሞባይል ካርድ ስጦታም ያገኛሉ ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
***********

የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• Telegram፡- https://t.iss.one/combankethofficial
በሀዋሳ ከተማ እንዲሁም አሪቦና ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ።

ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በተለምዶ " ሳዉዝ " እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በደረሰ የተሽከርካሪዎች ግጭት በሰዉ ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

የሳይክል ፣ የሞተርና መኪና ግጭት መፈጠሩን ተከትሎ ሳይክል ሲያሽከረክር የነበረ የ17 አመት እድሜ ያለዉ ታዳጊ ህይወቱ ሲያልፍ ፤ ሞተር ያሽከረክር የነበረዉ ወጣት ላይ ከፍተኛ አደጋ ደርሷል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያዊ የሰጡት የአካባቢው የትራፊክ አባል ሳጅን አገኘሁ አቡ ፤ ጉዳቱ በፍጥነት ችግር የተከሰተ መሆኑን በመግለጽ አሁን ላይ በህይወት ቢተርፍም ጉዳት ያስተናገደዉን ሞተረኛ ለህክምና ወደ ሪፈራል ሆስፒታል መላኩን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ፥  ከአዲስ አበባ ወደ መተሀራ በሚወስደው ዋና መንገድ  በምስራቅ ሸዋ ቦሰት ወረዳ ልዩ ስሙ " አሪቦና "በተባለ ሥፍራ በደረሰ የመኪና አደጋ አንድ ሰው ሞቷል።

አደጋው የደረሰው " ኒሳን ፖትሮል " መኪና ከአይሱዚ መኪና ጋር ተጋጭተው ሲሆን አንድ ሰው ሲሞት ሌሎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ኢፕድ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ኢፕድ (አሪቦና)

@tikvahethiopia
" በወንድሜ አንተነህ ጌታሁን ጉዳይ ፍርድቤት ለሁለተኛ ጊዜ የዋስ መብት ቢፈቅድም ፖሊስ ሊፈታልን አልቻለም " - ዳግም ጌታሁን

" ተጨማሪ ምርመራ በማስፈለጉ ፖሊስ ህጋዊ መንገድ ተጠቅሞ ተጠርጣሪዉን ሊያቆየዉ ችሏል " - ፖሊስ

አንተነህ ጌታሁን የተባለ ወጣት በሀዋሳ ከተማ " በሶሻል ሚዲያ የምትጽፈዉ ጽሁፍ ወጣቱን ለሽብር ያነሳሳል !! " በሚል በቀን 26/05/2016 ከጓደኞቹ ጋር በሚዝናናበት ወቅት በፖሊስ ተይዞ ታስሯል።

ይህ ወጣት አንተነህ ጌታሁን ሁለተኛ ጊዜ ፍ/ቤት ቀርቦ የዋስ መብቱ ቢከበርም ፖሊስ ሊፈታዉ ፈቃደኛ አልሆነም ሲል ወንድሙ ዳግም ጌታሁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

" እሁድ ምሽት ከጓደኞቹ ጋር በመዝናናት ላይ እንዳለ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አባላት ለጥያቄ ትፈለጋለህ " በሚል ወሰዱት የሚለዉ ዳግም " የቀረበበት ክስ ተጨባጭ መረጃ የለዉም በሚል ፍ/ቤቱ የዋስ መብቱን ለ2ኛ ጊዜ መፍቀዱን ተከትሎ የታዘዘዉን 50 ሺህ ብር ብናስይዝም ወንድሜ ሊፈታ አልቻለም " ብሏል።

ወንድሙ የታሰረበት ዳግም ጌታሁን ፤ " እየመጡ ነው !! " በሚል የፋኖ ኃይሎችን የሚደግፍ ፅሁፍ በፌስቡክ ፅፈሃል በሚል እንደሆነ ተናግሯል።

በጉዳዩ ላይ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ የመምሪያዉ ፖሊስ አዛዣ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ እንደገለጹት ጉዳዩ ተጨማሪ ምርመራ የሚፈልግ ጉዳይ በመሆኑ በህጋዊ መንገድ ተጨማሪ ጊዜ ተጠይቆበት ተጠርጣሪዉ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዉ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

