TIKVAH-ETHIOPIA
በሶማሊያ ያለው ከፍተኛ ውጥረት ወዴት ያመራ ይሆን ? ⚫ የፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ መንግሥት አሕመድ ማዴቦ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል። የጁባላንድ መንግሥት ደግሞ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ እንዲታሰሩ ትዕዛዝ አውጥቷል። በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና በጁባላንድ ራስገዝ አስተዳደር መሪዎች መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ሰንበትበት ብሏል። ምክንያት ? በአገሪቱ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየውን ክልላዊ…
#Update
የጁባላንድ መንግሥት ከሶማሊያ ፌዴራሉ መንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን ይፋ አደረገ።
የጁባላንድ ካቢኔ ስብሰባ ካደረገ በኃላ ይፋ እንዳደረገው " ሙሉ በሙሉና በይፋ ከሶማሊያ የፌዴራል መንግሥት ጋር ያለውን የስራም ሆነ ማንኛውንም ግንኙነት " አቋርጧል።
የጁባላድ መንግሥት ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድን ፦
- ኃይላቸውን ያለ አግባብ በመጠቀም
- የእርስ በእርስ ጦርነት በማነሳሳት
- ሰራዊትን በማውደም
- በሙስና ... ከሷል።
ሕገመንግስቱን በማጣስ ወንጅሎም " በፌዴራል መንግሥት የተደረጉ የሕገመንግስት ማሻሻያዎችን አንቀበልም " ሲል አሳውቋል።
ቀደም ሲል የፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ መንግሥት በጁባላንድ ፕሬዝዳንት አሕመድ ማዴቦ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል።
የጁባላንድ መንግሥት በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ እንዲታሰሩ የእስር ትዕዛዝ በማውጣት አፀፋውን መልሷል።
በፌዴራል መንግሥቱ እና በጁባላንድ መንግሥት መካከል ውጥረቱ መባባሱ ተሰምቷል።
NB. ባለፈው አመት የፑንትላንድ መንግሥት ከማዕከላዊው የሶማሊያ መንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ማቋረጡን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
@tikvahethiopia

Photo
#Update
" አየር መንገዱ ላደረገው ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ማብራርያ እንዲሰጠን እንጠይቃለን " - የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በክልሉ ትራንስፓርት እና መገናኛ ቢሮ በኩል ባወጣው መግለጫ ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አክሱም ህዳር ፅዮን ዓመታዊ ክብረ በዓል ለመሳተፍ በተጓዙ ወገኖች ላይ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ አድርጓል አለ።
ይኸው የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ " ኢ-ፍትሃዊ እና አስደማሚ ነው " ብሎታል።
ቢሮ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ለፌደራል የትራንስፓርት ሚንስቴር በፃፈው ድብዳቤ እንደጠቆመው፤ " ተቋሙ የፈፀመው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ታማኝነቱ ጥያቄ ውስጥ ከማስገባት ባለፈ ሌላ ፓለቲካዊ መልክ የሚያስይዝ ነው " ሲል አብራርተዋል።
ስለሆነም የበደላቸው ተጓዥ ደንበኞቹ እንዲክስ ፣ እንዲደግፍና ተግባሩ እንዲፈፅም ምክንያት የሆነውን በቂ ማብራርያ ለህዝብ እንዲሰጥ ቢሮው ጠይቋል።
ከአክሱም ህዳር ፅዮን በዓል ተጓዥ ተሳታፊዎች ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያደረገው የትኬት ጭማሪ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ መወያያ አጀንዳ እንዳደረገው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል መረጃ ማጋራቱ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaMekelle

#Mekelle በመቐለም ሁለት ከንቲባ መሾሙ ተሰማ። የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለመቐለ ከተማ አዲስ ከንቲባ ሾመ። ከተማዋ በቅርቡ በም/ቤት ከንቲባ ተሹሞላት እንደነበር አይዘነጋም። በጊዚያዊ አስተዳደሩ አዲስ የተሾሙት ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ህወሓት ለሁለት ሳይሰነጠቅ የፓለቲካ ፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ ናቸው። በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ይፋዊ ደብዳቤ የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ከጦርነቱ…
#Update
በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተሾሙት የመቐለ ከተማ ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ስራቸውን በይፋ ጀመሩ።
ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወደ ቢሮ ሲገቡ በከተማው አመራሮች ሰራተኞች አቀባበል እንደተደረገላቸው ተሰምቷል።
ከንቲባው ዛሬ ዝግ ሰብሰባ የሚያደርጉ ሲሆን አብረዋቸው ከሚሰሩ አካላት ጋር ስለ ቀጣይ እቅዳቸው ይወያያሉ።
አዲሱ የመቐለ ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ በቀጣይ ስለ እቅዶቻቸው እና ስራዎቻቸውን ለሚድያ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከአቀባበሉ ስነ-ሰርዓት አዘጋጆች ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

#ሹመት : የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አቶ መሐመድ እድሪስን የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል። @tikvahethiopia
#Update
የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾሙ።
የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ከሕዳር 23/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳዳር ሆነው መሾማቸውን ገልጿል።
ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል። #ENA
@tikvahethiopia
የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾሙ።
የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ከሕዳር 23/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳዳር ሆነው መሾማቸውን ገልጿል።
ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል። #ENA
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ወጣት እንስቶችን በግፍ ከገደሉ ውስጥ አንዱ በእድሜ ልክ አስራት ሲቀጣ ፤ የተቀሩት ለፍርድ ተቀጥረዋል። የመቐለ የማእከላዊው ፍርድ ቤት ትላንት ባዋለው ችሎት ኣፀደ ታፈረ በተባለች እንስት ወጣት በተፈፀመ የግድያ ወንጀል በይን የሰጠ ሲሆን ዓድዋ ከተማ ላይ በተገደለችው ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ግድያ ተጠርጣሪዎች ላይ ውሳኔ ለመስጠት ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል። ሟች ወጣት ኣፀደ ታፈረን በአሰቃቂ…
#Update
" ውሳኔው በሌሎች ሴቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሚያስቡ ቆመም ብለው እንዲያስቡ የሚያስተምርና የሚያደርግ ነው " - አባት
በግፍ የተገደለችው የዓድዋዋ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ የፍርድ ሂደት ገዳዮች ላይ የሞት እና የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት በማስተላልፈ እልባት አግኝቷል።
የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ዛሬ ህዳር 23/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት በተማሪ ማህሌት ግድያ የተጠረጠሩት ሁለት ግለሰቦች ወንጀለኝታቸውን አረጋግጦ ፍርድ ሰጥቷል።
አንደኛው ወንጀለኛ በሞት ሁለተኛው ደግሞ በፅኑ የዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በትግራይ ማእከላዊ ዞን ዓድዋ ከተማ ታግታ ከወራት መሰወር በኋላ ተገድላ ተቀብራ ስለተገኘችው ወጣት ማህሌት ተኽላይ ጉዳይ ካለፈው ዓመት 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተከታታይ መረጃዎች ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል።
ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከሰጠ በኋላም የሟች አባት አቶ ተኽላይ አጭር አስተያየት ተቀብሏል።
የሟች አባት አቶ ተኽላይ " የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ እንደ ቤተሰብ ትክክል እና የሚሳምን ፤ በሌሎች ሴቶች ጥቃት ለመፈጸም የሚያስቡ ቆመም ብለው እንዲያስቡት የሚያስተምርና የሚያደርግ ነው " ብለውታል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