አቶ አንተነህ ለሶስተኛ ጊዜ ነገ ሰኞ ፍርድቤት ይቀርባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ጉዳዩን ተከታትለን የምንዘግብ ይሆናል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ  " ዛሬ ይመረቃል። አጫጭር መረጃዎች ስለ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ "  ፦ - በ5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ከምድር በታች ሁለት ደረጃዎችን ጨምሮ  5 ወለል እና 8 በሮች አሉት። - 8ቱ በሮች ፦ * የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ * የምዕራብ ጀግኖች በር፣ * የሰሜን ጀግኖች በር፣ * የደቡብ ጀግኖች በር፣ * የፈረሰኞች በር፣ * የአርበኞች በር፣ * የፓንአፍሪካኒዝም…
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ተመረቆ ተከፈተ።

ዛሬ በአዲስ አበባ መሀል ፒያሳ ላይ የተሰራው ግዙፉ የ " ዓድዋ ድል መታሰቢያ " በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተመርቆ ተከፍቷል።

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ፣ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ፣ የጦር መኮንኖች፣ ሚኒስትሮች ፣ የክልል ፕሬዜዳንቶች ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች ... ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እግዶችም ተገኝተው ነበር።

በስነስርዓቱ ላይ መልዕክት አስተላልፈው የነበረው ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፤ " የዓድዋ ድል ከሀገርና አኅጉር ተሻግሮ በዓለም የተስተጋባ አኩሪ ድላችን ቢሆንም ይህን በአንድ ቦታ በአግባቡ የሚገልጽ የዓድዋ ድል መታሰቢያ አለመገንባቱ የሚያስቆጭ ነው " ብለዋል።

" ዛሬ ላይ የዓድዋን ድል ታሪክ በሚመጥን አግባብ መታሰቢያ ተገንብቷል " ያሉት ፕሬዜዳንቷ ፤ ለዚህም ሐሳብ ከማመንጨት ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደረጉትን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደርን አመስግነዋል፡፡

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በበኩላቸው፤ " የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሌሎች የጥቁር ሕዝቦች ሀገራት ሊሠሩት ቢችሉም፤ የምኒልክ ልጅ፣ የባልቻ ልጅ፣ የገበየሁ ልጅ፣ የአሉላ አባ ነጋ ልጅ መሆን ግን አይችሉም " ብለዋል፡፡

" የድል መታሰቢያውን ሰርተንና ጥረን ያሳካነው ነው " ያሉ ሲሆን " ከ128 ዓመታት በኋላ ተገንብቶ ለትውልድ ማለፍ በሚችልበት መልኩ ኢትዮጵያን መስሎ ተሠርቷል " ሲሉ ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ " የዓድዋ ድል መታሰቢያን ማርከስ ማለት የአባቶቻችንን አጥንት እና ደም ማርከስ ነው " ሲሉም ተደምጠዋል።

Photot Credit - PMOfficeEthiopia & S.H

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እቴጌጣይቱ " ብርሃን ዘኢትዮጵያ " እየተባሉ ለሚጠሩት ስመ ጥር የሀገር ባለውለታ እቴጌ ጣይቱ ብጡል በትውልድ ቦታቸውና ለቁምነገር በበቁበት በደብረታቦር ከተማ የመታሰቢያ ሀውልት ቆመላቸው። ሀውልቱ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ተገንብቶ በዛሬው እለት መመረቁ ተነግሯል። እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ ነሀሴ 12 ቀን 1832 ዓ.ም በጌምድር ውስጥ ደብረታቦር ከተማ ነበር የተወለዱት። ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ…
" ብርሃን ዘኢትዮጵያ "

የዓድዋ ድል ሲነሳ ስማቸው በግንባር ቀደምነት ከሚነሳው አንዱ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ናቸው።

" ብርሃን ዘኢትዮጵያ " እየተባሉም ይጠራሉ።

ነሀሴ 12 ቀን 1832 ዓ.ም በጌምድር ውስጥ ደብረታቦር ከተማ የተወለዱት እቴጌ ጣይቱ በጊዜያቸው በሀገር አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ፣ ለዓድዋ ጦርነት ድል መሳካት ሚናቸው ከፍተኛ ነበር ፣ የውጫሌ ውል ችግር እንዳለበት በመረዳት እንዲሰረዝ ከፍተኛ ሙግት አድርገዋል፣ የዓድዋ ጦርነት እንደማይቀር ሲያቅዉም የአዲስ አበባ ሴቶችን በማስተባበር ሎጅስቲክስ አዘጋጅተዋል፤ ወደ ጦርነት ስፍራም የተመደበላቸውን ጦር  እየመሩ ተመዋል።

ከዚህ ባለፈም ለዛሬዋ የኢትዮጵያ መቀመጫ አዲስ አበባ ከተማ ምስረታ መሰረት የጣሉ ናቸው።

በርካታ ሴቶችም እቴጌ ጣይቱን በነበራቸው ብርታት፣ ብልህነት፣ ጥንካሬ፣ ሀገር ወዳድነት እንደ ዓርአያ ይመለከቷቸዋል።

እቴጌ ጣይቱ ልክ በዛሬው ቀን የካቲት 4 ቀን 1910 ዓ/ም ነው  ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

ለክብራቸው እና ለሀገር ባለውለታነታቸው በደብረ ታቦር እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ (የዓድዋ ድል መታሰቢያ ማዕከል) ሃውልት ቆሞላቸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ኢትዮጵያ ላይ የሚመጣ ማንኛውም የውጭ ስጋት ካለ በአግባቡ ለከላከል ዝግጁነት እንዳለ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል። ይህን ጉዳይ ያነሱት ስለ ባህር በር እና ስለ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ባነሱበት አውድ ነው።  " ሶማሊያ ውስጥ የምንሞተው የእነሱ ሰላም የእኛ ሰላም ስለሆነ ነው " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ፤ " ለሶማሊያ ሰላም ሶማሊያ ውስጥ እንደ እኛ የሞተ የለም፤ መግለጫ ያወጣ ግን…
" የቀረበው ሪፖርት ከእውነት የራቀ ነው " - የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ

በትግራይ ክልል " ከ200 በላይ ኢንዱስትሪዎች ስራ ጀምረዋል " በሚል ፓርላማ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው ሪፖርት " ከእውነት የራቀ ነው " ሲል የክልሉ ኢንዱስትሪ ቢሮ ወቀሰ፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጥር 28 ቀን 2016 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ተገኝተው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ከ200 በላይ ኢንዱስትሪዎች ስራ ጀምረው ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረጉ ነው ብለው ነበር፡፡

ይሁን እንጂ የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ፤ በክልሉ ከጦርነቱ በኋላ ስራ የጀመሩ ኢንዱስትሪዎችን በተመለከተ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበላቸው ሪፖርት በተጨባጭ መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር የተራራቀ ነው ሲል ሪፖርቱን ውድቅ አድርጓል፡፡

የቢሮው ም/ኃላፊ አቶ መሐሪ ገብረሚካኤል፤ " በአሁኑ ወቅት በክልሉ ስራ የጀመሩት ለትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ጥሬ ዕቃ የሚያቀርቡ 2 መቶ አነስተኛ ፣ 5 መካከለኛ እንዲሁም 12 ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ናቸው " ብለዋል።

" ነገር ግን ' 2 መቶ 17 ኢንዱስትሪዎች ሁለገብ ድጋፍ ተደርጎላቸው ስራ ጀምረዋል ' ተብሎ የተገለጸው ከእውነታው ጋር የተራራቀ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከፍተኛ የብድር እና የወለድ መጠንን ጨምሮ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ችግር አሁንም ግዙፍ  ኢንዱስትሪዎች ስራ እንዳይጀምሩ ትልቅ እንቅፋት ሆኖ በቀጠለበት አግባብ ሁለገብ ድጋፍ ተደርጓል ለማለት አያስደፍርም ሲሉ ተችተዋል።

በክልሉ በነበረው ግጭት የተነሳ የኢንዱስትሪ ዘርፉ ከነበረበት ከፍተኛ ጉዳት በዘላቂነት እንዲያገግም መሬት የወረዱና ተጨባጭ ድጋፎች እንዲደረጉም ነው የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሐሪ ጥሪ ያቀረቡት፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሀዱ ነው።

@tikvahethiopia