" ጊዜያዊ አስታዳደሩ የወሰደው እርምጃ ህዝቡን ወደአላስፈላጊ ቁጣና ግርግር የሚያስገባ ነው " - የመቐለ ከተማ ምክር ቤት አስተባባሪ ቋሚ ኮሚቴ
የመቐለ ከተማ ም/ቤት አስተባባሪ ቋሚ ኮሚቴ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከህዳር 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሰጠው የመቐለ ከንቲባ ሹመት ከመቃወም አልፎ " ህገ-መንግስት የጣሰ ተግባር " ብሎታል።
የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ህዳር 24/ 2017 ዓ.ም ከሰአት በኋላ ባወጣው የአቋም መግለጫ ፥ ህዳር 23/2017 ዓ.ም በመቐለ ከተማ አስተዳደር በምክር ቤት አብላጫ ድምፅ የተሾሙ ከንቲባ በስራ ላይ እያሉ የምክር ቤት እና የህዝብ ሉአላውነት በመጣስ ፓሊስ ስራቸው እንዳይሰሩ አግዷል ብሏል።
" በዚያው ቀን ከሰዓት በኋላ ህጋዊ ያልሆኑ ከንቲባ በአስተዳደሩ አንድ አዳራሽ መግለጫ እንዲሰጡ ተደርገዋል " ሲልም ገልጿል።
" በምክር ቤት በስርዓት የተሾሙ ከንቲባ ወደ ቢሯቸው እንዳይገቡ የመቐለ ፓሊስ ከህግ አገባብ ውጪ ፅህፈት ቤታቸው በማሸግ ህዝብ አገልግሎት እንዳይገኝ አስተጓጉለዋል " ሲል ከሷል።
" የፓሊስ ኢ-ህጋዊ ተግባር አገልግሎት ያጣ ህዝብ ወዳልተፈለገ ሽብርና ቀውስ እንዲገባ አድርገዋል " ብሏል።
በተጨማሪ የቋም ኮሚቴው በመግለጫ ምን አለ ?
👉 " በህገ-መንግስት የተሰጠ ስልጣን በመቀማት አምባገነን ስርዓት ለመትከል የተፈፀመ ተግባር ነው ይህንን እንኮንናለን። የተፈፀመው አግባብነት የጎደለው ተግባር በአስቸኳይ እንዲታረም ጥሪ እናቀርባለን። "
👉 " የመቐለ ፓሊስ አመራር በህገ-መንግስት የተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው የፈፀመው ህገ-ወጥ ተግባር በማስተካከል በምክር ቤት የተሾሙ ከንቲባ ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) ሳይውል ሳያድር ስራቸው እንዲሰሩ እና አገልግሎት እንዲሰጡ እንዲያደርግ እንጠይቃለን "
👉 " የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች የተፈፀመው የህግ ጥሰት በመገንዘብ ህግ እንዲያከብሩ ጥሪ እናቀርባለን "
👉 " የመቐለ ከተማ ህዝብ ህገ-ወጥ ተግባሩ በመቃወም ከምክር ቤቱ ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ እናቀርባለን "
👉 " የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የምክር ቤቶች ሉአላዊ ስልጣን በመጣስ የወሰደው እርምጃ ህዝቡ ወደ አላስፈላጊ ቁጣና ግርግር የሚያስገባ መሆኑ በመገንዘብ በዚሁ በህገ-መንግስት ጥሰት የተሳተፉት አካላት በህግ እንዲጠይቃቸው ጥሪ እናቀርባለን "
... ብሏል።
በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተሸሙት አዲሱ ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ መደበኛ ህዝባዊ አገልግሎት መስጠት አንደሚጀምሩ ታማኝ ምንጮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃ ሰጥተውታል።

" እናንተም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ነው የወጣችሁት፣ አታንገላቱን ወዴት እንደሚሄድ ንገሩን ብንል ምላሽ አላገኘንም ! ” - ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር እና የኦሮሚያ ክልል ም/ቤት አባል አቶ ታዬ ደንደአ ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ ከፈቀደላቸው እና ዛሬ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከወጡ በኃላ በር ላይ ተይዘው እስካሁን ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። አቶ ታዬ ደንደአ በዋስ እንዲለቀቁ የወሰነው…
#Update
የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር አቶ ታዬ ደንደዓ ዛሬ መኖርያ ቤታቸዉ ገቡ።
ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ተቀላቅለዋል።
ትናንት አመሻሹን ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተለቀው ቤተሰቦቻቸውን ሳይቀላቀሉ ከማረሚያ ቤቱ በራፍ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዳቸው ይታወሳል።
በኃልም የተወሰዱት ሜክሲኮ የወንጀል ምርመራ እነደነበር ታውቋል።
ዛሬ እኩለ ቀን ደግሞ ሜክሲኮ ከሚገኘው የወንጅል ምርመራ ማዕከል ተለቀው ቤታቸው መድረሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶይቼ ቬለ ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ ስንታየሁ " ጠዋት ቤተሰብ ሜክሲኮ ምግብ አድርሶላቸው ከተመለሰና ደህንነታው ከጠየቀ በኋላ ዛሬ እኩለ ቀን ምሳ ሰዓት ከማቆያው እንዲወጡ ተወስኖ 7 ሰዓት ግድም መኖራቸው ቤት ደርሰዋል " ብለዋል።
ባለፈው ሰኞ በፍርድ ቤት በ20 ሺህ ብር ዋስትና ክሳቸውን ከውጪ መከታተል እንዲችሉ በታዘዘው መሰረት ትናንት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቢለቀቁም ለምን ወደ ሜክሲኮ የወንጀል ምርመራ ማዕከል እንደተወሰዱ ግን ቤተሰብ እንዳልተረዳ ነው የተነገረው፡፡
መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

" በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል። ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል። የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ…
#Update
" የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው " - የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል
" ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው " ሲል የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።
ማዕከሉ እንዳስታወቀው የሲስተሙን ቮልቴጅ በማረጋጋት የተቋረጠውን ኃይል ደረጃ በደረጃ ለመመለስ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው።
በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በክልል ከተሞች የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት መመለሰ መጀመሩን ገልጿል።
የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ አልተፈታም።
ችግሩ ሙሉ በሙሉ እስኪፈታ ድረስ በትዕግስት ተጠባበቁ ተብሏል።

" እስካሁን ከ50 በመቶ በላይ በሚሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል መመለሱን " - የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል በመላው ሀገሪቱ ከተቋረጠው ኃይል ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ። ማዕከሉ እንዳስታወቀው ፦ - በአዲስ አበባ 85 በመቶ በሚሆነው በአብዛኛዎቹ አካባቢ ፣ - በአዳማ፣ - በሀዋሳ፣ - በጅማ፣ - በአርባምንጭ፣…
#Update
ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ ተከስቶ የነበረው የኃይል መቋረጥ ወደነበረበት መመለሱን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታውቋል። #EEP
@tikvahethiopia
ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ ተከስቶ የነበረው የኃይል መቋረጥ ወደነበረበት መመለሱን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታውቋል። #EEP
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አሳድ የሩስያን ድጋፍ በማጣታቸው ሶሪያን ለቀው ሸሽተዋል " - ትራምፕ ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የሶሪያው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ የሩስያን ድጋፍ በማጣታቸው ሀገራቸውን ጥለው መሸሻቸውን ገለጹ። ይህን ያሉት ' ትሩዝ ' በሚሰኘው ማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ ነው። " አሳድ ሄዷል " ያሉት ትራምፕ " ጠባቂው በቭላድሚር ፑቲን የሚመራው ሩስያ፣ ሩስያ፣ ሩስያ ! ከዚህ በላይ እሱን…
#Update
አሳድ ሞስኮ ነው ያሉት።
ላለፉት 24 ዓመታት ሶሪያን ሲገዙ የነበሩት በሽር አላሳድ በታጠቁ ተቃዋሚዎች ከመንበራቸው ከተገረሰሱ በኃላ ሀገሪቱን ጥለው መጥፋታቸው መነገሩ ይታወሳል።
አሁን ላይ ሩስያ ዜና ምንጭ ' ታስ ' እንደዘገበው በሽር አላሳድ ከነቤተሰባቸው ሩስያ፣ ሞስኮ ነው የሚገኙት።
ሩስያ ለአላሳድ እና ለቤተሰባቸው በ ' ሰብዓዊነት ምክንያት ' ጥገኝነት እንደሰጠች ተነግሯል።
የአባታቸው መሞትን ተከትሎ ስልጣን የያዙት አሳድ ለ24 ዓመታት ሶሪያን ሲገዙ ቆይተዋል።
በተለይ ከ2011 በኃላ ሀገሪቱ የለየለት እልቂት ውስጥ ገብታ ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል፣ ሚሊዮኖች ሀገራቸውን ጥለት ተበትነዋል።
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የታጠቁት ኃይሎች በከፈቱት ዘመቻ ከመንበራቸው ተነስተዋል እሳቸውና ቤተሰባቸው በሰላም ምንም ሳይሆኑ ሩስያ ገብተዋል።
ሩስያ የበሽር አላሳድ መንግሥት ዋነኛዋ ደጋፊ እንደሆነች ይታወቃል።
በሌላ በኩል ፤ የደማስቆ ነዋሪዎች ወንዶች ፣ ሴቶችና ህጻናት ሳይቀሩ የአሳድ ቅንጡ ቤተመንግስታቸው ውስጥ ገብተው እየተዟዟሩ ቤቱን ሲመለከቱ፣ ወዲያ ወዲህ ሲሉ ነው የዋሉት።
ከቤተመንግስቱ ብዙ እቃዎች ተዘርፈው መወሰዳቸውም ተሰምቷል።
ከዚህ ባለፈ ታጣቂ ተቃዋሚዎቹ እጅግ ዘመናዊ እና ቅንጡ መኪናዎች የተከማቹበትን የአላሳድ ጋራጅ እንዳገኙም ተነገሯል። (ቪድዮው ከላይ ተያይዟል)